እምወድሽዋ!❤️ቅዳሜዋ!❤️ሸጋዬዋ!❤️
ማለዳ ከአልጋዬ ስነሳ አይኔን በአይበሉባዬ እያሸሁና የቆሙ ጸጉሮቼን ወደታች ለመመለስ እየታገልኩ ወደመጸዳጃ ቤት በእንግድግድ እርምጃዎች እገባና በሩን በሚዘጋበት ሀይል መጥኜ አሽቀንጥሬ እስኪዘጋ ሳልጠብቅ በፍጥነት ለተወጠረው ፊኛዬ ምላሽ ልሰጥ እቀመጣለሁ,,,,።
<<ኡፍፍ,,,,, መተንፈስን የፈጠርክ ፈጣሪ አለመተንፈስንም ፈጥረሀልና ትመሰገናለህ,,,,,!!>>
ጥርሴን ልቦርሽ መስታወቱ ፊለፊት ስቆም በህሊናዬ ተከስሼ ፍርዴን እየተጠባበቅኩ እንደቆምኩ አስቤው ቀፈፈኝ ።
የጥርስ ሳሙናውን ሆድ በጣቶቼ ተጭኜ ብሩሼ ላይ ካደረግኩ በኋላ በደመነፍስ አሁንም መስታወቱ ላይ አፈጣለሁ።
ጨብራራ ጸጉሬ ፣ ኩሉ የገፈፈ ቅንድቤን ፣ ወደአንድ በኩል ያጋደለው ሰፊው ቲሸርቴ ፣ የተጨናበሱ አይኖቼን አንገቴን አስግጌ ይበልጥ ቀርቤ በጣቶቼ ጥግ ማዕድን እንደሚፈልግ ሰው በረበርኳቸውና አጸዳኋቸሁ።
<< ለምንድነው ዳኛ መስለህ እፊቴ የተገተርከው,,,,? ለምንስ ከውበቴ እንከኔን ታሳየኛለህ,,,? ብሽቅቅ,,,,! >> ብሩሹ ላይ ያለውን ሳሙና ውሀ አስነካሁና መስታወቱ ላይ ረጫጨሁት ። አሁንም ይዳኘኛል,,,?
የአፌን አረፋ ተፋሁበት ።
<<ቱ! ግድ አይደለም ባንተ ውስጥ እራሴን ማየቴ እሺ ,,,,? በውጫዊው አካሌማ አትዳኘኝም! ከቻልክ ውስጤን እያሳየህ ጉድለቴን ነቅሰህ አውጣ ደካማ,,,,,!!>>
ጥርሴን ተጉመጥምጬና ታጥቤ ስጨርስ "እኝኝ "እንዳልኩ እንደልማዴ ወደመስታወቱ ፊቴን ሰገግ ሳደርግ በሳሙና ጭጋግ ተሸፍኗል። በስራዬ ተገርሜ እንከተከት ጀመር። እራሴው እንከኔን እንዳይነግረኝ ሸፍኜው የጸዳሁ ሲመስለኝ ፈለግኩት "ቂቂቂቂ...." አለ መኪ።
<< ለምንድን ጉድለታችንን ከሚነግሩን ይልቅ የሚክቡን ጋር መሆን ምቾት የሚሰጠን ? ደካሞች ነን,,,።
ብዙ ጠንካራ ጎን እያለን ለመጽናናት ፈንታ በድክመታችን ተሸማቀን ስለምንኖር ብርታታችንን መስካሪ እንጂ ጉድለታችንን ነቃሽ የማይመቸን,,,,,!! >>
(የሚቀጥል ግን የማይቀጥል,,)
✍መርየም
@EthioHumanity

