Ethio Journal ኢትዮ ጆርናል 🇪🇹
Photo
📰 የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሂደት፡ የኢሌክቶራል ሥርዓት አማራጮች፣ የቃለ-ጉባኤ ያዦች ስጋት እና የአበል ክፍያ ውዝግብ
1. የፖለቲካ እና የምርጫ ሥርዓት አጀንዳዎች
በምክክር ሂደቱ የምርጫ ሥርዓትን በተመለከተ “የአብላጫ ድምጽ”፣ “ተመጣጣኝ የውክልና ሥርዓት”እና “ቅይጥ የውክልና ሥርዓት”የሚሉ አማራጮች ለውይይት ቀርበዋል።
በተጨማሪም የፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀትን በተመለከተ በሁለት መሠረታዊ ሃሳቦች መካከል ያለው ልዩነት በምክክር እንዲፈታ ተጠይቋል።
👉አንድ ወገን፡ብሔርን መሠረት ያደረገ አደረጃጀት ቀርቶ ወደ ዜጋ ተኮር የፖለቲካ ሥርዓት እንዲሸጋገር ያንሰዋል።
👉ሌላው ወገን፡የብሔር አደረጃጀት የብሔር ብሔረሰቦችን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ሊነካ አይገባም የሚል ጥብቅ አቋም አለው።
2. የቃለ-ጉባኤ ያዦች የሥራ ዋስትና ስጋት
ኮሚሽኑ 50 አባላት ባሏቸው ንዑሳን ቡድኖች የሚደረጉ ውይይቶችን ለመሰነድ ከከፍተኛ ትምህርትና ሌሎች ተቋማት የተውጣጡ 256 ቃለ-ጉባኤ ያዦችን አሰልጥኖ ማሰማራቱ ይታወሳል።
ሆኖም አንዳንዶቹ ተቋማት ሰራተኞቻቸው (ቃለ-ጉባኤ ያዦቹ) ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ጥሪ በማድረጋቸው ምክንያት በሰራተኞቹ ዘንድ የሥራ ዋስትና ስጋት ፈጥሯል።ኮሚሽኑ ጉዳዩን በተመለከተ ከተቋማቱ ጋር እንደሚነጋገር አስታውቋል።
3. የክልሎች ከፍተኛ የአበል ክፍያ እና የወጪ ዝርዝር
ኮሚሽኑ የተሳታፊዎችን ወጪ ሙሉ በሙሉ እንደሚሸፍን ባሳወቀበት ሁኔታ፣ ባልተለመደ መልኩ የተወሰኑ ክልሎች ለተመካካሪዎቻቸው ተጨማሪ ከፍተኛ የአበልና የትራንስፖርት ክፍያ መፈጸማቸው ታውቋል።
የተከፈለው የአበል መጠን እንደ ክልሉ፡-
👉ሶማሌ ክልል፡ለአብዛኞቹ ተሳታፊዎች እስከ 80,000 ብር
👉አፋር ክልል፡እስከ 10,000 ብር
👉ኦሮሚያ ክልል፡ከአንዳንድ አካባቢዎች ለተወከሉ እስከ 9,000 ብር
👉ሲዳማ ክልል፡5,000 ብር
በተጨማሪም ለምክክሩ ከፍተኛ በጀት መመደቡ የተገለጸ ሲሆን፣ ተመካካሪዎች ላረፉባቸው እንደ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮ-ቻይና ኮሌጅ እና ሌሎች ሆቴሎች ከፍተኛ ክፍያ እየተፈጸመ ይገኛል።
(ምንጭ፡ ዋዜማ)
#ኢትዮጵያ #ሀገራዊምክክር #የኢትዮጵያሀገራዊምክክርኮሚሽን #ዋዜማ #ፖለቲካ #የምርጫሥርዓት #ዜጋተኮር #ብሔርተኝነት #ቃለጉባኤያዦች #የአበልክፍያ #Ethiopia #NationalDialogue #EthiopianNationalDialogueCommission #WazemaRadio #EthiopianPolitics

❤2
ለምክክር ጉባዔ መጥታ ወንድ ልጅ የተገላገለችው እናት የልጇን ሥም "ኮሚሽን" አለችዉ
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወክላ በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች።
ባሳለፍነው ሳምንት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በመሳተፍ ላይ የነበረች የጋምቤላ ክልል ተወካይዋ ወ/ሮ ክርኑዶ ኡጁሉ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላ ስሙም "ምክክር" መባሉ የሚታወስ ነው።
