ስብዕናችን #Humanity
25.7K subscribers
1.66K photos
79 videos
23 files
54 links
🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot
Download Telegram
ዛሬ በአስቸጋሪና ሊታለፍ የማይቻል የሚመስል ሁኔታ ውስጥ ከሆነ ያለኸው፤እመነኝ ይኼ ሁሉ ፈተና ይታለፋል!የሚገርመው ችግርህን አልፈኸውም ትረሳዋለህ።አሁን ብቻ መንፈስህን አጠንክርና የገጠመህን ፈተና ፊት ለፊት ተጋፈጠው፣ ፈርተህ ጥግህን ከያዝህማ መቼም ደረጃህን ከፍ ልታደርገው አትችልም።

🪐 ያለህ እድል በብልሀትና በጥበብ ከከበበህ የህይወት ፈተና ጋ በመጋፈጥ ለትግል መዘጋጀት ነው። ያኔ ድል ከአንተ ጋ ትቆማለች። ህይወትህም የጣፈጠ ይሆናል። ያኔ የድሮውን ህመም ትረሳዋለህ። ህይወትህንም እንድትጠላው አድርጎህ የነበረውን ስቃይ በአንድ ወቅት በህይወትህ ላይ መከሰቱንም ትዘነጋዋለህ።

🌪ይህ ማለት ግን ድሮ የደረሰብህን ህመም እረስተህ በሌሎች ላይ በአንተ ላይ የደረሰውን መንገላታት አድርግ ማለት አይደለም።እንዲያውም ምንም እንኳን አሁን ህመሙና ስቃዩ በላያችን ላይ ባይኖርም ሌሎች የኛ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሲገቡ ዝቅ በማለት ከጎናቸው በመሆንና ተስፋ በመስጠት ህይወታቸው የተቃናና በተስፋ የተሞላ እንዲሆን ማስቻል ነው።

📍የዕውቀት መገለጫው ብዙ ቢሆንም ሕይወትን በሙላት መኖር ዋነኛውና የሁሉ ነገር መሠረት ነው፡፡ ሕይወትን በእርግጠኝነት የምንኖረው ዛሬ ነውና ዛሬን በልቡ መሻት የሚኖር ሰው እሱ አዋቂና ነገ የእሱ እንዳልሆነች የተረዳ ነው። ለዚህ ማሳያ ደግሞ ቀጣይዋን ተረት እናስከትል።

አንድ ቀን በበረሃ የሚጓዝ ሰው እጅግ የሚያስፈራ ነብር በድንገት ከፊቱ ሲመጣ ተመሰከተ፡፡ በዚህ ጊዜ በድንጋጤ ወደኋላው ተመልሶ መሮጥ ይጀምራል። ጥቂት ርቀት ከሮጠ በኋላ ግን ትልቅ ገደል ከፊቱ ይጋረጣል፡፡ ነብሩ ከኋላው እየሮጠ እንደተከተለው የተረዳው ይኸ ሰው ራሱን ለማዳን አማራጭ ያደረገው በገደሉ ጫፍ ላይ የበቀለውን የወይን ሐረግ ተንጠልጥሎ ወደገደሉ መውረድ ነበረ።

🍇 የወይኑን ሐረግ በሁለት እጆቹ ጨብጦ ወደገደሉ ጥቂት ከወረደ በኋላ ቀና ሲል ሁለት አይጦች የተንጠለጠለበትን ሐረግ ግንድ በጥርሳቸው ሊገግዙ ተመለከተ፡፡ በዚያው ቅፅበት በእጆቹ ከጨበጠው ሐረግ አጠገብ የወይን ዘለላ በሌላ ቅርንጫፍ ላይ ተንዠርግጐ አየና ከዚያ እየቀጠፈ መብላት ሲጀምር እጅግ ጣፈጠው።ሁሉን ረስቶም ከሚጣፍጠው ወይን መብላቱን ቀጠለ፡፡ «ሕይወትም እንዲሁ ነች.....

