⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye)
13.4K subscribers
1.66K photos
7 videos
494 files
818 links
Download Telegram
Forwarded from ETHIO -LAW
The FDRE draft CPREC.pdf
1.7 MB
የወንጀል ሕግ ሥነ-ስርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ
👍7
የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደርን ለመደንገግ የወጣው አዲሱ አዋጅ ቁጥር 1324/2016፣ ከዚህ ቀደም ለሁለት አስርት ዓመታት ገደማ ሲሠራበት የነበረውን አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 456/1997) በመተካት በርካታ መሠረታዊና ዘመናዊ ለውጦችን ይዞ መጥቷል።
አዲሱ አዋጅ ካመጣቸው ዋና ዋና ለውጦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
1. የመሬት መጠቀሚያ መብትን ለባንክ በዋስትና ማስያዝ
ይህ የአዲሱ አዋጅ ትልቁና ታሪካዊ ለውጥ ነው።
* በፊቱ፦የገጠር መሬት መጠቀሚያ መብትን ለባንክ በዋስትና ማስያዝ አይቻልም ነበር። ይህም ገበሬው ለሥራ ማስፋፊያ የሚሆን ብድር እንዳያገኝ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።
* አሁን፦ማንኛውም ባለመብት (ገበሬ ወይም ባለሀብት) የመሬት መጠቀሚያ መብቱን ለፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች) በዋስትና በማስያዝ ብድር ማግኘት ይችላል። ተበዳሪው ዕዳውን ካልከፈለ ባንኩ የመጠቀሚያ መብቱን ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላል።
2. የመሬት ኪራይ ዘመን እና ሁኔታዎች
* በፊቱ፦ የኪራይ ዘመን በክልሎች ሕግ የሚወሰንና አጭር ነበር።
* አሁን፦አዋጁ የኪራይ ዘመንን በግልጽ አስቀምጧል። ለምሳሌ ለትልቅ ኢንቨስትመንት እስከ 50 ዓመት፣ ለመካከለኛ እስከ 30 ዓመት ሊከራይ እንደሚችልና እንደ አስፈላጊነቱ ሊታደስ እንደሚችል ይፈቅዳል። ይህም ለባለሀብቱ ዋስትና ይሰጣል።
3. ዲጂታል የመሬት መረጃ ሥርዓት (Cadastre)
* በፊቱ፦ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በአብዛኛው በእጅ የተጻፈና ለስህተት ወይም ለሐሰተኛ ሰነድ የተጋለጠ ነበር።
*አሁን፦ መሬትን በዘመናዊ የካርታ ሥራ (Cadastre) በመለካት መረጃዎችን በዲጂታል ሥርዓት መያዝ ግዴታ ሆኗል። ይህም የመሬት ክርክርን ይቀንሳል፣ የመረጃ ጥራትንም ይጨምራል።
4. የመሬት ማጠናከር (Land Consolidation)
* ለውጡ፦ አዋጁ የተበታተኑ ጥቃቅን የገበሬ መሬቶችን በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ በማጠናከር (Consolidation) ለሰፋፊ እርሻና ለዘመናዊ ግብርና እንዲመቹ የማድረግ ሥርዓት ዘርግቷል። ይህ ምርታማነትን ለመጨመር ታስቦ የመጣ ነው።
5. የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ (Land Use Planning)
* ለውጡ፦ መሬት ዝም ብሎ ሳይሆን ለታለመለት ዓላማ ብቻ መዋል እንዳለበት ያሳስባል። ለምሳሌ ለእርሻ የተከለለ መሬት ወደ መኖሪያነት ወይም ወደ ሌላ አገልግሎት እንዳይቀየር ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጋል።
6. የሴቶች እና የሕፃናት መብት
* ለውጡ፦ በይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ላይ የሴቶች ስም እንዲሰፍር እና በትዳር ውስጥ ወይም በውርስ ወቅት ያላቸው የመሬት መብት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲጠበቅ የሚያደርጉ ድንጋጌዎችን ይዟል።
7. የመሬት ይዞታን በፈቃድ መልቀቅ
* ለውጡ፦አንድ ገበሬ የገጠር መሬቱን በፈቃዱ ለክፍለ ከተማ ወይም ለልማት መልቀቅ ከፈለገ፣ የሚካስበትና ወደ ሌላ የሥራ ዘርፍ የሚሰማራበት ሥርዓት በአዋጁ ተመቻችቷል።
ባጭሩ፦አዋጅ ቁጥር 1324/2016 መሬትን ከማህበራዊ ዋስትናነት ባለፈ እንደ ትልቅ የኢኮኖሚ ምንጭ (ብድር መሳቢያ፣ ለረጅም ጊዜ መከራያ እና ለዘመናዊ ግብርና መዋያ) እንዲሆን የሚያስችል በር ከፍቷል።
ይህ አዋጅ በተለይ አንተ ቀደም ብለህ ለጠየቅከው "የገንዘብ አቅምን ማሳደግ" ለሚለው ሃሳብ ትልቅ ድልድይ ነው፤ ምክንያቱም መሬትን ተጠቅሞ ካፒታል ለማፍራት ስለሚረዳ ነው።
❤13
ክስ መተው