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኡራ ወረዳ የመጣችው ሌላኛዋ የምክክሩ ተሳታፊ ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ በተመሳሳይ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን፥ ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች።
የመውለጃ ጊዜዬ እየደረሰ መሆኑን ባውቅም ለኢትዮጵያዊያን አብሮነትና ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ በሚመከርበት በዚህ ጉባኤ መሳተፍ አለብኝ በሚል አቋም ተገኝቻለሁ ብላለች፡፡
በጉባኤው አጀንዳዎች ላይ ለሀገራችን ይበጃል የምትለውን ሀሳብ በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ስታደርግ የቆየች ሲሆን፥ በዚህ ታሪካዊ ወቅት ልጇን በመገላገሏ መደሰቷን ገልጻለች።
ዘገባዉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዲያ ነዉ።

🚨 የ100 ዶላር ውዝግብ፦ የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አበል አልቀበልም አለ!
ከአራት ወራት በፊት በቱርክ በተካሄደው "ፍሬንድሺፕ ካፕ" ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ውድድሩን 4ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ ይታወሳል።ይሁን እንጂ ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላ የተፈጠረው የኪስ ገንዘብ (አበል) ውዝግብ አሁንም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።
እውነታው እና የሁለቱም ወገኖች ምላሽ፦
የተጫዋቾች ቅሬታ፦
ከሀገር ሲወጡ የዕለት አበል እንደሌላቸው ቀድሞ እንዳልተነገራቸውና ለ10 ቀናት ቆይታ ቢያንስ $500 ዶላር ይጠብቁ እንደነበር የገለጹት 22ቱ ተጫዋቾች፤ የተሰጣቸው $100 ዶላር "በጣም አነስተኛ ነው" በማለት በጋራ "አንቀበልም" ብለው መልሰዋል።
(የቡድኑ አሰልጣኞች እና ሌሎች የልዑክ አባላት ግን ክፍያውን ተቀብለዋል)።
የፌዴሬሽኑ ምላሽ፦
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን በበኩላቸው፤ ጉዞው አስቀድሞ በዕቅድ ውስጥ ያልነበረና በጀት ያልተያዘለት እንደነበር ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ተጫዋቾቹ ይህንን ዓለም አቀፍ ዕድል እንዳያጡ በማሰብ ከራሳቸው ተቀናሽ የተደረገ $100 ዶላር የሰጧቸው መሆኑን እና ሁኔታው ቀድሞ በግልጽ ተነግሯቸው እንደነበር አስረድተዋል።
የገንዘቡ ፍጻሜ፦
ተጫዋቾቹ በተሰጣቸው አበል ባለመስማማታቸው ገንዘቡን አንቀበልም ማለታቸውን ተከትሎ ዶላሩ ሙሉ በሙሉ ወደ ፌዴሬሽኑ አካውንት መመለሱን ፌዴሬሽኑ አረጋግጧል።
#የኢትዮጵያእግርኳስ #የሴቶችእግርኳስ #U18Women #የስፖርትዜና #EFF #EthiopianFootball #SportsNews #LucyTeam #ኢትዮጵያ

❤1
Ethio Journal ኢትዮ ጆርናል 🇪🇹
Photo
የኢትዮ ቴሌኮም የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ዋና ዋና ነጥቦች 📊
🔹 ጠቅላላ ገቢ፡215.82 ቢሊዮን ብር (የ33.2% ዕድገት)
