ኢማም አልቡኻሪ የሸሪዓ እና የዐረብኛ ኮሌጅ

የስራ መደብ፦ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ

※ ብዛት፦ 2
※ ጾታ፦ አይለይም
※ ደመወዝ፦ በስምምነት

ለማመልከት፦
የትምህርት ማስረጃችሁን በ 0930491483 ቴሌግራም አድራሻ ብቻ ይላኩ።

ለበለጠ መረጃ፦ 0930491483 ቴሌግራም ላይ ያናግሩን።

ዝርዝር መረጃውን ለማየት የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።



#ለእርስዎ_ካልሆነ_ለሌሎች_ያጋሩ!
" ከሰሞኑን ለ15 ቀናት በቆየ ኦፕሬሽን በአዲስ አበባ፣ በሐረሪና በሌሎች አካባቢዎች ነው የተያዙት " - አቶ ጃይላን አብዲ

"እጅግ አደገኛ ናቸው" የተባሉ ሰው አዘዋዋሪዎች መያዛቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ " ከ60 በላይ ስደተኞች ለሞት እና በርካታ ሴቶች ለመደፈር ተጠያቂ ናቸው " ያላቸውን አደገኛ 17 ተጠርጣሪ የሰዎች አዘዋዋሪዎች መያዙን አስታውቋል።

ፖሊስ እንደገለጸው፣ በ"መሐመድ ጣሂር አደም (ወርዲ)" የሚመራው ቡድን ሰዎችን ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በደላሎች አማካኝነት በመልመል በጂቡቲና በየመን በኩል በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያዘዋውር ነበር።

እነዚህ አደገኛ የሰው አዘዋዋሪዎች ከ40,000 በላይ ሰዎች እንዳዘዋወሩ እና ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ እንደሰበሰቡ ተገልጿል።

ተጎጂዎች በየመን ውስጥ በመጋዘኖች ታግተው ድብደባ፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደተፈጸሙባቸው ሲገለጽ፣ ቤተሰቦቻቸውን ገንዘብ እንዲልኩ ለማስገደድ የስቃይ ቪዲዮዎች ይላኩ እንደነበር ተጠቁሟል።

በምርመራውም ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸውና በርካታ ሴቶች መደፈራቸው መረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።

የፌደራል ፖሊስ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ጄይላን አብዲ፣ ተጠርጣሪዎቹ ሰሞኑን ለ15 ቀናት በቆየ ኦፕሬሽን በአዲስ አበባ፣ በሐረሪና በሌሎች አካባቢዎች መያዛቸውን ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል።

ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹ የምርመራ ፋይል ለፍትሕ ሚኒስቴር መተላለፉን ገልጿል።

በስማቸው የነበሩ ቤቶች ፣ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ንብረቶችም መታገዳቸው ታውቋል።

[ቲክቫህ]
አዲስ አበባ የኦሮሚያ አካል እንድትሆን አማራጭ ሀሳብ ቀረበ!

​ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ባካሄደው ስብሰባ ተመካካሪዎች በቡድን ደረጃ ውይይታቸውን ቀጥለዋል።በኮሚሽኑ በቀረበው ሰነድ መሰረት የአዲስ አበባን ሕጋዊ አቋም በተመለከተ አራት ዋና ዋና አማራጮች ለውይይት ቀርበዋል፦

👉​ሲቲ ስቴት (ራስ ገዝ)

👉​የፌደራል አካል

👉​ራሷን የቻለች ክልል

👉​የኦሮሚያ አካል

​ከዚህ በተጨማሪም የከተማዋ ወሰን፣ የሥራ ቋንቋ፣ የበጀት ድርሻ፣ የፖሊስና ፍርድ ቤት ጉዳዮች በንዑስ አጀንዳነት የተካተቱ ሲሆን፣ የከተማዋ በፌደሬሽን ምክር ቤት የሚኖራት ውክልና ግን በሰነዱ አልተካተተም።

#ሀገራዊምክክር #አዲስአበባ #ሀገራዊምክክርኮሚሽን #የአዲስአበባህጋዊአቋም #ኦሮሚያ #ኢትዮጵያ #NationalDialogue #AddisAbaba #Ethiopia
Ethio Journal ኢትዮ ጆርናል 🇪🇹
Photo
🚨 ሰበር ዜና