[ The Enlightened One ] እውቀት የበራለት ሰው በዙሪያው ስለበዛው መከራ የሚጨነቅ ሳይሆን ዛሬ በአጠገቡ ባገኘው መልካም ነገርን አስተውሎ አመስግኖ ተደስቶ የሚያልፍ ነው።

📍እናም ወዳጄ

ያለፈው ላይ አትጨነቅ፣ እርሳው፤ አትኩሮትህ ዛሬ ላይ ይሁን፡፡ እውቀት ያለው ሰው በዚህ መንገድ ብቻ ሕይወትን መደሰት ይችላል፣ ስለ ሕይወትህ ችግር ከገጠመህ ወይም ጥያቄ ከተፈጠረብህ ዙርያህን አጥና... ያለህበት ሁኔታ ከሕይወትህ ጋር ያለውን መልካም አንድምታ መርምር በተለይ ትንሽ ትልቅ ሳትል በአቅራብያህ ያሉ ሰዎችን ህይወት በመመልከት ላንተ ምን መልእክት እንዳለው በትጋት ተከታተል ምክንያቱም የተፈጥሮ መንፈሳዊ አንደበት ናቸውና።

⌛️ከዘላለም አንፃር ስናየው የዚህ ዓለም ቆይታ አንዲት ሰዓት እንኳን አይሞላም፡፡ቢሆንም ትግል ባይኖር የድል ደስታ ፣ በሽታ ባይኖርበት የጤና ምስጋና አይኖርም ነበር፡፡ ጣፋጭን ያጎላው መራራ ነው።የሁሉን ሰው መከራ፣ ስደትና ስቃይ ፈጣሪ ይመለከታል። በጊዜው ፍቃድም የሰራውን የሚያፈርስ ራሱ የፈጠረው ነው።

🔑 ተስፋ አለና ትደርሳለህ ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየት ነው ከትላንት ያለፍከው፡፡ በርታ ሰው ሁን ፣ ሰው መሆን ትግል ነው ፣ ግፋ! ፅና! ሰው የድካሙን ፍሬ ሲያይ እና ሲበላ እንዳለ ያለ ታላቅ ደስታ የለምና...... ሁሉም አንተ ውስጥ ነው፡፡ አንተነትህንም ጨምሮ፡፡ ማነህ? ለምን መጣህ? ማን ነው ይህንን ሊመልስልህ የሚችለው? አይታይህም ጥያቄውም መልሱም አንተ መሆንህ?

                ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
👍6253
❤️ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ:-

እንኳን ለጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!

በዓሉ፦ የሰላም ፣ የፍቅር፣ የደስታ ፣ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እና የአንድነት በዓል እንዲሆን እንመኛለን።

  (መልካም ትንሳኤ ፤ መልካም በዓል!)❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
30👍6
❤️ከስሞች ሁሉ ምርጥ ስም  ከሰው ልጅ ከናፍራት ከወጡ ውብ ቃላት አንዱ ፣ እናት" ነው ።

የጥሪዎች ሁሉ ምርጡ  ጥሪ "እማ" ቃላቱ በፍቅር , እና ተስፍ የተሞላ ነው ፣ የምትጣፍጥ ቃል ከሰው ልጅ ጥልቅ ልብ የወጣች ናት። እናት ሁሉ ነገር ናት ፣ በችግር ሰአት አማካሪያችን ናት በጭንቀት ሰአት ተስፍችን ናት። በድክመት ሰአት ጥንካሪያችን ናት፣ እሷ እኮ የፍቅር , የእዝነት፣ የርህራሄ፣ ምንጭ ናት።

💟 እናት እንደ መሬት ሁሉን ቻይ ናት። ብትረገጥ ታግሳ ለወግ ማረግ ታበቃለች። ብትነቀፍና ብትተችም ፈገግታዋ አይከስምም። የዘሩባትን መልካም አድርጋ እንደምታበቅል እርሻ ልበ ንፁሁ እንዲሁም መልካም ፍሬ እንደምታፈራ ዛፍ አብራኳ ለምለም የሆነ የውበት የምጨረሻዋ ምእራፍና የመጨረሻዋ እውነተኛ ዓረፍተ ነገር ነች እናት። ልቧ ከፍቅር ድርና ማግ የተሸመነ ነውና ምን ቢያስቀይሟት የጥላቻ ጥርስ አትነክስም። ፊት ቢነሷት ፊት አትነሳም።

