ስብዕናችን #Humanity
25K subscribers
1.66K photos
79 videos
23 files
54 links
🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot
Download Telegram
ለጁምኣችን!
💚

ዓለም ሁለት ዓይነት ሌቦችን በውስጧ ይዛለች - ተራ ሌባ እና ሌባ ፖለቲከኛ።
.
.
.

👉 ተራ ሌባ

ገንዘብህን፣ ቦርሳህን፣ ስልክህን፣ ሰዓትህን በአጠቃላይ ንብረትህን ሰርቆ ክው ያደርግሃል።
.
.
.

👉 ሌባ ፖለቲከኛ በበኩሉ
ነገህን፣ ህልምህን፣ ስራህን፣ ደመዎዝህን፣ ትምህርትህን፣ ጤናህን፣ አቅምህን ፣ ጉልበትህን፣ ፈገግታህን ጠቅልሎ ይሰርቅሃል።
.
.
.

በሁለቱም ሌቦች መካከል ያለው አስደናቂ ልዩነት ተራ የሆነው ሌባ ስርቆት ለማከናወን አንተን ለይቶ ሲመርጥ ሌባ ፖለቲከኛውን ግን እንዲሰርቅህ የምትመርጠው አንተ መሆንህ ነው።
.
.
.

እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ ተራ የሆነውን ሌባ ለመያዝ ፖሊስ በባትሪ እያደነ ሲከታተለው ሌባ ፖለተኪኛው ግን በፖሊስ አጀብ በክብር መከበቡ ነው።
.
.
ሸጋ ጁምኣ!💚

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
#እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!


'ከሴተኛ አዳሪዋ ባሻገር'


ሴተኛ አዳሪ ነች። ለብዙ ሰው የሽፍደት ማስታገሻ ናት። እሷን ከወሲብ ጋር ብቻ አጋምደው
ነው የሚያስቧት ፤ የሚያዋሯት ፣ የሚደውሉላት የሚያገኟት።


በየቀደዳዎች ሽፍደት ፤አንሶላ ፤ቂጥ ፤ዳሌ ፤ስካር ዳንስ ዋነኛው አጀንዳቸው ያደርጉታል።


እኔ ራሴ


ውበቷ ፤ቂጧ ፤ዳሌዋ፤ ቅላቷ፤ ነፃነቷ ማርኮኝ ነበር የተዋወኳት ፤ለወሲብ ነበር የቀረብኳት


እንዳገኘኋት ነበር ማንነቷ የጣፈጠኝ ፤ብዙ ሰው ጋር ያለየሁት ወፍራም መውደድ
፤አዛኝነት፤ሃቀኝነት ያየሁባት


እሷ ራሷ
አንዲት ጠዋት ቅዳሜ እለት እንዲ አለቺኝ


ለምን ሴተኛ አዳሪነቴን ታስረሳኛለህ ፤ ለምን ካንተ ጋር ስገናኝ ሸርሙጣነቴን ታፈዘዋለህ ፤
ለምን ታገዝፈኛለህ አለቺኝ


ምን ላድርግ ብለሽ ነው


ተቃጥረን ስትመጪ የሚታየኝ ጨዋታሽ ፤ፍቅርሽ ፤የስብዕናሽ መዓዛ ነው ። እንደደረሽ
ደስስስ ይለኛል ያሻኝን ካለ ካልኩሌሽን እዘብካለሁ፤ እቀደዳለሁ። በቀደዳዬ ስትስቂልኝ ደስ
ይለኛል ፤ በቀልዴ የመጬ እከየፍ እና ከልቤ እፈግጋለሁ ።


ከዚ ደማቅ ሰው ወዳድነትሽ አልፌ

ከዚ ጣፋጭ የወዳጅነትሽ ሳቅ ነጥቤ

ከዚ ወዳጅነት ላይ የከተመች ልጅ ተሻግሬ

ከዚ የናፍቆት መጠማጠም ተሸጋግሬ

በክፉ ገጠመኝ ተጠላልፈሽ ፤በክፉ ሰዎች ተጎትጎተሽ የወደቅሽበት ግዚያዊ አንቺነትሽ
እንዴት ይታየኝ አልኳት


ቃል ሳትናገር


አቅፋኝ አንገት ውስጥ ተሸጉጣ አለቀሰች ። ሳግ ብቻ ነው የተሰማኝ


የሳጓ ትርጉም ነጋሪ ቢኖር እንዲህ የሚል ይመስለኛል
ወለድከኝ ፤ቆንጆ ሴት፤የተከበረች ፤ ለፍቅር እንደምመጥን አስዳሰስከኝ ከሚል አይዘልም