ጄኤፍኤም (JFM 106.7) የሬድዮ ጣቢያ ለስድስት ወራት ከስርጭት ታገደ


አዲስ አበባ— የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በጄኤፍኤም 106.7 (JFM) የሬድዮ ጣቢያ ላይ ለስድስት ወራት የሚቆይ ሙሉ የስርጭት እግድ መጣሉን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ባደረገው የይዘት ክትትልና በአካል በተደረገ የኢንስፔክሽን ምልከታ ጣቢያው በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 እና በፈቃድ ውል ስምምነቱ ላይ የተቀመጡ በርካታ ግዴታዎችን ሳይወጣ መቅረቱን ገልጿል።

ከተለዩት ዋና ዋና ግኝቶች መካከል፡-

👉የሀገራዊ ይዘት መጠን አለማሟላት፦ ከሳምንታዊ የስርጭት ጊዜው 60 በመቶውን ፈቃድ ለወሰደበት አካባቢ፣ ቀሪውን ደግሞ ለሀገራዊና ክልላዊ ፕሮግራሞች ማዋል ሲገባው ተግባራዊ አለማድረጉ፤

👉ትምህርታዊና አዝናኝ ፕሮግራሞች፦ሕዝብን የሚያስተምሩ፣ የሚያሳውቁና የሚያዝናኑ ይዘቶችን አለማቅረቡ፤

👉ልማታዊና ህገ-መንግስታዊ ግዴታዎች፦ለፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲሁም ለጋራ ሀገራዊ እሴቶች መጠናከር አስተዋፅኦ የሚያደርጉ አገልግሎቶችን አለመስጠቱ ተጠቅሰዋል።

ባለስልጣኑ አክሎ እንዳመለከተው፣ ለጣቢያው በተደጋጋሚ ግብረ-መልስ፣ የቃልና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያዎች ቢሰጡትም ምንም ዓይነት መሻሻል ሊታይ አልቻለም።

በዚህም ምክንያት ከረቡዕ ሐምሌ 01/2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ ለቀጣይ 6 ወራት ከስርጭት ሙሉ ለሙሉ እንዲታገድ ተወስኗል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን ለጣቢያው የተመደበውን 106.7 የሬድዮ ፍሪኩዌንሲ (ሞገድ) የእግድ ጊዜው እስከሚያበቃ ድረስ ጥቅም ላይ ማዋል እንደማይቻል ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ጣቢያው ለሕግ ተገዢ በመሆን ስርጭቱን እንዲያቆም እና የሚመለከታቸው አካላትም ውሳኔውን እንዲያስፈጽሙ ጥሪ አቅርቧል።

#BreakingNews #JFM1067 #የኢትዮጵያመገናኛብዙኃንባለስልጣን #ኢመብ #EMA #የሬድዮስርጭት #የስርጭትእግድ #የኢትዮጵያዜና #EthiopianMediaAuthority #BroadcastingEthiopia #JFM
ነጃሺ ቲቪ

ቪድዮ ኤዲተር ይፈልጋል።

ለማመልከት ቴሌግራም
👇👇👇


t.me/nejashistaffs
🚨 ጥንቃቄ፡ ከሐሰተኛ መረጃዎችና አሳሳች ሊንኮች (Clickbait) እንጠበቅ! 🚨

​በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ባለቤቱ አርቲስት አምለሰት ሙጬ ለዶንኪ ቲዩብ (ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ) ዳጎስ ያለ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ" ተብሎ የሚሰራጨው ወሬ ፍፁም የሐሰት መረጃ (Fake News) ነው!