🔹 ያልተጣራ ትርፍ (EBITDA)፡38.7 ቢሊዮን ብር
🔹 ጠቅላላ ደንበኞች፡90.12 ሚሊዮን
🔹 የቴሌብር ተጠቃሚዎች፡ 60.6 ሚሊዮን (4.19 ትሪሊዮን ብር ግብይት)
🔹 የ4ጂ ሽፋን፡82.23% (በ1,200 ከተሞች)
🔹 የ5ጂ ሽፋን፡ በ33 ከተሞች (340 ጣቢያዎች)
🔹 ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፡20.19 ሚሊዮን ዜጎች በበጀት ዓመቱ ተመዝግበዋል
📌 ልዩ ስኬት፡በኩባንያው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳታና ኢንተርኔት ገቢ (31.1%) ከድምፅ አገልግሎት ገቢ በመበለጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዟል።
#EthioTelecom #Telebirr #DigitalEthiopia #TelecomNews #Ethiopia #TechNews #ESX

🚨 «ቃል ተሽሮብናል፤ ፍትህ እንፈልጋለን!» — የመንዝ አካባቢ ነዋሪዎች
በ1.9 ቢሊዮን ብር በጀት በታህሳስ 2011 ዓ.ም ተጀምሮ በ3 ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው የ «ጣርማበር – ሞላሌ – ወገሬ – ሰፌድ ሜዳ» 118.87 ኪሎ ሜትር የመንገድ ፕሮጀክት፣ በ8 ዓመታት ውስጥ ከ25% በላይ ማደግ ሳይችል ከሐምሌ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ግንባታው ሙሉ በሙሉ መቆሙ ተገለጸ።
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት መቋረጥ በአካባቢው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ያስከተለ ሲሆን፦
👉 በጤናው ዘርፍ፦ ነፍሰ ጡር እናቶችና ከባድ ሕሙማን በወቅቱ ወደ ሆስፒታል መድረስ ባለመቻላቸው ለሕይወት መስዋዕትነት እየተዳረጉ ይገኛሉ።
👉 በኢኮኖሚው ዘርፍ፦ አርሶ አደሩ ምርቱን (ወተት፣ ቅቤና እህል) ወደ ገበያ ማውጣትና ማዳበሪያ በጊዜ ማግኘት ተስኖታል።
👉 በትራንስፖርት፦ ከፍተኛ የተሽከርካሪ ብልሽትና የታሪፍ ጭማሪ በህዝቡ ላይ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ጫና ፈጥሯል።
የመንገድ ስራ ጨረታውን አሸንፎ የነበረው መከላከያ ኮንስትራክሽን በግልፅ ባልታወቀ ምክንያት ስራውን አቋርጦ የထጣ ሲሆን፣ ለመንገዱ የቀረቡ ቁሳቁሶችም ባዶ ቦታ ላይ ወድቀው ይገኛሉ።
በአካባቢው ከነበረው መጠነኛ የፀጥታ ችግር ይልቅ የውል አስተዳደር፣ የተቋራጭ አቅም ማነስና የቢሮክራሲ መጓተት ለችግሩ ዋና ምክንያቶች መሆናቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ህዝቡ የመልማት ፍትሃዊ ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝና መንግስት የቆመውን ፕሮጀክት ትኩረት ሰጥቶ እንዲያስጀምርለት በጥብቅ ይጠይቃል።
✍️ ዋሱ መሐመድ
#የመንዝመንገድ #ጣርማበር #ሞላሌ #ሰሜንሸዋ #የመንገድግንባታ #የህዝብድምፅ #ኢትዮጵያ #ERA #ልማት #ፍትህ #Ethiopia #NorthShewa #Menz #Infrastructure #EthiopianRoadsAdministration

🎉 የታላቅ ስኬት ስጦታ ከኢትዮ ቴሌኮም!
ኢትዮ ቴሌኮም የ2018 በጀት ዓመትን በ215.8 ቢሊየን ብር ገቢ በላቀ ስኬት ማጠናቀቁን ተከትሎ፣ ለውድ ደንበኞቹ የደስታ መግለጫ ስጦታ ማዘጋጀቱን ገልጻል!
