Ethio Journal ኢትዮ ጆርናል 🇪🇹
Photo
📢 የሥራ ማስታወቂያ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN)

​የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) Freelance መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

💼 የሥራ መደቦች፡

​1. የዐረብኛ ቋንቋ ኤዲተር I (Gulaalaa I Afaan Arabaa)

​ብዛት፡ 1

​ደረጃ፡ 14

​የትምህርት ደረጃ እና ልምድ፡

​PhD - 1 ዓመት የሥራ ልምድ ወይም

​MA - 3 ዓመት የሥራ ልምድ ወይም

​BA - 5 ዓመት የሥራ ልምድ

​የትምህርት ዓይነት፡ በጆርናሊዝም፣ ኮሙኒኬሽን ወይም ቋንቋዎች (Languages)

​2. የዐረብኛ ቋንቋ አዘጋጅ III (Qopheessaa III Afaan Arabaa)

​ብዛት፡ 1

​ደረጃ፡ 13

​የትምህርት ደረጃ እና ልምድ፡

​MA - 2 ዓመት የሥራ ልምድ ወይም

​BA - 4 ዓመት የሥራ ልምድ

​የትምህርት ዓይነት፡ በጆርናሊዝም፣ ኮሙኒኬሽን ወይም ቋንቋዎች (Languages)

📌 ተጨማሪ መረጃዎች፡-

​የሥራ ቦታ፡ አዳማ

​ጾታ፡ ሁለቱም (ወንድ/ሴት)

​ደሞዝ፡ በ OBN የፍሪላንስ ስኬል መሠረት

📝 የማመልከቻ መስፈርቶች እና ማሳሰቢያ፡

​የምዝገባ ጊዜ፡ ከ 11/11/2018 እስከ 20/11/2018 ዓ.ም

​የማመልከቻ መንገድ፡ ማስረጃዎቻችሁን በ PDF ፎርማት ብቻ በማዘጋጀት ወደ

ኢሜይል
obnjobrecruitment2015@gmail.com በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ።

(ከPDF ውጪ ያሉ ፎርማቶች ተቀባይነት የላቸውም)

​የ8ኛ፣ የ10ኛ ወይም የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

​ተወዳዳሪው ከቅጥር በኋላ የትምህርት ማስረጃውን ማረጋገጥ የሚችል መሆን አለበት።

​ዋስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

​ከአፍአን ኦሮሞ ቋንቋ ጋር ተያይዞ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ መቻል ተጨማሪ ብቃት ነው።

​OBN ማስታወቂያውን የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።

📲 ለሚመለከታቸው ወዳጆችዎ ያጋሩ !

​የሥራ ማስታወቂያ ለ-Digital Media

​የሥራ መደቡ መጠሪያ፦   content creator

የሥራ አይነት፦ በትርፍ ጊዜ /ኮንትራት

ብዛት፦ 1

ፆታ ፦ ሴት

የስራ ቦታ፦ አዲስ አበባ -

የካ-ክፍለ ከተማ

​ዋና ዋና ተግባራትና ኃላፊነቶች፦

​ 1…በሳምንት አንድ ቀን ቀረፃ ማከናወን

​ 2…የቪዲዮ ይዘት በሁለት ወይም ለሶስት ጊዜ ተቆራርጦ የሚጫን


​ተፈላጊ ችሎታና ልምድ፦ አይጠይቅም

​ትምህርት ደረጃ፦  አይጠይቅም

​የሥራ ልምድ፦ ቲክቶክ ላይ አክቲቪ የሆነች ብንሆን ይመረጣል።


​ደመወዝ፦  8000 ብር

​ለማመልከት Telegram username
👇👇👇

 @Rwazza7

​አድራሻ፦ መገናኛ ።
1
" ከ415 ሺሕ ተፈታኞች ወደ 354 ሺሕ ተማሪዎች ናቸው ያለፉት " - የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ

የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ይፋ መደረጉን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ቡልቶሳ ኢርኮ (ዶ/ር) በሰጡን ቃል ውጤቱ ተለቋል ብለው፣ ያለፉት ተፈታኞች 86 በመቶ መሆናቸውን፣ ማለፊው 50 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ከአጠቃላይ ተፈታኞች መካከል 61 ሺሕ የሚሆኑት ተማሪዎች ማለፊያ ውጤት አላመጡም።