​የእነዚህ ገፆችና የሐሰት ዜናዎች ዋና አላማ ህዝብ የሚወዳቸውን ስሞች መጠቀሚያ በማድረግ ሰዎችን ወደ ተለያዩ የዩቲዩብ ፕሌይሊስቶችና ድህረ ገፆች መሳብ (Clickbait) እንዲሁም በሰው ስም የራሳቸውን እይታ (Views) ማሳደግ ነው።

📌 ልንጠነቀቃቸው የሚገቡ ነጥቦች፦

1️⃣ መረጃዎችን ማጣራት፡ ማንኛውንም ዜና ከትክክለኛው ባለቤት ወይም ኦፊሴላዊ (Official) ገጽ ካልሆነ በቀር ባናምንና ባናሰራጭ።

2️⃣ አሳሳች ሊንኮችን አለመንካት፡ የእይታ ቁጥር ለመሰብሰብ የሚለጠፉ የማታለያ ማስፈንጠሪያዎችን (Links) አለመንካት።

3️⃣ ሐሰተኛ ገፆችን ሪፖርት ማድረግ፡ የሰዎችን በጎ ስም በመጠቀም ጥቅም የሚሰብሱ ገፆችን ሪፖርት (Report) በማድረግ የሐሰት መረጃ ስርጭትን እንከላከል!

​ትክክለኛ መረጃዎችን ከኦፊሴላዊ ምንጮች ብቻ እንከታተል!

#FakeNews #Clickbait #Ethiopia #TeddyAfro #DonkeyTube #EshetuMelesse #SocialMediaAwareness #FactCheckEthiopia #የሐሰትመረጃ #ጥንቃቄ
📣 ለአመልካቾች በሙሉ የወጣ ክፍት የሥራ ጥሪ! 🇪🇹

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ተኛውን ዙር ቀሪ ጠቅላላ ምርጫ በአማራ ክልል በ8 ምርጫ ክልሎች ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

​በዚህም መሠረት ለመራጮች ምዝገባ እና ለድምፅ መስጫ ዕለት በሁሉም ጣቢያዎች ላይ የሚሠሩ ጊዜያዊ አስፈጻሚዎችን ገለልተኝነታቸውንና መሥፈርቱን ማሟላታቸውን አረጋግጦ በጊዜያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል።

📋 የምልመላ መሥፈርቶች፦

• ዕድሜ፦ 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ

• የፖለቲካ ተሳትፎ፦ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች

• የትምህርት ደረጃ፦ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ

• ቋንቋ፦ የክልሉን የሥራ ቋንቋ መናገር እና መጻፍ የሚችል/ምትችል

• የሥራ ቦታ፦ ቦርዱ ባቋቋማቸው የምርጫ ጣቢያዎች
​(ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ!)

🔗 እንዴት ማመልከት ይቻላል?

መሥፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት ትችላላችሁ፦

👉 https://nebe-election.org/recruitment

📅 የምዝገባ ጊዜ፦

ከዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ብቻ!

#NEBE #EthiopianElectionBoard #የኢትዮጵያብሔራዊምርጫቦርድ #የሥራማስታወቂያ #AmharaRegion #የአማራክልል #JobOpportunity #Ethiopia
1
Ethio Journal ኢትዮ ጆርናል 🇪🇹
Photo
📢 የሥራ ማስታወቂያ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN)

​የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) Freelance መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

💼 የሥራ መደቦች፡

​1. የዐረብኛ ቋንቋ ኤዲተር I (Gulaalaa I Afaan Arabaa)

​ብዛት፡ 1

​ደረጃ፡ 14

​የትምህርት ደረጃ እና ልምድ፡

​PhD - 1 ዓመት የሥራ ልምድ ወይም

​MA - 3 ዓመት የሥራ ልምድ ወይም

​BA - 5 ዓመት የሥራ ልምድ

​የትምህርት ዓይነት፡ በጆርናሊዝም፣ ኮሙኒኬሽን ወይም ቋንቋዎች (Languages)

​2. የዐረብኛ ቋንቋ አዘጋጅ III (Qopheessaa III Afaan Arabaa)

​ብዛት፡ 1

​ደረጃ፡ 13

​የትምህርት ደረጃ እና ልምድ፡

​MA - 2 ዓመት የሥራ ልምድ ወይም

​BA - 4 ዓመት የሥራ ልምድ

​የትምህርት ዓይነት፡ በጆርናሊዝም፣ ኮሙኒኬሽን ወይም ቋንቋዎች (Languages)

📌 ተጨማሪ መረጃዎች፡-

​የሥራ ቦታ፡ አዳማ

​ጾታ፡ ሁለቱም (ወንድ/ሴት)

