ስብዕናችን #Humanity
25.4K subscribers
1.66K photos
79 videos
23 files
54 links
🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot
Download Telegram
በዲግሪ የተመረቀ/ች
3 አመት የስራ ልምድ ያለው/ት
ብዛት 1
ላይሰንስ ያለው/ት

የስራ ቦታ እሪቼ ባቡር ፌርማታ መስከረም ማዞሪያ የድሮው መስከረም ሆቴል ፊት ለፊት

@Nagayta
ነገ ሸጋዋ ቅዳሚት ነች ዛሬ ዋዜማዋ ነው ለዋዜማዋ እንካቹ.......



የ ክ ራ ር ግርፋት እየሰማሁ የቃሎቻችንን ዋጋ እመዝናለሁ። እንደጉም እያየነው ስለተበተነው ትዝታችንም እተክዛለሁ። በእኛ መለያየት መውደቂያ ስለሚያጡ የቀትር ሕልሞቻችንም እጨነቃለሁ። በስስት የተሳሳምንባቸውንም ከንፈሮቻችንን በሚረሱ ሸክም ገላዎቻችን አፍራለሁ።

እ ን ደ ቃ ሎ ቻ ች ን ፥ እንደሕልሞቻችን ዘልዓለማዊነት ቢሆን ጀርባ ስንሰጣጥ ብቻ ሞተናል። ያ ፈጣሪ እንኳ በቃሉ ዓለምን የሠራ ከዘፍጥረት ቀድሞ ዋሾነታችንን አወቀብንና ቃሎቻችንን ኀይል ነሣ። ልንል በምንችለውና ልናደርግ በምንሻው መሀል ፈቃድን ሰጠን። ከእንግዲህ ወዲህ ያልነውን እስከምንሆን ብዙ ፈተና አለብን። ቃላችንና ግብራችን እስከሚገጥም ድረስ ፍጹም መጽደቅ የለም።

ለ ቃ ላ ች ን ስለማንሞት ውብ ሐረጋትን ብቻ የሚተፉ ሕያው መሣሪያዎች ሆነናል። እያንዳንዱ ሰው አዲስ ሰው ሲተዋወቅ በአንደበቱ ከዚህ በፊት ምንም ያለበት አይመስልም። እናም ዛሬም ፥ ነገም ፥ ከነገ ወዲያም እንግዳ ሰው እንቀርባለን። እናሞኛለን ፥ ፍቅርን ከመላመድ እናምታታለን ፥ እንተኛለን ፥ እንከዳለን ፥ ዘወር እንላለን። አዲስ እንለምዳለን። ሌላም ፥ ሌላም ፥ ሌላም።

“እ ን ዲ ህ ብለሺኝ እንዳልነበር
እንዲህ ብለኸኝ እንዳልነበር”

ስ ለ አ ለ ፈ ው ቃል ማን ይጠይቀናል? ቢጠይቀንስ የት ይደርሳል? በመጨረሻስ ሄዶ ሄዶ ምን ያመጣል? እያየን ፥ እየተመለከተን ያልነው ጠፍቶ የወለድነው ያድጋል። ልጃችንም ቢጤያችን ነውና ለቃሉ ሽረት ሞት አያውቅም። ማዕተብ አያሥረውም። ከተማውን ሸንጋይ ሞላው። በተራ ቃሎቻችን ምክንያት ቃላት በውስጣቸው የሚይዙት የትርጉም ልዕልና እየረከሰ ሄደ።

“እወድ ሻ/ሃ ለሁ (!)
አፈቅር ሻ/ሃ ለሁ (!)
እሞትልሻ/ሃ ለሁ (!)
ካን ተ/ቺ በቀር (!)
እስከ ዘልዓለም (!)”

ብ ን ል ም ቃሉ የትርጉም ጥልቀት የለውም። መዋደዳችን ፥ ፍቅራችን ሲፈተን — ዘልዓለማችንም አጭር ነው። አለማፈር ብቻ ሕይወታችንንና ኑሯችንን አራመደው።

እ ና ም ፍቅር ስለማናውቅ ቃሉ አፋችን ላይ አያምርብንም። ባይሆን ዝቅ ያለው ሙዚቃ ድምፁ ከፍ ቢል መልካም ነው።

“አ ራ ት መቶ ፍቅር ፥ ሦስት መቶ ትዝታ
የምችለው ስጠኝ ፥ አቤት የ'ኔ ጌታ”

እሱባለውአበራ ንጉሴ


@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ!ሸጋዬዋ


ፌቨን ትባላለች ፤ ፍቅረኛዋን ትወደዋለች ። ሁሌ በትንሹም በትልቁም ታነሳዋለች ፤ ከእለታት በአንዱ እለት ምኑን በደንብ ትወጂለታለሽ ???አልኳት