በክልሉ ወደ 415 ሺሕ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና መውሰዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት ቡልቶሳ (ዶ/ር)፣ ከእነዚህ ውስጥ "ወደ 354 ሺሕ ተማሪዎች ናቸው ያለፉት" ሲሉ ተናግረዋል።

ተፈታኞች ውጤታቸውን በአድሚሽን ካርድ ቁጥር መመልከት እንደሚችሉና መመልከቻው "ክፍት" መሆኑን የገልጸዋል።

https://oromia.ministry.et/#/
የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሞት ቅጣት ሊፈጸምባቸው ስለተቃረቡ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ስጋቱን ገለጸ

የአፍሪካ ሰብአዊና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን (ACHPR) በሳዑዲ ዓረቢያ በሞት ቅጣት ሊፈጸምባቸው ተቃርበዋል ስለተባሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ስጋቱን ገልጿል።

ኮሚሽኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ እያደረገ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚያውቅ ገልጾ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎቹን ሕይወት ለማዳን የሚችለውን ሁሉንም የዲፕሎማሲ መንገዶች እንዲጠቀም ጠይቋል።

በተጨማሪም፣ በተፈረደባቸው የሞት ቅጣቶች ላይ የሕግ እና የዲፕሎማሲ መንገዶችን በመጠቀም ማሻሻያ እንዲደረግ፣ የፍትሐዊ ፍርድ ሂደትና ዓለም አቀፍ መስፈርቶች እንዲከበሩ፣ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመጠበቅ የሕግ ድጋፍ፣ የቆንስላ አገልግሎት እና የቅድመ ጉዞ ግንዛቤ ፕሮግራሞችን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርቧል።

ኮሚሽኑ ከሳዑዲ ዓረቢያ ባለሥልጣናት፣ ከክልላዊ ተቋማትና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ትብብር በማጠናከር የኢትዮጵያውያንን መብትና ሕይወት እንዲጠበቅ አሳስቧል።

በቅርቡ በሳዑዲ ባለሥልጣናት በተደረገ የምሕረት አዋጅ 1,971 ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በሕግና በፍርድ ሂደት ላይ ባሉ ሌሎች ዜጎች ጉዳይም ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር በከፍተኛ ደረጃ ውይይቱን እየቀጠለም አስታውቆ ነበር።
Ethio Journal ኢትዮ ጆርናል 🇪🇹
Photo
📰 የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሂደት፡ የኢሌክቶራል ሥርዓት አማራጮች፣ የቃለ-ጉባኤ ያዦች ስጋት እና የአበል ክፍያ ውዝግብ

1. የፖለቲካ እና የምርጫ ሥርዓት አጀንዳዎች

በምክክር ሂደቱ የምርጫ ሥርዓትን በተመለከተ “የአብላጫ ድምጽ”፣ “ተመጣጣኝ የውክልና ሥርዓት”እና “ቅይጥ የውክልና ሥርዓት”የሚሉ አማራጮች ለውይይት ቀርበዋል።

በተጨማሪም የፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀትን በተመለከተ በሁለት መሠረታዊ ሃሳቦች መካከል ያለው ልዩነት በምክክር እንዲፈታ ተጠይቋል።

👉አንድ ወገን፡ብሔርን መሠረት ያደረገ አደረጃጀት ቀርቶ ወደ ዜጋ ተኮር የፖለቲካ ሥርዓት እንዲሸጋገር ያንሰዋል።

👉ሌላው ወገን፡የብሔር አደረጃጀት የብሔር ብሔረሰቦችን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ሊነካ አይገባም የሚል ጥብቅ አቋም አለው።

2. የቃለ-ጉባኤ ያዦች የሥራ ዋስትና ስጋት

ኮሚሽኑ 50 አባላት ባሏቸው ንዑሳን ቡድኖች የሚደረጉ ውይይቶችን ለመሰነድ ከከፍተኛ ትምህርትና ሌሎች ተቋማት የተውጣጡ 256 ቃለ-ጉባኤ ያዦችን አሰልጥኖ ማሰማራቱ ይታወሳል።

