ስብዕናችን #Humanity
25.4K subscribers
1.66K photos
79 videos
23 files
54 links
🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot
Download Telegram
ሸጋ ብስራት!
📗📒📕

ጀመኣው እንዴት አመሻቹ.... ማንበብ ለሚወዱ ብቻ ሳይሆን የድሮ መፅሐፍት መሸመት የምትወዱ ሰዎች በየአመቱ ሰፍ ብለን የምንጠብቀውን የጠፉ መፅሃፍት አውደርእይ ተዘጋጅቷል።
እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት የሚገርም የከተማ ማእከል አለ::
እዚያ ከመጋቢት 24-26 ከች በሉና ያሻችሁን ሸምቱ!!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@balmbaras
ማራኪ ገፆች! (ለምሽታችን)
📗📗

ጀመኣው ዛሬ ከመሸ የመጣሁት ስለ አንድ ቆንጆ መፅሀፍ ማራኪ ገፅ ለመግለጥ ነው። "የመሀል ልጅ" ይሰኛል በቤዛዊት ዘሪሁን በቅርብ የወጣ መፅሐፍ ነው።ከመፅሐፉ ማራኪ ገፆች ከመቆንጠራችን በፊት ግን አንድ ማለት የምፈልገው እና ሁሌ ጥያቄ የሚሆንብኝ ነገር አለ። እሱም ምንድነው እንደ ሌሎቹ የሙያ ዘርፎች የሴት ደራሲያት ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ የሆነበት ምክንያት ምንድነው ? እስቲ ምክንያት ብላቹ የምታስቡትን ነገር ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል ። ከቀድሞቹ ማለት ከአንጋፋዎቹ የሴት ደራሲያት የተሳካላቸው 4 ሴቶችን አውቃለሁ ፀሐይ መላኩ ፣ የዝና ወርቁ ፣ ሕይወት ተፈራ ፣ ውዳላት ገዳሙ ....በኔ ትውልድ ደሞ የተሳካላቸው ጥራ ብባል በእኔ የንባብ እውቀት ሜሪ ፈለቀ ብዬ አፌን ሞልቼ እናገራለሁኝ ምናልባት ወደፊት እንደ ቤዛዊት አይነት ደፋር ደራሲያት ከመጡ ቁጥሩን ከፍ ያደርጉታል ብዬ አስባለሁ። መፅሐፉን ገዝታቹ ብታነቡት ትጠቀሙበታላቹ በጣም ደስ የሚሉ ፍልስፍናዎች የያዘ ሸጋ መፅሐፍ ነው። ከመፅሐፉ ማራኪ ገፆች አንዱን እንግለጥ እንግዲህ.........
.
.
.

የኛ ሰው <ጦስህን ይዞት ይሂድ> የሚያውቀው ብርጭቆ ስትሰብር ብቻ ነው አንተ ስትወድቅ ግን <ብዬ ነበር> ይላል እንጂ ማንም እጁን ሰዶ ሊያነሳህ አይጥርም አይዞህ እኔም አልፌበታለሁ ማለት ክብሩን መሳት ይሆንበታል ። ደግመህ እንደማትንሰራራ እርግጠኛ ነው። ምፅ ብሎ በቁምህ ይቀብርሃል። ከትቢያ አራግፈህ ለመነሳት ትንፈራፈራለህ ምፅ ይሉልሀል ምፅ እናቱ ሞታ እኮ ነው ምፅ በጣም አንባቢ ስለነበር እኮ ነው ምፅ ካይሆኑ ሠው ጋር ገጥሞ እኮ ነው እያሉ በምፅ ሲፈራረቁብህ ፈሪ ትሆናለህ። የሚቀጥለውን እርምጃህን መቼም አታምነውም ወደኋላ ስታይ ግዜህ ይነጉዳል። በዚህ ሁሉ መሀል ህይወት እንደ ክፉ አስተማሪ መቅጣቷን አታቆምም። አይምሮህ ከገደብ በላይ ይሆንበታል ትደክማለህ በቃ ሰው ነሃ!!

#የመሀል_ልጅ

ያማረ ምሽት ጀባታ!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta
ለጁምኣችን!
💚
ብርሌ በመሰለ ዓለም ፡ መውጪያው ጠባብ በሆነ ፡ በግንባር መደፋት ማለት ማምለጥ ነው ፡ መቃናት ማለት መቅረት ነው ።

📝fksh Ayelgn

በዙፋን ላይ ካለ ንጉስ በሱጁድ ላይ ያለ ሙእሚን ይበልጣል!!