አንገቴን የሚያርሰው እምባ ውስጥ ህይወት ፍቅር ተስፋ ሲረማመድ ይሰማኛል።


ወድጃታለሁ ሴተኛ አዳሪነቷ ለኔ አይሰማኝም


ታከብረኛለች፤ሰው ትወዳለች፤ ጨዋታዬ ስጋቴ ህመሜ ሳቄ ይሰማታል። እኔ ስቀጥራት
ከፕሮፌሰሩ ፣ ከባላሃብቱ ፤ ከባለስልጣኑ በላይ ሰፍፍፍ ትልልኛለች ፤ የምላትን ትሰማኛለች
ከማንም ጋር ስሆን ከሚሰማኝ ደስታ በላይ ከእሷ ጋር ስሆን እደሰታለሁ ። እማወራው
አያልቅብኝም እ ....እ.... እ... እወዳታለሁ እንደወደድኳት ፤ ብዙ ወር መጥቶ ሄደ ፤ ፍቅራችን፣ አንዳችን ላንዳችን ያለን ነገር አልቀነሰም። የምግብ ዝግጅት ተምራ ጨረሰች ።ዘርፍ ቀየረች ።


እቺን የመሰለች ልጅ እንዴት ብዬ በትላንቷ ምክንያት ልተዋት? እንዴትም !


#ማስታወሻ
ሁሉም ግርር ብሎ ከሚያየው የሚታይ ነገር ጀርባ ብዙ ያልተስተዋለ ያፈጠጠ እውነት አለ !!


* ሸጋ ቅዳሚት!*

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
👍2
መጨነቅና መጨናነቅ ማንንም ሰው ከችግሩ ሲያድነው ታይቶና ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ በመጨነቅና በመጨናነቅ ምክንያት ግን ሰዎች ቀስ በቀስ ወደሞት ሊያዘግሙ እንደሚችሉ መረጃዎችና ማስረጃዎች ሞልተዋል፡፡

🌤እናንተ ማድረግ የምትችሉትን አድርጉ፡፡ እናንተ ማድረግ የማትችሉትን ደግሞ ሊያደርግላችሁ የሚችል ሰው ካለ አስደርጉ፡፡ ማንም ሊያደርግ የማይችለው ሁኔታ ውስጥ ካላችሁ ግን ጉዳዩን ለፈጣሪ አሳልፋችሁ ስጡና ኑሯችሁ ላይ አተኩሩ፡፡

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!❤️

ዶ/ር እዮብ ማሞ
🌤🌤🌤🌤🌤🌤
@EthioHumanity
@EthioHumanity
. . .በዚህ ዓለም ላይ ሁሉን ነገር ለማወቅ፣ሁሉን ነገር ለማግኘት፣ሁኔታዎች በፍፁም አይፈቅዱም አንዱን የጨበጠ ሌላውን ያጣል፣ወደ አንድ ነገር የቀረበ ከሌላው ይርቃል፣ አንዱን ያወቀ ሌላውን አያውቅም ።ዝርዝሩ ብዙ ነው። ይህ ህግ በሁሉም ሰው፣በሁሉም ቦታ፣ በሁሉም ዘመን ላይ ተፈፃሚ ነው። ልዩነቱ የዓይነትና የመጠን ብቻ ነው።
. . . . እና እላችዋለው ያላቹ ላይ አተኩሩ/እናተኩር

💜. . . ሕይወት ትላንት ወይም ነገ አይደለችም።ሕይወት አሁን ናት። አሁንነት ሲያልፍ ትላንት ይሆናል የወደፊት አሁንነት ደግሞ ነገ ይሆናል። ሕይወት ተኖረ የሚባለው በአሁንነት ውስጥ ጤናማ በሆነ መልኩ ስንኖርበት ብቻ ነው። በአሁንነት ውስጥ ያልተኖረ ሕይወት የመከነ ሕይወት ነው።ዳሩ ግን ብዙዎቻችን በአሁንነት ውስጥ እየኖርን አለመሆኑ ነው። አእምሯችን በባለፈውና በወደፊቱ ጊዜ የተሞላ ነው። ከዚህም የተነሳ አዘውትሮ ያስባል ይጨነቃል።

እኔ ግን እደኔ ስላቹ. . በትላንትናና በነገው አፍራሽ ስሜቶች ከመሞላትና ከመረበሽ በዛሬው ማንነት ውስጥ በትክክል መኖር ምርጫቹ አድርጉ/እናድርግ።. . . !!!!!!