🎁 የስጦታው ዝርዝር፡
🔹 1.5 GB የኢንተርኔት ዳታ
🔹 15 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ
🔹 30 የጽሑፍ መልዕክቶች (SMS)
⏰ አገልግሎቱ የሚቆይበት ጊዜ፡
📌 ቀን፡ እስከ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም
📌 ሰዓት፡ ከሌሊቱ 6:00 እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት
#EthioTelecom #FreeGift #Telebirr #Ethiopia #DigitalEthiopia #TechNews

" የአንድ አክስዮን ዋጋ ከ300 ብር በአሁኑ ወቅት ወደ 852 ብር ከፍ ብሏል " - ኢትዮ ቴሌኮም
• እስካሁን ከቀረቡ 47ሺ የሚጠጉ የአክሲዮን ግዢ ጥያቄዎች ውስጥ 96 በመቶ የሚሆኑት አክሲዮኖች የባለቤትነት ማረጋገጫ አግኝተዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት በፋይናንስ አፈጻጸም፣ በሀብት እድገትና በካፒታል ገበያ ተሳትፎው የተሻለ ስኬት ማስመዝገቡን የበጀት አመት አፈጻጸሙን ይፋ ሲያደርግ ጠቅሷል።
ይፋ በተደረገው መሰረትበሪፖርቱ የኩባንያው ጠቅላላ ሀብት (Total Assets) የ27 በመቶ እድገት በማሳየት 420 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል።
ይህ እድገት የተመዘገበው ኩባንያው በመሠረተ ልማት፣ በዲጂታል ፕላትፎርሞችና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ባደረገው ኢንቨስትመንት መሆኑ ገልጿል።
ይህም ለባለአክሲዮኖችና ለባለድርሻ አካላት ከፍተኛ እሴት የሚፈጥር መሆኑን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይፋ አድረገዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ሕዝባዊ አክሲዮን ማኅበርነት ከተሸጋገረ በኋላ በግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው የሁለተኛ ደረጃ የአክስዮን ገበያ ግብይት የአንዱ አክስዮን ዋጋ በ300 ብር የተጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ወደ 852 ብር ከፍ ማለቱን ተገልጿል።
እስካሁን ድረስ ወደ 47,000 የሚጠጉ የአክሲዮን ግዢ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ 96 በመቶ የሚሆኑት አክሲዮኖች የባለቤትነት ማረጋገጫ (Share Dematerialization) ሂደት መጠናቀቁ በዛሬው ዕለት ተገልጿል።

🏛️ መንዝ እና መረሃቤቴ — ከጀግንነትና ታሪክ ማዕበል እስከ ልማት ጥያቄ!
"መንዜው" ሲባል ወይም "መሬ" ተብሎ ሲጠራ በኩራት የማያብጥ፣ በጀግንነቱና በማንነቱ የማይኮራ የለም! "መሬ" የሚለው ስም ብቻውን ድንበር ተሻግሮ የታወቀ፣ የጀግንነትና የቁርጠኝነት መግለጫ ነው።
🌄 መንዝ እና መረሃቤቴ ምን አላቸው?
በተፈጥሮና በታሪክ: የጓሳ ጥብቅ ማህበረሰብ ስፍራ፣ የአሎባህር፣ የአፍቀራ ገደል፣ የታላቂቷ ተጉለትና ሞፈር ውሃ ውበት ለታጠቀ ይቅርና አርጩሜ ለያዘ ሰው ልብ ያሞቃል።
በገዳማትና በሃይማኖት: እመጓ ኡራኤል፣ እርባራ መድኃኔዓለም፣ ዘብር ገብርኤል እና የበርካታ ፃድቃንና ቅዱሳን አስክሬን የሚገኝበት የፈውስ ምድር ነው።
በባህልና በምግብ: የበርኖስና የባና ብርድ ልብስ ማቂያ፣ በዋንጫ ከቀረበ አራት ቀን ከሞላው እርጎ ጋር የሚበላው ደስ የሚል የደጋ ገብስ ጥረሾ... በፆም እንኳን ምራቅ የሚያስውጥ የታላቅ ባህል መገኛ!
በጀግንነትና በሀገር ሰሪነት: መንዝ አልሞ ተኳሽ፣ ቅንድብ በእርሳስ የሚላጭ፣ በንጉሳውያን ታሪክ እነ ነጋሲ አንባን ያፈራ፣ ሀገር በመገንባትና በማቆም ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም የሆነ ህዝብ ነው።
🛣️ ታዲያ የልማቱ ጥያቄ ወዴት ደረሰ?
