♦️ለመኖር የመጓጓታችንን ያህል መኖራችን ውስጥ የተሰጠንን ፀጋ ምን ያክል እናስተውላለን? ከውልደት እስከ ሞት የሚዘረጋው የስብዕናችን ተረክስ ሁነኛ ልኩ ምንድነው?
የህይወት ዳርቻ ስትደርስ ጨለማውን ታየዋለህ። ተስፋ ካልተለየህ ጭላንጭሏ ላይ ታተኩራለህ። እሷ እንዳታመልጥህ ትታገላለህ። ካመለጠችህ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መውደቅህን ታውቃለህ ፣ ሰው አንዳንዴ የተስፋው ጭላንጭል ስትሟጠጥ እና የህይወቱ ገመድ ተገዝግዛ ልትበጠስ ስትደርስ የመጨረሻው ንቃት ላይ ይደርሳል፣ ታድያ በዚች ቅፅበት ጨለማውን የሚገፍ የተስፋ ብልጭታና እንደገና ጨብጦ የሚወጣበት የምርጫ ገመድ ሲያገኝ የሚፈጠረው ለውጥ አቻ አይኖረውም።
🔷ዛሬ ብንሞትስ ብለህ አስብ እስኪ
ለነገ ያሳደርካቸው ብዙ ሀሳቦች አብረውህ ይሞታሉ ፣ ለነገ ያቆየሀቸው ስንት ግቦች መቃብር ይወርዳሉ ፣ዛሬ ሳታወጣው የደበቅከው ተሰጥኦህ አብሮህ ይቀበራል ሳይፈነጥቁ የቆዩ ብዙ ተስፋዎች ይቀጫሉ ፣ ለሰዎች ያላሳየሃቸው ስንት ደግነቶች አፈር ይበላቸዋል ያልተነገሩ ስንት ይቅርታዎች ይሞታሉ ነገ እደሰታለሁ ብለህ ቀን ስትጠብቅ ቀኑ ይጨልምብሀል ስለዚህ አስብ እየአንዳንዷን ቀን እንደ መጨረሻ ቀን ቁጠራት ማድረግ ያለብህን ዛሬ እያደረክ ተደሰት።
🔶መኖር ጥሩ ነው። ሌላው ትርፍ ነው።አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' አይምሰልህ ፣ ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ለህይወትህ በይበልጥ ዋጋ የምትሰጠው ልክ የአንበሳ መንጋጋ ገብቶ በተአምር እንደ ተረፈ ነብይ ወይም ጻድቅ ነው።
🔷ከክፉ በሽታና ከሞት ጥግ መመለስ ራሱ ጽድቅ ነው፣ የደረሰበት ብቻ ያውቀዋል፣ ያወቅክ የመሰለህ ያላወቅኸው ብዙ አለና። ዋናው ነገር ለተሰጠህ ለምታውቀውም ለማታውቀውም በረከት ፈጣሪህን አመስግን ፣ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!
ውብ አሁን❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍@Ethiohumanitybot

❤77👍52👎1
📍ፈጣሪ ለምን ፈጠረኝ ብለህ አስበህ ታውቃለህ?
❣እኛ የሰው ልጆች ፈጣሪ ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ አናውቅም!! እሱ በጣም ድንቅ አንጎል እና ስሜት ያለበት አፍቃሪ ልብ ሰጥቶናል፣ለመናገር እና ስሜታችንን ለመግለጽ በሁለት ከንፈሮች ባርኮናል፣ ውበትን የሚያዩ ሁለት ዓይኖች፣ በሕይወት መንገድ ላይ የሚራመዱ ሁለት እግሮች፣ ለእኛ ሁለት የሚሠሩ እጆች፣ እና የፍቅር ቃላቶች የሚሰሙ ሁለት ጆሮችን ሰጥቶናል።
ፈጣሪ ሰውን ሲፈጥር የራሱን ትክክለኛ ባህሪ እንዲላበስ ነው ፤ የፈጣሪ ባህሪ ርህራሄ ቸርነት ፣ ይቅርታ ፣ ፍቅር እና ደስታ ናቸው። እኛም እሱ እንደፈጠርን ሰው ሆነን መኖር ይገባናል።
♦️ሰው ሁኖ መኖር ማለት፦ ከራስ አልፎ ለሌሎችም ማሰብ መቻል ነው፡፡ ሰው ሁኖ መኖር ማለት ሰውን መግደልና መግፋት ሳይሆን ማዳንና መደገፍ ፣ ማበረታታትና ማረጋጋት ነው፡፡ ሰዎችን ገንዘብንና ስልጣንን ፣ ጉልበትንና ጊዜን ተጠቅመው መከራ የሚያሳዩ ሰዎች ሰው ሁነው ተፈጥረው ዳሩ ግን ሰው ሁነው መኖር ያልቻሉ ወገኖች ናቸው፡፡
♦️ሰው ያለሰው ፤ ሰው ያለዙሪያው ህይወትን ሙሉ በሙሉ ሊኖራት አይችልም። ሰው ስንል ግዴታ በአንድ ጣሪያ ስር የሚኖርን ወዳጅ አይደለም፤ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ እንጂ። እኛ ከአለም ውጪ አለም ከእኛ ውጪ አንደኛችም መኖራችን አይረጋገጥም ። ለሰው ማሰብ አለመቻል ኅሊና ማጣት ነው፡፡ አንተ ያስፈለገኽና የሚያስፈልግኽ ለሌሎች የማያስፈልጋቸው የሚመስልህ ከሆነ ራስህን ፈትሽ።
ሰው አድርጎ መፍጠር የፈጣሪህ ድርሻ ሲሆን ሰው ሁኖ መኖር ግን ያንተ ድርሻ ነው፣ ማንነትን የመርሳት መድሀኒቱ ፈጣሪ ስለሆነ በምንችለው መንገድ ሁሉ ወደእርሱ በመቅረብ ማንነትን ከመርሳት በሽታ እንፈወስ!
ውብ አዳር ❤️