ውብ ምሽት
💜💜💜💜💜
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
❤️ፍቅር የልጅነት ስሜት ነው ።" ልጅነት እውነት ነው። ስሜት ደግሞ የማይዙትና የማይቆጣጠሩት። ፍቅር የማይዙትና የማይቆጣጠሩት እውነት ነው። ከተሰማ ሊክዱት የማይችል ፤ ከሌለም የማይፈጥሩትና ሊያስመስሉት የማይችል እውነት።

💙ፍቅር ዓመፀኛም ነው በምክንያት የማይገዛ ፤ ለዉይይት የማይመች ፤ የማያሰሩት፤ የማይጋልቡት ልጓም የሌለው ፈረሰ። ከፍት ቀዳሚ ፤ ጋላቢ ወሳጅ ፤ እምቢ ባይ ፤ ይቅርብህ አይሆንም የማያውቅ ፤ የፈለገውን እስኪያገኝ የማይተኛ ፤ የልቡ ሳይደረስ የማያርፍ።

💛ካፈቀረክ ፍቅር ምላሽ አይፈልግም ፤ የግድ መፈቀርን አይሻም ። ማፍቀር በራሱ ደሰ ይላል ፤ ቀኑን በመልካም ስሜት ሸፍኖ፤ ሌቱን በመልካም ህልም ያሳርፋል።

📖አለመኖር ከገጽ -239 የተወሰደ
❤️💙💛❤️💙💛❤️💙💛❤️💙
@EthioHumanity
@EthioHumanity
👍1
ለምሽታችን!
❤️💪✌️


ሰብዓዊነት የገዘፈበት የፍትህ ኮከብ!


ምነም እንኳን የአርጀንቲናዊ ተወላጅ ቢሆንም እሱ ለኔ አገር አልባ የዓለም ነው። እሱ ብዙ ነው ፊዚስት፣ፀሀፊ፣አስተማሪ፣ዲፕሎማት፣
የጦርሀይል አዛዥ እና የመብት ተሟጋች ነው ። ይህ ሰው ማነው
ስመ ገናናው ዓለማቀፋዊው የነጻነት ፋኖ ተዋጊ .....ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ
ያላደለው በቀበሌ ፤ በወረዳ ፤በብሄር ፤በሃይማኖት ተሰባጣጥሮ በጎጥ ተተብትቦ
ይጣመዳል ይቧቀሳል የኔ ጀግና ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ ለዘመዶቹ ለሰው ልጆች ዘብ ይቆማል
ይህ ሰው ቅዱስ ነው።ቅድስና ማለት ህይወትቱን ሙሉ ለሰው ልጆች ነፃነት መታገል
ብሎም አንድያ ነፍሱን መገበር አይደለምን ?ካለምንም ስስት ማንነትን ዘርን ሳይቆጥር ሰው
መሆን ክብር ነው ብሎ ለሰው ልጆች ነፃነትን ሊለግስ አቅም አልባዎችን አለሁላቹ እሚል
ለኔ ይህ አለማቀፍ የነፃነት አርበኛ ቅዱሴ ነው።


አለም ህዝቦቿ ሁሉም ሰዎች በእኩልነት እና በሰላም ይኖሩ ዘንድ ለማየት ተመኘ
ህልሙንም እውን ለማድረግ ጣረ ይህ ክንፍ አልባ በምድር የተመላለሰ መልአክ ነው።
እውነተኛ ኮሚኒስት ነው ኮሚንዝም የአለም ማህበረሰብን ወደፊት እሚያስጉዝ እና አዲስ
ማህበረሰብን ለመፍጠር ያስችላል ብሎ ለሰው ልጆች እኩልነት ለማምጣት ከጨቋኞች ጋ ታገለ ማን ?....ዶክተር ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ የአለም ሰዎች በሰላም የመኖር እና ያለመኖር እጣ ፈንታ በልእለ ሃያል አገሮች መውደቅ ፍትሃዊነት የገደለው ነው ያለው ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ ወደ ሰሜን አፍሪካ አቀና በአልጄርያ
እርእሰ ከተማ በአልጀርስ ንግግር አደረገ ቋንቋው ሁሉ ጭቆና ፤ ግፍ ፤በደል ይቁም ነው ።