እ.............የምወድለት

ለኔ ያለውን ግዙፍ ፍቅር ፤ በየስፍራው በየጊዜው ይዳስሰኛል ። ሲፈልገኝ ፤ሲቀና፤ ሲጠረጥረኝ ፤ ለኔ ያለውን የፍቅር አሻራ በነካሁት እና ባየሁት ቁጥር እወድዋለሁ።

የለም

በደንብ የምወደው መልካምነቱን ነው ። በዙርያዎቹ ያሉቱን ሰዎች ፤ሲቆረቆርላቸው ፤ሲጠቅማቸው፤ሲሞገትላቸው ።ለተጠቃ ድምፅ ሲሆን እንድወደው አድርጎኛል ።

ኖ ......እሱም አይመስለኝም

ሲወስበኝ ያለውን ጀብደኝነቱ ነው የምወደው ። ወሲብ ላይ ያለው ወኔ ድፍረት እና ብልግናውን ነው የምወድለት ።

እሱም ብቻ አይደለም !?

ለአምላኩ ያለውን ታማኝነት፤ሃቀኝነቱን ለሚያምንበት ነገር የሚሄደውን ርቀት፤ ብቻውን የመቆም አቅሙን ፤ ሁሉም ታዝቦት ላገኘው ሰው ሁሉ ትክክል ነኝ እያለ ሙሾ አለማውረዱን ነው የምውድለት !!

ኖ ሳቁን ነው

ደመቅ ብሎ ለዛ ያለው ሳቁን ነው የምወድለት ። ያቺ ልቤን የምታርደው ሳቁን ነው የምወድለት ። ያቺ ከልቡ ሲስቀው ብቻ የሚስቃትን ሳቁን ነው የምወድለት ።

ኖ .....የለም

ሲያወራ የሚያወናጭፈው አለንጋ ጣቱ ናቸው የሚስቡኝ ። አወራሩ ጀንተል ብሎ በስሜት ቃል አጣጣሉ ነው የሚማርከኝ

እ..... ይሄ ን ብቻ ግን አይለም የምወድለት

ያለውን Commitment ። ከብዙ ሰው ጋር ሆ አለማለቱን ነው !! ከመዘባረቁ በፊት ስለሁኔታው ለመረዳት አጠያየቁን ፤ አነባበቡን ነው የምወድለት
.
.
ግን ምክንያቴ ነው ብዬ ከዘበዘብኩት በላይ አስሬ የማጣቅሰው ምክንያት ። የመንሰፍሰፌ ምንጭ ምክንያት አንድ ይመስለኛል .........የኔ ስለሆነ( ።)


የኔ ስለሆነ ነው የሚተችበትን ሳይቀር የማቆለባብሰው

ከካደኝ ፤ከተወኝ፤ ከጠላኝ፤ ሀይማኖተኝነቱን አክራሪ እለዋለው፤ ጠያቂነቱን መንቻካ እላለሁ፤ መልካምነቱን ብኩን ማለቴ አይቀርም ።

ማስታወሻ
ከውበት በላይ ፍቅር ያሱባል !!!


የተገማሸረ ደርባባ ቅዳሜ ይሁንላችሁ !

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
🔑Conditioned Mind

"It is not because things are difficult that we do not dare; it is because we do not dare that things are difficult." - Seneca
---
🔆በሕንድ መንደሮች ውስጥ ሲዘዋወር የቆየ አንድ እንግዳ ሰው ነዋሪዎቹ ዝሆኖቻቸውን የሚጠብቁበት መንገድ ግራ አጋብቶታል... እጅግ ግዙፍ የሚባሉ ዝሆኖች በቀላሉ ሊበጠሱ በሚችሉ ገመዶች ታስረው በጸጥታ የመቆማቸው ምስጢር እውነትም እንቆቅልሽ ነበር... 'እንዴት ሊሆን ይችላል?'...

⚜️ግራ መጋባቱ እየቀጠለ ሲሄድ ወደ አንድ የዝሆኖች አሰልጣኝ ዘንድ ቀርቦ 'ይህን እንዴት ማድረግ ቻላችሁ?... ዝሆኖች በምድር ላይ በጉልበታቸው ተስተካካይ የሌላቸው ፍጥረታት መሆናቸው ይታወቃል... በዚህ ሰላላ ገመድ ታስረው እንዲቆዩ ያደረጋቸው ምስጢር ምንድነው?...' ሲል ጠየቀ... 'ደህና...' አለ ዝሆኖችን የሚገራው ሰው... በእንግዳው ሰው ጥያቄ አንዳችም መገረም ሳያሳይ... 'በዚህ ገመድ መታሰር የሚጀምሩት ከደረጁ.. ጉልበት ካበጁ በኋላ አይደለም... ገና ግልገል ሳሉ ነው... በዚያ የማለዳ ዕድሜ አሁን የምታየው ገመድ እነርሱን አስሮ ለመቆየት በቂ ነበር... እየቆዩ ሲሄዱ ገመዱን የሚበጥስ አቅም ቢፈጥሩም በልጅነታቸው የታተመባቸው እምነት ግን ዛሬም ገመዱን መበጠስ እንደማይችሉ ይነግራቸዋል'...