💎ፊት ለፊት ትይዩ የተገነቡ ሁለት ቤቶች አሉ ። በሁለቱ ቤቶች ጣሪያዎች ላይ ደግሞ የእግር መርገጫ ስፋት ብቻ ያለው የጣውላ መረማመጃ ድልድይ ቢጋደምና በላዩ ላይ ተራምዳችሁ ከአንዱ ጣርያ ወደሌላው እንድትሻገሩ ብትጠየቁ ፈቃደኛ ላትሆኑ ትችላላችሁ ። ይኸው ጣውላ መሬት ላይ ተጋድሞላችሁ እንድትራመዱበት ብትጠየቁ ግን ህፃን ፣ ወጣት ፣ አዛውንት ሳይባል ፣ ሁላችሁም ሳትወድቁ ትራመዱበታላችሁ ።
📜 የጣውላ መረማመጃው ያው ነው ፤ እናንተም ያው እናንተው ናችሁ ፤ ታድያ ጣውላው በቤቶቹ ጣሪያዎች ላይ በተጋደመ ጊዜ እንድትራመዱበት ስትጠየቁ ለምን እምቢ አላችሁ? መሬት ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ብዙ ሰዎች ሳይወድቁ ተረማምደውበታል ። ታድያ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ ያለው ሌላ ቦታ ነው ።
🔑 መሬት ላይ ተጋድሞ ሳለ ጣውላው ላይ ለመረማመድ ንቁ መሆን አያስፈልግም ።ንቃት አልባ ሆናችሁ ልትራመዱ ትችላላችሁ ። በጣውላው ላይ ተረማምዳችሁ ከጣሪያ ጣርያ ለመሻገር ግን ንቁ መሆን ይኖርባችኋል ። ንቃት እንደሌለን እናውቃለን ፤ በዚህም ምክንያት ወድቀን እንዳንሞት እንፈራለን ። መሬት ላይ ስንራመድ ግን ብንወድቅ እንኳን እንደማንሞት እናውቃለን ።
💎 አልፎ አልፎ አደጋ በሚያጋጥመን ቅፅበት ንቃት ይኖራል ። ሌላ ግዜ ግን እንቅልፍ ላይ ነን ። ሞት ሲቀርበን ንቃት ይኖራል ፤ አለዚያ ግን ንቁ አይደለንም ። ልማዶቻችንን መቀየር የማንፈልገው ለዚህ ነው ፤ ምክንያቱም ልማዶች ሲለወጡ ንቁ መሆን ያስፈልጋል ። አሮጌ ልማዶች የእናንተን ንቃት አይፈልጉም ።
📖 የንቃት ፀሃይ /ኦሾ/
ገጽ 99-100
ትርጉም ✍ መርሻ በነበሩ
💎🔑💎🔑💎🔑💎🔑💎🔑💎🔑
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot

☯There's a reason you can learn from everything: you have basic wisdom, basic intelligence, and basic goodness.“Would you like to save your country from destruction ? Then step away from Mass movements and quietly go to work on your own self-awareness.
☯If you want to Awaken all of humanity, then Awaken all of yourself. If you want to eliminate the suffering in your country, then eliminate all that is dark and negative in yourself. Truly, the greatest gift you have to give is your own self-transformation.”
🔆we can simply explore Humanity and all of creation in the form of ourselves. Everything that human beings feel, we also feel. We can become extremely wise and sensitive to all of Humanity and the whole universe simply by knowing ourselves,Just as we are.
የሰው ልጅ እኩልነትን እንደማስረጃ ከሚያሳዩት አንዱ"ሰው"መሆን ነው።
🔆ሰው መሆን ማለት ደግሞ፤ ራቁታችንን ከተወለድን በኋላ፤ ከልብስ ጀምሮ አካላችንን ከሚሸፍኑት የማንነት ሽፋኖች መላቀቅ ነው። ሰው ራቁቱን በመወለድ ይዞት የመጣውን መሰረታዊ ማንነት፦ ማለትም መወለድ፣ መኖርና መሞትን ይዘነጋል።
☯ገላው በእናቱ ሆድ የለመደው ሙቀት ሲቀርበት እንዳይበርደውና እንዳይቆረፍድ ልብስ መደረብን፣ ቆይቶ መለያ ስምን፣ ሃይማኖት፣ ዘር፣ ብሄር፣ በተሰብ፣ ሙያ፣ ትምህርትና ስፍርን የመሰሉ ግዑዝና ምናባዊ አልባሳትን በመደረብ" ሰው- ነቱን" ያጣል።
🔆በቀረ ዘመኑ ሁሉ ይዞት የተወለደውን ማንነት ፍለጋ አውቆም ሆነ ሳያውቅ ሲዳክር ይኖራል። ሰው መሆን ከዚህ ሁሉ ድርብርብ ሽፋን የበለጠ መሆኑን ሳያውቅ ወይንም ሳይረዳ ህይወቱን ይገፋል። ሰው መሆንን ለማወቅ የሚሄድበት ትግል፣ ሁሉም ከብርድ ለመሽሽ ከሌላና ጥላ፣ እንዲሁም ሽፋን እንደመፈለግ ነው።
☯ለዚህ ማሳያው የአብዛኛው ሰው ቋሚ ፍላጎት ህይወትን"መለወጥ" ነው። ሁሉም ሰው "ራሴን ለውጬ" ፣ "በተሰቤን ለውጬ" ፣ "መለወጥ አለብኝ ...።" ፤ " ቤተሰቤን ልለውጥ" ፣ "ሀገሬን ልለውጥ" ፣ " ሀይማኖቴን ልለውጥ "እያለ ይኖራል።
✨ከዚህ ሁሉ ለውጥ ውስጥ እያንዳንዱ አድስ ለውጥ አሮጌ ህይወት እየሆነ እንደ ልብስ ከመደረብ ውጭ እውነተኛ ለውጥ ሳይሆን ይቀራል ። እውነተኛ ለውጥ የማይኖረው ሰው ስላልጣራና ስላልሞከረ ሳይሆን ለውጥ ሂደት እንጂ መድረሻ ባለመሆኑ ነው ።
🔆በአንድ ለውጥ መርጋት በሰው ተፈጥሮ ውስጥ ከማይቻሉት ሀቆች አንዱ ነው። በመሆኑም ሰው ቢለውጥ፣ ቢለውጥ ከደረባቸው የማንነት አልባሳት አንዱን ወይንም ሌላውን እንጂ ሰው -- ነቱን" ሊሆን አይችልም።
☯ከዚህ የማንነት ግራ መጋባት ነፃ የሚወጣው በሞቱ ነው።
ሞት ትልቁ ነፃ አውጪ ነው። እንዳልነበረ ይረሳል። ስሙና ማንነቱን ሌላ ይወርሰዋል ።
✍አለመኖር ገፅ፡ 111- 112
በዳዊት ወንድምአገኝ /ዶክተር /
☮🔆☯🔆☮🔆☯🔆☮🔆☯🔆
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot

ለውብ ቀን!
💚
፩ (አንድ)
ግለ-ሰብ የትግል አርማ ሊሆን አይገባም። የትግል አርማ መሆን ያለበት የትግሉ ውጤት ነው። ግለሰብ ግለሰብ ነው። ይውሸለሸላል፤ይማልላል፤ይሻፍዳል፤
ይታበያል፤ይሰርቃል ፤ይደክማል ፤ይሳሳታል፤ ይደለላል። ግለሰብ ላይ የተንጠለጠለ ድል ግለ-ሰብ ላይ ያልተንጠለጠለ ስርአት ካልተዘረጋ ድሉ ድል አይደለም ።
፪ (ሁለት)
በየትኛውም የግፍ ዘመን ውስጥ ዳር ሆኖ ያየ ትልቅ ነኝ ባይ፤ የተሳተፈ ፤ዝምታን የመረጠ አባት፤ ያልመከረ ምሁር ፤ በደልን ያስተባበለ አንዱም ሳይቀር በየደረጃው ሃጥያተኛ ነው።
፫ (ሷስት )
.....
ብልህ በተበጀለት ሽል ውስጥ ሆኖ አይወራጭም። የራሱን መወራጫ ነገን ያማከለ ርእይ በውብ ሃሳብ በልኩ ያጎለብታል እንጂ ።
፬ (አራት)
ከተወለድንበት ሰፈር፤ ከምንከተለው ሃይማኖት ፤ አሽቆልጠን ከምናገኘው ፍርፋሪ፤ ግዜ ከሚያፈዘው ስልጣንም ሆነ ሳንቲም ሁሉ ሰውነት ይገዝፋል።
፭ (አምስት)
ሁሌም ጥግ ለጥግ ሆነው ከሚካረሩት አክራሪዎች ይልቅ መሃል ላይ ያሉ እንዳይበጠስ የሚዳክሩት ቅዱስም ምስጉንም ናቸው🙏🙏
ውብ ቀን!💚
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@balmbaras

❤️ደግነት በቃላት ሲገለጽ ልበ ሙሉነትን ያመጣል፡፡
ደግነት በኃሳብ ሲሆን የስብዕና ጥልቀት ይፈጥራል፡፡
ደግነት በመስጠት ሲሆን ፍቅር ከውስጡ ያብባል፡፡
ውብ ምሽት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
ደግነት በኃሳብ ሲሆን የስብዕና ጥልቀት ይፈጥራል፡፡
ደግነት በመስጠት ሲሆን ፍቅር ከውስጡ ያብባል፡፡
ውብ ምሽት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
ሸጋ ብስራት!
📗📒📕
ጀመኣው እንዴት አመሻቹ.... ማንበብ ለሚወዱ ብቻ ሳይሆን የድሮ መፅሐፍት መሸመት የምትወዱ ሰዎች በየአመቱ ሰፍ ብለን የምንጠብቀውን የጠፉ መፅሃፍት አውደርእይ ተዘጋጅቷል።
እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት የሚገርም የከተማ ማእከል አለ::
እዚያ ከመጋቢት 24-26 ከች በሉና ያሻችሁን ሸምቱ!!!