አላህም እንዲህ ብሎ እውነትን ተናገረ
(و اسجد و اقترب) 19 – العلق
«ስገድ፤ወደ አላህ ተቃረብም።»
.
.
አንድ ሰው ከአላህ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ እያለ እንደሆነ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ተናግረዋል።

ኢብነል አልጀውዚ ውብ የሆነ ንግግር አላቸው....

የአላህን ስፍር ቁጥር የለሽ ውለታ ብትገነዘብ ኖሮ ነፍስህን የሃያጥት ባሪያ ባላደረካት ነበር። አላህ "ኢብሊስን" ከእዘነቱ ያባረረው ላንተ የክብር ሱጁድ ለማድረግ አሻፈረኝ በማለቱ መሆኑን እንዴት ዘነጋኸው? ... አግራሞትን የሚያጭረው ጉዳይ የጠላትህ ኢብሊስ ወዳጅ በመሆን ወዳጅህ የሆነው አላህን መክዳትህ ነው።

ከመንገዱ በፊት!!!!!

ረጅም ነው ዙሩ፤ የዱንያ ጎዳና፤
በመሮጥ በመክነፍ፤ መች ይደረስና፤
እባክህ ጀሊሉ፤ ሶብር ይዘህ ናማ።
የመንገዱ ነገር፤ አቀበት ጉብታው፤
ቁልቁለት ሸለቆ፤ ሜዳና ኮረብታው፤
አላስኬድም ካለ፤
ገደላ ገደሉ፤ጭቃና ዝቅታው፤
ከመንገዱ በፊት፤
በርከክ ሲሉ ነው፤ ቁጥሩ የሚፈታው።

እናማ፤
ከመንገዱ በፊት፤
መንገዱን ጀምረው፤ ስጁድ ያለፋቸው፤
ይኸ ሁላ መንገድ፤
በሩጫ ሚደፈር እየመሰላቸው፤
ተቆጥረው አያልቁም፤
መንገድ እየሄዱ፤መንገድ የበላቸው።
እመዋ እመዋ!!!!

((( ጃ ኖ )))💚💛

ሸጋ ጁምኣ!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta
🛑 አንድ ሊቅ ተጠየቀ :- ማነው ብልህ . . . ? ቢሉት - ከእያንዳንዱ ሰው ሊማር የሚችል

~ ማነው ጠንካራ ሰው ? ስሜቱን የሚቆጣጠር ,

~ ማነው ሀብታም ቢሉት . . . በቃኝን የሚያውቅ ,

~ ማነው የተከበረ ሰው . . . ሰውን የሚያከብር ,

~ ማነው ቶሎ ነገር የሚገባው ? ቢሉት . . . በትዕግስት ሰውን የሚያደምጥ ሰው ,,

ድንቅ ሊቅ ድንቅ እይታ❤️

ውብ ቀን❤️

በዓሉ ግርማ ' ሀዲስ
@EthioHumanity
@EthioHumanity
ሰዓት እላፊ! (የቅዳሚት መዳረሻ!)


".....እኔና አንቺ ተለያይተን እዚህና እዚያ ስንቆም ቃሎቻችን ወደ የት ይሄዳሉ? ያልኩሽ÷ ያልሺኝ÷ የተባባልናቸው ነገሮች መጨረሻቸው ምንድነው?
Does they even exist anymore?°°°°?

📝እሱባለው አበራ ንጉሤ

@EthioHumanity
@EthioHumanity
እምወድሽዋ!ቅዳሜዋ!ሸጋዬዋ!

የግጥም ጥግ (ርዕሱ አይደለም) ዛሬ ደርባባዋ ቅዳሚት ነች! እና የዛሬ ቀናችንን ለቅዳሜ በሚመጥኑ በልኳ በወርዷ ልክክ ባሉ ግጥሞች ስንሞሽራት እንውላለን!! የግጥም ጥግ አንድ...