🔆ሰውየው በጥበባቸው ተገረመ... ግዙፉን ዝሆን ለማሰር ግዙፍ ሰንሰለት አላስፈለጋቸውም... አስተሳሰባቸውን የሚያስር የማለዳ ልማድ በቂ ነበር... ነገሩ ሰንሰለት ካሰረው ልማድ ያሰረው ነው... 'ልማድ ከብረት ይጠነክራልና' ሼክስፒር እንዳለው...

🔆የኑረት ውበት በየደረሱበት መጠየቅ... የሰውነት ከፍታም በየመዳረሻው መርቀቅ ቢሆንም ከተነገረው ዘሎ 'ለምንና እንዴት' ለማይል አዕምሮ የነበረን ማስጠበቅ እንጂ 'አዲስ ነገር' ማፍለቅ አይሆንለትም... የኑረት ስኬትም ሆነ ውድቀት በእምነትህ ልክ ይገነባል... ቡድሃ "All that we are is the result of what we have thought. The mind is everything. What we think we become. " የሚለውን ቃል በትምህርቱ መጀመሪያ ላይ ያስቀመጠው ለዚሁ ነበር...

💫የምታምናቸውን ነገሮች ለምን እንዳመንካቸው ጠይቀህ ታውቃለህ?... የተቀበልካቸውን እሳቤዎች ልክነት በ'እንዴት' ዓይን መዝነህ ታውቃለህ?... የነገሩህን መጽሐፍትና ያስተማሩህን አንደበቶች መርምረህ ታውቃለህ?... እርግጠኛ ስለሆንክባቸው ጉዳዮች ቢያንስ ለራስህ በታማኝነት የምታቀርበው መልስ አለህ?... ወይስ እንደ ግዙፉ ዝሆን በሰላላ የአስተሳሰብ ወደሮ ታብተሃል?... መጠየቅስ አድክሞህ ይሆን?... Wynn Bullock የተባለ ሰው... "If you stop searching, you stop living, because then you're dwelling in the past. If you're not reaching forward to any growth or future, you might as well be dead." ብሎ ነበር... ሶቅራጥስ በበኩሉ "The unexamined life is not worth living" ብሏል...

ከማለዳ ውልደት እስከ ውድቅት ህልፈት የምትሳበው ኑረት ሁለንተናዋ በጠነከረ ልማድ የተቀየደ ነው... ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ የትወናዋን አካሄድ የሚወስንላት መራሔ ተውኔት ልማድ ወይም እምነት ይባላል... የምታምነውን ነው የምትሆነው... ግና.. የማለዳ እምነትህ ረፋድ ላይ... የረፋድ እሳቤህ ቀትር ላይ... የቀትር ግንዛቤህ በተሲዓት... የተሲዓት እውነትህ በምሽት ካልተመረመረ ከልማድ እስረኛነትህ ሳትፈታ ውድቅትህ ይመጣል... "The world is a prison and we are the prisoners.Dig a hole in the prison wall and let yourself out." ይልሃል ሩሚ...

🔑'ተለምዷል' የሚልህ ሰው ሲበዛ ጠርጥር... ቅኝት ነው... 'ምንም ማድረግ አይቻልም' ካለህ ተቃኝቷል በቃ... 'ያለ ነው'... 'ባሕል ነው'... 'አሰራር ነው'... 'እከሌ የሚባል ሰው ወይም መጽሐፍ ላይ ሰፍሯል'... ወዘተረፈዎች የቅኝት መገለጫዎች ናቸው... እዚህ መንደር ውስጥ 'ለምን' ባይ የተገኘለት የእብደት ታፔላ ይለጠፍለታል...

🔆ዕድሜ ልኩን ጥርሱን ሳያጸዳ የኖረ ሰው ለተወሰኑ ቀናት ብሩሽ ተጠቅሞ በመተዉ የአፉን ሽታ ቢያስተውል ሊል የሚችለው አንድ ነገር 'የጥርስ ሳሙና አፍ ያሸታል' ነው... ብሩሽ ከመጠቀሙ በፊት ሽታውን ተላምዶት ስለቆየ 'አፍህ ይሸታል' ቢሉት አይቀበልም ነበር... ብሩሹ ካለመደው ንጽህና በኋላ ግን የትኛውንም ሽታ መረዳት ይጀምራል... ተለማምዶ እስኪዘነጋው ድረስ... ጠረን እንድትለይ የሚረዱህን 'ብሩሾች' ስንቴ 'ያሸታሉ' ብለህ ጣልክ?... ስንቴስ ወደ ቀደመ ሽታህ ተመለስክ?...