አንድ ክስ ከቀረበ በኋላ በማናቸዉም ጊዜ ከሳሹ ያቀረበዉን ክስ በማንሳት ከተከሳሾቹ አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑትን ከክሱ ዉጭ ለማድረግ ወይም ያቀረበዉን ክስ በሙሉ ወይም በከፊል ለመተዉ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/1/ ስር የተመለከተ ሲሆንፍርድና ቤቱ አቤቱታዉን ተቀብሎ ትእዛዝ በሚሰጥበት ጊዜ ከሳሽ ወገን ክሱን ለማንሳት ወይም ለማቋረጥ የጠየቀበትን ምክንያት መርምሮ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ ከሳሹ አዲስ ክስ ለማቅረብ የሚችልበትን መብት መጠበቅ የሚችል ስለመሆኑ በዚሁ ድንጋጌ ንኡስ አንቀጽ(2) ስር ተመልክቷል።

ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብእንደሚቻለዉ በአንድ በኩል ከሳሹበግልጥ ጉዳዩ ላይ የመወሰን መብቱን ተጠቅሞ ክሱን ለመተዉ የሚችል መሆኑን በሌላ በኩል ከሳሹ በፈቃዱ በተወዉ ነገር ላይ አዲስ ክስ ለማቅረብ የሚችለዉ ፍርድ ቤት መብቱን የተጠበቀለት ሲሆን ብቻ መሆኑን ነዉ፡፡

በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/2/ ስር እንደተመለተዉተከሳሹም በሌላ ጊዜ አዲስ ክስ እንዲያቀርብ ሊፈቅድለት የሚችለዉም በክሱ አቀራረብ ስርዓት ጉድለት ያለበት ሲሆን ወይም አዲስ ክስ ለማቅረብ ሊያስፈቅድለት የሚችል በቂ ምክንያት ሲኖር እና ፍርድ ቤቱ ምክንያቱን ተቀብሎ መብቱን የጠበቀለት እንደሆነ ነዉ፡፡

በሌላ አገላለጽ በቁጥር 278/2/ የተነገረዉን ባለመጠበቅ ከሳሹ ከፍርድ ቤት ፈቃድ ሳይቀበል ክሱን በሙሉ ወይም በከፊል የተወ እንደሆነ አዲስ ክስ ለማቅረብ እንደማይችል በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 289/1/ በግልጽ ተደንግጓል፡፡

ስለዚህም የቀረበዉ አዲስ ክስ ተገቢነት ያለዉ መሆን አለመሆኑ የሚወሰነዉ ክሱ በፍርድ ቤት ፈቃድ ወይም ያለፍርድ ቤት ፈቃድ የተቋረጠ ወይም የተተወ መሆን አለመሆኑ በመመርመር እንደሆነ ያስገነዝበናል።

በተያዘዉ ጉዳይ ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ ይዘት መገንዘብ እንደተቻለዉ አመልካች ቀደም ሲል በዚሁ ጉዳይ በመ/ቁ/ 153563 ላይ ያቀረበዉን ክስ ለመተዉ መፈለጉን ገልጾ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበዉ ማመልከቻ መሰረት መዝገቡ የተዘጋ ስለመሆኑና መዝገቡም የተዘጋዉ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ 278/1/ መሰረት መሆኑን ያመላክታል።

መዝገቡ እንደሚሳየንአመልካችና በቀን 10/04/2011ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ ያቀረበዉ ማመልከቻ ይዘት ‹‹…ክርክሩእየገፋ በመምጣቱ ከሳሽ አላስፈላጊ ዉጣ ዉረዶችን በመተዉ የጀመርኩትን ክስ ክርክር በሙሉ ፈቃድ ክሴን ለማቋረጥ …›› በሚል በቃለ መኃላ ተደግፎ የቀረበ አቤቱታ መሆኑን
የሚገልጽ እንጂ በጉዳዩ ላይ ሌላ ጊዜ አዲስ ክስ ለማቀርብ የፍርድ ቤቱን ፈቃድ የጠየቀ
መሆኑን የሚያሣይ አይደለም፡፡

ክሱን ለማቋረጥ ያቀረበዉም ምክንያትም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/2/ ስር ከተደነገጉት ምክንያቶች አንዱም ስለመኖሩ የማያሳይ ነዉ፡፡

ፍርድ ቤቱ ማመልከቻዉን መርምሮ የሰጠዉ ትእዛዝ ይዘትም ክሱ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/1 መቋረጡን የሚገልጽ እንጂ አዲስ ክስ ለማቅረብ መብት የተጠበቀለት መሆኑን አያሣይም፡፡

የመዝገቡ ይዘት ይህንን የሚያሳይ ሆኖ እያለ አመልካች ፍርድ ቤት ፈቃድ አግኝቻለዉ በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ መሰረት ያለዉ ሆኖ አላገኝም፡፡