ማነህ ላለኝ ....
በዘመን ላይ የበቀልኩ
የአንድ ሰሞን አበባ ነኝ ።

📝ቴዎድሮስ ካሳ




ኦ ፥ የሽቱዉ ቅመም
የሁሉ ቃና
እባክህ አትሂድ ፥ እባክህን .. ና !
ሁሌም ከጎኔ እንደክንፍ ኹነኝ
ከሚንበለበል ከኩራዝህ ፍም ፥ እንደ እሳትራት ለሞት አቅርበኝ ።
~
በልቤ ፍሰስ በልቤ ሙላ
ሌት ቀን ስባዝን የሚያጫዉተኝ ፥ ካንተ በስተቀር ምናለ ሌላ !!
የመናፈቅ ጥም ጉም ካለበሰዉ
ቀረበኝ ያልኩት እየነካካ ከሚያስለቅሰዉ
ከስጋየ ስር ፥ ከዚህ ቀርቀሃ
ከነፍሴ በታች ካለዉ በረኻ
ማነህ ተጫዋች ፥ ባለ ሙዚቃ
ይኸን ሙት በድን የምታስደንስ በጠፍ ጨረቃ

ቴዎድሮስ ካሳ

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta
❤️የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ፤ ጫማ ስለሌለህ እግርህ አይታይም ፤ የጭንቅላትህን ዋጋ በኮፍያክ ይተምኑሀል ፤ መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩት ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል፤ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ።

🌗እኔ ትንሽነቴን አልረሳም ማወቄም አያመፃድቀኝም ።ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሣይሆን ታግሎ ያለፈ ነው። ሁሌም ቢሆን እራስህን ተመልከት። የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው።
ልትጥለው የሞከርከው ሰው ግን ገልብጦህ ከላይ ሆኖ ታገኘዋለህ።

❤️ሁሉንም በገንዘብ እገዛዋለው ብለህ አታስብ በገንዘብ የምትገዛው ርካሹን ነገር እንጂ ውድ ነገሮች የዋጋ ተመን የላቸውም።🙏
ውብ ምሽት
🌗❤️🌗❤️🌗❤️🌗❤️🌗❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
ለሰንበታችን!
💚

የመኖራችን ህያው ምልክት ፣ የትናንሽ ትውስታ ሰነድ ፣የትናንት መንገድ አሻራ ፣ የዛሬ እውነት የነገ ታሪክ ፣ የትናንሽ ትርክት ዳና ፣ የነገ የገዘፈ ጣዕማም ሀውልት ይመስለኛል ትዝታ ለኔ።

ዛሬን በትናንት መነፅር ስመለከተው የመግዘፍም የመስነፍም ማንነት በህይወቴ ብራና ላይ ተከትቦ ይገኛል ፣ ከአትሮኖሱ አኑሬ ሳስሰው ፣ ስፈትሸው ደግሞ ይህ ነው የህይወት መስህቡ ፣ የመኖር ውሉ ያሰኘኛል....እንደ እድሜዬ ሁሉን ላይ መታደልን ደግሞ ኖርኩት ያሰኛል።

የአፍላነት የፍቅር ትኩሳት የሚጀመርባት ፣ በተወጋ እና የደም ነጠብጣብ ያሸበረቀ የደብዳቤ ዘመን ፍቅር ፣ የየዋህነት ዓለም ፣ ምግብ የማያስበላ ስሜት ፣ የአመት በዓል ፖስት ካርድ ፣ ንፁህ ስሜት ፣ ከቁሳዊ አለም የራቀ ቁርኝት ፣ ብዙ ያለመመኘት ፣ በትንሽ የመርካት እድሜዬ ውል ትለኛለች

ለፀብ ተጋግዘን ፣ ተቧድነን የምንራኮትበት ፣ እንደምን ናቀከኝ ብለን የተቧቀስንበት ፣ ስለት የመያዝ ትልቅ ጀብድ የሚያሰኝበት ፣
ጉርምስናዬ ትናፍቀኛለች ፣

በዚህ የእኔ የህይወት አምድ ውስጥ አብራችሁ የከተማችሁ ፣ በህይወት ግሳንግስ ላለመውደቅ የምትባትሉ ፣ የህይወት ማዕበል ወደ እዛኛው የህይወት አለም የገፋችሁ ፣ እንደ ምሰሶ በጠነከረ ወዳጅነት ዛሬ ድረስ የዘለቃችሁ ነፍሴ አብዝታ ታከብራችኋለች..... የትዝታ ማህደራችሁን እየፈተሻቹ ትናንታችንን ታስዳስሱን ዘንድ እየተጠየቃችሁ ካላችሁበት ይህን ዘፈን ተጋበዙልኝማ