ኒቼ በተወልን ድንቅ መስመር የማያልቀውን እንጨርስ... "If you have a 'why' to live by, you can live with any 'how'."

የ'ለምን' እና 'እንዴት' ድፍረት ይስጠን!!
ሰላም...❤️

ደምስ ሰይፉ
🔆🔑🔆🔑🔆🔑🔆🔑
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
ደስታችሁ በግልፅ የሚታይ ሀዘናችሁ ነው ። ሳቃችሁ የሚመነጭበት የዓይናችሁ ጉድጓድም አብዛኛውን ጊዜ በራሳችሁ እንባ የተሞላ ነው ። ከዚህስ ሌላ እንዴት ሊሆን ይችላልን? ....

💙 << ሀዘን የበለጠ ጠልቆ በውስጣችሁ በተቀረፀ ቁጥር የበለጠ ደስታ ማግኘት ትችላላችሁ . . .

💜<< ደስ ሲላችሁ ዘልቃችሁ ወደ ልባችሁ ውስጥ ተመልከቱ ። የዚያኔ ደስታን እየሰጣችሁ ያለው ያ ሀዘን ሰጥቷችሁ የነበረ ነገር ብቻ እንደነበር ትደርሱበታላችሁ . . .

<< ሀዘን ባጠላባችሁ ጊዜም እንደገና ወደ ልባችሁ ውስጥ ጠልቃችሁ ተመልከቱ ። አሁንም በእውነቱ የምታለቅሱት በዚያ ደስ ሲያሰኛችሁ በነበረው ነገር መሆኑን ትገነዘባላችሁ . . .

💙<<አንዳንዶቻችሁ <ሀዘን ከደስታ ያይላል> ትላላችሁ ። ሌሎቻችሁ ደግሞ <የለም የሚያይለው ደስታ ነው> ትላላችሁ ። እኔ ግን የማይነጣጠሉ መሆናቸውን እነግራችሁዋለሁ . . .

💜 የሚመጡትም አብረው ነው ። አንዱ ለብቻው ገበታችሁ ላይ ሲቀመጥ ፣ ሌላኛው በአልጋችሁ ላይ መተኛቱን አስታውሱ . . .

እውነት እውነት እላችዋለሁ ፣ ልክ እንደ ሚዛን በሀዘናችሁና በደስታችሁ መካከል ተንጠልጥላችሁዋል ። ሳታጋድሉ ሚዛናችሁን ጠብቃችሁ የምትቆዩት፣ባዶ በሆናችሁ ጊዜ ብቻነው ።
ካህሊል_ጅብራን

ውብ አሁን❤️
💜💙💙💙💙
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
1
ሰዓት እላፊ!
💚


"ሌሎችን በማፅናናት የተዋጣላቸው ሰዎች ራሳቸውን ማፅናናት ግን አይቻላቸውም"

ጊዜው 94 ዓመታትን ወደ ኃላ ይወስደናል... በወቅቱ አንድ ራሺያዊ ከያዘው ድብርት እና ጭንቀት እንዲገላግለው ምክር ፍለጋ ወደ ሳይካትሪስት ይሄዳል... ዶክተሩም አስፈላጊውን ምርመራ ካደረገ በኃላ እንዲ ሲል ምክርን ለታማሚው ይለግሳል...
"አሁን ካለህበት ለመውጣት አስጨናቂ እና አሳዛኝ ከሆኑ ነገሮች መራቅ ይኖርብሃል... ይህ በዕለት ተዕለት ህይወትህ እንደ ልማድ ካደረከው ንባብ ላይም ጭምር ይሁን... አስጨናቂ ፣ ዘግናኝ ፣ አስፈሪ እና አሳዛኝ ታሪክ ካላቸው ንባቦች መራቅ አለብህ... በምትኩም አስደሳች እና አዝናኝ (Comic Stories) ማንበብ አለብህ ለምሳሌም የሚካኤል ዙሽንኮ (Mikhail Zushenko) ፁሁፎችን አንብብ "
ይሄን ጊዜ ታማሚው ለዶክተሩ የሰጠው ምላሽ ዶክተሩን አስገረመው
"እኔኮ ሚካኤል ዙሽንኮ ነኝ"

ለፁሁፉ መጀመሪያ የተጠቀምኩት የ Albert Hubbard አባባል ይህን የ ሚካኤል ዙሽንኮን ታሪክ በትክክል ገላጭ ነው
Those who are good at comforting and comforting others often fail to console themselves...


➬ ሰላም እደሩ!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta
ተማሪ ነው ለሱፊው መምህሩ ጥያቄውን ያቀረበው ፡-
‹‹ለመሆኑ ሰው በአምላኩ የሚረካው መቼ ነው?›› የመምህሩ ምላሽ ታዲያ ድንቅ ነው!