ከዚህ አኳያ በተጠሪ በኩል የቀረበዉን መቃወሚያ መነሻ በማድረግ የስር ፍርድ ቤትም መ/ቁ/153563 ላይ የተጀመረዉ ክርክሩ የተቋረጠበትን አግባብ መርምሮ ከሳሹ ክሱን በራሱ ፈቃድ የተወዉ መሆኑን እንጂ በፍርድ ቤት ፈቃድ የተወዉ መሆኑን የሚያሣይ አይደለም የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ ስህተት ነዉ የሚባልበት ምክንያት የለም፡፡

የሰ/መ/ቁ. 202734 ቀን ፡- ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ/ም
👍6❤5👏1
በወንጀል ህግ አንቀፅ 541(1)(ለ) መሰረት ደም ፍላትን የሚያስከትል ተግባር ተፈጽሟል ለማለት የሚቻለው እነዚህ 3 ሁኔታዎች ሲሟሉ ስለመሆኑ:-
#በሟች የተፈፀመው ተግባር አንድ ምክንያታዊ ሰውን ራሱን እንዳይቆጣጠር የሚያደርግ መሆኑ፤
#በዚህ ተግባር ምክንያት በወቅቱ የወንጀል ድርጊት ፈፃሚው በርግጥም ራሱን የማይቆጣጠርበት ሁኔታ ውስጥ የነበረ መሆኑ እንዱሁም
#ድርጊቱ በፍጥነትና ምንም የመረጋጊያ ጊዜ ሳይሰጥ የተፈፀመ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።

➤የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ/ም
➤ሰ/መ/ቁ 251759
👍10❤2
#የፌደራል_ሰበር_ሰሚ_ችሎት በመዝገብ ቁጥር .262248 በጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ያልታተመ የሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ በወንጀል ድርጊት ተከሶ ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ ጥፋተኛ የተባለበት ድንጋጌ ቅጣት እንዳይገደብ ክልከላ ያላደረገ እና ሕጻናት ልጆች ካሉት ቅጣት መገደብ ግደታ ስለመሆኑ።

💦ተከሳሽ #ጥፋተኛ የተባለበት #ድንጋጌ ቅጣት እንዲገደብ በህጉ #ክልከላ #ካልተደረገበት በስተቀር ተከሳሽ #ህጻናት #ልጆች #የሚያስተዳድር መሆኑን ገልጾ ባቀረበበት ፍ/ቤት በህጻናቱ ላይ ሊደርስ የሚችለውን #ቁሳዊ እና #ስነ ልቦናዊ ጉዳት ለማስቀረት ሲባል #ቅጣቱ #ያለመገደብ መሠረታዊ የህግ ስህተት ስለመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ/ቁ 262248 በቀን 06/02/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል።
➤ሰ/መ/ቁ. 262248
➤06/02/2017 ዓ/ም
👍4
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ/ም በሰበር መ/ቁ. 262248 ተከሳሹ ሕጻናት ያሉት ከሆነ እስራቱ ሊገደብለት የሚገባ ስለመሆኑ የሰጠው ገዥ ውሳኔ-
👍9❤2
የመሬትና የቤት ስም ዝውውር የሚፈፀምባቸው መንገዶች
****
የባለቤትነት (የይዞታ) ስም ዝውውር የሚደረገው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦

• በሽያጭ (Sale): በሻጭና በገዥ መካከል በሚደረግ የውል ስምምነት
• በስጦታ (Gift): በቤተሰብ ወይም በግለሰቦች መካከል በሚደረግ ነጻ ስጦታ
• በውርስ (Inheritance): በሕግ ወይም በኑዛዜ ለወራሾች የሚተላለፍ
• በፍርድ ቤት ትእዛዝ: በዕዳ ወይም በሌላ የሕግ ክርክር ምክንያት
በውርስ፣ በሽያጭ እና በስጦታ ስም ለማዛወር የሚያስፈልጉ ሂደቶችና መረጃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።
________
1. በሽያጭ (Sale)

አስፈላጊ መረጃዎች፦
o ዋናው የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ (Original Title Deed)
o በሰነዶች ማረጋገጫ የጸደቀ የሽያጭ ውል
o የሻጭ እና የገዢ የታደሰ መታወቂያ
o ንብረቱ በጋራ ሀብትነት የተመዘገበ ከሆነ የትዳር ጓደኛ ስምምነት
o ከዕዳ እና እገዳ ነፃ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ
o የግብር ደረሰኝ
________

2. በውርስ (Inheritance)

ውርስ የሚፈጸመው ባለቤቱ በህይወት በሌለበት ወቅት ሲሆን፣ ህጋዊ ወራሽነትን ማረጋገጥ ቀዳሚው ተግባር ነው።
አስፈላጊ መረጃዎች፦
o የሟች የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ
o የሟች የሞት ምስክር ወረቀት
o ከፍርድ ቤት የተሰጠ የሕጋዊ ወራሽነት ማረጋገጫ (Heirship Certificate)
o ወራሾች ንብረቱን ለመከፋፈል ከተስማሙ በሰነዶች ማረጋገጫ የጸደቀ የውርስ ክፍፍል ስምምነት
o የወራሾች የታደሰ መታወቂያ
________
3. በስጦታ (Gift)