​ደሞዝ፡ በ OBN የፍሪላንስ ስኬል መሠረት

📝 የማመልከቻ መስፈርቶች እና ማሳሰቢያ፡

​የምዝገባ ጊዜ፡ ከ 11/11/2018 እስከ 20/11/2018 ዓ.ም

​የማመልከቻ መንገድ፡ ማስረጃዎቻችሁን በ PDF ፎርማት ብቻ በማዘጋጀት ወደ

ኢሜይል
obnjobrecruitment2015@gmail.com በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ።

(ከPDF ውጪ ያሉ ፎርማቶች ተቀባይነት የላቸውም)

​የ8ኛ፣ የ10ኛ ወይም የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

​ተወዳዳሪው ከቅጥር በኋላ የትምህርት ማስረጃውን ማረጋገጥ የሚችል መሆን አለበት።

​ዋስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

​ከአፍአን ኦሮሞ ቋንቋ ጋር ተያይዞ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ መቻል ተጨማሪ ብቃት ነው።

​OBN ማስታወቂያውን የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።

📲 ለሚመለከታቸው ወዳጆችዎ ያጋሩ !

​የሥራ ማስታወቂያ ለ-Digital Media

​የሥራ መደቡ መጠሪያ፦   content creator

የሥራ አይነት፦ በትርፍ ጊዜ /ኮንትራት

ብዛት፦ 1

ፆታ ፦ ሴት

የስራ ቦታ፦ አዲስ አበባ -

የካ-ክፍለ ከተማ

​ዋና ዋና ተግባራትና ኃላፊነቶች፦

​ 1…በሳምንት አንድ ቀን ቀረፃ ማከናወን

​ 2…የቪዲዮ ይዘት በሁለት ወይም ለሶስት ጊዜ ተቆራርጦ የሚጫን


​ተፈላጊ ችሎታና ልምድ፦ አይጠይቅም

​ትምህርት ደረጃ፦  አይጠይቅም

​የሥራ ልምድ፦ ቲክቶክ ላይ አክቲቪ የሆነች ብንሆን ይመረጣል።


​ደመወዝ፦  8000 ብር

​ለማመልከት Telegram username
👇👇👇

 @Rwazza7

​አድራሻ፦ መገናኛ ።
1
" ከ415 ሺሕ ተፈታኞች ወደ 354 ሺሕ ተማሪዎች ናቸው ያለፉት " - የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ

የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ይፋ መደረጉን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ቡልቶሳ ኢርኮ (ዶ/ር) በሰጡን ቃል ውጤቱ ተለቋል ብለው፣ ያለፉት ተፈታኞች 86 በመቶ መሆናቸውን፣ ማለፊው 50 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ከአጠቃላይ ተፈታኞች መካከል 61 ሺሕ የሚሆኑት ተማሪዎች ማለፊያ ውጤት አላመጡም።

በክልሉ ወደ 415 ሺሕ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና መውሰዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት ቡልቶሳ (ዶ/ር)፣ ከእነዚህ ውስጥ "ወደ 354 ሺሕ ተማሪዎች ናቸው ያለፉት" ሲሉ ተናግረዋል።

ተፈታኞች ውጤታቸውን በአድሚሽን ካርድ ቁጥር መመልከት እንደሚችሉና መመልከቻው "ክፍት" መሆኑን የገልጸዋል።

https://oromia.ministry.et/#/
የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሞት ቅጣት ሊፈጸምባቸው ስለተቃረቡ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ስጋቱን ገለጸ

የአፍሪካ ሰብአዊና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን (ACHPR) በሳዑዲ ዓረቢያ በሞት ቅጣት ሊፈጸምባቸው ተቃርበዋል ስለተባሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ስጋቱን ገልጿል።

ኮሚሽኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ እያደረገ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚያውቅ ገልጾ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎቹን ሕይወት ለማዳን የሚችለውን ሁሉንም የዲፕሎማሲ መንገዶች እንዲጠቀም ጠይቋል።

በተጨማሪም፣ በተፈረደባቸው የሞት ቅጣቶች ላይ የሕግ እና የዲፕሎማሲ መንገዶችን በመጠቀም ማሻሻያ እንዲደረግ፣ የፍትሐዊ ፍርድ ሂደትና ዓለም አቀፍ መስፈርቶች እንዲከበሩ፣ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመጠበቅ የሕግ ድጋፍ፣ የቆንስላ አገልግሎት እና የቅድመ ጉዞ ግንዛቤ ፕሮግራሞችን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርቧል።