ይህ ፍትሀዊ የፍትህ ተወርዋሪ ኮኮብ
በምድር እነሆ ላይፈዝ በሰው ልቦች ደሞቆ እና ህያው ሆኖ አልፏል።
# ስለአለማቀfዊነት ! ስለ ሰውነት ጥግ ሳስብ አእምሮዬን ላይ ድቅን የሚልበኝ አንድ ሰው
ነው. ....Che Guevara
ገፁ ሰውነትን የሚያገዝፍልኝ አርማ ነው!!! አለማቀፋዊነት ዜማ የሚያቀነቅን ሰንደቄ
አድራጓቱ ከመረዳት አቅም በላይ ጥልቅ የሰውነት ትርጉምን ተሸክሞል።
ህልመኛም ጭምር ነው 1956 ስምንት ሆነው ከሜክሲኮ ተነስተው የገዜው አንባገነኑን
የባቲስታ መንግሥት ለመገልበጥ ወደ ኩባ አቀኑ ለስምንት
በኩባ ጫካዎችም የጉሬላ ውጊያ ጀመሩ
አምባገነኑ የባቲስታ መንግሥት የመጣል ትግሉም ቼ ወሳኝ ሚና ተጫውቶ በድል
ተጠናቀቀ። ይህ ጀግናዬ ማለም ብቻ ሳይሆን መተግበርም ይችልበታል።
በተተኪው የካስትሮ አስተዳደርም የካስትሮ ቀኝ እጅ ሆኖ እስከ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርነት ድረስ ላልወለደው የኩባ ህዝብ አገለገለ።ምከንያት እሱ ዘመዶቹ የሰው ልጆች ናቸውና ።
ቼኮ ከጨቋኝ ሃያላን ጋ ሲታገል ከተጨቆኝ ጋ ሲያብር ኖሯል የእውነት!!እንደምን ሰው
ከተሸናፊ ጋር በፍቅር ይወድቃል ??
ቼ!! መለክያው እኩልነት ነበር ተጨቆኝና ጨቆኝ የሌለበት ምድር ለመፍጠር ።
ዛሬ የERNESTO CHE GUEVERA መፅሀፍ ባአሜሪካ ሳይቀር በአለም መፅሀፍት ቤቶች
ይገኛል የቼ ምስል ያረፈበት ሰአቶችን ቲሸርቶች በሺዎች ይቸበቸባሉ የላቲን አሜሪካ ተማሪዎች ጠዋት ጠዋት እነደ ብሄራዊ መዝሙር ቼ እንወድሀለን ቼ አንተን እንወርስሀለን
እያሉ ያዜማሉ።


ቼ የፍትህ ተወርዋሪ ኮኮብ ነው !!❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@balmbaras
💙በዚህ አለም ከላይ ስንደርስ ታች የነበርንበት ከንቱ ይሆናል፣ የጨበጥነውን እንረግጣለን፣ ክብር የሰጠነውን እናዋርዳለን፣ <ከዚህ በላይ የለም> ያልነውን ተራ ነገር እናደርገዋለን፤ አለሙ እንደዚሁ ነው። ንፋስ እንደመከተል ነው፣ የሚያረካ የሚያስደስት ምንም ነገር የለም።"

❤️ "ጊዜ ሲረዝም እድሜ ሲያልቅ ደሞ ሞት ነው። ሞት መራራ ከሆነ ምነው የጊዜ መባከን ቢያንስ ህመም አይሆንብንም? ሰው ቀጥሮህ ሲቀር ከእድሜህ እየቀነሰብህ ነው። የሆነ ሰው ያለ አግባብ የወሰደብህን ገንዘብ አንድ ቀን ሊመልስልህ ይችላል፤ የወሰደብህን ጊዜ ግን መቼም አይመልስልህም። አንድ ሊቅ እንዳለው ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታህ ጊዜ ነው። እንዴት? የሰጠኸው ጊዜ ከእድሜህ ላይ የቀነስከው ነውና!"

💙 "...መጥፎ ሰው ጥሩ ባለሙያ ሊሆን አይችልም፤ መጥፎ ባለሙያም መልካም ሰው ሊሆን አይችልም። የተዋጣላችሁ ለሀገር ለወገን መከታ የምትባሉ ምሁር ባለሙያ የምትሆኑት የተስተካከለ ስብዕና ሲኖራችሁ ነው።

❤️ቅንነትን፣ደግነትን፣አዛኝነትን፣ታታሪነትን ለመማር ዝግጁነትንና ፈጣሪን መፍራትን ገንዘብ አድርጉ። በጋራ መስራት እንጂ በጋራ ማሰብ አይቻልም። ብቻችሁን ሁናችሁ አስቡ ስራ ላይ ግን ተባበሩ!"