አስፈላጊ መረጃዎች፦
o ዋናው የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ
o በሰነዶች ማረጋገጫ የጸደቀ የስጦታ ውል
o የሰጪ እና የተቀባይ የታደሰ መታወቂያ
o የጋራ ሀብት ከሆነ የትዳር ጓደኛ ስምምነት
________

የመረጃው ምንጭ፡- የተሸሻለው የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥ እና ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 61/2010
(የመ/ይ/ም/መ/ኤ)
❤20
7 (ሰባት) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ የሰበር ውሳኔ፤ መዝገብ ቁጥር 246230

ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁ 186946 የተሰጠው ውሳኔ ‘‘በአንድ ቦታ ላይ ሁለት የተለያዩ ሰዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቢኖራቸው አንደኛው ቤት ቢሰራ ሌላኛው ወገን በይዞታዬ ላይ እየተቃወምኩኝ ቤት ስለሰራ ያፍርስልኝ በማለት መጠየቅ የማይችል መሆኑን’’ የሚገልጸው ውሳኔ ተለውጧል፡፡

7 (ሰባት) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት መዝገብ ቁጥር 246230
“በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ186946 በሚያዝያ 26/2013 ዓ.ም የተሰጠው አስገዳጅ ትርጉም እና ሌሎች መዝገቦች ላይ የተያዘዉ ተመሳሳይ አቋም ተለውጦ፤ በአንድ ባለይዞታ ሊመዘገብ የሚገባን የከተማ ይዞታ ከአንድ በላይ የሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ወይም ካርታ ለተለያዩ ሰዎች ተደርቦ ተሰጥቶ ሲገኝ ለቦታው ባለመብትነት ቅድሚያ የሚሰጠው መጀመሪያ ያስመዘገበው ሰው ነው’’ በሚል ተተርጉመዋል፡፡
❤15
⚖️⚔️ ወሳኝ የሰበር ዉሳኔ መ. ቁ 224265📢
👌 ከሳሽ የሆነ ወገን በክሱ ተከሳሽ የሚያቀርበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አስቀድሞ ገምቶ ለዚህ የሚረዳውን ማስረጃ ከክሱ ጋር አያይዞ እንዲያቀርብ አይጠበቅም፡፡
👌ከሳሽ ላቀረበው ክስ ከተጠሪ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተመልክቶ መቃወሚያውን ውድቅ ለማስደረግ የበኩሉን ክርክር በማቅረብ ክርክሩንም በማስረጃ ለማስደገፍ የሚያቀርበው ጥያቄ ተገቢነት ያለው በሚሆኑ ከሳሽ አስቀድሞ በክሱ ካቀረበው የፅሑፍ ማስረጃ ዉጭ የቃል ክርክርን ተከትሎ የተነሳበትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ለማስተባበል አዲስ ማስረጃ ለማቅረብ ከጠየቀ ሊፈቀድለት እና ማስረጃውን በመቀበል ከቀረበው መቃወሚያና ከክሱ ይዘት አንጻር ተመርምሮ ብይን ሊሰጥ ይገባል እንጂ በክስህ ዘርዝረህ ያላቀረብከዉን አዲስ ማስረጃ ማቅረብ አትቺልም ሊባል አይገባም! ( የፍ/ሥ/ሥ/ቁ 245 )
👍11❤4
♧ ሰ.መ.ቁ. 212950 [ቅፅ 27]

♧ ተከሳሽ ይከላከል ከተባለ በኋላ በመከላከያ ማስረጃው ማስረዳት የሚጠበቅበት በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ነው ወይስ ጥርጣሬ መፍጠር ????

♧ በወንጀል የተከሰሰ ሰው መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ የሚታዘዘው በዓቃቤ ህግ ማስረጃ የተረጋገጠበትን ክስ እና ማስረጃን እንዲያስተባብል ሲሆን ማስተባበል ማለት ደግሞ የተከሳሹን የወንጀል ድርጊት እና ጥፋተኝነት አረጋግጠዋል በተባሉት ማስረጃዎች ላይ በእንድም ይሁን በሌላ መንገድ ጥርጣሬ እንዲፈጠር በማድረግ በማስረጃዎቹ የማስረዳት አቅም ላይ መተማመን እንዳይኖር ማድረግ በመሆኑ ከተከሰሰው ሰው የሚጠበቀው በመከላከያ ማስረጃው በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዳት ሳይሆን የዐቃቤ ህግ ማስረጃን አስመልክቶ ቀድሞ በተያዘው አቋም ላይ ጥርጣሬን መፍጠር ብቻ ስለመሆኑ ተወስኗል
❤12
#ምንጩ #ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ በማከማቸት #የሙስና ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ክስ የቀረበበት ተከሳሽ የማስረዳት ግዴታ ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከገለፀውና በማስረጃ ካረጋገጠው ውጭ ተከሳሽ ሌላ ገቢ የሚያገኝበት ስራ ወይም የገቢ ምንጭ ያለው መሆኑን #ብቻ ለፍርድ ቤቱ #በማሳየት የሚወሰን #ሳይሆን፣ #በዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ #ከተረጋገጠው ገቢ #ውጭ በእጁ እንደተገኘ የተረጋገጠው ገንዘብና ሀብት #ትክክለኛ #ምንጭ #ምን #አንደሆነ #የማስረዳት #ግዴታና #ኃላፊነት #ያለበት ስለመሆኑ
🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢

የሰበሩ የውሳኔ ትንታኔ⛑
💦💦💦💦

➤ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 419 ንዑስ አንቀጽ 1//ሀ/ እና /ለ/ ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻለው ዐቃቤ ሕግ የመንግስት ሠራተኛ የሆነው ወይም የነበረው ሰው ያገኝ የነበረውና የሚያገኘው ገቢ ምን ያህል እንደሆነና የመንግስት ሠራተኛው በራሱ ስምም
ሆነ በቤተሰቡ ስም ከሕጋዊ ገቢው ውጪ ይዞት የሚገኘውን የገንዘብና የንብረት ግምት የማስረዳት ግዴታ ያለበት መሆኑን በመግልፅ ተደንግጓል፡፡

➤በሌላ በኩል የመንግስት ሠራተኛ የነበረው ሰው ከነበረውና ከሚያገኘው ገቢ በላይ ይዞት የተገኘው ገንዘብ ወይም ሀብት ትክክለኛው ምንጭ ምን እንደሆነ የማስረዳት ግዴታ እንዳለበት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 419 ንዑስ አንቀጽ 1 ሶስተኛው ፓራግራፍ ፣ “… የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ወይም ያለው ንብረት ወይም የገንዘብ ምንጭ በእጁ እንዴት እንደገባ ለፍርድ ቤቱ ካላስረዳ በስተቀር” ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ይዞ በመገኘቱ ጥፋተኛ ተብለው በሕጉ የተደነገገው ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችል በመግለፅ ይደነግጋሉ፡፡

ከዚህም የምንረዳው ዐቃቤ ሕግ በግልፅ ከሚታወቀው ሕጋዊ ገቢ በላይ ነው በማለት በክሱ የተገለፀውንና በማስረጃ ያረጋገጠውን ሀብት ትክክለኛ ምንጭ የማስረዳት ግዴታ / Burden of Proof/ በተከሳሾች ላይ የሚወድቅ መሆኑን ነው፡፡

የተከሳሾች የማስረዳት ግዴታም ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከገለፀውና በማስረጃ ካረጋገጠው ውጭ ተከሳሽ ሌላ ገቢ የሚያገኝበት ስራ ወይም የገቢ ምንጭ ያለው መሆኑን ብቻ ለፍርድ ቤቱ በማሳየት የሚወሰን ሳይሆን፣ በዐቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ከተረጋገጠው ገቢ ውጭ በእጁ እንደተገኘ የተረጋገጠው ገንዘብና ሀብት ትክክለኛ ምንጭ ምን እንደሆነ የማስረዳት ግዴታና ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ከወንጀል ሕግ አንቀፅ 419 ንዑስ አንቀጽ 1 ሶስተኛው ፓራግራፍ ድንገጌ አቀራረፅና ይዘት ለመረዳት ይቻላል፡፡

➤ስለሆነም #ምንጩ #ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ በማከማቸት #የሙስና ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ክስ የቀረበበት ተከሳሽ የማስረዳት ግዴታ ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከገለፀውና በማስረጃ ካረጋገጠው ውጭ ተከሳሽ ሌላ ገቢ የሚያገኝበት ስራ ወይም የገቢ ምንጭ ያለው መሆኑን #ብቻ ለፍርድ ቤቱ #በማሳየት የሚወሰን #ሳይሆን፣ #በዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ #ከተረጋገጠው ገቢ #ውጭ በእጁ እንደተገኘ የተረጋገጠው ገንዘብና ሀብት #ትክክለኛ #ምንጭ #ምን #አንደሆነ #የማስረዳት #ግዴታና #ኃላፊነት #ያለበት ስለመሆኑ፡- የወንጀል ሕግ አንቀጽ 419 /1//ሀ/ እና /ለ/ መሠረት በማድረግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 137672 ህዳር 25 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል።
❤6👌1
"የማህበራዊ ፍርድ ቤት #ሥልጣን_ሳይኖረው የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ባይሻርም ተፈፃሚነት የለውም!"

በአገራችን የሕግ ሥርዓት ውስጥ የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የተቋቋሙት ቀላልና አነስተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ግጭቶችን ለመፍታት ነው። ነገር ግን፣ እነዚህ ፍርድ ቤቶች የሕግ ሥልጣን ከሌላቸው ጉዳይ ውስጥ ገብተው ውሳኔ ቢሰጡ ውጤቱ ምን ይሆናል?