ወንድሙ ጅራ
የእኔ ትዝታ

መልካም ሰንበት!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
🕯🕯📜🕯🕯🕯📃🕯🕯🕯📜

ከመሰበር እንቃና፣ከማጎንበስ እንበል ቀና
ሃገር በእኛ እንድትቀና....ሃገር የምትቀናው እውቀት ላይ በተመሰረተ፣ በመከባበር መንፈስ ውስጥ ባደረ፣ ለለውጥ እራሱን ባሰናዳ ባለቅኔ ትውልድ ብቻ ነውና ባለቅኔ የሆናችሁ የነገይቱ ተስፋ ልጆች ተቀላቀሉን! ሃሳባችሁን፣ እምነታችሁን እና እውቀታችሁ እያጋራችሁ በመጋራት መንፈስ ለታላቅነት በእውቀት ክነፉ. .
🕯📃🕯🕯……………🔰🔰


ተቀላቀሉን

👇👇👇👇👇👇👇

@keneyalew
@keneyalew
@keneyalew
@keneyalew
የድል ቀን!
💚💛❤️💪

እግርኳስ ከስፖርት በላይ ነው !

አንድነትን ይፈጥራል ፣ ሰላምን ያሰፍናል በጥላቻ ውስጥ ገብቶ ፍቅርን ይገነባል ።

ከ14 አመት በፊት ዲዲየ ድሮግባ የዛሬ ተጋጣሚያችን ለአምስት አመታት የቆየውን እርርስ በርስ ሲጨረሱ ጎል አስቆጥሩ በመማፀን ብቻ ጦርነቱን አስቁሞ ነበር ። ይሄ ሁሉ የሆነው በእግርኳስ ነው !

እግርኳስ ከሴክስ በላይ አስደሳች ነው ይለናል የባርሴሎናው የመሀል መሀንዲሱ ሰርጂዮ ቡስኬትስ ልክ 2010 አለም ዋንጫን ባነሱባት ቅፅበት ደስታውን ሲገልፅ ።

በ1915 እኤአ በእንግሊዝና ጀርመን መካከል በነበረው ጦርነት ለአዲስ አመት ሰላም ያሰፈኑበት ወታደሮቹ እግርኳስን በመጫወት ነው ። ለዚ ነው ከሱስም በላይ ነው ምንለው !!

አሁን የኛም ህዝብ በውስጡ ብዙ ነገሮች አሉበት በብዙ ነገር አንዱ ከአንዱ ተለያየቷል አድነታችን ከምንጊዜውም በላይ እየሻከረ የመጣበት ወቅት ነው 120 ሚሊየን ህዝብን በ90 ደቂቃ ተጋድሎ አንድነት ፍጠሩለት !!🙏🙏🙏

እውቁ ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ እሁድ እለት እንዲህ ሲል መልእክቱን ለጥቁር አንበሳዎቹ እንዲህ ሲል አድርሷል....

"ስራው አልተጠናቀቀም። እናንት ውድ የሃገራችን ልጆች ዛሬ ጨርሱትና #ፖለቲካ የረበሸውን ህዝባችሁን በእግሮቻችሁ ምትሃት ሰብስቡት፤ ሁሉም ያያችኋል፤ አንድነትን አሳዩት፤ የረሳውን ህብረት አስታውሱት፤ ችግሩን አስረሱት፤ ቁስሉ ባይሽር እንኳን ማስታገሻ ሁኑለት፤ የወዲያኛውን ሠፈር ከዚህኛው ሠፈር ጋር ቀላቅላችሁ ወደ ህብረቱ መልሱት፤ በጋራ የሚደሠትበትን ዕድል ስጡትና እግርኳስ ከስፖርትም በላይ መሆኑን አስተምሩት።"


ድል ያለ ድል ለሃገሬ ዛሬ ሁላችንም የምንደሰትበት በጋራ ስለ ኢትዮጵያችን የምንዘምርበት ካጠላብን ጥላ ትንሽም እንኳን ቢሆን ገፈፍ የሚልበት የድል ቀን!!
💚💛

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta
1
ቃላት ስሜትን መሸከምም ሆነ መግለጥ አቅቷቸዋል!!!💚💛

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹


🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹


እንኳን ደስ አለን!!!!💚💛💚💛💚💛