❤61👍46
💔 ወርቃማው ጥገና!
በጃፓን ሃገር ውስጥ ለብዙ መቶ አመታት የከረመ ልምምድ አለ፡፡ ጃፓኖች አንድ ከሸክላ የተሰራ እቃ ሲሰበርባቸው እንደገና የመጠገኑን ስራ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) ብለው ይጠሩታል፡፡
ይህ ቃል የሁለት የጃፓንኛ ቃላት ጥምረት ነው፡ “ኪን” (Kin) ማለት ወርቃማ ማለት ሲሆን፣ “ሱጊ”(Tsugi) ማለት ደግሞ ጥገና ማለት ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቃላት ጥምረት የሚሰጣቸው ይህ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) የተሰኘ አንድ ቃል ትርጉም አንድ ነገር ከተሰበረ በኋላ እንደገና በወርቅ መጠገንን የሚያመለክት ነው - ወርቃማ ጥገና!
ከዚህ ልምምዳቸው የተነሳ አንድ የተሰበረ የሸክላ እቃ እንደገና ሲጠገን ይህ የጥገና ሂደቱ በእቃው ታሪክ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ እቃው በመሰበሩ የተነሳ እንደገና ሲጠገን በሶስት መልኩ የላቀ ሆኖ ይወጣል፡- 1) ጥንካሬው ይጨምራል 2) ዋጋው ይጨምራል፣ 3) ውበቱ ይጨምራል፡፡
በሕይወታችሁ ልባችሁን ሰብሮና ስሜታችሁን አቁስሎ የነበረ ያለፈ ልምምድ ካለ፣ አሁንም ተመሳሳይ ልምምድ ውስጥ በማለፍ ላይ ካላችሁና ወደፊትም በሚሰብር ልምምድ ውስጥ ስታልፉ ይህንን የጃፓኖችን የጥገና ሂደት አትዘንጉ፡፡ በሁኔታው ተስፋ በመቁረጥና ተሰብራችሁ ለመቅረት ራሳችሁን ካልጣላችሁ በስተቀር እንደገና ትጠገናላችሁ፡፡ ከተጠገናችሁ በኋላ ግን ከበፊቱ ይልቅ ጠንካራ ሰዎች፣ ዋጋችሁ የከበረና ከበፊቱ ይልቅ እጅግ ውብ ሆናችሁ ነው የምትወጡት፡፡
✨ሆኖም፣ ጥገና ጊዜን እንደሚፈልግ አትዘንጉ፡፡ ጥገና ያለፈውን ረስቶ ፈጣሪን በመታመን ወደፊት የመገስገስን ቆራጥነትም እንደሚፈልግ አትርሱ፡፡
Beauty can be found in imperfection.
✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ
ውብ አዳር ❤️
@EthioHumanity

👍62❤38
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔱 እርግጠኛ ነሽ አርግዘሻል?
ዝሆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ ፀነሱ፡፡ ከሶስት ወራቶች በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ዝሆኗ እንዳረገዘች ከስድስት ወር በኋላ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች ፣ ዘጠኝ ወር ደግሞ ሌሎች ብዙ ቡችሎች ወለደች፡፡ የእርግዝና ስርዓቱ ቀጠለ ፡፡ ውሻዋ በየሦስት ወሩ መውለዷን ቀጠለች።
በአሥራ ስምንተኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝሆኗ ጥያቄ ይዛ ቀረበች ፣
✨“እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር ነሽ? አሁን በሆድሽ ጽንስ አለ? ምክንያቱም በተመሳሳይ ቀን ነፍሰ ጡር ሆነናል ብለን ነበር፣ ከ16 በላይ ቡችሎች ወለድኩኝ እና አሁን ግማሾቹ በዚህ ሰዓት አድገው ትልቅ ውሾች ሆነዋል ፣ ግን አንቺ አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ ትያለሽ፡፡ ምን እየሆነ ነው?
ዝሆኗም “እኔ እንድትረጂ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፣ በማህጸኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው ፡፡ እኔ በሁለት ዓመት ውስጥ አንዱን ብቻ እወልዳለሁ፡፡ የምወልደው ግን ተራ እንስሳ ስላልሆነ ልጄ መሬቱን ሲመታ ምድር ይሰማታል፡፡ ልጄ መንገዱን አቋርጦ ሲሻገር የሰው ልጅ ቆሞ እያደንቀው ይመለከታል ፣ እርሱ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ይንቀጠቀጣል፣ የኔ ልጅ የፍጥረትን ትኩረትን ይስባል ፡፡
✨ሌሎች እንደ መቅስፈት በሚመስል ጊዜ ነገራቸው ሲቀየርና የተሳካላቸው ሲመስልህ በነሱ አትቅና፣ እምነትህም አይጥፋ በፍጹምም ተስፋ አትቁረጥ፣ ምክንያቱም የአንተም ጽንስ የሚወለድበት ጊዜ ይመጣል፣ ምንም ጊዜ ወስዶ የማይመጣ ቢመስልም የተሻለው መምጣቱ የማይቀር ነው፣ እናም ሲመጣ ሰዎችን ሁሉ የሚያነጋግርና የሚያስደንቅ ይሆናል! የዘገየው የተሻለ ስለሆነ ነውና የራስህን ጉዞ ከሌላ ከማንኛውም ሰው ጋር አታነፃፅር !
ውብ የስኬት ጊዜ❤️