💎 እናት ምድራዊት ፈጣሪ (እግዜር)ናት። በምህረትና በልግስናዋ ልጇን እንደ መልአክ ትንከባከባለች። "ጀነት በእናቶች እግር ስር ትገኛለች" እንዲል ቅዱስ ቁርአንም፣ እናትነት ሰው የመሆን የመጨረሻው ደረጃ ነው። ቅድስና በእናትነት መንገድ የሚደረሰበት የህሊና ንቃት ነው። የእናት ፍቅር የመጨረሻዋ የፅድቅ ፅዋ ነች።

እናት የፍጥረት ሁሉ የመጅመሪያ ምሳሌ ናት፣ ሙሉ የሆነ ውበት እና ፍቅር ተምሳሌት ናት። ከሁሉም በላይ እናት የሚተመንላት ዋጋ የላትም፡፡ ከዋጋ በላይ ናትና፣ ብዙ ድንቅ ፍጥረቶች አሉ ፣ ከነዚህ ሁሉ የምትበልጠው ግን እናት ነች‼️

ውብ የእናቶች ቀንን ተመኘን❤️
                  
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
97👍24👎4
🛑ጦርነት!!!

የሰው ልጅ የውድቀቱ ጥግ፣ የድንዛዜው ቁንጮ፣ የኋላቀርነቱ መስታወት...

ሰልጥነን እንደ ሰየጠን፣ ዘምነን እንደ ጎመዘዝን የሚናገርብን እውነት... በቁስ ተጊጠን በመንፈስ እንደነጠፍን የሚያሳብቅ ገጽታ፣ በሳይንስ ተራቀን በሞራል እንደቀነጨርን መስካሪ ሃቂቃ...

ጦርነት!!...

🔉የሰው ልጅ የትኛውንም ዓይነት አመክንዮ ቢደረድር፣ የትኛውንም ዓይነት ሰበብ ቢያግተለትል ልክ የማይሆንበት ተግባሩ የጦርነት ግብሩ ነው፣
𒌇ድህነት ጦርነት አይቀሰቅስም - የሌጣ አዕምሮ ግልፍተኝነት ግን ጠብ ጭሮ ሌማት ያራቁታል፣
𒌇'የድንበር መገፋት' ጦር አያሳብቅም - የትዕግስት አልባ ችኩል ግብር ግን የእግር መቆሚያ ይነጥቃል...
𒌇የሃሳብ ልዩነት ሳንጃ አያማዝዝም - የአምባገነን ግትር አቋም ግን ምንግዴ ትውልድ ይወልዳል፣
𒌇ኢጎህን መግደል አቅቶህ ሰው መግደል የቀለለህ ዕለት ያኔ አንተ ቀለሃል!... 

እናም እነሆ ቃል - ማኔ ቴቄል ፋሬስ!!

"The greatest victory is that which requires no battle." ~ Sun Tzu 'The Art of War'

🔷'የዘመነ' የጦር መሳሪያ መስራትህ ዘመናዊ አያደርግህም - ጥበቡን ለከንቱ ዓላማ ያዋለ ባለእጅ እንጂ፣ ራስን የማሸነፊያ ብስለት ስለሌለህ ሌሎችን የምታጠቃበት ሰይፍ መሳልህ ብልሃተኛ አያደርግህም - ጦረኛ እንጂ...