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 256261 (ሰኔ 2017 ዓ.ም) በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የሚከተሉትን ነጥቦች ግልጽ አድርጓል፦

🔍 ዋና ዋና ነጥቦች፦

የሥልጣን ወሰን፦ የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የገጠር የእርሻ መሬትን በሚመለከት ክርክር አይተው የመወሰን የሥነ-ነገር (Subject Matter Jurisdiction) ሥልጣን የላቸውም።

የሕገ-መንግሥት ጥሰት፦ አንድ ፍርድ ቤት በሕግ ያልተሰጠውን ሥልጣን ተጠቅሞ ውሳኔ መስጠቱ የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 78(5) እና 40(3)ን የሚጥስ ተግባር ነው።

"ሳይሻር የቆየ ውሳኔ" ውጤት፦ የማህበራዊ ፍርድ ቤት ሥልጣን ሳይኖረው የሰጠው ውሳኔ፣ በወቅቱ በይግባኝ ባይሻርም እንኳ፣ ውሳኔው ከመሠረቱ የሕግ መሠረት የሌለው (Null and Void) በመሆኑ "ውሳኔው አልተሻረም" በሚል ምክንያት ብቻ ተፈፃሚ ሊሆን አይችልም።

የሰበር ትርጉም፦ ቀደም ሲል በሰ/መ/ቁ 105677 ላይ "የማህበራዊ ፍርድ ቤት ውሳኔ በይግባኝ ካልተሻረ ይጸናል" ተብሎ የተሰጠው ትርጉም፣ መደበኛ የሥነ-ሥርዓት ግድፈቶችን እንጂ የሥልጣን (Jurisdiction) ጉድለትን አይጨምርም።

💡 ትምህርቱ ምንድን ነው?

አንድ ፍርድ ቤት (በተለይም የማህበራዊ ፍርድ ቤት) በሕግ ያልተሰጠውን የዳኝነት ሥልጣን ተጠቅሞ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ፣ በማንኛውም ጊዜ ሊታረም እንደሚችልና ተፈፃሚነት እንደሌለው ሊታወቅ ይገባል።
"የሥልጣን ጥሰት በዝምታ አይጸድቅም!"

የማህበራዊ ፍርድ ቤት ሥልጣን ሳይኖረው የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ባይሻርም ተፈፃሚነት የለውም።

(ሰ/መ/ቁ 256261)
❤12
በቤት ሽያጭ ውል ላይ የቤቱ ስመ ሀብት በገዢ ስም ስለዞረ ብቻ ሻጭ ንብረቱን የመሸጥ ሕጋዊ መብት እንደነበረው ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም
🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛

➤በቤት ሽያጭ ውል ላይ ሻጭ ቤቱን ለማስተላለፍ የሚያስችል ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ሕጋዊ መብት እንዳለው ሊረጋገጥ ይገባል።

➤ይህ ካልተረጋገጠ የራስ ባልሆነ ንብረት ላይ የተደረገ ውል ውጤት አይኖረውም።

➤በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1195 መሠረት የማይንቀሳቀስ ንብረት በስሙ የተመዘገበለት ሰው የንብረቱ ባለቤት እንደሆነ ቢገመትም ይህ ግምት ግን በሌላ ማስረጃ ሊፈርስ የሚችል ነው።

➤የቤቱ ስመ ሀብት በገዢ ስም ስለዞረ ብቻ ሻጭ ንብረቱን የመሸጥ ሕጋዊ መብት እንደነበረው ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም።

➤የቤቱ ስመ-ሀብት በገዢው ስም መዛወሩ ብቻ ውሉን ሕጋዊ አያደርገውም በማለት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ.208266 ሚያዝያ 24/8/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል። ➡(ቅጽ 26)
❤18👏3
ዋስትና መከልከል
አዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና ማስረጃ መድብለ ሕግ ዐዋጅ ቁ.1410/2018 የዋስትና መብት ከመከልከል አኳያ ብዙ ለውጦችን አድርጎአል::
ለምሳሌ:-
1. #በሴቶችና ሕጻናት ላይ በተፈጸመ ወንጀል የተጠረጠረ ሰው በፖሊስ ዋስትና (police bond) ሊወጣ አይችልም::
*መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪውን የግድ ወደ ጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት በማቅረብ በዋስትና ጉዳይ ላይ ዳኛ ብይን እንዲሰጥበት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ (አንቀጽ 117(3)

2. #በሴቶችና ሕጻናት ላይ በተፈጸመ ወንጀል መጠርጠር/መከሰስ በፍ/ቤት ዋስትና ለመከልከል በቂ ምክንያት ነው:: አንቀጽ 139(2/መ)
*[በርግጥ ሴቶችና ሕፃናት በመድብለ ሕጉ ውስጥ ልዩ ትኩረት አግኝተዋል::]

3. #ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ ቋሚ አድራሻ ከሌለው ዋስትና ለመከልከል በቂ ምክንያት ነው:: (አንቀጽ 139(2/ሐ)::
*ስለዚህ ቋሚ አድራሻ አለመኖር ዋስትና ለመከልከል በቂ ምክንያት አይደለም የሚለው የሰበር ውሳኔ ተሽሮአል::
*ያለው አማራጭ "ቋሚ አድራሻ"ን ላይ በሰበር ሰፋ አድጎ ከዋስትና ሕገ መንግሥታዊ መርኅነት አኳያ ማስተርጎም ብቻ ነው::