ሆኖም አንዳንዶቹ ተቋማት ሰራተኞቻቸው (ቃለ-ጉባኤ ያዦቹ) ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ጥሪ በማድረጋቸው ምክንያት በሰራተኞቹ ዘንድ የሥራ ዋስትና ስጋት ፈጥሯል።ኮሚሽኑ ጉዳዩን በተመለከተ ከተቋማቱ ጋር እንደሚነጋገር አስታውቋል።

3. የክልሎች ከፍተኛ የአበል ክፍያ እና የወጪ ዝርዝር

ኮሚሽኑ የተሳታፊዎችን ወጪ ሙሉ በሙሉ እንደሚሸፍን ባሳወቀበት ሁኔታ፣ ባልተለመደ መልኩ የተወሰኑ ክልሎች ለተመካካሪዎቻቸው ተጨማሪ ከፍተኛ የአበልና የትራንስፖርት ክፍያ መፈጸማቸው ታውቋል።

የተከፈለው የአበል መጠን እንደ ክልሉ፡-

👉ሶማሌ ክልል፡ለአብዛኞቹ ተሳታፊዎች እስከ 80,000 ብር

👉አፋር ክልል፡እስከ 10,000 ብር

👉ኦሮሚያ ክልል፡ከአንዳንድ አካባቢዎች ለተወከሉ እስከ 9,000 ብር

👉ሲዳማ ክልል፡5,000 ብር

በተጨማሪም ለምክክሩ ከፍተኛ በጀት መመደቡ የተገለጸ ሲሆን፣ ተመካካሪዎች ላረፉባቸው እንደ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮ-ቻይና ኮሌጅ እና ሌሎች ሆቴሎች ከፍተኛ ክፍያ እየተፈጸመ ይገኛል።

(ምንጭ፡ ዋዜማ)

#ኢትዮጵያ #ሀገራዊምክክር #የኢትዮጵያሀገራዊምክክርኮሚሽን #ዋዜማ #ፖለቲካ #የምርጫሥርዓት #ዜጋተኮር #ብሔርተኝነት #ቃለጉባኤያዦች #የአበልክፍያ #Ethiopia #NationalDialogue #EthiopianNationalDialogueCommission #WazemaRadio #EthiopianPolitics
2
ለምክክር ጉባዔ መጥታ ወንድ ልጅ የተገላገለችው እናት የልጇን ሥም "ኮሚሽን" አለችዉ

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወክላ በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች።

ባሳለፍነው ሳምንት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በመሳተፍ ላይ የነበረች የጋምቤላ ክልል ተወካይዋ ወ/ሮ ክርኑዶ ኡጁሉ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላ ስሙም "ምክክር" መባሉ የሚታወስ ነው።

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኡራ ወረዳ የመጣችው ሌላኛዋ የምክክሩ ተሳታፊ ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ በተመሳሳይ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን፥ ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች።

የመውለጃ ጊዜዬ እየደረሰ መሆኑን ባውቅም ለኢትዮጵያዊያን አብሮነትና ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ በሚመከርበት በዚህ ጉባኤ መሳተፍ አለብኝ በሚል አቋም ተገኝቻለሁ ብላለች፡፡

በጉባኤው አጀንዳዎች ላይ ለሀገራችን ይበጃል የምትለውን ሀሳብ በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ስታደርግ የቆየች ሲሆን፥ በዚህ ታሪካዊ ወቅት ልጇን በመገላገሏ መደሰቷን ገልጻለች።

ዘገባዉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዲያ ነዉ።
🚨 የ100 ዶላር ውዝግብ፦ የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አበል አልቀበልም አለ!

​ከአራት ወራት በፊት በቱርክ በተካሄደው "ፍሬንድሺፕ ካፕ" ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ውድድሩን 4ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ ይታወሳል።ይሁን እንጂ ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላ የተፈጠረው የኪስ ገንዘብ (አበል) ውዝግብ አሁንም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።

​እውነታው እና የሁለቱም ወገኖች ምላሽ፦
​የተጫዋቾች ቅሬታ፦

ከሀገር ሲወጡ የዕለት አበል እንደሌላቸው ቀድሞ እንዳልተነገራቸውና ለ10 ቀናት ቆይታ ቢያንስ $500 ዶላር ይጠብቁ እንደነበር የገለጹት 22ቱ ተጫዋቾች፤ የተሰጣቸው $100 ዶላር "በጣም አነስተኛ ነው" በማለት በጋራ "አንቀበልም" ብለው መልሰዋል።