ኮሚሽኑ ከሳዑዲ ዓረቢያ ባለሥልጣናት፣ ከክልላዊ ተቋማትና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ትብብር በማጠናከር የኢትዮጵያውያንን መብትና ሕይወት እንዲጠበቅ አሳስቧል።

በቅርቡ በሳዑዲ ባለሥልጣናት በተደረገ የምሕረት አዋጅ 1,971 ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በሕግና በፍርድ ሂደት ላይ ባሉ ሌሎች ዜጎች ጉዳይም ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር በከፍተኛ ደረጃ ውይይቱን እየቀጠለም አስታውቆ ነበር።
Ethio Journal ኢትዮ ጆርናል 🇪🇹
Photo
📰 የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሂደት፡ የኢሌክቶራል ሥርዓት አማራጮች፣ የቃለ-ጉባኤ ያዦች ስጋት እና የአበል ክፍያ ውዝግብ

1. የፖለቲካ እና የምርጫ ሥርዓት አጀንዳዎች

በምክክር ሂደቱ የምርጫ ሥርዓትን በተመለከተ “የአብላጫ ድምጽ”፣ “ተመጣጣኝ የውክልና ሥርዓት”እና “ቅይጥ የውክልና ሥርዓት”የሚሉ አማራጮች ለውይይት ቀርበዋል።

በተጨማሪም የፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀትን በተመለከተ በሁለት መሠረታዊ ሃሳቦች መካከል ያለው ልዩነት በምክክር እንዲፈታ ተጠይቋል።

👉አንድ ወገን፡ብሔርን መሠረት ያደረገ አደረጃጀት ቀርቶ ወደ ዜጋ ተኮር የፖለቲካ ሥርዓት እንዲሸጋገር ያንሰዋል።

👉ሌላው ወገን፡የብሔር አደረጃጀት የብሔር ብሔረሰቦችን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ሊነካ አይገባም የሚል ጥብቅ አቋም አለው።

2. የቃለ-ጉባኤ ያዦች የሥራ ዋስትና ስጋት

ኮሚሽኑ 50 አባላት ባሏቸው ንዑሳን ቡድኖች የሚደረጉ ውይይቶችን ለመሰነድ ከከፍተኛ ትምህርትና ሌሎች ተቋማት የተውጣጡ 256 ቃለ-ጉባኤ ያዦችን አሰልጥኖ ማሰማራቱ ይታወሳል።

ሆኖም አንዳንዶቹ ተቋማት ሰራተኞቻቸው (ቃለ-ጉባኤ ያዦቹ) ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ጥሪ በማድረጋቸው ምክንያት በሰራተኞቹ ዘንድ የሥራ ዋስትና ስጋት ፈጥሯል።ኮሚሽኑ ጉዳዩን በተመለከተ ከተቋማቱ ጋር እንደሚነጋገር አስታውቋል።

3. የክልሎች ከፍተኛ የአበል ክፍያ እና የወጪ ዝርዝር

ኮሚሽኑ የተሳታፊዎችን ወጪ ሙሉ በሙሉ እንደሚሸፍን ባሳወቀበት ሁኔታ፣ ባልተለመደ መልኩ የተወሰኑ ክልሎች ለተመካካሪዎቻቸው ተጨማሪ ከፍተኛ የአበልና የትራንስፖርት ክፍያ መፈጸማቸው ታውቋል።

የተከፈለው የአበል መጠን እንደ ክልሉ፡-

👉ሶማሌ ክልል፡ለአብዛኞቹ ተሳታፊዎች እስከ 80,000 ብር

👉አፋር ክልል፡እስከ 10,000 ብር

👉ኦሮሚያ ክልል፡ከአንዳንድ አካባቢዎች ለተወከሉ እስከ 9,000 ብር

👉ሲዳማ ክልል፡5,000 ብር

በተጨማሪም ለምክክሩ ከፍተኛ በጀት መመደቡ የተገለጸ ሲሆን፣ ተመካካሪዎች ላረፉባቸው እንደ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮ-ቻይና ኮሌጅ እና ሌሎች ሆቴሎች ከፍተኛ ክፍያ እየተፈጸመ ይገኛል።