💡‹‹በበረከቱ ግዜ የሚያገኘውን ደስታ በመከራው ጊዜ መግለጥ ከቻለ በርግጥም በአምላኩ ረክቷል ማለት ነው››፡፡

❤️በአሁና ደቂቃ ብቻ የተሰጠንን በረከት ብንቆጥር፤ ያለንን መልካም ነገር ብናስተውል ………..
ወደ መሬት ጎንበስ ብለን የምናመሰግንበት አንድ ሺ አንድ ምክንያቶች አሉን!! አንድ ሺ አንድ !!!!

መልካም ዛሬ!!!

💡💡💡💡💡💡💡💡💡
@EthioHumanity
@EthioHumanity
🌗"ትጋት የተስፋ ልጅ ናት።"

🌗 "ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው በሕይወቴ ውስጥ መልካም ነገሮች ወይም ስኬት ብዬ ከማስባቸው ውስጥ ማስተርስ ዲግሪዬ ወይም ዶክትሬት ዲግሪዬ አይደለም፡፡ ልጆቼ፡ ትዳሬ፡ ቤቴ ናቸው! በሕይወቴ ትልቁ ቁም ነገር ትልቁ ስኬት እነርሱ ናቸው! እናም አሁን ሳስበው የተጓዝኩበት የሕይወቴ አቅጣጫ ትክክል ነበር፡፡ አካሒዴም በእኔ ምኞት እና መምህሬ ባሰበልኝ ሳይሆን ፈጣሪ በመረጠልኝ ስለነበር በጎ መሆኑን የኋላ ኋላ ተገንዝቢያለው፡፡

🌙እናም በሰዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳን ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው፡፡ ሕይወት ጠመዝማዛም ብትሆን ውብና ተስፋን የተሞላች ናት! በዚህ ዓለም ሁሉም ነገር አበቃ አከተመ! ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል! የምናውቀውና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር ዙሪያችን! ጭው ያለ በርሃ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ ላይ እንዳለ ተምሪያለው፡፡

🌗ዕድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜም ቢሆን እንኳን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም፡፡ ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛ እና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና! "

🗞ከሰበዝ መጽሃፍ የተመዘዘ/ገጽ 97/

ጣፋጭ እንቅልፍ❤️❤️
🌗🌙🌗🌙🌗🌙🌗🌙🌗🌙🌗🌙
@EthioHumanity
@EthioHumanity
ለጁምኣችን!
💚

በመካ ከተማ አንድ ሰው ግራ ቀኙን እየቃኘ በመንገድ ሲያልፍ አንዲት አሮጊት እርጅና ባጎበጠው እድሜ ባሰለላቸው እጆቻቸው እየተንቀጠቀጠቀጡ ምግብ የሚያበስሉበትን እንጨት ተሸክመው ወደቤታቸው ሊሄድ ሲያጣጥሩ ይመለከታል። በአሮጊቷ ተግባር ልቡ የተነካው ይህ ሰውም በቀስታ ወደሴትየዋ ተጠግቶ « ቤትዎን ያሳዩኝ እኔ ተሸክሜ አደርስልዎታለሁ» አላቸው።
የሴትየዋ ቤት እጅግ እሩቅ ከመሆኑ ባሻገር ጸሀዩ ሲጠብሰው የዋለው አሸዋ ልክ በጋለ ፍም ላይ የመራመድ ያክል እግርን ክፉኛ ይለበልብ ነበር! ጸሀዩዋም መካ ብቻ ጓዟን ጠቅላ የሰፈረች ይመስል እንደእሳት ትፋጃለች። በነፋሱ እየተንሳፈፈ የሚመጣው የአሸዋ ብናኝም ፊትን በሀይል ይጋረፋል! እንግዲህ ይህን ፈተና ችሎ ነው ሰውየው የአሮጊቷን የደረቁ እንጨቶች ለመሸከም የወሰነው
በሰውዬው ድርጊት እየተገረሙና እየተደነቁ ቤታቸው የደረሱት ምስኪኗ አሮጊትም መልካሙን ሰውዬ ትኩር ብለው እየተመለከቱ እንዲህ አሉት ..
«ልጄ ሆይ እንዲያው ባሮጊት አንደበቴ እመርቅሀለሁ እንጂ ላደረግህልኝ ነገር መካሻ ይሆን ዘንድ የምሰጥህ አንዳች የሌለኝ ምስኪን ደሀ ነኝ ልጄ እባክህ ከሰማኸኝ አንድ ምክር ልለግስህ። ወደህዝቦችህ ወደመካ ስትመለስ እዚያ አንድ ነብይ ነኝ የሚል ሙሀመድ የሚሉት ደጋሚ ሰው አለ። በፍጹም እሱን እንዳትከተል እንዳታምነውም!» አሉት።
ሰውዬውም ረጋ ብሎ «ለምን?» ብሎ ጠየቀ!
አሮጊቷም «ልጄ እርሱ መጥፎ ስነምባር ነው ያለው ሲሉ ሰምቻለሁ» ብለው መለሱ።ሰውዬው በሴትየዋ ንግግር ተገርሞ «እኔስ ሙሀመድ ብሆን?» አላቸው። ሴትየዋም የሰሙት ነገር በጣም አስገርማቸው ለካስ ይህ ደግ ሰው ራሳቸው ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.አ.ወ) ነበሩ። አስተውሉ ... ነብዩ ለአሮጊቷ ቸርነትን ሲያደርጉ ሀይማኖታቸውን ፈፅሞ አልጠየቁም። ፍቅር የሀይማኖትን ድንበር፣ የዘርና የጎሳን አጥር እንደሚያልፍ ያውቁ ነበርና። ስብከት ያልሰበረውን ልብና ትምህርት ያላንበረከከውን ማንነት ፍቅር ብቻ ትህትናና በጎ ምግባር ብቻ ያንበረክከዋል!