♦️በጠብመንጃህ ነድተህ የፈጠርከውን ጠብ ቢሸሽ ፈሪ አይባልም - ስሜት ከሚነዳው ጋር የማይታገል ጠቢብ እንጂ፣ ፍርሃትህን የምትገራበት መላ ስለሌለህ ሌሎችን በፍርሃት ውስጥ የሚከት ጠብመንጃ ታከማቻለህ።

በራስህ ዓለም የሁልጊዜ ባለስልጣን የመሆን ክህሎት ሲያጥጥህ ተሰባሪ ወንበር ለማስጠበቅ ለጋ ሕልም ትሰብራለህ...

📍ጦርነት እምቅ ሀብትን አውዳሚ
እምቅ እውቀትን በታኝ እምቅ ሀይል ያለው ትውልድን አጥፊ ነው ። በአለም ላይ የተደረጉ ጦርነቶች በሙሉ በስተ መጨረሻ ሁሉም ሰው በሰላም ለመፍታት ቢሞክር ይህ ሁሉ ባልሆነ ነበር የሚሉ አንድምታ ይፈጥራሉ።

💡ጦርነት ማለት፦ "አሳምረው የሚተዋወቁ፣ የሚጠላሉና ቅራኔያቸውን በሠላም መፍታት ያልቻሉ፣ ዕድሜያቸውን ያመነዠጉ ሰዎች - የማይተዋወቀውን፣ የማይጠላላውንና ቅራኔውን በሠላም ለመፍታት የማይገደውን ወጣት፣ በሠላም ከተቀመጠበት ከሞቀ ቤቱ ጠርተው፣ እርስበርሱ የሚያጨፋጭፉበት የተረገመ መንገድ ነው"

እኔ ነኝ ልክ ፣ እኔ ነኝ አሸናፊ
በማለት የሚነሳ ትውልድ በእልህ የታነቀ ፣ ቂምን ያረገዘ ሰለሆነ የሚመጣውን የሀገር ውድመት አያስተውልም።

🔑ይህቺን አለም መገንባትም ሆነ ማፍረስ በእኛ የማስተዋል ጥበብ እጅ ነው። በጠንካራ ትውልድ የታነፀች አለም እንድትኖረን ከስህተቶች መማር አለመግባባትን በሰላማዊ ክርክሮች መፍትሄ መፈለግ ትውልድ ፍቅርን፣ አንድነትን ፣መረዳዳትን እንዲማር ማድረግ ይገባናል።

📍ፍቅር የበጎ ነገሮች መክፈቻ ነው፡፡ በፍቅር ያልተዘጋ ሴራ የለም፡፡ በፍቅር ያላበቃለት ጦርነት የለም፡፡ በፍቅር አደብ ያልገዛ ጦረኛ የለም፡፡ ፍቅር የነገሮች መጠቅለያ፣ የበጎ ነገሮች መሠረት ነው፡፡ የሠው ልጅ ጭንቅላቱን በፍቅር ከሞላ ክፉ ሃሳቦችና ተልካሻ ሴራዎች ወደእሱ ድርሽ አይሉም፡፡ በፍቅር የተሞላ ጭንቅላት ትርፉ በፍቅር መኖር ነው፡፡

"Mankind must put an end to war before war puts an end to mankind." ~ John F. Kennedy

ደምስ ሰይፉ

ውብ አሁን❤️

@Bridgethoughts
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
100👍14👎1
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ

🌼አዲስ ሀሳብ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣
ከትላንት ስህተቶች የምንማርበት፣
አዲስ አላማ ቀርፀን የምናሳካበት፣
ጥላቻና ልዩነትን አስወግደን በአንድነትና በፍቅር ወደ ተሻለ እድገት የምንሸጋገርበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን።

🌻ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ 2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ።

🌻ጥላቻና ልዩነትን አስወግደን በአንድነትና በፍቅር ወደ ተሻለ እድገት የምንሸጋገርበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን ! 

