አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ከሁለተኛ ዲግሪ በላይ ያሉትን ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸው ተገለፀ
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸው ተጠቆመ፡፡ የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ደግሞ ከየትምህርት ተቋሞቻቸው የሚላኩላቸውን የትምህርት ሰነዶች እያነበቡ እንደሚቆዩ ተገልጿል፡፡
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኤባ ሚጀና በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት በዚህ ወቅት ይካሄድ ስለነበረው የከፍተኛ ተማሪዎች የምረቃ መርሃ ግብር ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት፣ በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርቱን እንዲከታተሉና ከአማካሪዎቻቸው ጋርም የሚገናኙበት ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ባይኖርም አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ እንደ ጀመሩ አመልክተው፣ በዚህም ጅማና ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡ ትምህርታቸውን ያልጨረሱ ተማሪዎችም እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡
ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ለመጨረስ የቻሉት በተመቻቸው የቴክኖሎጂ የማስተማሪያ ዘዴ በአግባቡ መጠቀም በመቻላቸው፣ እንዲሁም በተማሪውና በአማካሪዎቻቸው ጥንካሬ እንደሆነ የጠቆሙት ዶክተር ኤባ፣ የትምህርት ተቋማቱም በየጊዜው አስፈላጊውን ክትትልና ግምገማ በማድረግ ውጤታማ መሆኑ መቻላቸውን አመልክተዋል፡፡
የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በተመለከተም ዶክተር ኤባ እንዳብራሩት፣ በወረርሽኙ ምክንያት ባለመማራቸው፣ አንዳንዶችም የመጀመሪያ መንፈቅ (ሴሚስተር) ፈተና ለመውሰድ ዝግጅት ላይ እያሉ ወረርሽኙ በመከሰቱ ምክንያት ባለመፈተናቸው በዚህ ክረምት ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች አይኖሩም፡፡
እነርሱን በተመለከተ መደረግ ስላበት ነገር በየሳምንቱ ከየትምህርት ተቋማቱ የትምህርት አመራሮች ጋር ግምገማ እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተው፣ ወረርሽኙ ቢገታ ወይም ቢቆም መደረግ ስላለበት ሁኔታ ከወዲሁ ዝርዝር ዕቅድ ያዘጋጁ የትምህርት ተቋማት መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡
ዝርዝር ዕቅዱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ምን ላይ እንዳቆሙ እና ካቆሙበት በመቀጠል ደግሞ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ በመሸፈን ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ እንደሚችሉ የሚያሳይ እንደሆነም አስረድተዋል።
Via:- EPA
Share share ...
See more...@wollomedia

የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ገና አላበቃም ሲሉ አስጠነቀቁ።
ሜርክል ዛሬ ወረርሽኙን ለመከላከል የተወሰዱ እርምጃዎችን ማላላት ከጀመሩ የምሥራቅ ጀርመን ግዛቶች መሪዎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት መግለጫ የኮሮና ተህዋሲ እልጠፋም ጀርመንም የተሻለ መቆጣጠሪያ ቢኖራትም ተህዋሲው ግን አሁንም አለ ሲሉ ተናግረዋል።
አሁንም የወረርሽኙ መነሻ ላይ ነን ያሉት ሜርክል በሽታው እንዴት በፍጥነት እንደሚሰራጭ ስለምናይ በጣም መጠንቀቅ አለብን ሲሉ አሳስበዋል።
በጀርመን በኮሮና ተህዋሲ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሲቀንስ መንግሥት ጥብቅ የመከላከያ እርምጃዎች በመጠኑ አላልቷል።
አሁን የተደነገጉት ደንቦች እስከ መቼ እንደሚቀጥሉ የሃገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች ፖለቲከኞች መስማማት አልቻሉም።ሜርክል አሁን ሃላፊነቱ በይበልጥ በግዛቶቹ ጫንቃ ላይ ይሆናል ብለዋል።
Via:- Dw
Share share ...
See more....@wollomedia

The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 18 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.