በፍቅር እደሩ❤️
❤️💙❤️💙❤️💙❤️💙❤️💙
@EthioHumanity
@Ethiohumanity
ለጁምኣችን
💚

የሀይማኖት መብት ሳይከበርላቸው በሀገራቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታዩ የሀይማኖት፣የኢኮኖሚ እና የመሳሰሉት ጥያቄ እያለባቸው....ስለ ሀገራቸው ክብር የንጉሱን ጥሪ ተከትለው ለዘመቱት የሙስሊም ገበሬዎችና የጦር አበጋዞች እንዲሁም ለሁሉም የአድዋ ዘማቾች ክብር ለነሱ!

ክርስትያኑ ንጉሥ ነገሥት በማርያም እየማለ ተከተሉኝ ያለውን አዋጅ እና የዘመቻ ጥሪ ተቀብሎ የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበው ለእናት ሀገሩ እና ለራሱ ክብር ሲል የተዋደቀው ይህ ሙስሊም የእግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር የሀገራችንን ዳይቨርስቲ ደመቅ አድርጎ ከሚያሳዩ ምንጊዜም ከማይረሱ ሁነቶች ውስጥ የሚመደብ እና ክብር የሚገባው ነው።

#ሙስሊሞቹ የጦር አበጋዞች እና ዓድዋ

በተለያዩ ጠሀፊወች በተደጋጋሚ እንዳስተዋልነው በታላቁ የአድዋ ጦርነት ለድሉ ከፍተኛውን ድርሻ ያበረከተው በራስ ሚካኤል ዓሊ ሥር የዘመተው የፈረሰኛ ጦር ነበር፤ በሌላ ግንባር ሲዋጉ የተማረኩት የጠላት ወታደሮች ሳይቀር የሚወረወረውን የፈረሰኛው ጦር ሚና እጅጉን የላቀ መሆኑን ሳይዘነጉ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ይህ ጦር በዓድዋ ጦርነት ወቅት ከንጉሠ ነገሥቱ ምኒልክ በእስከ ቀኝ በኩል ተሰልፎ የጠላትን ጦር እንዳልነበር ያደረገ እና ውሽመጣቸውን የቆረጠ ነበር። በጦርነትም ጄነራል አልበርቶኒን ሊረዳ የመጣውን በጄነራል ዳቦርሜዳ የሚመራውን ሙሉ ብርጌድ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር የደመሰሰው ይኼ ፈረሰኛ ሰራዊት ነው። የጄነራል ዳቦርሜዳ ሬሳ እንኴን አልተገኘም፤ ምንም ምርኮኛም አልነበረም። እንደሚታውቀው ይኼ ጦር Proper Wollo ከሚባለው የዛሬው ደቡብ ወሎ ክፍል የተውጣጣ በአብዛኛው የእስልምና ተከታይ የነበረ የገበሬ ወታደር ሲሆን በሙስሊም የጦር አበጋዞችም ይመራ ነበር።
.
ከታዋቂወቹ ከእነዚህ ሙስሊም ጦር አበጋዞች ዋናዋናወቹ የእርቄው ገዢ የሞሀመድ ቃንቄ ልጅ ደጅ አዝማች ይመር ሞሀመድ፣ የዓሊ ቤት ገዥ ራስ በሽር፣ የኮሬብ ገዥ ደጅ አዝማች ሊበን በሽር በጉልህ ስማቸው የሚነሳ ነው። አንዳንድ የውጭ ሀገር የታሪክ ጠሀፊወች ሀገራችንን ከውጭ ሆነው ክርስትያን ነገሥታቱን ብቻ በማየት በርካታ ሙስሊም ማህበረሰብ መኖሩን በመዘንጋት በጣፏቸው ማስታወሻወች ይኼን የእስልምና ተከታይ የዓድዋ ዘመቻ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር በዓድዋ ላይ ያደረገውን ተጋድሎ ለክርስትያን አገር የተከፈለ መስዋትነት በማለት ድሉን ለማጥበብ ይሞክራሉ። ክርስትያኑ ንጉሥ ነገሥት በማርያም እየማለ ተከተሉኝ ያለውን አዋጅ እና የዘመቻ ጥሪ ተቀብሎ የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበው ለእናት ሀገሩ እና ለራሱ ክብር ሲል የተዋደቀው ይህ ሙስሊም የእግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር የአገራችንን ዳይቨርስቲ ደመቅ አድርጎ ከሚያሳዩ ምንጊዜም ከማይረሱ ሁነቶች ውስጥ የሚመደብ እና ክብር የሚገባው ነው። ዓድዋ ከተካሄደ ከሁለት ዓመት በኋላ የትግራዩ ራስ መንገሻ ሲያምጥ ከራስ መኮነን ጦር ጋር ተቀናጅቶ በቀላሉ ራስ መንገሻን በቁጥጥር ሥር ያዋለው በእነ ራስ በሽር እና ፊታውራሪ ሥራህ ብዙ የሚመራው ይኼው ጦር ነበር።
.