❤️በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የፍቅር አመት እንዲሆን እንመኛለን።

   መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችን
          💛 ስብዕናችን 💛

@EthioHumanity
@EthioHumanity
58👍2
📍ስለነገ ሳስብ አዝናለሁ። ዛሬ የሚሆነው ሁሉ ከአቅማችን በላይ እንደሆነ እናስባለን አይደል? መራሩ እውነት ግን ነገ ይብሳል። በአለማችን ብዙ የመከራ ድግስ ተደግሷል። እንደግለሰብ የተወሰኑ ግለሰቦች ህይወት ነገ ከዛሬ ሊሻል ይችላል ግን ብዙሀኑ የአለም ህዝብ ነገው ከዛሬ የከፋ ነው። ለዚህም ነው አዲስ የሚወለዱ ልጆች የሚያሳዝኑኝ።

የተፈጥሮ ውጤቶች ሆነን ሳለን አኗኗራችን ከተፈጥሮ ተቃራኒ ሆኗል። ወንድ እንደወንድ መሆን እያቃተው ነው፤ ሴት የሴትነት ወጉን እየተነፈገች ነው። በማንም አልፈርድም ማትሪክሱ ነው ዋናውን ሚና የሚጫወተው። የሰው ልጆች ከጤናማ የጊዜ ፈሰስ በላይ በሆነ ፍጥነት እንዲሰሩ ይገደዳሉ። ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን እንዲሁም ልጆች እና ወዳጆጃቸውን የሚንከባከቡበት በቂ ጊዜና የአእምሮ ትኩረት እያጡ ነው።

🌖የምንረግጣት ምድር ፍሬ አላፈራ ያለች ይመስል፤ ጤናችንን የሚጎዳ ሰው ሰራሽ አትክልት ፍራፍሬና ምግቦች ያውም በውድ ገዝተን ነው ብዙዎቻችን እንድንበላ እየተደረግን ያለነው። የምንወጋው መርፌ፤ የምንውጠው ኪኒን ከምን እና ለምን እንደተሰራ ብዙዎች አናውቅም። በዘመናዊነት ውስጥ የተደበቀችውን ጸረ-ሰብዕ መርዝ አናይም። በነጻነት ስም የሚጠመጠምብንን የእስር ሠንሠለት አናይም።

ሰብዓዊነት እንዲመናመን ለዘመናት ተሰርቱዋል- እነሆም ፍሬው ጎምርቱዋል። ነገን ስናስብ ዛሬን ከልብ በነገሮች ሁሉ አመስጋኝ ሆኖ መኖር ብልህነት ነው። ትውልዱ ቀልቡ በቁሳቁስ እንዲሸፍት ተደርጓል። በየInstagramu በሚታየው አርቴፊሻል ውበት የወንዱ ልብ ይሸፍታል፤ የሴቱ ልብ ኢንሴክዩርድ (insecured) ይሆናል። በየሚዲያው በሚታዩ ፊልተርድ በሆኑ መልከኞች ባለትዳሩ ቀልቡ ይሸፍታል፤ የትዳር ተጓዳኙ ውበት አልታይ ይለዋል።

🌗በላባቸው ሰርተው የሚኖሩ ታታሪ ወገኖች ሁልጊዜም ውድ ልብስ ለብሰው ፎቶ ሲለጥፉ ከሚውሉ ሰዎች ራሳቸውን እያወዳደሩ እድለቢስነት ይሰማቸዋል። ነገሩ እድል ብቻ አይደለም  የአንዳንድ ሰዎች ስኬት መሰረቱ ህሊናን መሸጥ ነው። ምንም እንኳ ብዙሀኑ ለፍቶ አደር የሚገባውን የሚያገኝበት ሲስተም ውስጥ ባንሆንም እንኳ ህሊናቸውን ሸጠው የበላይነትን ከተቆናጠጡ ግለሰቦች ራስን ማወዳደር ፈጽሞ ልክ አይደለም፤ ቢያንስ ለፍቶ አደሩ በአንድ እነሱ በሌላቸው ከሁሉ የላቀ ሀብት ይበልጣቸዋል - ንጹህ ህሊና።