(ምንጭ፡ ዋዜማ)

#ኢትዮጵያ #ሀገራዊምክክር #የኢትዮጵያሀገራዊምክክርኮሚሽን #ዋዜማ #ፖለቲካ #የምርጫሥርዓት #ዜጋተኮር #ብሔርተኝነት #ቃለጉባኤያዦች #የአበልክፍያ #Ethiopia #NationalDialogue #EthiopianNationalDialogueCommission #WazemaRadio #EthiopianPolitics
2
ለምክክር ጉባዔ መጥታ ወንድ ልጅ የተገላገለችው እናት የልጇን ሥም "ኮሚሽን" አለችዉ

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወክላ በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች።

ባሳለፍነው ሳምንት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በመሳተፍ ላይ የነበረች የጋምቤላ ክልል ተወካይዋ ወ/ሮ ክርኑዶ ኡጁሉ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላ ስሙም "ምክክር" መባሉ የሚታወስ ነው።

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኡራ ወረዳ የመጣችው ሌላኛዋ የምክክሩ ተሳታፊ ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ በተመሳሳይ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን፥ ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች።

የመውለጃ ጊዜዬ እየደረሰ መሆኑን ባውቅም ለኢትዮጵያዊያን አብሮነትና ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ በሚመከርበት በዚህ ጉባኤ መሳተፍ አለብኝ በሚል አቋም ተገኝቻለሁ ብላለች፡፡

በጉባኤው አጀንዳዎች ላይ ለሀገራችን ይበጃል የምትለውን ሀሳብ በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ስታደርግ የቆየች ሲሆን፥ በዚህ ታሪካዊ ወቅት ልጇን በመገላገሏ መደሰቷን ገልጻለች።

ዘገባዉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዲያ ነዉ።
🚨 የ100 ዶላር ውዝግብ፦ የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አበል አልቀበልም አለ!

​ከአራት ወራት በፊት በቱርክ በተካሄደው "ፍሬንድሺፕ ካፕ" ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ውድድሩን 4ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ ይታወሳል።ይሁን እንጂ ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላ የተፈጠረው የኪስ ገንዘብ (አበል) ውዝግብ አሁንም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።

​እውነታው እና የሁለቱም ወገኖች ምላሽ፦
​የተጫዋቾች ቅሬታ፦

ከሀገር ሲወጡ የዕለት አበል እንደሌላቸው ቀድሞ እንዳልተነገራቸውና ለ10 ቀናት ቆይታ ቢያንስ $500 ዶላር ይጠብቁ እንደነበር የገለጹት 22ቱ ተጫዋቾች፤ የተሰጣቸው $100 ዶላር "በጣም አነስተኛ ነው" በማለት በጋራ "አንቀበልም" ብለው መልሰዋል።

(የቡድኑ አሰልጣኞች እና ሌሎች የልዑክ አባላት ግን ክፍያውን ተቀብለዋል)።

​የፌዴሬሽኑ ምላሽ፦

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን በበኩላቸው፤ ጉዞው አስቀድሞ በዕቅድ ውስጥ ያልነበረና በጀት ያልተያዘለት እንደነበር ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ተጫዋቾቹ ይህንን ዓለም አቀፍ ዕድል እንዳያጡ በማሰብ ከራሳቸው ተቀናሽ የተደረገ $100 ዶላር የሰጧቸው መሆኑን እና ሁኔታው ቀድሞ በግልጽ ተነግሯቸው እንደነበር አስረድተዋል።

​የገንዘቡ ፍጻሜ፦

ተጫዋቾቹ በተሰጣቸው አበል ባለመስማማታቸው ገንዘቡን አንቀበልም ማለታቸውን ተከትሎ ዶላሩ ሙሉ በሙሉ ወደ ፌዴሬሽኑ አካውንት መመለሱን ፌዴሬሽኑ አረጋግጧል።

#የኢትዮጵያእግርኳስ #የሴቶችእግርኳስ #U18Women #የስፖርትዜና #EFF #EthiopianFootball #SportsNews #LucyTeam #ኢትዮጵያ
1