የመንዝ ህዝብ በንጉሱም ዘመን፣ በደርግም ሆነ በኢህአዴግ ጊዜ የሚገባውን ያህል ልማት አላገኘም። በተለይም የመንገድ እጦት ለህዝቡ ትልቅ እንግልት ሆኖ ቆይቷል።
በአንድ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዘመን በአገር ሽማግሌዎች ጥረት መንገዱ እንዲጀመር ተደርጎ፣ ስራው ለትልቅና ለሚከበር ተቋም ተሰጥቶ እንደነበር ይታወቃል። ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች፣ በአመራሮች ዘንድ በነበረ መሸኮርመም እና በነበሩ ችግሮች ምክንያት መንገዱ ሳይጠናቀቅና ህዝቡ ሳይገላገል ዘመናት አልፈዋል።
"ልማትን መጠየቅ መሰልጠን እና መብትን ማስከበር እንጂ መነቋቆር አይደለም!"
ዛሬ ደርግም የለም፣ ወያኔም የለም! ሀገራችን ደግሞ ፊቷን ወደ ልማት በዞረችበት በዚህ ወቅት፦
የመንዝ እና የመረሃቤቴ እናቶች እስከ መቼ በእንግልት ይኖራሉ?
ከአካባቢው የተመረጡና ስልጣን ላይ ያሉ አመራሮቻችን የህዝቡን እውነተኛ እንግልት ለምን አያቀርቡም?
ይሄን የጣርማበር መገንጠያ እና አካባቢውን መንገድ በምስል እንኳን አዘጋጅቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚያቀርብ አመራር ታጣ?
እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ህዝብ የሚያንገላታ መንገድ በምስል እንኳን ቢያዩት፦ "እናቶቼ እኔ እያለሁ በእንግልት አይሞቱም" ብለው ወዲያውኑ መፍትሔ እንደሚሰጡ አንጠራጠርም። ግን ማን ያስረዳ? ማን ያቅርበው?
💡 የመፍትሔ ሃሳብና ጥሪ፦
መንዝ የኢትዮጵያ ማዕከልና እንብርት ላይ የሚገኝ ምድር ነው። ከደብረ ብርሃን በጅሁር በኩል አድርጎ በቀጥታ ወደ መንዝ፣ ከዛም ወደ ወሎና ጎጃም የሚያያይዘው መንገድ ቢሰራ ለቀጠናው ኢኮኖሚ ትልቅ መነቃቃት ይፈጥራል።
የሌሚ - ደብረ ብርሃን መንገድ እንቅስቃሴና የሌሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ መምጣት መልካም መነቃቃት ፈጥሯል። ለአቶ ብዙአየሁ፣ ለዶክተር ደረጀ፣ ለፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፣ ለሀገር ሽማግሌዎችና ለአርሶ አደሮቻችን ምስጋና ይገባቸዋል።
አሁንም ቢሆን ወደ ዓለም ከተማ የሚወስደው መንገድና አምስቱም መንዞች ዘላቂ የመንገድ መፍትሔ ይፈልጋሉ።
በመሆኑም፦
ባለሀብቶችና ምሁራን፦ ከአካባቢው የወጣችሁ ተወላጆች ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር በመምከር ድምፅ ሁኑ።
አመራሮች፦ ከስልጣን ስጋት ወጥታችሁ የህዝቡን የልማት ጥያቄ በግልጽ አቅርቡ።
ህዝባችን፦ እንመካከር፣ እንጠይቅ፣ እንተባበር! መንገድ ማለት ህይወት ነው፤ ያለ መንገድ ኑሮ ዝግ ነው።
✍️ ባለሀገሩ ተሾመ (ከሸዋ)
ፈጣሪ ሀገራችንን ይባርክ፤ ይጠብቅ! አሜን።
#Menz #Merehabete #Shewa #ShewaEthiopia #Guassa #GatwayToShewa #Ethiopia #Development #Infrastructure #AmharaRegion #CultureAndHeritage #EthiopianRoads

እናት ፓርቲ በዓባይ ቅድስት አርሴማ ገዳም ላይ የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት አወገዘ፤ የመንግሥትን ማብራሪያ ጠየቀ
አዲስ አበባ — በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዓባይ ቅድስት አርሴማ ገዳም ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ እናት ፓርቲ ድርጊቱን አጥብቆ እንደሚያወግዝ ባወጣው የአቋም መግለጫ አስታወቀ።