❤131👍69
SHEGER SHELF JULY 31_154591_Default_1545919870.mp3
ስብዕናችን {@ABYSINIA}
❤️እኛ ኢትዮጵያውያን
🔶ኢትዮጵያዊያን የሰው ክብረቱ ስራ እና አእምሮ መሆኑን ገና አላወቅንም። ሰርዐት የሌለው ህዝብ የደለደለ ሀይል የሌውም። ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው። የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው።
ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!
✍ በዓሉ ግርማ
🔷 ያለፈው ታሪክ የድሮውም የአሁኑም ኑሮዋችን እጅግ ያሳዝናል። በመላው አለም ላይ ሰላም ሲሰፋ አእምሮም ሲበረታ እኛ በጨለማ እንኖራለን። እርስ በእርሳችን መጠራጠርን አልተውነም። ህዝቦች ሁሉ እርስ በርሳቸው በፍቅር ተቃቅፈው ስለ ልማታቸው ሲደክሙ እኛ አንድ ዘርና ወንድማማች መሆናችን ገና አልተገለፀልንም። እርስ በርሳችን መፋጀት እስከ ዛሬ ጀግንነት ይመስለናል።
♦️ዘወትርም በስምምና በፍቅር አድረን ብንሆን እስከ ዛሬ ድረስ ብዙውን ትልልቅ ነገር መፈፀም እንችል እንደነበር ጥርጥር የለውም። ፈጣሪ ብዙ በረከት ሰጥቶናል ፣ ካለመስማማታችን የተነሳ ግን ሌሎች ህዝቦች በአእምሮና በጥበብ እየበረቱ ሲሄዱ እኛ ወደ ኋላ ቀረን። እንደ አረመኖች እስኪቆጥሩን ድረስ።
♦️ምነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንቅልፍህ መቸ ትነሳለህ? በአለም ላይ የሚደረገውን ነገር ለማየትስ ዓይንህን መቸ ትከፍታለህ? ለውጥንስ መቸ ትናፍቃለህ?
✍ ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ
ውብ አዳር ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanitybot

❤32👍21
🔴 ሕይወት በሚታይና በማይታይ ማዕበል የተከበበች ናት!
ሰው ሃሳቡ በግንባሩ ላይ ቢጻፍ ማን ማንን ቀና ብሎ ያያል? ደግነቱ በውስጣችን ያለውን ማንም አያውቅብንም። የምናስበውን አስበን፤ የፈለግነውን አሳውቀን የምንደብቀውን ደብቀን የመኖር ጥበቡ ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠ ጥበብ ነው። ልብ በሃዘን ደምቶ ፊት በፈገግታ ሲፈካ ፤ ግንባር ኮስተር ብሎ ልብ በሃሴት ሲሞላ ፤ ጉልበት ተንበርክኮ ልብ በትዕቢት ሲቆም ፤ አፍ እንደ ማር ጣፍጦ ልብ እንደ እሬት ሲመር ፤ ማን ማንን ያውቃል ያሰኛል?!
የሰው ልጅ በሚታየውና እና በማይታየው ማዕበል ውስጥ ያልፋል፤ የሚታየው ማዕበል ሌሎች የሚረዱት እና የሚያዩት ችግራችን ሲሆን፤ የማይታየው ማዕበል ደግሞ ከሌሎች ደብቀን ለብቻችን የምንጋፈጠው ችግር ነው”።
ሌሎች የማውቁት ምን አይነት ጭንቀት ይሆን እያንዳንዳችን በውስጣችን ያለው? ምን አይነት የማይታይ ማዕበል እየተጋፈጥን ይሆን?
🔷አዎ በሰው ፊት እንስቃለን ለብቻችን ግን እንባችንን በገዛ መዳፋችን ያለማቋረጥ እናብሳለን። ከሰው መሃል ደምቀን ለብቻችን ስንሆን መግቢያ እናጣለን። ከህዝብ ፊት ከብረን በቤታችን ግን የሰው ያህል የሚቆጥረን የለም። ጠንካራ መስለን፤ ልባችንን ግን በክህደት ስብርብሩ ወጥቷል። ከላይ ሰላም የሰፈነብን እንመስላለን፤ ውስጣችን ግን በተስፋ መቁረጥ ማዕበል ይተራመሳል። ከውጪ ሲታይ ቤታችን የደመቀ ቢመስልም ውስጡ ግን እንደ ዋሻ ቀዝቅዟል። ተለቀም አነሰም ሁላችንም ለሌሎች የማይታይ ለብቻችን የምንጋፈጠው ማዕበል አለን።
🔵እናም በየመንገዳችን ስንተላለፍ ልብ እንበል፤ ሌላው ከኛ ያነሰ ትግል የሚታገል እየመሰለን ፊት አንንሳው፤ እየረገጥን አንለፈው። የኔ ችግር እና ጭንቀት ከሌላው ይበልጣል የሚል አስተሳሰብ ሲኖረን ለሌሎች የምንዘረጋው እጅ ያጥረናል። ትኩረታችን ሁሉ የራሳችን ችግር ላይ ሲሆን ይበልጥ እናማርራለን፤ ሌሎች ለብቻቸው የሚገፈጡትን ማዕበል ስለማናይ “ምነው እኔን ብቻ” እያለን የሃዘናችንን ጉድጓድ ይበልጥ ወደታች እንቆፍረዋለን።
♦️ከትዳር አጋራችን ጋር ክንድ ተንተርሰን እያደርን፤ እርስ በርሳችን የምንፋለመውን ትግል አናውቅም። ለዚህ ነው ጭቅጭቅ ሲነሳ መሸናነፍ እና እርቅ ማውረድ የሚከብደን፤ ማን የማንን ማዕበል ያያልና? እናም በየመንገዳችን የሚያጋጥሙን ሰዎች ሁሉ የራሳቸው የሆነ ታሪክ አላቸው፤ በጫማቸው ሳንቆም አንፍረድ። በደቂቃ ውስጥ ያየነውን ምግባራቸውን ተንተርሰን አንፍረድ።
🔴ሌላውም እንደኔ ስሜት አለው የሚል አስተሳስብ መያዝ ስንጀምር፤ የሌላው ህመም ይሰማናል እናም ብዙ ስህተቶችን ከመፈጸም እንድናለን። ምናልባት ለብቻሽ/ ለብቻህ የምትጋፈጠው ማዕበል ካለህ በርታ… አጋዥ የለኝም ብለህ አትስጋ ፈጣሪ የማትችለውን ችግር አይሰጥህም። አንተ/አንቺ ብቻ ከሰው የተለየ መከራ አልተሰጠሽም/አልተሰጠህም እንደየአቅማችን ለሁላችንም የታደለን ነው እንጂ……ከምንም በላይ ግን እርስ በርሳችን እንተጋገዝ፤ እየተገፈታተርን መተላለፉን እናቆም ምክንያቱም ሁላችንም ለየብቻችን በምንጋፈጠው ማዕበል ደክመናልና።
✍ሚስጢረ አደራው
ውብ አሁን ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanitybot

👍76❤32
📍ወዳጄ ሆይ
ብሩህና መልካም ነገር አስብና! ተነስ
ወደፊት ስለሚሆነው አትጨነቅ ሁሉንም ነገር እንደ ችግር አትመልከት። በራስህ ችግር አትፈጠር። እያንዳንዱ ፈተና ታርሞ ውጤት እንደሚሰጠው ሀሉ ያንተም ችግር እንደተጋፈጥቀው መጠን ለስኬትህ ግብአት እንደሆነ አስብ፣ ስኬት የተለያዩ ደረጃዎች እንዳሉት እወቅ።
📍የስኬት መጨረሻ የውድቀት መጀመሪያ እንደሌለ እወቅ ፣ ስኬት በተገኘ ነገር ላይ በመርካት እንደሚለካ አስብ። ስኬትን ከአእምሮ እርካታ ጋር እንጂ ከቁስ ጋጋታ ጋር አታዛመድ፣ የሰው ልጅ እራሱን ሊያስደስት የሚችለው በመልካም ባህሪውና በሚሰራው ጥሩ ሥራ እንጂ የሚያምር መልክና አቋም ወይንም በርካታ ሀብት ስላለው አይደለም ... የሚያምር አቋምህና ሀብትህ ምድር ላይ ቀሪ ናቸው ..መልካም ስራህ ግን ለነገ ስንቅ ይሆንሐል ! ባለህበት የህይወት ደረጃ መርካት ከቻልክ በራሱ ስኬት እንደሆነ እወቅ።
እናም ወዳጄ
🔑 ሰውን ለመርዳት ጥግ አትያዝ እራስህን ሆነህ ደግ ስራ። በዚህ ምድር ትልቁ ነገር ሰው ሁኖ መፈጠር ሳይሆን ሰው ሆኖ መገኘት ነው ፣ ባለህ ነገር ተደሰት ፣ ተጨማሪ ቁሰ የአኗኗር አማራጭ እንጂ የህይወት ግዴታ እንዳልሆነ እወቅ። ማግኘት የምትችለውን ቁስ እንጂ አንተን የሚፈጥርህ ቁስ ለማግኘት አትጨነቅ ፣ እጅና እግሮችህ ሀብት እንደሆኑ እወቅ ፣ ህልውናህ ብቻውን ስኬት እንደሆነም ላፍታ አትዘንጋ፣ ሁሉም ነገር ሚሆነው አንተ ስትኖር ነው፣ ስለዚም በህይወት ሳለህ ወሳኝ" እና "ጠቃሚ" ሰው ሁነህ ተገኝ ሰዎችን እርዳ። መልካም ሰው መሆን በተግባር እንጂ በትንታኔ ወይም በምላስ አይገለፅምና ፣በምትኖረው ህይወት ቁም-ነገር ያለው ጥሩ ነገር ሰርተህ እለፍ።
ውብ ጊዜ ❤️