ማራኪ ገፆች! (ለምሽታችን)
📗📗
ጀመኣው ዛሬ ከመሸ የመጣሁት ስለ አንድ ቆንጆ መፅሀፍ ማራኪ ገፅ ለመግለጥ ነው። "የመሀል ልጅ" ይሰኛል በቤዛዊት ዘሪሁን በቅርብ የወጣ መፅሐፍ ነው።ከመፅሐፉ ማራኪ ገፆች ከመቆንጠራችን በፊት ግን አንድ ማለት የምፈልገው እና ሁሌ ጥያቄ የሚሆንብኝ ነገር አለ። እሱም ምንድነው እንደ ሌሎቹ የሙያ ዘርፎች የሴት ደራሲያት ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ የሆነበት ምክንያት ምንድነው ? እስቲ ምክንያት ብላቹ የምታስቡትን ነገር ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል ። ከቀድሞቹ ማለት ከአንጋፋዎቹ የሴት ደራሲያት የተሳካላቸው 4 ሴቶችን አውቃለሁ ፀሐይ መላኩ ፣ የዝና ወርቁ ፣ ሕይወት ተፈራ ፣ ውዳላት ገዳሙ ....በኔ ትውልድ ደሞ የተሳካላቸው ጥራ ብባል በእኔ የንባብ እውቀት ሜሪ ፈለቀ ብዬ አፌን ሞልቼ እናገራለሁኝ ምናልባት ወደፊት እንደ ቤዛዊት አይነት ደፋር ደራሲያት ከመጡ ቁጥሩን ከፍ ያደርጉታል ብዬ አስባለሁ። መፅሐፉን ገዝታቹ ብታነቡት ትጠቀሙበታላቹ በጣም ደስ የሚሉ ፍልስፍናዎች የያዘ ሸጋ መፅሐፍ ነው። ከመፅሐፉ ማራኪ ገፆች አንዱን እንግለጥ እንግዲህ.........
.
.
.
የኛ ሰው <ጦስህን ይዞት ይሂድ> የሚያውቀው ብርጭቆ ስትሰብር ብቻ ነው አንተ ስትወድቅ ግን <ብዬ ነበር> ይላል እንጂ ማንም እጁን ሰዶ ሊያነሳህ አይጥርም አይዞህ እኔም አልፌበታለሁ ማለት ክብሩን መሳት ይሆንበታል ። ደግመህ እንደማትንሰራራ እርግጠኛ ነው። ምፅ ብሎ በቁምህ ይቀብርሃል። ከትቢያ አራግፈህ ለመነሳት ትንፈራፈራለህ ምፅ ይሉልሀል ምፅ እናቱ ሞታ እኮ ነው ምፅ በጣም አንባቢ ስለነበር እኮ ነው ምፅ ካይሆኑ ሠው ጋር ገጥሞ እኮ ነው እያሉ በምፅ ሲፈራረቁብህ ፈሪ ትሆናለህ። የሚቀጥለውን እርምጃህን መቼም አታምነውም ወደኋላ ስታይ ግዜህ ይነጉዳል። በዚህ ሁሉ መሀል ህይወት እንደ ክፉ አስተማሪ መቅጣቷን አታቆምም። አይምሮህ ከገደብ በላይ ይሆንበታል ትደክማለህ በቃ ሰው ነሃ!!
#የመሀል_ልጅ
ያማረ ምሽት ጀባታ!💚
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