💫የነገን ለነገ ትተን የዛሬን እንዲህ ማድረጉ የተሻለ ይመስለኛል። በነገር ሁሉ ማመስገን- በማመስገን ውስጥ ብርታት ይገኛል፤ ሀዘን እና ጭንቀት ይቀንሳል እናም መልካም መንፈስ ይቀርበናል። በፈተና ሁሉ ነገሮችን የምንቋቋምበት አቅም እንዲኖረን ራስን ማዘጋጀት እንጂ ፈተና እንዳይኖር ማድረግ አይቻልም። ሌላው ለፍላጎቶቻችን ገደብ ማበጀት( እንደቤት እንጂ እንደጎረቤት አለመኖር) በቡድሂዝም አስተምሮት ከዋነኞቹ Four noble truths መሀል Nirodha የሚባል አለ።

Desire is the mère source of suffering, It is possible to end suffering by letting go of craving and attachment. This state of liberation is called Nirvana (Nibbana), a state of perfect peace and freedom from all suffering. ማለት ነው። እኛ ግን ሙሉ በሙሉ ከdésire or attachement መላቀቅ ስለሚከብደን boundary በማበጀት ስቃይን መቀነስና ሰላምን መጨመር እንችላለን።

📍ከአቅማችን በላይ የሆኑ ነገሮች ስለሌሉን የምናዝን ከሆነ በአቅማችን ያገኘናቸው በረከቶች ደስታን አይሰጡንም። ዋነኛው ትኩረታችን ለመኖር የሚያስፈልጉንን መሰረታዊ ነገሮች ለማሟላት መጣር፤ ሲሟሉም እለት እለት እያመሰገኑ ባሉን ነገሮች ደስታን ለማግኘት መሞከር ቁልፍ የደስታ ሚስጥር ነው። ይህ ማለት ግን የተሻለ ለማሳካት ጥረት ማድረግ የለብንም ማለት አይደለም። እንደ Maslow hiérarchie of needs ቅደም ተከተሉን ልንጠብቅ ይገባል ማለት እንጂ።

ሁሉን በአንዴ ለማሳካት የምንጥር ከሆነ ግን በማያቋርጥ ወሰን አልባ ጭንቀት እና እርካታ ማጣት ውስጥ እንናውዛለን ለዚህች አጭር ህይወት። ሌላው ፍቅር ነው። ከpossession የጸዳ ማፍቀርን መለማመድ ሌላው የቀና መንፈስ ቁልፍ ነው። ማንኛውንም ፍጡር መልካም ጎን ባየን ቅጽበት ሁሉ እንውደድ።

🔑ማትሪክሱ እርስ በእርስ እንዳንዋደድ እና ከመተባበር ይልቅ በፉክክር መንፈስ ጠላት እንድንሆን ነው እያደረገን ያለው። ስለዚህ ጥላቻን በፍቅር እናሸንፈው፤ ፍቅር የራስ የሆነን ነገር ብቻ ማፍቀር አይደለም። ማንኛውንም ሊፈቀር የሚገባ ነገር ሁሉ በማፍቀር በሌሎችም ሆነ በራሳችን ልብ ውስጥ ቀና መንፈስን መዝራት  ማለት ነው።

የቃላት ቤት

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
132👍28
🎄በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እመነት ተከታይ እህት ወንድሞቻችን እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።

💛ይህንን ቀን ስናከብር በአንድነት፣ በርህራሄ  የወደቀን የምናነሳበት፣ የታመመን የምንጠይቅበት፣ ለተቸገሩ የምንረዳበት የልግስናን መንፈስ በመቀበል ያገኘነውን በረከት የምናካፍል እንሆን ዘንድ መልካም ፈቃዱ ይሁን።