👍73❤50
💎 ለመቶ ሚሊየን ሰው 1 ፀሀይ ነው የምትወጣው እንጂ ለሁሉም የተለያየ ፀሀይ አይወጣም፡፡ ፀሀይ ስራዋ መውጣት ነው መሞቅ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ አዲሷ ፀሀይ አዲስ እድል አዲስ ተስፋ አዲስ ስኬት ይዛ በማለዳው ህይወትህን ልታሞቀው ስትወጣ አንተ ዛሬም በትላንት መጥፎ ታሪክህ በእንባ ጥላ ተጠልለህ ትደበቃታለህ፡፡ ሳታሞቅህ ዜናዋን ሳታበስርህ ትገባለች፡፡
💡ተፈጥሮ ሁሌም ለሁሉም እኩል ናት ፡፡ ለሁሉም አንድ ፀሀይ ነው የሚወጣው ዛሬም በፍቅር ከመኝታህ ተነስ የዛሬዋን ፀሀይ በተስፋ ሙቃት አትደበቃት ከውድቀትህ እንቅልፍ እራስህን ቀስቅስ፣ብርሃን የድምቀት መገለጫ ነው ፣ደማቅ ቀን በብርሃን ውስጥ ደግሞ ደጋግሞ ያበራል። የሚሰጠህ ውስጣዊ ስሜት በፈጠርከው ብሩህ ቀን ይወሰናል ተግባር የእምነት ፍሬ ናትና ።
💎 ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። ስኬትህ የመንገድህ ጥግ ላይ ነው፣ ከምታስበው በላይ ቀርብ ነህ፣ ትንሽ መዘግየቱ የሚመጣው ነገር ስለሚበልጥ ነው፣ ትንሽ ታገስህ መንገድህን ቀጥል ፣ ድልህ ቅርብ ይሆናል።
💡አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገሰህ ተራመድ ፤ የህይወትህ ፀሀይ መውጣቷ አይቀርም! ከጨለማው ምሽት በኋላ ሁል ጊዜ ፀሀይ ትወጣለች፣ አንተም በውስጥህ ያለውን ጥንካሬ ሰብስበህ ቀጥል።
ውብ ቅዳሜ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanityBot

❤70👍53
✨ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444'ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
ዒድ ሙባረክ!❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
❤13👍10
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአረም የተወረረ እርሻ አትሁን!
አንዳንድ ሰው የአረም እርሻ ነው። ብዙ የማይጠቅሙ ሃሳቦችን ተሸክሞ ይዞራል፣ አንተ ግን የማይጠቅሙ ሃሳቦችን ከአእምሮህ ጓዳ ቶሎ ቶሎ አጽዳ!
በረከቶችህን እንጂ ጉዳቶችህን አትቁጠር፣አእምሮ ሰነፍ ጮማ ስጋ ነው። መጥፎም ይሁን ደግ የተነገረውን ለቀም ነው።ለአእምሮህ የምትነግረው ደግ ደጉን ይሁን። አለዚያ መጥፎ ሃሳብ ከሰጠኸው ያንን ይዞ ይመርዝሃል።
አዘውትረህ የምታስበው ሃሳብ በውስጥህ ይደድራል። ውሎ አድሮም ይገዝፋል፣ ሃሳብ ለአእምሮ፣ ስፖርት ለጡንቻ እንደሆነው ነው።መጥፎ ምግብ ሰውነትን ይመርዛል።መጥፎ ሃሳብ አእምሮን ይመርዛል።በመጨረሻም ሰውየውን ገላፈቻ (ከጥቅም ውጭ) ያደርገዋል።
መጥፎ ሃሳብን አታመንዥክ የጥላቻ ሃሳብን አታመንዥክ። ይልቅስ መጥፎ ሃሳቦችን ከአእምሮህ እያጸዳህ በመልካም ሃሳቦች ተካቸው፣ስለሰው ስታስብ የሰውየውን መልካም ጎን ለይተህ ለማሰብ ሞክር፣ ችግርን ተጋፈጥ። መልካም ሃሳብን ዝራ፣ መጥፎን በመልካም ሃሳብና ድርጊት ተዋጋ።
ይህ ሁሉ ሆኖ ከመጥፎነት አልመለስ ለሚሉ በመጥፎ ሃሳባቸው እንዳትጠመድ ከእነርሱ ራቅ። ሁሌም ደግ ደጉን እናስብ። ደግ ደጉን እንሥራ። መልካምነት ሌላው ቢቀር የአእምሮ ሰላም ይሰጣል። ከጨጓራ ህመም ያተርፋል።
ነገ ሲነጋልህ፣ ተነስና በረከቶችህን ቁጠር። ለጤናህ ፈጣሪህን አመስግን። ለቀጣዩ ቀን ውሎህ ሰላምና ስኬት ፈጣሪህን በጥበባዊ ጸሎት ለምን። በዚህ ምን ትጎዳለህ? የተሻለ ምርጫስ አለህ?
የቀን ውሎህን አቅድ። ለሥራህ ተዘጋጅና ቆፍጠን ብለህ ውጣ። ፈገግታ ከፊትህ አይጥፋ! ጎበዝ ገበሬ ሁን! የጎበዝ ገበሬ እርሻ ከአረም የጸዳ መልካም ቡቃያ ነው።
✍ Getu k toughe
ውብ ጊዜ❤️