(የቡድኑ አሰልጣኞች እና ሌሎች የልዑክ አባላት ግን ክፍያውን ተቀብለዋል)።

​የፌዴሬሽኑ ምላሽ፦

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን በበኩላቸው፤ ጉዞው አስቀድሞ በዕቅድ ውስጥ ያልነበረና በጀት ያልተያዘለት እንደነበር ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ተጫዋቾቹ ይህንን ዓለም አቀፍ ዕድል እንዳያጡ በማሰብ ከራሳቸው ተቀናሽ የተደረገ $100 ዶላር የሰጧቸው መሆኑን እና ሁኔታው ቀድሞ በግልጽ ተነግሯቸው እንደነበር አስረድተዋል።

​የገንዘቡ ፍጻሜ፦

ተጫዋቾቹ በተሰጣቸው አበል ባለመስማማታቸው ገንዘቡን አንቀበልም ማለታቸውን ተከትሎ ዶላሩ ሙሉ በሙሉ ወደ ፌዴሬሽኑ አካውንት መመለሱን ፌዴሬሽኑ አረጋግጧል።

#የኢትዮጵያእግርኳስ #የሴቶችእግርኳስ #U18Women #የስፖርትዜና #EFF #EthiopianFootball #SportsNews #LucyTeam #ኢትዮጵያ
1
Ethio Journal ኢትዮ ጆርናል 🇪🇹
Photo
የኢትዮ ቴሌኮም የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ዋና ዋና ነጥቦች 📊

🔹 ጠቅላላ ገቢ፡215.82 ቢሊዮን ብር (የ33.2% ዕድገት)

🔹 ያልተጣራ ትርፍ (EBITDA)፡38.7 ቢሊዮን ብር

🔹 ጠቅላላ ደንበኞች፡90.12 ሚሊዮን

🔹 የቴሌብር ተጠቃሚዎች፡ 60.6 ሚሊዮን (4.19 ትሪሊዮን ብር ግብይት)

🔹 የ4ጂ ሽፋን፡82.23% (በ1,200 ከተሞች)

🔹 የ5ጂ ሽፋን፡ በ33 ከተሞች (340 ጣቢያዎች)

🔹 ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፡20.19 ሚሊዮን ዜጎች በበጀት ዓመቱ ተመዝግበዋል

📌 ልዩ ስኬት፡በኩባንያው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳታና ኢንተርኔት ገቢ (31.1%) ከድምፅ አገልግሎት ገቢ በመበለጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዟል።

#EthioTelecom #Telebirr #DigitalEthiopia #TelecomNews #Ethiopia #TechNews #ESX
👆👆👆ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ከ NBC TV
Ethio Journal ኢትዮ ጆርናል 🇪🇹
Photo
🚨 «ቃል ተሽሮብናል፤ ፍትህ እንፈልጋለን!» — የመንዝ አካባቢ ነዋሪዎች

​በ1.9 ቢሊዮን ብር በጀት በታህሳስ 2011 ዓ.ም ተጀምሮ በ3 ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው የ «ጣርማበር – ሞላሌ – ወገሬ – ሰፌድ ሜዳ» 118.87 ኪሎ ሜትር የመንገድ ፕሮጀክት፣ በ8 ዓመታት ውስጥ ከ25% በላይ ማደግ ሳይችል ከሐምሌ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ግንባታው ሙሉ በሙሉ መቆሙ ተገለጸ።

​ይህ የመንገድ ፕሮጀክት መቋረጥ በአካባቢው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ያስከተለ ሲሆን፦

👉 በጤናው ዘርፍ፦ ነፍሰ ጡር እናቶችና ከባድ ሕሙማን በወቅቱ ወደ ሆስፒታል መድረስ ባለመቻላቸው ለሕይወት መስዋዕትነት እየተዳረጉ ይገኛሉ።

👉 በኢኮኖሚው ዘርፍ፦ አርሶ አደሩ ምርቱን (ወተት፣ ቅቤና እህል) ወደ ገበያ ማውጣትና ማዳበሪያ በጊዜ ማግኘት ተስኖታል።

👉 በትራንስፖርት፦ ከፍተኛ የተሽከርካሪ ብልሽትና የታሪፍ ጭማሪ በህዝቡ ላይ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ጫና ፈጥሯል።