4. #ተጠርጣሪው/ተከሳሹ የተጠረጠረበት ወይም የተከሰሰበት ወንጀል አፈጻጸም አደገኛ ከሆነ ወይም ወንጀሉ አሰቃቂ በመሆኑ ምክንያት ተጠርጣሪው/ተከሳሹን በዋስትና መልቀቅ ዜጎች በፍትሕ ላይ ያላቸው አመኔታ የሚያሳጣ ነው ፍ/ቤቱ ካመነ ዋስትና ሊከለክል ይችላል::
*ይህም ከPresumption of innocence ጋር የሚጋጭ ይመስላል::

5. #በተደጋጋሚ በጽኑ እሥራት የሚያስቀጣ ወንጀል መፈጸም ዋስትና ያስከለክላል:: (አንቀጽ 139(2/ሀ)
*ያልገባኝ፥ የቀድሞ የወንጀል ጥፋተኛነት ባሕርይ (previous conviction) ከፍርድ በፊት ስለ ዋስትና ብይን ለመስጠት ተገቢነት ሊኖረው ነው?

6. #በሞት ወይም፣ 15 ዓመት እና ከዚያ በላይ ሊያቀጣ በሚችል ሰው በሞተበት ወንጀል የተጠረጠረ/የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብት የለውም:: (አንቀጽ 138(2,3)
*ይህ እንኳን ነባር ነው—የቀድሞውን የወ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 63 ያጸና::
❤8👍1
በአዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች ...

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ዘመኑን የዋጁ እና የሰብዓዊ መብቶችን አጠባበቅ የሚያጠናክሩ በርካታ የሕግ ማዕቀፎች ተካተውበታል፡፡

ከ6ዐ ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 በመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል።

ከተሻሻሉ ዋና ዋና ሕጎች መካከል የዲጂታል ማስረጃዎች ዕውቅና አንዱ ሲሆን ይህም የቴክኖሎጂ ለውጥን ያገናዘበ የሕግ ማዕቀፍ ነው፡፡

ለአብነትም የቪዲዮ ምስሎች፣ የድምፅ ቅጂዎች፣ የኮምፒውተር መረጃዎች እና የማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክቶች እንደ ትክክለኛ ማስረጃ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ሕጋዊ መሠረት ሰጥቷል።

ሌላው የተሻሻለው የምርመራ ዘዴዎች እና የሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከት ሲሆን፤ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ያላቸው መብት፣ የምርመራ ጊዜ ገደብ እና በምርመራ ወቅት ጠበቃ የማግኘት መብታቸው በግልጽ ተቀምጧል።

በዚህም መሰረት አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ሲውል ጠበቃው እስኪመጣ ቃሉን ያለመስጠት መብቱ የሚጠበቅለት ሲሆን የተጠርጣሪው የምርመራ ገደብ ከአራት ወር እንዳይበልጥ በማድረግ ተጠርጣሪ ለረጅም ጊዜ በምርመራ እንዳይቆይ ያስችላል።

የተጎጂዎችን መብት በሚመለከት የወንጀል ድርጊት የተፈጸመባቸው ሰዎች በፍትሕ ሂደቱ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ፣ ጉዳታቸው የሚካካስበት መንገድ እና የሚደረግላቸው ጥበቃ ትኩረት አግኝቷል።

ሌላው የዋስትና መብትን እንደ መሠረታዊ መብት መከልከልን እንደ ልዩ ሁኔታ የሚመለከት ሕግ ሲሆን፤ በዚህም ሕጉ ግልጽ የሆኑ የዋስትና ዓይነቶችን አስቀምጧል።

እነሱም በግል ማረጋገጫ በሰው ዋስትና፣ በንብረት ዋስትና ወይም በገንዘብ ማስያዝ የሚልን አካትቷል።

ሌላኛው የምስክሮች እና የጠቋሚዎች ጥበቃ የሚመለከት ሲሆን በከባድ ወንጀሎች ላይ መረጃ የሚሰጡ ጥቆማ ሰጪዎች እና ምሥክሮች ከበቀል ወይም ከጥቃት እንዲጠበቁ የሚያስችል የሕግ ከለላ መስጠትን ይመለከታል።

በተመሳሳይ የዐቃቤ ሕግ የክስ ድርድርን በተመለከተ አንድ ተጠርጣሪ ወይም ተከሳሽ ጥፋተኛነቱን አምኖ ከዐቃቤ ሕግ ጋር በመደራደር ቅጣቱ እንዲቀልለት ወይም ክሱ እንዲቋረጥ የሚያስችል ሥርዓት በሕጉ እንዲካተት ተደርጓል።

በዚህም በአዋጁ ዐቃቤ ሕግ ክስ ለማንሳት የሚችልባቸው ምክንያቶችና ቅድመ ሁኔታዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል።

የክስ ድርድር በሚመለከት ክስ ከመመሥረቱ በፊት ወይም ክስ ከተመሠረተ በኋላ ፍርድ እስከሚሰጥ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ ጥፋተኛነቱን አምኖ ከዐቃቤ ሕግ ጋር ሊደራደር ይችላል።