ሸጋ ጁምኣ!💚

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@balmbaras
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልብህ ያሰበውን ጥሩ ነገር ከመፈጸም አትቦዝን። ሃሳቡ በውስጥህ አርጅቶ እስኪሞት አትጠብቅ። ሰዎች ምን ይሉኝ ብለህ አትፍራ። ሰዎች ብትሠራም ባትሠራም የሆነ ነገር ማለታቸው አይቀርም። ብቻ መጠንቀቅ ያለብህ አንድ ነገር አለ። ያም ነገር ድርጊትህ በጎ መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ ላይ ነው። ድርጊትህ ጥሩ መሆኑን ካመንክበት ለመተግበር ተጣጣር።

🔱 ድርጊትህ ሙሉ በሙሉ ባይሳካ እንኳ በመሞከርህ ብቻ የህሊና እረፍት ታገኛለህ። በተከታታይ ከሠራህ ደግሞ እየሠራህ ማሻሻልህ አይቀርም።

🔆ጥሩ ነገር ለማድረግ ምቹ ጊዜ አትጠብቅ። ምቹው ጊዜ ሃሳቡ ወደ ጭንቅላትህ የመጣበት ጊዜ ነው።

🔱መማር ባለብህ ጊዜ ተማር፣ መሥራት ባለብህ ጊዜ ሥራ፣ መዝፈን ባለብህ ጊዜ ዝፈን፣ መዘመር ባለብህ ጊዜ ዘምር፣ መጻፍ ባለብህ ጊዜ ጻፍ፣ ማረፍ ባለብህ ጊዜ እረፍ።
Toughe G kebede

ውብ አሁን❤️
🔆🔆🔆🔆🔆🔆
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
#እምወድሽዋ!ቅዳሜዋ! ሸጋዬ


፩ .
ሰዓዲ ይቀጥላሉ

"ከፀደይ ደመና አንዲት የዝናብ ጠብታ ወደ ምድር ወደቀች - ሰፊውን ባህር ስታይ በሀፍረት አቀረቀረች :: እንዲህም አለች :- " ባህሩ ሁሉ በሞላበት ፤ እኔ የት ነኝ ?በእርግጥም በህለውና የለሁም ልበል እንጂ ! "

በሀዘን ስታንጎራጉር በነበረበት ወቅት ነው አንድ የባህር ኦይስተር [Oyster] ወደ ሆዱ ውጦ ያስቀራት ፤ እጣ ክፍሏም ከትንሽ የዝናብ ጠብታ ወደ ክቡር ታላቅ የከበረ - ማዕድን ወደ ዕንቁነተ ቀየራት :: "

"ይሄው ነው" ይላሉ :- "አየህ ትሁት ነበረች ፥ ተከበረች ፤ ያለ መኖርን በር አንኳኳች ፥ ራሷን አሳነሰች ህልው የክቡራን ፅዋ - ተርታ ተቸራት :: "

፪.
አሁንም ሰዓዲ ይቀጥላሉ
ቀዘል አርሰላን ብርቱ የቤተ-መንግስት አጥር ነበረው - ቁመቱ ከ አልወንድ ተራራ የሚስተካከል [alofty mountain situated in Hamden , north-west of Isfahan] :: ከግንብ አጥሩ ውስጥ እንደ ሙሽራ ፀጉር በአፀደ - ፅጌያቱ ውስጥ እየተጠማዘዙ የሚዘልቁ ጎዳናውች ሞልተውታል ፤ በውስጧ ያሉ ኖሪዎቿ ሁሉ ያላንዳች ስጋት የተጠበቁ ነበሩ ::

ቀዘል በአንድ እለት - አንድ ጠቢብ መንገደኛ ያገኝና ይጠይቀዋል - ባንዳች የኩራት መንፈስ

" ከዚህ በፊት ይህን የመሰለ ብርቱ ግርማም የግንብ አጥር በተጏዝክበት ሁሉ አይተህ ታውቅ ይሆን ?"

" በእርግጥ ግሩም ነው !" ብሎ መለሰና :- " ነገር ግን አንዳች ብርታት እንደ ጎደለው አስባለሁ ፤ ካንተ በፊት የነብረው ንጉስ እጅ ላይ እንደ ነበር ሳስታውስ ፣ አሁንም ካንት በኇላ በሚነግሰው እጅ ላይ መውደቁን ሳስብ፣ ከዛም ደግሞ የነገሰው ንጉስ ከተስፋህ አፀድ ውስጥ ያሻውን ፍሬ ሲቢላ ይታየኝና - እውንትም አንዳች ጉልበት ፥ የሚመክትበት የተነሳው ነው እላለሁ :: "

In the estimation of the wise , the world is a false gem that passes each moment from one hand to another .

