ኢትዮ ትምህርት
51 subscribers
148 photos
33 videos
302 files
59 links
በዚህ ችናል የተለያዩ ትምህርቶች(በ pdf, short notes,general knowledge ),አዝናኝ ቀልዶች በተጨማሪም ወቅታዊ መረጃዎችን ታገኙበታላችሁ
Download Telegram
# አጫጭር የአገር ውስጥ እና የውጭ ስፖርታዊ መረጃ እነሆ ❗️

⚡️ሱዳን ሁለት የእግር ኳስ መሪዎቿን በሞት አታለች።

⚡️የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የንክኪ ልምምድ ለመፍቀድ ነገ ስብሰባ ያካሂዳሉ።

⚡️ኢጋሉ የዩናይትድ ውሰት ውሉን ጨርሶ በዚህ ሳምንት ወደ ቻይና ይመለሳል።

⚡️ዝላታን በልምምድ ወቅት ከባድ ጉዳት እንዳጋጠመው ተነግሯል።

⚡️ቫንፐርሲ በእግር ኳስ ካሰለጠኑት አሰልጣኞች ውስጥ ፈርጉሰን የእርሱ ምርጥ እነደሆነ ተናግሯል።
Share..share..share...
see more....@wollomedia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን አራት ትምህርት ቤቶችን ለአንድ ዓመት አገደ።

ባለሰልጣኑ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የትምህርት ቤት ክፍያቸውን እስከ 70 በመቶ እንዲቀንሱ መመሪያ ቢያስተላልፍም ትምህርት ቤቶቹ ግን 100 ፐርሰነት ክፍያ አስከፍለው ነው።ለአንድ ዓመት ከታገዱት ትምህርት ቤቶች መካከልም 3ኤም ትምህርት ቤት፣ገነት መሰረተ ክርስቶስ፣ሮማን አካዳሚ እና ለምለም ትምህርት ቤቶች በ2013 ዓመት ተማሪ እንዳይቀበሉ ተወስኖባቸዋል።

Via Ethio FM
Share share....
See more....@wollomedia
በአዲስ አበባ ከ10 000 በላይ የሚሆኑ ሴተኛ አዳሪዎች ተለይተው ድጋፍ መሰጠት ተጀምሯል ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ለችግር የተጋለጡ ከ10 000 በላይ ሴተኛ አዳሪዎችን መለየቱን ተናግሯል፡፡ በሆቴሎች፣ በመንገድ ላይ እና በተለያዩ መጠጥ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ ሴቶች በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ለችግር መጋለጣቸው ተነግሯል፡፡በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎችም ያካተተ መሆኑን ሸገር ከቢሮው ሰምቷል፡፡በአዲስ አበባ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ቢሮ የተለዩት ከ10 000 በላይ የሚሆኑ ሴተኛ አዳሪዎች ዝርዝር ሁኔታ ለአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ መተላለፉንም ሰምተናል፡፡

Via Sheger FM
Share share...
See more....@wollomedia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥታቸው ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ገለጹ❗️

⚡️“ሰዎች እንደመሆናችን ያለፍንበትን የታሪክ ውጣ ውረድ በቀላሉ እንረሳለን፤ የአካባቢያችንን፣ የአኗኗራችንን፣ የከተሞቻችንንና እና የሀገራችንን ሁኔታ እኛ ከዚህ የተሻለ አይገባንም፤ ቅብጠት ነው፣ ለድኻ ይሄ መች አነሰው ብለን እንቀጥላለን።" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ብልጽግና የሚመጥናቸው እና የሚገባቸው መሆኑን፣ አስተዳደራቸውም ለዚህ መሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስምረውበታል።

⚡️በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ በቤተ መንግሥቱ ቅጽር ግቢ እና በአዲስ አበባ ከተማ እየተለወጡ ያሉ ነገሮች ለራስ ከፍ ያለ ቦታ እንድንሰጥ የሚያስችሉ በመሆናቸው መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

⚡️“ከጥቂት ዓመታት በፊት በእነዚህ በሮች ያለፉ ኢትዮጵያውያን በግቢው ሕይወት ለመዝራት የተሠራውን የፈጠራ ችሎታ እና ጉልበት ሳያደንቁ አያልፉም፣ በአንድነት የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ለመገንባት በዓላማ፣ በሐሳብ እና በትጋት እንነሣ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገፃቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት።
Share share....
See more.....@wollomedia
ለኮቪድ-19 ክትባት ምርምር ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ተሰበሰበ ❗️