የድርድር ዓይነቶችን በሚመለከት ከባድ የሆነውን ክስ ወደ ቀለል ያለ የወንጀል ዓይነት በመቀየር መደራደር እንዲሁም በቅጣት ድርድር በክሱ ላይ ተስማምቶ ቅጣቱ እንዲቀልለት መደራደር የሚል ይገኝበታል።

በዚህም በድርድሩ የተደረገው በፈቃደኝነት መሆኑን፣ ተከሳሹ መብቶቹን መረዳቱን እና ድርድሩ የሕዝብን ጥቅም የማይጎዳ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ማረጋገጥ አለበት።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ድርድሩን ውድቅ የማድረግ ሥልጣን ያለው ሲሆን በተለይም ዐቃቤ ሕግ የክስ ድርድር ሲያደርግ የወንጀል ተጎጂዎችን ፍላጎትና ስሜት ግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት ሕጉ ይደነግጋል።

ተጎጂው ካሳ የሚያገኝበት መንገድም በድርድሩ ውስጥ የተከካተተ ሲሆን ይህም ተከሳሹ የቅጣት ቅናሽ እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም ድርድሩ መንግሥት ለምስክሮች እና ለረጅም ክርክር የሚያወጣውን ወጪ ይቆጥባል፣ ተጎጂዎች ደግሞ የፍርድ ሂደቱን ሳይጠብቁ ካሳ ወይም ይቅርታ ሊያገኙ ይችላሉ።

በአጠቃላይ እነዚህ ለውጦች ፍትሕን በፍጥነት ለመስጠት እና የተጠርጣሪዎችንም ሆነ የተጎጂዎችን መብት በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ማሻሻያዎች ናቸው፡፡

ይህም በሀገሪቱ የፍትሕ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ አፈጻጸሙም ከሕገ መንግሥቱ እና ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

FBC በታሪክ አዱኛ
❤17
7 (ሰባት) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ የሰበር ውሳኔ፤ መዝገብ ቁጥር 271726

ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 249795 ላይ “ሠራተኛዉ በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ቢቀር እንኳ ከሥራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሠሪዉ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) ሳይሰጥ የሥራ ዉልን ለማቋረጥ እንደማይችል” ተገልጾ የተሰጠው የህግ ትርጉም ተለውጦ “የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ለ) ድንጋጌ ሠራተኛዉ በዚሁ አዋጅ ከተመለከቱ እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ዉጭ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ላይ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ዉልን ያለ ማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ይቻላል” በሚል ተተርጉሟል፡፡

የውሳኔውን ሙሉ ይዘት በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ከቴሌግራም ቻናላችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
👍14❤4
ከመንፈስ መጫን ምክንያት ዉጪ ስጦታን ለመቀነስ ወይም ለመሰረዝ የሚቀርብ ክስ ይርጋ 10 ዓመት መሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰመቁ 232628 የሰጠዉ የህግ ትርጉም።

የፍ/ሕግ ቁጥር 2441(1) ይዘት ስጦታ እንዲቀነስ ወይም እንዲሰረዝ የሚቀርብ ጥያቄ፣ ስጦታው ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ለዳኞች ካልቀረበ በስተቀር ዋጋ የለውም ይላል።

የክርክሩ አመጣጥ

አመልካች በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ሲሆን፣ 1ኛ ተጠሪ በጀርመንኛ የተጻፈ ውክልናን ትርጉም በማዛባት የአመልካችን የውርስ ድርሻ ለ2ኛ ተጠሪ በስጦታ አስተላልፈዋል በማለት የስጦታ ውሉ እንዲፈርስ ክስ አቅርበዋል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው አመልካች ቀደም ብለው ድርሻቸውን መልቀቃቸውን እና ክሱ በሁለት ዓመት ይርጋ ይታገዳል በማለት ተከራክረዋል።

የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ

የስጦታ ውልን ለመቃወም ያለው የይርጋ ጊዜ 2 ዓመት ነው በሚል ክሱን በይርጋ ውድቅ አድርገውታል።

የሰበር ሰሚ ችሎቱ ውሳኔው

ምንም እንኳን ይህ የሕግ ቁጥር (2441) በስጦታ ላይ የሁለት ዓመት ገደብ ቢያስቀምጥምየሰበር ችሎቱ
በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2441 የተመለከተው የ2 ዓመት ይርጋ የሚያገለግለው በስጦታ ሰጪው ላይ "የመንፈስ መጫን" (Undue Influence) ተፈጥሮ የተደረገን ስጦታ ለማፍረስ በሚቀርብ ክስ ላይ ብቻ ነው።

ከመንፈስ መጫን ውጭ ባሉ ሌሎች ምክንያቶች (ለምሳሌ በውክልና ሥልጣን ያለአግባብ መጠቀም) የሚቀርብ የስጦታ ውል ለማፍረስ ወይም ለመቀነስ የሚቀርብ ክስ በሕግ ቁጥር 1845 መሠረት በ10 ዓመት የይርጋ ደንብ የሚመራ መሆኑን ችሎቱ ወስኗል።
👇👇
https://t.me/ethiolawtips
❤13👏2