እንደ እናት ፓርቲ መግለጫ ከሆነ፣ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ምክንያት፦
👉የሰው ሕይወት ጉዳት፦ 2 መነኮሳት ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ 14 እናቶች ደግሞ ከባድ ቁስለት አስተናግደው በመካነ ሰላምና በደሴ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ።
👉የንብረት ውድመት፦ የገዳማውያኑ የዓመት ቀለብ፣ የማብሰያ ቁሳቁስ፣ የውኃ ታንከር እና የውኃ ማስተላለፊያ መስመሮች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል።
እናት ፓርቲ ድርጊቱ «ሥርዓታዊ እና በጥላቻ ላይ የተመሠረተ ነው» ሲል የገለጸ ሲሆን፣ መንግሥት ለተፈጸመው ጥቃት ሙሉ ኃላፊነት እንዲወስድ፣ ስለ ድርጊቱ የቪዲዮና የፎቶ መረጃዎች ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ እና ለተጎዱት ገዳማውያን አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።
በጉዳዩ ላይ ከመንግሥትም ሆነ ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም። (ስለ ክስተቱ ዝርዝር ሁኔታ እና ስለ ጥቃቱ አመጣጥ ከመንግሥት ወይም ከገለልተኛ አካላት ተጨማሪ ማብራሪያ እንደተገኘ የምናቀርብ ይሆናል።)
#እናት_ፓርቲ #የዓባይ_ቅድስት_አርሴማ_ገዳም #ደቡብ_ወሎ #ቦረና_ወረዳ #የድሮን_ጥቃት #የጸጥታ_አካላት #የኢትዮጵያ_ዜና #ኢትዮጵያ #ወቅታዊ_መረጃ #EnatParty #Ethiopia

ነጃሺ ኢስላማዊ ማኅበር በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው አልተወከልኩም ሲል ቅሬታ አቀረበ!
እየተካሄደ በሚገኘውና ታሪካዊ ሂደት ባለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ "አልተወከልኩም" ሲል የነጃሺ ኢስላማዊ ማኅበር ቅሬታ ማቅረቡን ሀራምቤ ሬዲዮ ዘግቧል ።
ማኅበሩ አንገብጋቢ ባላቸው ጉዳዮች ላይ በጉባኤው ተሳታፊ ለመሆን ለኮሚሽኑ በደብዳቤ ማሳወቁን ቢገልጽም፣ እስከ አሁን ምንም ዓይነት ምላሽ እንዳላገኘ አስታውቋል።
"ከዚህ ቀደም ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ቅሬታችንን አቅርበን የነበረ ቢሆንም፣ አሁን በማን እንደተወከልን የምናውቀው ነገር የለም። ኮሚሽኑ ቅሬታችንን ተቀብሎ እንዲያስተናግደን እንጠይቃለን።"
— አቶ ጀዋር ሳዲቅ (የማኅበሩ የሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ)
በሌላ በኩል ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ፣ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች አማካኝነት ለኮሚሽኑ የቀረቡ ተሳታፊዎች በጉባኤው እየተሳተፉ እንደሚገኙ ለሬዲዮ ጣቢያው ገልጸዋል።
ላለፉት አራት ዓመታት በኮሚሽኑ አሠራር ላይ ቅሬታ በማንሳት እራሳቸውን ከምክክሩ አግልለው የነበሩ ሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሰሞኑ ጉባኤውን መቀላቀላቸው ይታወሳል።
[ሃራምቤ ሬዲዮ]
#ኢትዮጵያ #ሀገራዊምክክር #ነጃሺኢስላማዊማኅበር #ሀራምቤሬዲዮ #ዜና #አዲስአበባ #የምክክርኮሚሽን #Ethiopia #NationalDialogue #EthiopianNews #HarambeRadio #Nejashi #EthiopianPolitics #AddisAbaba #NewsUpdate