በአሉ የሰላም የፍቅርና የደስታ እንዲሆን እንመኛለን።
        
    🏑 መልካም የገና በአል 🏑

           ❤️ስብዕናችን❤️

@ETHIOHUMANITY
@ETHIOHUMANITY
24👍5
🛑በደስታ እና በሀዘን መሀል አንድ ድልድይ አለ ሰላም። ሰላም ከሁሉ ይልቃል የህይወት ሚዛን ነውና። ደስታም ሆነ ሐዘን ወጀብ ናቸው - በዓይነት የተለያዩ ህመሞች። ሰላም ከነዚህ ሁለቱ ኋላ የሚመጣ ስክነት ነው። ሌላ ወጀብ እስኪመጣ የሚሰማን ዘላለማዊነት። በፊዚክስ ውስጥ የሚዛናዊነት (የEquilibrium) ጽንሰ ሀሳብ ማዕከላዊ ነው። አንድ ስርዓት በውጫዊ ኃይሎች ቢገፋም እንኳ ወደ መጀመሪያው ሁኔታው ​​ወይም ወደ አዲስ የተረጋጋ ሁኔታ የመመለስ ዝንባሌ አለው።

📍ሐዘን እና ደስታ በሰው አእምሮ ውስጥ የሚሠሩ ተቃራኒ ኃይሎች ተብለው ሊታዩ ይችላሉ። ደስታ ወደ ላይ የሚገፋ (ተነሳሽነትን የሚጨምር) ኃይል ሲሆን ሐዘን ደግሞ ወደ ታች የሚጎትት (ጉልበትን የሚቀንስ) ኃይል ነው። ሰላም ደግሞ እነዚህ ሁለቱ ኃይሎች እርስ በርስ ሲጣፉ የሚፈጠር የተጣራ ዜሮ ኃይል (Net Zero Force) ሁኔታ ነው። ነገር ግን ይህ ዜሮ ማለት እንቅስቃሴ የለም ማለት ሳይሆን ሚዛኑ ተለዋዋጭ (Dynamic) ነው ማለት ነው። ልክ እንደ አንድ አቶም ያለማቋረጥ በሚንቀሳቀሱ ኤሌክትሮኖች ዙሪያ ባለው ቋሚ ምህዋር ውስጥ እንዳለ መረጋጋት ነው።

🔷ሰው ደስታን ሲያሳድድ ጤናውን፣ ገንዘቡን፣ ህሊናውን፣ በዙሪያው ያሉ ወዳጆቹን እና ራሱን ያጣል። ደስታን በእጅጉ የሚያሳድድ ሰው በእጅጉ ሰላም ያጣ ሰው ነው- ሰላም ማጣት ትልቁ የሀዘን አይነት ነው።  አዕምሮን የሚያልፍ ሰላም ነው ትልቁ ደስታ፣ ትልቁ ስኬት፣ ትልቁ አሁናዊነት። ይህም መገኛ ምንጩ ሚዛናዊነት ነው። በማንኛውም mental state ውስጥ ብንሆን balanceን እንፈልግ።
በቴርሞዳይናሚክስ ሚዛናዊነት ማለት ኢንትሮፊ (Entropy- የስርዓት መበታተን/ውዥንብር) ከፍተኛ ሲሆን እና የኃይል ፍሰት መቆም ማለት ነው። የሰው ልጅ ደስታን ማሳደድ የአዕምሮን ኢንትሮፊ ይጨምራል - ሚዛን የለሽ ጥረት፣ ጭንቀት፣ ጤናን ማጣት።

♦️ሰላም ደግሞ ይህ የውስጥ ውዥንብር የሚቀንስበት እና አእምሮ ወደ ዝቅተኛው የኃይል ሁኔታ ወይም Lowest Energy State የሚደርስበት ሁኔታ ነው። ሰላም ከፍተኛውን የውስጥ ሥርዓት ይፈጥራል፣ ይህም ከፍ ያለ የህሊና ብቃት እና ጤና ያመጣል።
ይህ የፊዚክስ ዋና መርህ ነው። ኃይለኛ የስሜት ፍንዳታን (Explosion) ለማስወገድ፣ በደስታም ሆነ በሐዘን ጊዜ የመለስተኛነት መርህ/ በመጠኑ መሆን (Principle of Moderation) አስፈላጊ ነው።