❤72👍53
A SHORT LIFE LESSON!
💎 Someone graduated at the age of 22, but waited 5 years before securing a good job.
📍 Someone became a CEO at 25, and died at 50, While another became a CEO at 50, and lived to 90 years.
💎Someone is still single, while someone from his school group has become grandfather.
📍Obama retired at 55 & Trump started at 70, Everyone in this world works based on their time zone.
💎People around you might seem ahead of you & some might seem to be behind you. But everyone is running their own race, in their own time, Do not envy them.
📍They are in their time zone, and you are in yours.
So, relax.
✨You're not late.You're not early.
You are very much on time, and you will achieve your desired goals for Life (Be Encouraged).
Happy Saturday❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@EthiohumanityBot

❤78👍38
📍በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።
📍መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል። ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። በአጋጣሚ ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።
📍ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል።
💎ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም።
ሁሉንም ክብርና ምስጋና የፈጠረን ይውሰድ።
📖አርምሞ
ወብ አዳር ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot

❤116👍56
ወዳጄ ሆይ
💡በራስህ መስታወት የራስህ አቅም የቱንም ያህል ጉዙፍ መስሎህ ቢታይህም በሕይወትህ ረጅም መንገድ የለህምና የወደቀውን በማንሳት ፈንታ በውድቀቱ አትሳቅ፣በእብደቱ አትሳለቅ ፣ በማጣቱ አትፈንድቅ ፣ እብሪት የውድቀት ዋዜማ ነው ፣ በኋላም ሆነ ነገ ጊዜ ባንተ ላይ ምን እንደሚያመጣ አታውቅምና ስትኖር ጥላቻ ሳይሆን ፍቅርን፣ በቀል ሳይሆን ይቅርታን፣ትዕቢትን ሳይሆን ትህትናን በልብህ ሰንቅ።
ወዳጄ ሆይ
💡ዛሬን ማግኘትህ ትልቅ ስጦታ ነውና በጥልቅ ሀሴት ተሞልተህ ደስ ይበልህ፤ የፈጠረህን በእጅጉ አመስግን፣ በትንሹ ለፀሐይ ብርሃን፣ለምትተነፈሰው አየር ክፈል ብትባል ቅንጣቱን እንደማትችል ሁሉ አስበህ ከማንም እንደማትበልጥ፤ከማንም እንደማታንስ አውቀህ ተራመድ ፣ በተሰጠችህ እያንዳንዷ ቀን በመልካምና በደስታ ለመኖር ሥጋህን ተጠንቀቀው፤ነፍስህን ቁጠራት፣እምነትህን ጠብቀው፡፡
የትም ግባ፣የትም ውጣ በነገሮች አትደነቅ፣ብርቅ አይሁንብህ ዓለምን በሩጫም በእርምጃም ብታስስ ከድካምህ ባለፈ አዲስ ነገር አታይም ፣ ደግሞም ለምድሪቱ ትልቅ ስራ ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ መውደድ ነውና ዋጋ ለማታወጣበት ነገር ለማንም ያልተጓደለ ክብር ስጥ፣ፍቅር አሳይ፡፡
ወዳጄ ሆይ
💡ዕድሜህ ሃያ ዓመትህ ስለሆነ ብቻ ከዚህ በኋላ ብዙ ቀሪ ዕድሜ እንዳለህ እያሰብክ አትኮፈስ በሆነ ገጠመኝና ክስተት ዛሬን ሳያገኙ በምሽቱ ምድሪቱን የተሰናበቱ አያሌ ናቸውና፡፡ ደግሞም ባለህ አያሌ ሀብት፣ባለህ የተንጣለለ ህንፃ፣ባለህ ሠፊ ዕውቀት፣ባለህ ችሎታህ፣ባለህ ጉብዝናህ፣ባለህና በተማመንክበት ሁሉ ዛሬን ለማለፍ ዋስትናህ አይደለምና ከሚሆነው ነገር ተጠበቅ፣ከምታደርገውም ነገር ተጠንቀቅ፡፡
እናም ወዳጄ
💡ተግባርህ በመልካም የተሞላ ይሁን፣አንድ ዳቦ አጥተው ጎዳና የወደቁ ሠዎች መኖራቸውን ባይንህ እያየህ ባንክ ላጠራቀምከው ሚሊዮን ብሮች ከሳሳህ ሠው የመሆን ድርሻህ ምንድነው? ምድር ላይስ የመቆየት ዓላማህ ምን ይሆን? የገነባህው ህንፃ፣ያጠራቀምከው ገንዘብ፣ያነፅከው መኖሪያ ቪላ ከሠዎች ማግኘት ማጣት፣መብለጥ ማነስ በሚል ስሌት አትስራበት፡፡ በመኖርና በመሞት መካከል ያለው ርቀት የቅፅበት ያህል ነውና፡፡
🔑 በዓለም ላይ የትኛውንም ያህል የገንዘብ ብዛት አንድ ቀንን ገዝቶ የአንተንም ዕድሜ፣የዓለምን ፍፃሜ የማራዘም አቅም የለውም። ስለዚህም በምድር ነገር መኩራራትህን ትተህ፣ባለ ነገር መኮፈስህንም አቁመህ፣ምንም ይዘህ እንዳልመጣህና፣ምንም ይዘህ እንደማትሄድ ከገባህ መሽቶ በነጋ ቁጥር ፈጣሪህን ታመሰግናለህ !!!
ዛሬ በሕይወት ስላለህና ይህንንም መልዕክት በማንበብህ ዕድለኛ ነህ.. ደስ ይበልህ!! ይህንን ካነበብክ በኋላ ምን ተሰማህ??