ለጁምኣችን!
💚
ብርሌ በመሰለ ዓለም ፡ መውጪያው ጠባብ በሆነ ፡ በግንባር መደፋት ማለት ማምለጥ ነው ፡ መቃናት ማለት መቅረት ነው ።
📝fksh Ayelgn
በዙፋን ላይ ካለ ንጉስ በሱጁድ ላይ ያለ ሙእሚን ይበልጣል!!
አላህም እንዲህ ብሎ እውነትን ተናገረ
(و اسجد و اقترب) 19 – العلق
«ስገድ፤ወደ አላህ ተቃረብም።»
.
.
አንድ ሰው ከአላህ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ እያለ እንደሆነ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ተናግረዋል።
ኢብነል አልጀውዚ ውብ የሆነ ንግግር አላቸው....
የአላህን ስፍር ቁጥር የለሽ ውለታ ብትገነዘብ ኖሮ ነፍስህን የሃያጥት ባሪያ ባላደረካት ነበር። አላህ "ኢብሊስን" ከእዘነቱ ያባረረው ላንተ የክብር ሱጁድ ለማድረግ አሻፈረኝ በማለቱ መሆኑን እንዴት ዘነጋኸው? ... አግራሞትን የሚያጭረው ጉዳይ የጠላትህ ኢብሊስ ወዳጅ በመሆን ወዳጅህ የሆነው አላህን መክዳትህ ነው።
ከመንገዱ በፊት!!!!!
ረጅም ነው ዙሩ፤ የዱንያ ጎዳና፤
በመሮጥ በመክነፍ፤ መች ይደረስና፤
እባክህ ጀሊሉ፤ ሶብር ይዘህ ናማ።
የመንገዱ ነገር፤ አቀበት ጉብታው፤
ቁልቁለት ሸለቆ፤ ሜዳና ኮረብታው፤
አላስኬድም ካለ፤
ገደላ ገደሉ፤ጭቃና ዝቅታው፤
ከመንገዱ በፊት፤
በርከክ ሲሉ ነው፤ ቁጥሩ የሚፈታው።
እናማ፤
ከመንገዱ በፊት፤
መንገዱን ጀምረው፤ ስጁድ ያለፋቸው፤
ይኸ ሁላ መንገድ፤
በሩጫ ሚደፈር እየመሰላቸው፤
ተቆጥረው አያልቁም፤
መንገድ እየሄዱ፤መንገድ የበላቸው።
እመዋ እመዋ!!!!
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!💚

🛑 አንድ ሊቅ ተጠየቀ :- ማነው ብልህ . . . ? ቢሉት - ከእያንዳንዱ ሰው ሊማር የሚችል
~ ማነው ጠንካራ ሰው ? ስሜቱን የሚቆጣጠር ,
~ ማነው ሀብታም ቢሉት . . . በቃኝን የሚያውቅ ,
~ ማነው የተከበረ ሰው . . . ሰውን የሚያከብር ,
~ ማነው ቶሎ ነገር የሚገባው ? ቢሉት . . . በትዕግስት ሰውን የሚያደምጥ ሰው ,,
ድንቅ ሊቅ ድንቅ እይታ❤️
ውብ ቀን❤️
✍ በዓሉ ግርማ ' ሀዲስ

ሰዓት እላፊ! (የቅዳሚት መዳረሻ!)
❤
".....እኔና አንቺ ተለያይተን እዚህና እዚያ ስንቆም ቃሎቻችን ወደ የት ይሄዳሉ? ያልኩሽ÷ ያልሺኝ÷ የተባባልናቸው ነገሮች መጨረሻቸው ምንድነው?
Does they even exist anymore?°°°°?
📝እሱባለው አበራ ንጉሤ

እምወድሽዋ!❤ቅዳሜዋ!❤ሸጋዬዋ!❤
የግጥም ጥግ (ርዕሱ አይደለም) ዛሬ ደርባባዋ ቅዳሚት ነች!❤ እና የዛሬ ቀናችንን ለቅዳሜ በሚመጥኑ በልኳ በወርዷ ልክክ ባሉ ግጥሞች ስንሞሽራት እንውላለን!!❤ የግጥም ጥግ አንድ...
ማነህ ላለኝ ....
በዘመን ላይ የበቀልኩ
የአንድ ሰሞን አበባ ነኝ ።
📝ቴዎድሮስ ካሳ
ኦ ፥ የሽቱዉ ቅመም
የሁሉ ቃና
እባክህ አትሂድ ፥ እባክህን .. ና !
ሁሌም ከጎኔ እንደክንፍ ኹነኝ
ከሚንበለበል ከኩራዝህ ፍም ፥ እንደ እሳትራት ለሞት አቅርበኝ ።
~
በልቤ ፍሰስ በልቤ ሙላ
ሌት ቀን ስባዝን የሚያጫዉተኝ ፥ ካንተ በስተቀር ምናለ ሌላ !!
የመናፈቅ ጥም ጉም ካለበሰዉ
ቀረበኝ ያልኩት እየነካካ ከሚያስለቅሰዉ
ከስጋየ ስር ፥ ከዚህ ቀርቀሃ
ከነፍሴ በታች ካለዉ በረኻ
ማነህ ተጫዋች ፥ ባለ ሙዚቃ
ይኸን ሙት በድን የምታስደንስ በጠፍ ጨረቃ
✍ቴዎድሮስ ካሳ
ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