Ethio Inside FX $$( የስራ ማስታወቂያ)
2.4K subscribers
275 photos
10 videos
14 files
377 links
All insider is here
$$
get your work improve your carrier with us
We provides a community focused on building financial knowledge and long-term wealth.
Forex • Cryptocurrency • Wealth Education

Contact us: @zedreamer
Download Telegram
ሪፐብሊካኑና ዲሞክራቱ በአሜሪካ በጀት ላይ ስላልተስማሙ የአሜሪካ ፌደራል መንግስት መሰረታዊ ከሚባሉት የደህንነት እና ህክምና ካሉ አገልግሎቶች ውጪ ሌሎች ስራዎችን አቁሟል።

@memicrypto
Forwarded from Watcher Guru
JUST IN: Michael Saylor says "no new orange dots this week."

"Just a $9 billion reminder of why we HODL."

@WatcherGuru
History Has Been made, Gold is now above 4K

@memicrypto
🇺🇸🇨🇳 ትራምፕ ቻይና ለንግድ ስምምነት ዝግጁ ነች ብለዋል። ከሰሞኑ ትራምፕ ሃገራቸው ከቻይና ጋር የንግድ ጦርነት ውስጥ መሆኗን ካሳወቁ በኋላ የአለም ኢኮኖሚ ተረብሾ ነበር።

@memicrypto
ጋና ክሪፕቶከረንሲ መጠቀምን ህጋዊ ለማድረግ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አፀደቀች።

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ጋና የናይጄሪያ እና ኬንያን ፈለግ በመከተል ክሪፕቶከረንሲ መጠቀምን ህጋዊ የሚያደርግ ህግ በፓርላማዋ አጽድቃለች።

በ2025 ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት የሚደረገው የክሪፕቶከረንሲ የንግድ መጠን ከ205 ቢሊየን ዶላር የተሻገረ ሲሆን ሃገራት ከዘርፉ ለመጠቀምና ለመቆጣጠር ህጎችን እያወጡ ይገኛሉ።

ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት ናይጄሪያ በንግድ መጠኑ ቀዳሚ ስትሆን ጋና፣ ኢትዮጵያ ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ተከታዮች መሆናቸው ተነግሯል።

የጋና 3 ሚሊየን ወጣት ክሪፕቶከረንሲ ይጠቀማል ሲባል ዘርፉ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ይንቀሳቀስበታል ተብሎም ይገመታል።

ጋና ታዲያ ይህንን ዘርፍ የሃገሪቱ ማዕከላዊ ባንክና የሰነደ ሙአለ ንዋዮች ኮሚሽን እንዲቆጣጠረው እና ወደ መደበኛ ኢኮኖሚ ገብቶ ሃገሪቷ እንድትጠቀም የሚያስችል ህግ አፅድቃለች።

ጋና የክሪፕቶከረንሲ አገልግሎት ሰጪዎች ከሁለቱ አካላት ፈቃድ እንዲወስዱ ያስቀመጠች ሲሆን ይህም ዘርፉ የሚተችበትን የገንዘብ ማጭበርበር ለመከላከል ይረዳል ተብሏል።

ክሪፕተከረንሲ በተደጋጋሚ ከገንዘብ ማጭበርበር ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን ናይጄሪያ ከዚህ ቀደም ባይናንስ የተሰኘውን የክሪፕቶከረንሲ መለዋወጫ የኢኮኖሚ ጥቅሜን አሳጥቶኛል በሚል የ81 ቢሊየን ዶላር ክስ መክፈቷ ይታወሳል።

የጋና ማዕከላዊ ባንክ ገዢ ጆንሰን አሲያማ ከዚህ ቀደም በጨዋታው ወደኋላ ቀርተናል ብለው የህግ ለውጥ እንደሚኖር መናገራቸው ሲታወስ አሁን በፓርላማው የፀደቀው ህግ ያለውን ስጋት ለመቆጣጠር የሚያስችል ማዕቀፍ ይሰጣል ብለዋል።

Source: tikvahethmagazine

@memicrypto
1
የወርቅ ዋጋ በታሪክ ከፍተኛው ላይ ደርሷል።

ወርቅ በ Ounce በአለም አቀፍ ገበያ ከ5100 ዶላር በላይ ተሻግሯል።
$1.6B liquidations hit crypto in 24 hours

Join ➣ @memicrypto
1
ብሔራዊ ባንክ P2P ላይ ያወጣውን አዲስ መመሪያ ተከትሎ Bybit ከመጪው ሰኞ (ማርች 9) ጀምሮ በብር የሚደረጉ የP2P ግብይቶችን እንደማያከናውን በይፋ ገልጿል።
1
የቢትኮይን ዋጋ በኢድ ቀናት 🌙