❤77👍48
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሚያሳዝነው እኛ ሰዎች ሙሉ ሕይወታችንን መኖር ለመጀመር በመጠባበቅ ላይ ሆነን ሳንኖር መሞታችን ነው። Eckhart Tolle
“ይህንን ባገኝ ደስተኛ እሆን ነበር” የሁላችንም መፈክር አይደለም? ወይም የለመድነው የኑሮ ሂደት። ከላይ የሰፈረው የኤካርት ቶሌ አባባል ይህንን አኗኗራችን በደንብ ይገልጸዋል ብዬ አስባለው ። ሰዎች ኑሮን ለመጀመር እየጠበቁ ኑሮን ሀ ብለው ሳያጣጥሙ የእድሜያቸው ጀንበር ትጠልቃለች። ጥሩ ስራ ሲኖረኝ፤ ትዳር ስመሰርት፣ አላማዬን ሳሳካ ደስተኛ እሆናለው እያለን ለኑሮዋችን ቀጠሮ ስንሰጥ፤ ያሰብነው እስኪሳካ ደስተኛ ላለመሆን እየወሰንን ነው።
የሰው ልጅ ምኞት ማለቂያ የለውም። በጠየቅን ቁጥር ፈጣሪ ያልነውን ቢሰጠን እንኳን እንደሰው እረክቶ ለመኖር ይከብደናል። ለዚህ ነው ደስታችንን ነገ ከምናገኛቸው ነገሮች ጋር መቋጠር ዛሬን በሰመመን እንድንኖር የሚያደርገን፣ ያሰብኩት እስኪሳካ ደስተኛ መሆን አልችልም ማለት ነው “አስከዛው አልኖርም” ማለት ነው። የነገው ህይወታችን ትልቅ ትርጉም አለው፤ ዋጋው ግን የዛሬን ያህል በፍጹም አይሆንም።
በዚች አጭር ፁሁፍ እንለያይ፣
ለመኖር ስሟሟት ነበር :-
"በመጀመሪያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ለመጨረስ እና ኮሌጅ ለመጀመር ስሟሟት ነበር፣ ከዚያም ኮሌጅ ጨርሼ ሥራ ለመጀመር ተሟሟትኩ
ቀጥሎም አግብቼ ልጅ ለመውለድ ስሟሟት ነበር ፣ከዚያም ልጆቼ አድገው እድሜያቸው ለትምህርት እንዲደርስ እኔም ወደ ሥራ ቶሎ ለመመለስ ስሟሟት ነበር።
ከዚያም ጡረታዬ ደረሰ እሱንም ለማግኘት ተሟሟትኩ ፣አሁን ግን መሸብኝ እኔም እየሞትኩ ነው።በሕይወቴ ውስጥ ለነገዬ ስሟሟት፣ዛሬን መኖርን እንደረሳሁ ድንገት ገባኝ" ይላል ፀሀፊው።
እናም ወዳጄ ውብ አሁን! 😊

❤69👍39👎1
📍ልብን እና አዕምሮን ማቆሸሽ ራስን እንደመጣል ይቆጠራል፡፡ ሕሊና ቢስ መሆንም ሕሊናን በራስወዳድ ሃሳብ ማጨቅየት ነው፡፡ አስተሳሰብን ማጠልሸት፣ አመለካከትን ማጨለም አንጎልን በቆሻሻ መበከል ነው፡፡
ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶ በነበረበት ጊዜ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ ለጆሮ በሚከብድ ቃል እንዲህ ብሎት ነበር:: "ንጉስ ሆይ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"
ንጉስ ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ወደፈጣሪው ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም ፣ ነገር ግን ፈጣሪ ልቦናውን አይቶ እድሜ ጨመረለት። ንጉስ ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ሲሉ ይጠይቁታል
ንጉስ ሕዝቅያስ ግን ከአልጋው ሳይወርድና ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ "ልቡን" ነበር::
አንተም ፈጣሪን የሚፈራ ልብ ይኑርህ ፣ ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። ዓሣ ከውኃ ወጥቶ ከቆየ ወዲያው እንደሚሞት ሰውም ከህሊናው ከፈጣሪው ከወጣ እንደዚሁ ይሞታል፡፡ ዓሣው ቶሎ ተምልሶ ወደ ውኃው ሲገባ እንደሚድን ሰውም ከልቡ ሆኖ ይቅርታ ሲጠይቅ ፣ፈጣሪ የይቅርታውን በር ይከፍትለታል።
🔑ወዳጄ ሆይ ልቦናህን አጥራው፣ ስሜትህን ግራው፣ ሕሊናህን ዘወትር በአዲስና በበጎ ሃሳብ ሞርደው፣ ምን ዘንካታ ብትሆንና አለባበስህ ቢያምር ሕሊናህ ከቆሸሸ በሚያምር ቤትህ ውስጥ ቆሻሻ እንደመከመር ነው፡፡ አንተ ግን ልብህን ካስተካከልክ ቤትህ፣ ስራህ፣ ቤተሰብህ፣ ትዳርህ፣ በዙሪያህ ያሉ ችግሮችህ እና የሚያስጨንቁህ ነገሮች ሁሉ ይስተካከላሉ።
ውብ ምሽት❤️