ያማረ ጁምኣ!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta
ውበትን ማድነቅ

🔆አለምን የናቀ አንድ መነኩሴ ከሌሎች መነኩሴዎችጋር አብሮ በመንገድ ሲሄድ እጅግ አብዝታ የተዋበች ቆንጆ ሴት አይኑ ውስጥ ትገባለች፡፡ መነኩሴውም በሴቷ ውበት እጅጉን በጣም ከመደነቁ የተነሳ አይኑን ከሷ ላይ መንቀል ጭራሽ አቃተው፡፡ ይህን ድርጊቱን የተመለከቱ አብረውት የነበሩት ሌሎች መነኩሴዎች በድርጊቱ በአፍረት ተሞልተው ተጠጉትና፡-

‹‹ወንድማችን አንተ አለምን እንደኛ የናቅህ መነኩሴ ሆነህ ሳለ በሴት ልጅ ውበት እንዲህ ተደንቀህ ፈዘህ ስናስተውልህ አዝነናል፡፡ አለማዊ ድርጊት እየፈፀምህ መሆንህን አላስተዋልክምን?››በማለት ይጠይቁታል፡፡

🔆‹‹ወዳጆቼ በዚህች ቆንጆ ሴት ውበት ውስጥ እየተመለከትኩ የማደንቀው ውበትን እንዳሻው እየለዋወጠ በስራው የሚደሰተውን ፈጣሪዋን እንጂ እሷን አልነበረም፡፡ አይኖቼ የተዋበን ስጋ ሳይሆን የተዋበ ነገር የሚፈጥረውን ፈጣሪ ለማየት እንደተሰሩ አምናለሁ፡፡ በዚያም የተዋበን ነገር መፍጠር የሚችለውን የአምላክ ችሎታ ሥጋ ለብሶ አየዋለሁ መደነቄም በዚህ የተነሳ ነው፡፡››በማለት መለሰላቸው፡፡

በውበት ውስጥ የምናደንቀው የተፈጠረውን ነገር ብቻ ሳይሆን ከበስተጀርባው ሆኖ ያንን የተዋበ ነገርን የፈጠረውንም ማድነቅ ከቻልን በርግጥም ታላቅ ፀጋና ጥበብ ከኛ ጋር ነው፡፡

ውብ አሁን!!!❤️

ነፀብራቅ ብርሀኔ
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
@EthioHumanity
@EthioHumanity
#እምወድሽዋ!❤️ ቅዳሜዋ!❤️ሸጋዬ❤️


እንድርያስ ይባላል.... ከወንበሬ ፊት ለፊት ነው የሚቀመጠው ባልደረባዬ ነው ዝምተኛም ተግባቢም ነው....ያነባል ታሪክ ፣ፖለቲካ ፣ ኪነጥበብ ይተነትናል

...አብረን ነው የምንሰራው

ቃል ኪዳን ትባላለች ትህትናዋ ከፍርሃት ጋ የተዋሃደባት ልጅ ነች ፤ በምሰራበት ድርጅት በፅዳት ከተቀጠረች ቆየች.... ያልቆሸሸ ሁለት ልብስ ብቻ እንደምትለብስ አስተውያለሁ . .. .የገንዘብ ውስንነት እንዳለባት ታስታውቃለች

እንድርያስ ለቃልኪዳን ከኔ በተሻለ ያዝንላታል ለሷ እንደሱ ማዘን ስላልቻልኩ እራሴን እወቅሰዋለሁ .....እሱ ከኔ የተሻለ ነፍስ እንዳለው እረዳለሁ!!!