2010: $0.06
2011: $3
2012: $5
2013: $100
2014: $450
2015: $280
2016: $660
2017: $2,550
2018: $6,650
2019: $7,400
2020: $8,700
2021: $45,400
2022: $38,000
2023: $27,100
2024: $67,500
2025: $83,500
2026: $70,500
በአሜሪካና ኢራን ጦርነት የተነሳ ሃገራት ለነዳጅ ግዢ ከአሜሪካን ዶላር ይልቅ የቻይና ዩሃንን እየተጠቀሙ እንደሆነ የደች ባንክ ገልጿል።
የአሜሪካ ዶላር ሲታተም ለመጀመሪያ ጊዜ በገንዘብ ሚኒስትሩ ቦታ የፕሬዚዳንቱ ፊርማ ይሰፍርበታል።

ዶናልድ ትራምፕም በዶላር ላይ ፊርማቸው የሚሰፍር የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ይሆናሉ።
ትራምፕ ኢራን ያለ ጊዜ ገደብ የኒውክሌር መርሃ ግብሯን ለማቆም መስማማቷን እና ምንም አይነት የታገደ የአሜሪካ ገንዘብ እንደማትቀበል ተናገሩ።

በቅርቡም ተጨማሪ ንግግሮች እንደሚጠበቁ ግጭቱን ለማስቆም የተደረሰው ስምምነት መጠናቀቁን ገልጿል። ሆኖም ኢራን የሆርሙዝ ባህርን እንደገና ከመክፈት በዘለለ እነዚህን የይገባኛል ጥያቄዎች ወይም ሰፋ ያለ ስምምነት አላረጋገጠችም።

የዩኤስ ተደራዳሪ ቡድን አመራር እና የመጨረሻ ውሎችን ጨምሮ ቁልፍ ዝርዝሮች አሁንም አልተፈቱም።

@memicrypto
ሆርሙዝ ወሽመጥ ለንግድ መርከቦች ሙሉ ለሙሉ ክፍት መሆኑን ኢራን አስታወቀች

በሊባኖስ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም የንግድ መርከቦች ክፍት መሆኑን የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ አባስ አራግቺ አስታውቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገፃቸው እንዳሰታወቁት በሊባኖስ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል ንግድ መርከቦች እንዲያልፉ ሙሉ ለሙሉ ክፍት ተደርጓል ብለዋል።

​የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ወሸመጥን መተላለፊያ ሙሉ በሙሉ ለንግድ መርከቦች ክፍት መሆኑንና ለጉዞ ዝግጁ በማድረጓ አመሰግናለሁ ብለዋል።

ይህም ርምጃ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ቅናሽ ማሳየቱንና ለንግድና ለቀጠናው መረጋጋት ትልቅ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል።
🔥 Just History: On this day 15 years ago, the first cryptocurrency ‘based on Bitcoin’ was developed called “Namecoin”

More than 100 million coins have been launched since.

@memicrypto
ዴስፔራዶስ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባቱ ተሰማ።

ዴስፔራዶስ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ኢንቨስትመንት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የገባው በሄይኒከን ኢትዮጵያ አማካኝነት መሆኑን ሰምተናል።

​ሄይኒከን ኢትዮጵያ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የቆየ ታሪክ ያለው ዴስፔራዶስ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መቀላቀሉን ተናግሯል።

ዴስፔራዶስ በተለይ በላቲን አሜሪካ አሜሪካ እና የተወሰኑ ኤዥያ ሀገራት የሚታወቅ ሲሆን በኢትዮጵያ በቂሊንጦ በሚገኘው የሄኒከን ኩባንያ እንደሚመረት ሰምተናል።

Source: ሸገር
@memicrypto
በውስጥ የደረሰውን መረጃ በመጠቀም ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ከስልጣናቸው እንደሚነሱ ቁማር በመጫወት ከ400 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ ያገኘው የአሜሪካ ጦር አባል በቁጥጥር ስር ውሏል።

@memicrypto
📢 Advertising in this channel

You can place an ad via Telega․io. It takes just a few minutes.

Formats and current rates: View details
ጄሮም ፖውል ከ8 አመታት ቆይታ በኋላ በይፋ ከአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ(FED) ገዢነቱ ተነስቷል።

በእሱ ምትክ ኬቭን ዎርሽ ተተክተዋል።