#ቅዱስገብርኤል
#ሐምሌ19

በውቢቷ ሀዋሳ በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን በተገኘበት እየተከበረ ይገኛል።

ከማለዳ ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም ከሀዋሳና ከአካባቢው የመጡ ምዕመናን በቤተክርስቲያን በመገኘት በዓሉን በቅደሴ፣ በጸሎት፣ በዝማሬ እና በተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓቶች እያከበሩ ይገኛሉ።

በስፍራው የኃይማኖት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን እና ምዕመናን በኦሮቶዶክሳዊ ስርዓት አልባሳት ደመቀው በዓሉን እያከበሩ ሲሆን በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢና በአካባቢው እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተሰብስቧል።

የከተማው ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የከተማው አመራሮችም በበዓሉ ላይ የተገኝተዋል።

የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል በዓል በሀዋሳ በየዓመቱ በደማቅ መንፈሳዊ ድባብ የሚከበር ሲሆን፣ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚመጡ ምዕመናንን የሚሰባሰቡበት ታላቅ ኃይማኖታዊ በዓል ነው።

[ቲክቫህ]
1
ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ

በሚዲያው ዘርፍ የላቀ ችሎታ እና የፈጠራ አቅም ካሎት፣ አብረውን እንዲሠሩ እንጋብዛለን! በሚከተሉት የሥራ መደቦች ላይ ብቁ አመልካቾችን አወዳድረን መቅጠር እንፈልጋለን ሲል አፍሪካ ቲቪ ገልጿል ።

🎙 1. ፕሮግራም አቅራቢ (Host)

📱 2. የዲጂታል ይዘት አዘጋጅ (Digital Content Producer)

🎬 3. የይዘት አዘጋጅ (Content Producer)

ፍላጎቱ እና ልምዱ ካሎት አሁኑኑ ለማመልከት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ፦

📌 ለፕሮግራም አቅራቢ፡- https://docs.google.com/forms/d/11tw9GUeiibzFZi_UtgyAzX3UTuHiP2ZP3IezM4GQBvs/edit

📌 ለዲጂታል ይዘት አዘጋጅ፡ https://docs.google.com/forms/d/1nXvARerViy_wbH7RJKRLCtS9PjQwyvGs9c7uYzUFY04/edit

📌 ለይዘት አዘጋጅ፡ https://docs.google.com/forms/d/1RuGGykR_oifb-udFZ5CPpeFzPtRkEWlg84tjg-e7FrY/edit

የፈጠራ ባለሙያዎች የተሰባሰቡበትን የሚዲያ ቡድናችንን ዛሬውኑ ይቀላቀሉ!

አፍሪካ ቲቪ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኢስላማዊ የቲቪ ቻናል
በቀድሞ ዙር ያመለጣችሁ ሐምሌ 25 ለሚጀምረው የጋዜጠኝነት ሥልጠና መመዝገብ ትችላላችሁ!
ከዲጂታል ፈርቀዳጅነት እስከ ብስክሌት ስፖርት መሪነት! 🚴‍♂️🇪🇹

​የድሬ ቲዩብ (DireTube) እና የፋናን ፔይ (FananPay) መስራችና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢኒያም ነገሱ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ!

​ፌዴሬሽኑ ባካሄደው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አቶ ቢኒያም ነገሱ በቀጣዮቹ 4 ዓመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ በአብላጫ ድምፅ መርጧቸዋል::

​በቴክኖሎጂውና በዲጂታል ሚዲያው ዘርፍ የነበራቸውን የፈጠራና የስራ ፈጠራ (Entrepreneurship) ክህሎት አሁን ደግሞ ወደ ስፖርቱ ዘርፍ አመራርነት መጥተዋል።

አቶ ቢኒያም ከምርጫው በኋላ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሰጡት አስተያየት "የኢትዮጵያ ብስክሌት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማድረግ እሰራለሁ" ብለዋል።

​በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሀገራዊ ተጽዕኖ መፍጠር የቻሉት ቢኒያም ነገሱ፣ የኢትዮጵያን የብስክሌት ስፖርት ወደ አዲስ የስኬት ምዕራፍ እንደሚያሸጋግሩት ባለሙሉ ተስፋ ነን!

​እንኳን ደስ አለዎት! 💐

#BiniamNegessu #DireTube #FananPay #EthiopianCyclingFederation #EthiopianSports #Ethiopia #TechToSports #Leadership #CyclingEthiopia #BreakingNews #EthiopianNews