⚡️በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘትና መድሃኒት ለማምረት የሚያግዝ ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት አስታወቁ።

⚡️ፕሬዝዳንቱ የተሰበሰበውን ገንዘብ " መሰረት የጣለ" ካሉ በኋላ የዓለም ሕዝብ ቫይረሱን ለመዋጋት ህብረት ያሳየበት መሆኑን ገልፀዋል።

⚡️የአውሮፓ ኮሚሽን ለክትባት እና መድሃኒት ማምረቻ የሚሆን ገንዘብ እንዲያዋጣ ጥሪ ያቀረበው ከዚህ ወር ቀደም ብሎ ሲሆን በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ የሚቀርብ ክትባትና መድሃኒት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲቀርብ ይሰራል ተብሏል።

⚡️በቅድሚያ የአውሮፓ ህብረት ስብሰባው ባደረገበትና ይህንን ሃሳብ ባቀረበበት ወቅት 6.5 ቢሊየን ፓውንድ ከ40 አገራት እና ለጋሽ ድርጅቶች ተሰብስቦ ነበር።

•አሜሪካና ሩሲያ በዚህ የገንዘብ ማዋጣት ሂደት ውስት አለመሳተፋቸው ታውቋል።

©BBC
Share share ...
See more....@wollomedia
ባለስልጣናት እና አመራሮች ሀብታቸውን በ42 ቀናት እንዲያስመዘገቡ ቀነ ገደብ ተሰጣቸው። የፌደራል የስነምግባርና የፀረሙስና ኮሚሽን፤ በጊዜ ገደቡ የሀብት ምዝገባ በማያከናውኑት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

Via Ethiopia Insider
Share share...
See more....@wollomedia
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በኮሮና ቫይረስ በክልሉ ተይዘው ከነበሩት 7 ሰዎች ስድስቱ ማገገማቸውን አስታውቋል።በሀገራችን ዛሬ 8 ሰዎች ማገገማቸው በጤና ሚኒስቴር ከተገለፀ ሲሆን ሁለቱ ከላይ የተጠቀሱት ሲሆኑ ስድስቱ ደግሞ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው።
Share share ...
See more....@wollomedia
⬆️ኮቪድ 19ን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የወጣ ሪፖርት ፣

ቫይረሱ የተገኘባቸው ክ/ከተማዎችና የተያዙ ሰዎች ቁጥር :

1. ልደታ 122
2.አዲስ ከተማ 69
3.ቦሌ 54
4.ጉለሌ 38
5.ኮልፌ ቀራኒዮ 38
6.ንፋስ ስልክ ላፍቶ 27
7.የካ 25
8.አራዳ 18
9.አቃቂ ቃሊቲ 8
10.አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያሉ 18 ሲሆኑ በድምር በከተማዋ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 436 ነው።

Via Addis Ababa City P.S
Share share....
See more....@wollomedia
በአማራ ክልል በወባ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በ73 በመቶ መጨመሩን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ በዚህ አመት 411 ሺህ 744 ሰዎች በወባ የተያዙ ሲሆን የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል።የኮሮናን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የተሰጠው ትኩረት ለወባ በሽታ መጨመር አንድ ምክንያት መሆኑን ኢንስቲቱዩቱ ገልጿል።

Via ELU
Share share...
See more...@wollomedia
#ስፔን በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎችን ለማሰብ 10 የሐዘን ቀናትን አወጀች❗️

⚡️ስፔን በኮሮናቫይረስ የሞቱትን ዜጎቿን ለማሰብ ከረቡዕ ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት የሐዘን ቀን ሆኖ እንዲታሰብ መወሰኑን የመንግሥት ቃል አቀባይዋ ማሪያ ጂሰስ ሞንቴሪዮ አስታወቁ።

⚡️በእነዚህ ቀናት በሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ወታደራዊ መርከቦች የአገሪቱ ባንዲራ በግማሽ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ገልፀዋል።
የአስረኛው ቀን ላይም የመታሰቢያ ዝግጅት እንደሚኖር ተገልጿል።