​የመንገድ ስራ ጨረታውን አሸንፎ የነበረው መከላከያ ኮንስትራክሽን በግልፅ ባልታወቀ ምክንያት ስራውን አቋርጦ የထጣ ሲሆን፣ ለመንገዱ የቀረቡ ቁሳቁሶችም ባዶ ቦታ ላይ ወድቀው ይገኛሉ።

በአካባቢው ከነበረው መጠነኛ የፀጥታ ችግር ይልቅ የውል አስተዳደር፣ የተቋራጭ አቅም ማነስና የቢሮክራሲ መጓተት ለችግሩ ዋና ምክንያቶች መሆናቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

​ህዝቡ የመልማት ፍትሃዊ ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝና መንግስት የቆመውን ፕሮጀክት ትኩረት ሰጥቶ እንዲያስጀምርለት በጥብቅ ይጠይቃል።


✍️ ዋሱ መሐመድ

#የመንዝመንገድ #ጣርማበር #ሞላሌ #ሰሜንሸዋ #የመንገድግንባታ #የህዝብድምፅ #ኢትዮጵያ #ERA #ልማት #ፍትህ #Ethiopia #NorthShewa #Menz #Infrastructure #EthiopianRoadsAdministration
1
🎉 የታላቅ ስኬት ስጦታ ከኢትዮ ቴሌኮም!

​ኢትዮ ቴሌኮም የ2018 በጀት ዓመትን በ215.8 ቢሊየን ብር ገቢ በላቀ ስኬት ማጠናቀቁን ተከትሎ፣ ለውድ ደንበኞቹ የደስታ መግለጫ ስጦታ ማዘጋጀቱን ገልጻል!

🎁 የስጦታው ዝርዝር፡

🔹 1.5 GB የኢንተርኔት ዳታ
🔹 15 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ
🔹 30 የጽሑፍ መልዕክቶች (SMS)

አገልግሎቱ የሚቆይበት ጊዜ፡

📌 ቀን፡ እስከ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም
📌 ሰዓት፡ ከሌሊቱ 6:00 እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት

#EthioTelecom #FreeGift #Telebirr #Ethiopia #DigitalEthiopia #TechNews
Ethio Journal ኢትዮ ጆርናል 🇪🇹
Photo
" የአንድ አክስዮን ዋጋ ከ300 ብር በአሁኑ ወቅት ወደ 852 ብር ከፍ ብሏል " - ኢትዮ ቴሌኮም

• እስካሁን ከቀረቡ 47ሺ የሚጠጉ የአክሲዮን ግዢ ጥያቄዎች ውስጥ 96 በመቶ የሚሆኑት አክሲዮኖች የባለቤትነት ማረጋገጫ አግኝተዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት በፋይናንስ አፈጻጸም፣ በሀብት እድገትና በካፒታል ገበያ ተሳትፎው የተሻለ ስኬት ማስመዝገቡን የበጀት አመት አፈጻጸሙን ይፋ ሲያደርግ ጠቅሷል።

ይፋ በተደረገው መሰረትበሪፖርቱ የኩባንያው ጠቅላላ ሀብት (Total Assets) የ27 በመቶ እድገት በማሳየት 420 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል።

ይህ እድገት የተመዘገበው ኩባንያው በመሠረተ ልማት፣ በዲጂታል ፕላትፎርሞችና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ባደረገው ኢንቨስትመንት መሆኑ ገልጿል።

ይህም ለባለአክሲዮኖችና ለባለድርሻ አካላት ከፍተኛ እሴት የሚፈጥር መሆኑን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይፋ አድረገዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ሕዝባዊ አክሲዮን ማኅበርነት ከተሸጋገረ በኋላ በግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው የሁለተኛ ደረጃ የአክስዮን ገበያ ግብይት የአንዱ አክስዮን ዋጋ በ300 ብር የተጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ወደ 852 ብር ከፍ ማለቱን ተገልጿል።

እስካሁን ድረስ ወደ 47,000 የሚጠጉ የአክሲዮን ግዢ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ 96 በመቶ የሚሆኑት አክሲዮኖች የባለቤትነት ማረጋገጫ (Share Dematerialization) ሂደት መጠናቀቁ በዛሬው ዕለት ተገልጿል።
1