ከዕለታት በአንዱ ቀን የመቶ ብር ኖቶች ፀጉርሽን መሰርያ ብሎ ሲሸጉጥ በጨረፍታ አይቼው አውቃለሁ.... አንገቷን ስብር አድርጋ ተግደርድራ ተቀበለችው። አመሰገነችውም

በልቤ አንተ ከቅዱሳን መሃል ትገኛለህ አልኩት

ከእኔ በተሻለ ይቆረቆርላታል . እሷ ወንበሩን በመወልወል እንዳትደክም ሳትመጣ ሲወለውል አይቸው አውቃለሁ

መልካምነቱ ያደበዝዘኛል

ለእሷ ባለው ቦታ እኔ እራሴ እደስትበታለሁ። የፃዲቅ መልካምነት የሚጀምረው በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች ነው።

ከብዙ ጊዜ በኋላ በቀደም ቅዳሜ ደወለችልኝ እንደትንሽ ልጅ ፈራ ተባ እያለች በተሰበረ በለሆሳስ ድምፅ "ላናግርህ ፈልጌ ነበር አለችኝ" .....?መሳቀቋን ላለማድመቅ በቶሎ እሺ አልኳት....ተገናኘን

የለበሰችውን አመድማ ሹራብ እጅጌ ጎትታ ጣቶቿን አልብሳዋለች ። ማድያቷ እንዳ'ፍንጫዋ ከሩቁ መታየት ጀምሯል ። ፊቷ ክስም ፤ግርጥት ብሏል። ልቅም ያለች ወብ መሆኗ ይሄ ሁላ ጉስቁልና አላወደመውም

ይቅርታ በጣም "ከአንተ በላይ የሚቀርበው ሰው ስለማላውቅ ነው"

ዝም ብዬ ተመለከትኳት

* እንድርያስን እንድታናግርልኝ ነው "🙏 ስለምንጉዳይ ???..... አቀረቀረች .... በሆዴ የያዝኩት ልጅ የእሱ ነው አይንሽን ላፈር አለኝ ሳረግዝ ጠላኝ .....

ዞረብኝ ....

አፈጠጥኩኝ......

" አገባሻለሁ ተማሪ እያለ እየመከረ ፣እየወደደ፣ እየተንከባከበ፣ በፍቅር አክንፎ .....በፍቅር አባብሎ .....ስፀንስ ተፀየፈኝ: የደረጃ ልዩነታችን ተገለፀለት ማነሴ ኮሰኮሰው

የትም ስትንዘላዘይ ያመጣሽውን አለኝ😭

አቀርቅራለች

ፀጥታ ሰፈነ .....ቀና ስትል አይኗ በእንባ ተጨማልቋል

*ቢያንስ አባትነቱን ይመንልኝ እኔ ከሱ ውጪ ወንድ እንደማላቅ እሱ እራሱ ምስክር ነው ። ከፈለገ ልጁ የሱ መሆኑን ያስመርምር*
.
.
እንድርያስ እኔንም ነው የከዳኝ ሰውነቴ ውስጥ ድብርት ሲፈስብኝ እየታወቀኝ ነው
በአይኗ ውስጥ በደሏን አይቼ ሰለራሴ... ስለእህቴ .....ስለ ነገ ልጄ.. ስለ ጓደኛዬ .....ውሃ መሳይ ፊቴ ላይ ከአይኔ እየወጣ ሲረማመድ ተሰማኝ
.......

#ማሳሰብያ

የሰይጣን አምሳያ የሆነው ሰው መምጫ መንገዱ መቼ ይታወቃል ።ከሚታዩ መጥፎ ነገሮች መልካም የሚመስሉ
መጥፎ ነገሮች ያከስማሉ
....

ደርባባ ቅዳሚት ትሁንልን!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta
👍1
#ዛሬ ሽቅርቅሯ ቅዳሚት ነች.. አንድ የቻናላችን ቤተሰብ የሆነች እንዲህ አለችኝ.... በእርግጠኝነት እንደኔ ይሄ ነገር የሚሰማቸው ፣ ግራ የሚያጋባቸው ፣ የተጎዱበት ......ህመሜ ህመማቸው ይኖራሉ እና ይሄን እዚህ ቻናል ላይ ለጥፍልኝ አለችኝ.....#ከዚህ በታች ያለውን ስሜቷን ህመሟን ግራ መጋባቷን እንዲህ አስቀምጣዋለች......#ምናልባት ይሄን የምታነቡ ቤተሰቦች እናተም በዚህ ነገር ውስጥ ናቹ ወይንም አልፋችሁት ይሆናል........ተጋበዙልኝ🙏🙏