⚡️" በአካል አብረውን የሉም፣ ነገር ግን በትውስታችን ውስጥ ሁሌም ይኖራሉ፤ ስለዚህ እንደሚገባቸው መጠን ትዝታቸውን በይፋ እንዲሁም በርዕሰብሔሩ በሚመራ ስነስርዓት እናከብራለን" ብለዋል ቃል አቀባይዋ።

•ስፔን በኮሮናቫይረስ ምከንያት 26 ሺህ 834 ዜጎቿን ማጣቷን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ያሳያል።
Share share...
See more....@wollomedia
የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የሰራው የኮቪድ-19 #ክትባት #ኬንያ ውስጥ ሊሞከር ነው❗️

⚡️" ኬምሪ ዌልካም " ትረስት የተሰኘው ይህ ተቋም 400 የጤና ባለሙያዎችን ለጥናቱ በበጎ ፈቃደኝነት ይፈልጋል።

⚡️የዚህ ጥናት ዓለማ " አንድ ክትባት ለሁሉም" የሚል መሆኑን ተገልጿል።

⚡️በመላው ዓለም ተመራማሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን እያከናወኑ ነው። የኦክስፎርዱ ዩኒቨርስቲ "ChAdOx1 nCoV-19" የተሰኘ ክትባት ሰርቶ ከዩናይትድ ኪንግደም ለተውጣጡ ከአንድ ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች ላይ ሙከራ አድርጓል።

⚡️አሁን ደግሞ የኬንያው የሕክምና ምርምር ተቋም የክትባቱን መገኘት ለመደገፍ አብሮ እየሰራ ነው።

⚡️አራት መቶዎቹ በጎ ፈቃደኞች እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ መሆን ያለባቸው ሲሆን በኪሊፊ የጤና ባለሙያ ሆነው እየሰሩ የሚገኙ መሆን እንዳለባቸውም ተገልጿል።

⚡️የኮሮናቫይረስ እስካሁን ድረስ ፈዋሽ መድሃኒት ወይም ክትባት ባይገኝለትም ነገር ግን ክትባት መገኘቱ የቫይረሱ ስርጭትን ለመግታትም ሆነ ሕሙማንን ለማከም ወሳኝ ሚና እንዳለው የዓለም ጤና ድርጅት ይናገራል።

⚡️አክሎም የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም በማለማመድ ሻይረሱን በመዋጋት እንዳይታመሙ ያደርጋል ይላል።

•ነገር ግን አሁንም ቢሆን የክትባት ሙከራ ጉዳይ አፍሪካውያንን እያከራከረ ነው። በክርክሩ ገበታ ከፊት የሚሰየመው ደግሞ በነዚህ ሙከራዎች ጀርባ "የቅኝት ግዛት አስተሳሰብ" መንፀባረቁ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው።

©BBC
Share share.....
See more...@wollomedia
#በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭት አሳሳቢ እየሆነ ነው ❗️

⚡️ኮቪድ 19 ባለፈው #መጋቢት ወር በኢትዮጵያ የተከሰተ ቢሆንም በተለይ #በግንቦት ወር በእጅጉ እየተስፋፋ መምጣቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለጹ።

⚡️ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንም ገልጸዋል።

⚡️ይህም መንግስትና ህዝብን በእጅጉ እያሳሰበ ነው ብለዋል አቶ ንጉሱ።

⚡️የኮቪድ 19 ስርጭት አሁን ላይ #ከጋምቤላ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተስተዋለ መሆኑንም ጠቁመዋል።

⚡️በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የስርጭት መጠኑ እየጨመረ በመሆኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማክበርና መተግበር ይገባል ነው ያሉት።

• "መዘናጋትና ችላ ማለት ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ለመከላከል የጋራ ጥረትና ጥንቃቄ ያስፈልጋል" ብለዋል።

⚡️በተለይ ደግሞ የትራንስፖርት አገልግሎት አካባቢዎች፣ የንግድና የገበያ ስፍራዎች እንዲሁም የአምልኮ ስፍራዎች ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብለዋል።

©ኢዜአ
Share share.....
See more....@wollomedia
በአማራ ክልል በዛሬው ዕለት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠውን 15 ሰዎች ጨምሮ በአጠቃላይ በአማራ ክልል 44 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ፦
➡️ ምዕ/ጎንደር - 29 ሰዎች
➡️ ማ/ጎንደር - 3 ሰዎች
➡️ ጎንደር ከተማ - 1 ሰው
➡️ ደሴ ከተማ - 1 ሰው
➡️ ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
➡️ አዊ - 3 ሰዎች
➡️ ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
➡️ ሰ/ወሎ - 1 ሰው