፫ .
አንድዎን የወሎ ሼኽ አንድ ያዲስ አበባ ሰው ሊኻድማቸው ወስዳቸው አሉ :: አሉ ነው መቼስ

ሁሉ ሁሉ ቀረበ ፣ ተበላም ተጠጣም :: ዱዓ ተያዘ ::

"ሼኾቹ እንግዲህ ያማረ ሀብት ፣ ያማረ መሬት ፣ ያማረ ቦታ ነው 'ምሻ በሉ ዱዓ ያርጉልኝ " አለ ከፊት ሆኖ እያያቸው

"እንግዲህ " አሉ :- " እንግዲህ አላህ ታንዱ ወስዶ ቲያበቃ ላንዱ ነው 'ሚሰጥና .. " እንዳሉ ሳያስጨርሳቸው

" ኧረ እነ ሸኽ እኔ የራሴን ነው 'ምፈልገው "

ቆጣ ብለው መለሱ :-

" ኧረግ ታያ ላንተ ተብሎ አዲስ መሬት አይዘረጋ !"

ምንጭ -Sa'adi collected works (Delphi classics)

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@balmbaras
❤️በሰላም ቤትህ ገብተህና ተኝነተህ በነጋታው ጠዋት በሰላም መነሳትህን በፍጹም አትልመደው (Never take it for granted)፤ ይህንን እድል ያላገኙ ብዙ ሰዎች አሉና!

🌗ይህንን ከፈጣሪ ብቻ ልታገኝ የምትችለውን የየቀን ተአምር እንዳልረሳኸው ለራስህ ለማስታወስ ከፈለክ ነገ ጠዋት በጥሩ አእምሮ ስትነቃ አንድን ነገር ለማድረግ አስበህ መተኛት ትችላለህ፡፡ ነገ የአንድን ሰው ችግር የሚያቃልል አንዲትን ተግባር ማከናወን ትችላለህ፡፡

❤️ዋጋ ከፍለህ ብታደርገው የአንተን ህልውና የማይነካ፣ ለሌላው ለጨነቀው ሰው ግን የህልውና ጉዳይ የሚሆን አቅም በእጅህ ካለ የፈቃደኝነት ጉዳይ ነው እንጂ ያንን ከማድረግ ምንም ነገር እንደማይከለክልህ አትዘንጋ፡፡ አንድ ቀን የተጨመረልን አንድን ነገር በሰዎች ሕይወት እንድንጨምር እንደሆነ አትዘንጋ፡፡


ውብ እንቅልፍ❤️

ደ/ር እዮብ ማሞ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
ሰዓት እላፊ!
💚

# መፅሐፍ በዞረበት ከዞርኩኝ ሁለት ወር አልፎኝ ነበር (ለምንም ነገር ስሜት አጥታቹ ታውቃላቹ..?)እንደዛ ነገር! .....አስታወሳችሁት ከዚህ ቀደም ስለዚህ መፅሐፍ አውርቻቹ ነበር #በመሀል ለምን አልደግመውም በሚል መፅሐፉን ደገምኩት በቃ የተለየ ስሜት ነው የተሰማኝ በድጋሚም.......

#ተከተሉኝ
.
.
.