👇👇👇



በቃ አንዳንዶች አሉ
.
.
ፍላጎታቸው በትክክል ምን እንደሆነ የማይገቡህ::
የትውውቃችሁ መጀመሪያ አከባቢ ጥሩ ይሆኑልህና ከትንሽ ግዜ በኋላ
የሚቀየሩብህ::አንተን የፍቅር ስሜት ውስጥ ከከተቱህ በኋላ ከነሱ ተመሳሳይ ስሜት
ስትፈልግ የማይመልሱልህ::
.
.
...በቃ አንዳንዶች አሉ!
.
.
ካንተ ጋ መሆን እየፈለጉ ነገር ግን በህይወቴ ሌላ ሰው ቢመጣስ ብለው ወይም ደግሞ
ባለፈ የፍቅር ህይወታቸው ፍራቻ ፍቅርህን የማይቀበሉ::የማይሸሹህ!..የማይቀረቡ!..ሄዱ
ስትላቸው የሚመጡ!..መጡ ስትላቸው የሚሄዱ::
.
.
በቃ አንዳንዶች አሉ!
.
.
ሌላ ሰው እስከሚተዋወቁ አንተን እንደ ባጣ ቆየኝ የመጠቀሙ!
.
.
በቃ አንዳንዶች አሉ!
.
.
ሁሌ አንተ ቀድመህ መልዕክት እንድትልክላቸው ወይም ደግሞ እንድትደውልላቸው
የሚፈልጉ!አንተም አያስችልህም መልዕክት ትልካለህ!..ትደውላለህ!...እንደ ነገሩ
ያዋሩሀል!..ግን ደግሞ ብልጦች ናቸው!...ጨርሰህ እንድትለያቸው ስለማይፈልጉ ተስፋህን
ሙሉ ለሙሉ አይነጥቁህም!..ጭላንጭል ያስቀሩልሀል!..አንተም የቀረህን ጭላንጭል
ተስፋ ይዘህ አብረሀቸው መንገድ ትቀጥላለህ!
.
.
የሆነ ሰዓት ይሰለችሀል!ልትደውልላቸው ስልክህን ታነሳና መልሰህ
ታሰቀምጠዋህ!..ከራስህ ጋ ብዙ ትታገላለህ!..በመርሳትና በፍቅር ስሜት መሀል ሆነ
ለረጅም ግዜ ዝምምም ትላቸዋለህ::
.
.
የዚህን ግዜ የነሱ ተራ ይጀምራል!..እያንዳንዷ የተሰማህ ስሜት የሰማቸዋል!..እያንዳንዷ
ያመምህ ህመም ያማቸዋል!...ይቁነጠነጣሉ!..አስር ግዜ መልዕክት
ይልኩልሀል!...ይደውሉልሀል!...ቀን ሙሉ ያስቡሀል!
.
.
በቃ አንዳንዶች አሉ!...
.
.
ፍቅር ስትሰጣቸው ጀርባ ሰጥተውህ ስትርቃቸው የሚከተሉህ!
.
.
ስታዋራቸው ዝም ብለው ዝም ስትላቸው የሚያዋሩህ!.!
.
.
ግራ የተጋቡ!የተወሳሰቡ..በትክክል ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ የማትረዳቸው!....
.

ፀዲ

ሀሳብ ካላቹ ....ማካፋል ትችላላችሁ 🙏

ሽብርቅርቅ ያለች ቅዳሜ!

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta
<< የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር መውደድ የለበትም... >>

📖መነሻ ሃሳብ :- " ማታ ማታ - ገጽ 110

🔺" ማሰብ ተፈጥሮአዊ ባህሪህ ቢሆንም በማሰብ ላይ ያለህ ብስለት ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ ካንተ የተለየ ሀሳብ ሲያጋጥምህ ለሃሳቡ በምትሰጠው ምላሽ(ግብራዊ) ነው ። እምትወደው ሰው የግድ ባንተ ሃሳብ የሚስማማ ወይም አንተ የምትወደውን ብቻ የሚወድ መሆን የለበትም ። እንደዛ አይነት ሰው ከፈለግክ ያንተን ሁሉ አሜን ብሎ የሚቀበል የሀሳብና የፍላጎት_ወዛደር እንጂ አሳቢን አታገኝም ።

❤️የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር በመውደድ አይደለም መዋደዱ የሚገለጸው ። ካንተ ለተለየ ነገር ሁሉ ጥላቻ ከሆነ ምላሽህ በትክክል ማሰብ መቻልህ ጥያቄ ውስጥ ይገባል ። በሃሳብ መፋለስ የልዩነት እንጂ የጥላቻም ሆነ ያለመዋደድ መንስኤም ሆነ ምልክት አይደለም ። አንተ ራስህ በየቀንና በየሰአቱ የምታስባቸው ሃሳቦች ልዩነት ሊኖራቸው ይችላል ግን አቻችለሀቸው እየኖርህ ነው ። ታድያ የሰውን ልዩነት ማቻቻልስ እንዴት ያቅትሀል...…?

ለራሳችን ጥያቄ ሰተነው እንደምድም::

የሀሳብ ልዩነቶችን ለምን በስድብ እናጣጣቸዋለን?…………

ሰዎች እኛ ያልደገፍነውን ስለደገፉ ለምን እንዲያፍሩ እናደርጋቸዋለን?...……"

ፍቅር አሁን !
@keney_serezoch
@EthioHumanity