ምንጭ፦ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ
Share share....
See more...@wollomedia
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 100,000 አለፈ።

በአሜሪካ አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 100,103 በላይ የደረሰ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1.7 ሚሊዮን አልፏል። እንዲሁም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 469,049 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።
Share share ...
See more....@wollomedia
☑️የ46ቱ ታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ

-45 ኢትዮጵያውያን እና 1 የእስራኤል ዜጋ ሲሆኑ 29ወንድ እና 17ሴት ናቸው። እድሜያቸው ከ12 -79አመት መሆናቸው ተገልጿል።

የጉዞ ታሪካቸውን ስንመለከት

-34ሰዎች የውጪ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ 4 ሰዎች ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው። 8 ሰዎች ደግሞ የውጪ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸው ተረጋግጧል።

የመኖሪያ ቦታቸውን ስንመለከት
_
•13 ሰዎች- ከአዲስ አበባ የተገኙ ሲሆኑ ( 4ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና 1 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው እና 8 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው)

•3ሰዎች- ከትግራይ ክልል ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው።

•15ሰዎች - ከአማራ ክልል የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ

•11ሰዎች- ከሱማሌ ክልል የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው።

•4ሰዎች - የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እና ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ናቸው።

በተጨማሪም በትላትናው ዕለት 14ሰው (8ሰዎች ከደቡብ ክልል እና 6 ሰዎች ከአዲስአበባ) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 167 ደርሷል።
Share share...
See more...@wollomedia
የጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ሰዎች ጉዳይ አሳስቦታል!

በርካቶች በኮቪድ-19 ከሚያዙባት ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ ክልሉ የሚገቡ ዜጎች ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።በደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ከ800 በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውንና 8 ሰዎችም መሞታቸውን ዛሬ የወጣ መረጃ ያሳያል።እስካሁን በቫይረሱ የተያዘ ሰው ያልተመዘገበበት የጋምቤላ ክልል ከዚህች ጎረቤት አገር ጋር በሰፊ ድንበር ይዋሰናል።ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በተገበረችው የአስቿኳይ ጊዜ አዋጅ በድንበር አካባቢ የሰዎች እንቅስቃሴ ተገድቧል።ይሁን እንጂ የድንበሩን ስፋት ተገን በማድረግ በየዕለቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ደቡብ ሱዳናዊያን ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢዜአ ገልጿል።

Via ENA
Share share ....
See more.....@wollomedia
ኢትዮጵያ ለዲፕሎማቶች እና ለአለም አቀፍ ሰራተኞች የለይቶ ማቆያ ግዴታዎችን አላላች!

ኢትዮጵያ ከውጪ አገር የሚመለስ ማንኛውም መንገደኛ ለለይቶ ማቆያ በተመረጡ ሆቴሎች ለ 14 ቀን ተለይቶ እንዲቆይ ያስቀመጠችውን ግዴታ ለዲፕሎማቶች እንዲሁም በሀገሪቱ ለተመዘገቡ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ሰራተኞች አላላች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተቋማቱ በላከው ደብዳቤ ከማክሰኞ ግንቦት 18፤ 2012 ጀምሮ የሚመለሱ ዲፕሎማቶች እና የየድርጅቶቹ ሰራተኞች በመኖሪያ ቤታቸው ወይም በየኤምባሲዎቻቸው ውስጥ ተለይተው መቆየት እንደሚችሉ ገልጿል።

Via Ethiopia Insider
Share share.....
See more......@wollomedia
የጭነት መኪና ተገልብጦ አሽከርካሪውን ጨምሮ የ10 ሰዎችን ሕይወት አለፈ❗️

⚡️ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ ከጃቢ ገነት ወደ ደብረ ኤልያስ ከተማ እህል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ10 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

⚡️ዛሬ ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓም ከቀኑ 6፡00 ላይ ነው የጭነት መኪናው በመገልበጡ አሽከርካሪውና ዘጠኝ ጫኝና አውራጅ ሠራተኞች ሕይወታቸው ያለፈው፡፡

⚡️የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳዉ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

©አብመድ
ShAre share...
See more...@wollomedia