❤80👍42
✨ለውብ ቀንህ
ፍሬድርክ ኒቼ በደስታና በፈንጠዝያ የምፎልሉትን እንሰሳት ተጠጋና ጠየቃቸው።
"ለምንድነው እንደዚህ ደስተኛ ልትሆኑ የቻላችሁት?" የሚል ነበር ጥያቄው። እነሱም
ባንድነት፣ ባንድ ቃል መለሱለት።
✨ምንም ሳይወያዩ፣ ምንም ነገር ሳይፎካከሩ፣ መንፍሳቸውም ሳይቀናና፣ አንዱም ሌላውን
ሳይተች፣ ደመ-ነሳቸው በሚነግራቸው መሰረት፣ " ከሳለፍነው ታሪክ ጋር ምንም ቁርኝት (Attachment) ስለሌለን ነዋ!" አሉት።
ከአፍታ በሁዋላ "ምን አላችሁኝ? እስኪ ድገሙልኝ?" ሲል
ጥያቄዎቹን አዥጎደጎደባቸው ።
እነሱ ግን የሰጡት መልስ አጭርና አስገራሚ ነበር።
"ምኑን ነው የምንደግምልህ?" የሚልና
ክው አድርጎ የሚያስቀር ………ፎቶው ከፅሁፉ ጋር የሚገናኘው ምኑ እንደሆነ ታውቃላችሁ?
እኛም በየቀኑ አዳዲስ የሆኑ እድል ይሰጡናል። የትናንት ጭንቀቶች አጥብቀን ምንሸከም ከሆነ ግን ዛሬን በሙሉ ሀይላችን መኖር አይቻለንም ፣ዛሬ የትናንት ተማሪ ነው፡፡ ዛሬ ነገን ውብ ቀን ለማድረግ የሚሰራ በእጃችን ያለ መክሊታችን ነው፡፡ የትናንትን ኋላቀርነት የሚደግም የዛሬ ቀን ለዛሬም አይሆንም፣ ለነገም አይተርፍም፡፡ ያለፈውን ደካማ ነገር መሻር ሲገባ የምንደግም ከሆነ ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡ ትናንትን ወደነገ የሚያሻግረው ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ የትናንት ምርጥ ተማሪ ካልሆነ ነገውን ውብ ማድረግ አይችልም፡፡
✨ሕይወትን አስደሳች እና ቀላል አርጎ መኖር ይችላል። የተሸከመከውን የሀሳብ ክብደት ለመተው ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅብሀል፣ የሕይወት እውነተኛ ክስተት አሁን ነው። አሁን ባለህ ጊዜ ሰላም ፍጠር! ዛሬን እንደዛሬ በአዲስ ለመመልከት ፣ ትናንትህን መልቀቅ አለብህ፣ እራስህን አትጋርድ።

👍60❤32
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መረጋጋት የውሃ ተፈጥሮን በጥሩ ሁኔታ ይወክላል።ለእኛ ለሰው ልጆች አርአያ ሊሆነን ይገባል ምክንያቱም ውሀ ሀይሉን የሚሰበሰበው በእርጋታ ነው።
ራሳችንን የመቀየር ሀሳብ ካለን ቅድሚያ አስተሳሰባችን ምን እንደሚመስል መቃኘት አለብን። ረጋ ብለን ለደቂቃ በጥሞና ውስጣችንን ብንሰማ፤ እጅግ እንገረማለን። ሃሳባችን አንዴ ከትላንት፤ አንዴ ከዛሬ አንዴ ከነገ፤ ሳያቋርጥ ይጋልባል፣ልክ ያለማቋረጥ እንደሚማሰል ኩሬ መንፈሳችንን ያደፈርሰዋል።
አእምሮአችን ያለ ማቋረጥ ሀሳብ ሲያበዛ ጭንቀትና ድካም ያስከትላል፣ ውሃን ብቻውን ስንተወው ሳይታወክ ጥርት ረጋ ይላል፣ የረጋ ውሀ ለአናጢው እንኳን ሳይቀር በውሀ ልክ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፣ግንባታን እኩል ያረጋል።
ውሃን ካስተዋልከው ይፈሳል ምንም ጠንካራ ነገር ከመጓዝ አያቆመውም፣ ሁልጊዜ ወደፈለገበት ቦታ ይሄዳል፣ውሃ ትግል አያቅም እንቅፋት ሲገጥመው ዞሮ ያልፋል፣ጠብ እያለም ድንጋይ ይንዳል፣ ስናየው ስስ ነው ግን እሱን የሚያህል ጠንካራ ነገር የለም።በእርጋታ ጊዜ ውሃ እንዲህ ተአምር ከሰራ የሰው ልጅ መንፈስ ረጋ ቢል ምን ውጤት ያመጣል ብለህ አስብ?
ወዳጄ ሆይ አንተም አስታውስ ግማሽ አካልህ ውሃ ነው ፣በእርጋታህ ሀይል መሰብሰብ ትችላለህ ፣እንቅፋት ውስጥ ማለፍ ካልቻልክ አትታገል በዙሪያው እለፍ ፣ በሁኔታዎች አትታሰር ግትር መሆን ጅልነት ነው። በብዙ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ደግሞ ብልህነት ነው።
💧ብልህነት ሁል ጊዜም እንደ ጅረት ውሀ መፍሰስ ነው፣ ነገ የገዛ ራሱን አጋጣሚ ይዞ ይመጣልና የትላንቱ ሃሳብህ ላይ የሙጥኝ አትበል፣የሰው ልጅ እራሱ ከሚፈጥራቸው የመንፈስ ካቴናዎች ነጻ ወጥቶ የመኖር አቅም አለው።የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው።
ውብ ጊዜ❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanitybot

❤71👍40👎2