የጊዜ ዑደት የማይለውጠው ነገር አይኖረውም የማይችለው ነገር ቢኖር መሆን ያለብንን እና መሄዳችንን ብቻ ይመስለኛል ከዛ ውጭ ጊዜ ሁሉን እየወለወለ፣ እየከለሰ እያደሰም ሆነ እያፈረሰ እሳቤን፣ማንነትን ያሳየናል።ከጊዜ ጋር የማይበስል፣ በጊዜ እሳት ተጥዶም እንጭጭ የሚሆን አይጠፋም... ላውራላችሁ ያሰብኩት ስለ ጊዜ ሳይሆን ስለ አንድ መፅሀፍ ነው መቼቱን የወያኔ እንቅስቃሴ በተማሪዎች ላይ ሰርፆ በገባበት ወቅት ያረገው ይህ መፅሀፍ ከሀርቡ ተነስቶ በሀሳብ እና በፍልስፍና እየጎለበተ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የተማሪዎች እንቅስቃሴን ያስቃኘናል....ልጅ ሳለሁ የአንባቢ ጣሪያ የሰብለን እና የበዛብህን ታሪክ ፍቅር እስከ መቃብር ላይ አንቦ መጨረስ ይመስለኝ ነበር(ያኔ ይህ መፅሀፍ ሊነግረን የሚፈልገው ፍቅራቸውን ብቻ ይመስለኝ ነበር) በቃ ፍቅር እስከ መቃብርን ያነበበ ካለ እሱ ለኔ የአንባቢ ጥግ ነበር....ለአሁኖቹ አንባቢያን ደግሞ አደፍርስ ይመስለኛል ገልጦ የጨረሰም አብጠርጥሮ የጨረሰም እኩል የምትወደው መፅሀፍ ሲባል አደፍርስ ይላል ይህን ሊል የሚችለው ግን ንባብን አዘውታሪ ከሆነ ብቻ ነው። ዛሬ ላይ ብዙ በገለጥን ቁጥር ብዙ እንደምናውቅ፤ ብዙ ባሰስን ቁጥር ብዙ እንደምናገኝ አውቃለሁ....አሁን ላወራላችሁ ያሰብኩት ስለ ሚክሎል ነው። ይህን መፅሀፍ ከገዛሁት ከወራቶች ቀደም ብሎም ያህል ቢሆነኝም ሁለቴ ገለጥኩት ሰሞኑን ነው ግን ውስጤን ሰቅዞ ስለያዘው እና ካተረፍኩት ደስታ ብትቃርሙ ብዬ ወደ እናንተ ያሳለፍኩት።


በፍቅር እስከ መቃብር ፣ በአደፍርስ እና አሁን ላወራላችሁ በፈለኩት ሚክሎል ውስጥ አንድ ከማህበረሰቡ በፍልስፍናቸው በእይታቸው እና በክዋኔያቸው አፈንጋጮች የተባሉ ግለሰቦች አሉ....ጉዱ ካሳ፣አደፍርስ እና ጉግሳ ነገር ግን ሁለቱ ከጉዱ ካሳ ጋር ሊያማስላቸው የሚችለው ነገር ማፈንገጣቸው ብቻ ሲሆን ሁለቱን ገፀ-ባህሪያት ግን አንዳንድ ተምሳሎት ስላላቸው ጥቂት ልበልላቸው። ሁለቱም ወጣት ናቸው የተገኙበትን ማህበረሰብ ማንቃት የሚሹ ፤ ሁለቱም ጥያቄ የሚጭሩ ሀሳቦችን የሚያነሱ ፤ ነገር ግን የሚክሎሉ ጉግሳ የማውቀው በቃኝ አይልም ሰው ይሰማል፣ የሚያጋጥሙትን ክስተቶች ችላ አይላቸውም ይማርባቸዋል ፤ በሚያወራው አደፍርስ ሲያደንቁት ሲያሞካሹት ይወዳል ጉግሳ ግን ለሙገሳ ቦታም የለው ፤ አንዳንዴ የአደፍርስ ሀሳቦች ከማህበረሰቡ ሲወርድ(ሲቀል) ይታያል ፤ አደፍርስ መስጠትን እንጂ መቀበልን የህይወቱ ኡደት ውስጥ አልከተታቸውም ምን አልባት ሀሳቦችን ተቀባይ እንዲሆን በጉግሳ የህይወት እንቅስቃሴ ላይ የተሳሉት ይህን ባህሪ ስላደሉት ይሆናል መሬት ወርዶ ከመሀይሙ፣ ከእብዱ፤ ከሴተኛ አዳሪው ይስማማል ይማራል....የልጅነት ፍልስፍናውን በአባቱ ቅኝት ምንም የሚያቅትህ ነገር የለም፣ ሁሌም ቢሆን ከቀልብህ ምከር እያሉ የቃኙት ወጣት የዩንቨርስቲ ተማሪ በንባብ ያካበተውን ወደ ውስጥ ተመልካችነት ክህሎት አንድ እብድ ጋር ያደርሰው እና ያለምክንያት መኖር ክልክል ነው የሚል ፍልስፍና ይቸረዋል....ምርጥ ስነ-ፅሁፍ፣ ቆንጆ የሀሳብ ፍሰት እና የህይወት ፍልስፍና በአንድ ጥራዝ ታትመው ቀርበዋል!!!


አስቸኳይ የንባብ እርምጃ ይወሰድበት!!!!! እውነት አንብቡት ትወዱታላቹ!!


@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta
,#አድዋ💚💛❤️

እንኳን ለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ አደረሰን🇪🇹

መልካም በአል ለሁላችን🇪🇹