ልክ አንድ መሐንዲስ ድልድይ ሲሠራ ከፍተኛውን ሸክም እና ንዝረትን የሚቋቋም ሚዛናዊ ንድፍ እንደሚጠቀም ሁሉ የውስጥ ሰላምም ከሁለቱም ከፍ ያለ ደስታ (Peak Joy) እና ከባድ ሀዘን (Deep Sorrow) የሚመጣውን ድንጋጤ የሚከላከል መዋቅር ነው። ሁሉም ዋና ዋና ሃይማኖቶች እና መንፈሳዊ ፍልስፍናዎች ሰላምን ከውስጥ ሚዛን፤ ከአመስጋኝነት እና ከራስን ከታላቅ ኃይል/መለኮት (energy) ጋር ጋር ያገናኙታል።

♦️በምስራቃዊ ሃይማኖቶችና ፍልስፍናዎች (ቡዲዝም፣ ታኦይዝም፣ ሂንዱይዝም) ሰላም የሚገኘው የዓለምን ሥርዓት (Dharma/Tao) በመቀበል ነው፤ ይህም ሰላም እንደ ሥርዓተ ኮስሞስ (Cosmic Order) ነው የሚመለከቱት። በቡዲዝም ሐዘን እና ደስታ እንደ Dukha ወይም የስቃይ ምንጮች ይታያሉ። ሰላም ወይም ኒርቫና ደግሞ ከምኞቶች (የደስታ ፍለጋን ጨምሮ) መገደብ እና መላቀቅ (Detachment) የመጣ ነው ብለው ያምናሉ።

በታኦይዝም ታኦ (Tao) የሁሉ ነገር የመጨረሻው መርህ ነው - ፍፁም ሚዛን። የ ዪን እና ያንግ Yin and Yang ጽንሰ ሀሳብ እንደሚያሳየው፣ ደስታ (ያንግ - ብርሃን) እና ሐዘን (ዪን - ጨለማ) እርስ በርስ የተያያዙ እና የሚደጋገፉ የሕይወት ክፍሎች ናቸው። ሰላም የሚገኘው እነዚህን ተቃራኒ ኃይሎች እንደ ወጀብ በመመልከት ሳይሆን እንደ የአንድ ሙሉ አካል በመቀበል ውስጥ ነው። አመስጋኝነት ወይም Gratitude የውስጥ ሚዛንን የሚጠብቅ መንፈሳዊ መልሕቅ (Anchor) ነው። አሉታዊ አስተሳሰቦችን ይቀንሳል እና የራስን ዋጋ ከውጫዊ ስኬት ይልቅ በውስጣዊ በረከት ላይ ያኖራል ይህም ከጤና እና ከሰላም ጋር የተያያዘውን የሕይወት ትልቁ ስኬት ሚዛን ያጠናክራል።

📍በጣም ደስ የሚያሰኝ ሁኔታ ሲገጥመን ለመረጋጋት ስሜቱን በአፍታ ፍንዳታ ላለማባከን እንሞክር ቀስ በቀስ እያጣጣምነው እድሜው ይራዘም፤ ይህ ከፍተኛ ሐዘን ሲገጥመንም explosion ተፈጥሮ አጓጉል እንዳንሰበር ይረዳናል። የአዕምሮን ሰላም (peace of mind) ለመጠበቅ የሚረዱን ነገሮች- ከአሉታዊ አስተሳሰቦች መራቅ፤ ፍላጎቶችን መገደብ፤ ራስን ከሌላው ጋር አለማወዳደር፤ ስላሉን በረከቶች ዘወትር ማመስገን፤ የህይወት ትልቁ ስኬት ሰላምና ጤና መሆኑን አለመዘንጋት። ደስታን እንደ ግብ ማሳደድ ሳይሆን ሰላምን እንደ የአሁናዊነት ምንጭ ( source of nowness) እና የሕይወት ሚዛን አድርጎ መቀበል ዘላቂ የሆነ መረጋጋት እና እውነተኛ ደስታን ያስገኛል።

                               የቃላት ቤት

             ውብ አሁን ♥️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
72👍6