Ethio Fm 107.8
20.2K subscribers
7.22K photos
16 videos
4 files
2.29K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
የዩጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ኬንያንና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ይቅርታ ጠየቁ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይቅርታ የጠየቁት የሃገሪቱ የምድር ጦር አዛዥ ኬንያን ለመያዝ ሁለት ሳምንታት በቂ ናቸዉ በሚል በቲዉተር ገጻቸዉ ላይ ላሰፈሩት መልዕክት ነዉ፡፡

ሙሴቪኒ የምድር ጦር አዛዥ የነበሩት ሙሆዚ ካይነሩጋባ የተላለፈዉ መልዕክት ፈጽሞ ከአንድ የመንግስት ባለስልጣን የማይጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ካይነሩጋባን ከምድር ጦር አዛዥነት ቢነሱም የሙሉ ጀነራል ሹመት እንደተሰጣቸዉና ከምድር ጦር አዛዥነታቸው ጎን ለጎን ደርበው ይዘውት የነበረውን የልዩ ዘመቻዎች የፕሬዝዳንቱ አማካሪነት ቦታቸውን እንደያዙ እንደሚቀጥሉ የሲጂ ቲ ኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
ለጤና ባለሙያዎች የምስጋና ፕሮግራም ሊዘጋጅ ነዉ፡፡

ሀገር በኮሮና ቫይረስ ችግር ዉስጥ በገባችበት ጊዜ ከፊት ሆነዉ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእዉቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ሊዘጋጅ ነዉ፡፡
ፕሮግራሙ የፊታችን ጥቅምት 12 በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል እንደሚካሄድ የገለጸዉ ዳንኪራጃም ኘሮሞሽን እና ኘሮዳክሽን ሲሆን በዕለቱም የጤና ባለሙያዎች ለሰሩት ስራ ይመሰገናሉ ተብሏል፡፡

የዳንኪራጃም ኘሮሞሽን እና ኘሮዳክሽን ኘሮግራም ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ እንደገለጹት፣ የህክምና ባለሙያዎች የኮቪድ 19 በሽታ እንዳይስፋፋ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመስራት፣ የበሽታው ምልክት የታየባቸውን በመመርመር እንዲሁም ህሙማንን በመንከባከብ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ውስጥ በመክተት ጭምር የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ ተቋማት እና ባለሙያዎች እውቅና እና የምስጋና ኘሮግራም ተዘጋጅቷል ነዉ ያሉት፡፡

በዕለቱ ከሚኖረዉ የምስጋና እና የዕዉቅና ፕሮግራም ባሻገር የመዝናኛ ዝግጅቶች እና የምክክር እንዲሁም የውይይት ኘሮግራም እንደተሰናዳም ገልጸዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በዓለምም በሃገራችንም ያስከተለዉ ቀዉስ የበርካታ ድርጅቶችን ኢንቨስትመንት አቃውሷል እንዲሁም የሀገራችን ኢኮኖሚ ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ አሳርፏል፡፡

ዳንኪራጃም ፕሮዳክሽን እና ፕሮሞሽን የኢትዮጵያን ባህል በተለይም የሙዚቃውን ኢንዱስትሪ በመላው ዓለም ለማስተዋወቅ ለኢትዮጵያዊያን የሙዚቃ ባለሙያዎች ድጋፍ በማድረግ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለምዕራቡ ዓለም እና በውጭ ላሉ ኢትዮጵያውያን በስፋት ሲያስተዋውቅ መቆየቱ በመግለጫዉ ላይ ተነስቷል፡፡

በእስከዳር ግርማ
መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 26-01-15

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡


አዲስ አበባ ሲገቡም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው “እንኳን ደህና መጡ” በማለት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡


ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በሁለትዮሽና የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬዉ እለት በይፋ አስጀምሯል፡፡


የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሳኡሳ፥ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ለማበረከት እና ተደራሽነቱን ለማስፋት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡


ሳፋሪኮም ባለፉት ሳምንታት በድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ አወዳይ፣ ጎንደር ፣ሞጆ፣ ሐረር፣ አዳማ፣ ሀረር፣ ቢሾፍቱና ደብረ ብርሃን ከተሞች የኔትዎርክ ሙከራ አገልግሎቱን መጀመሩንም ከኩባንያው የተገኘዉ መረጃ ያመላክታል፡፡


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም
የትምህርት ሚኒስቴር በ " ኮቪድ-19 ወረርሽኝ " ምክንያት የተዛባውን የትምህርት ካላንደር በዘንድሮው ዓመት እንደሚያስተካክል አስታወቀ፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዳሉት፣የ2015 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተናን በግንቦት ወር ለመስጠትም ታቅዷል።
" በ2015 ሁለት ፈተና ነው የምንሰጠው። አሁን የምንሰጠው ፈተና (ከመስከረም 30 ጀምሮ) የ2014ን ፈተና ነው።
ከኮቪድ ጊዜ ጀምሮ መርሀ ግብሩ እየተበላሽ በአጠቃላይ የትምህርት ስርዓታችን ግልፅ የሆነና ሁሉም የሚያውቀው የአካዳሚክ ካላንደር ሊኖረን አልቻለም ፤ እሱን በዚህ ዓመት እናስተካክላለን አሁን መስከረም 30 የምንሰጠው የ2014ን ነው ግንቦት ላይ የ2015 ተማሪዎችን እንፈትናለን ብለዋል።
ከዛ በኃላ ባሉት ጊዜያት የአካዳሚክ ካላንደሩ ከሞላ ጎደር ወደ ስርዓቱ ይገባል። "ነዉ ያሉት፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም
ብሔራዊ ባንክ የሀዋላ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል ያላቸውን የ392 ግለሰቦች የባንክ ሂሳብ አገደ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሕገወጥ የሀዋላ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል ብሎ የጠረጠራቸውን 392 ግለሰቦች የባንክ ሂሳብ ማገዱን ዛሬ አስታውቋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2015 ዓም እንዳስታወቁት፣ ተጠርጣሪዎቹ የባንክ ሂሳቸው ታግዶ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ትላንትና ሀሙስ በሰሜን ሜጫ ወረዳ በ " አምቦ መስክ " ቀበሌ አቅጣጫውን ከባህር ዳር ወደ ማርቆስ ያደረገ ሰሌዳ ቁጥር " አማ 17492 " የሆነ ተሽከርካሪ ወይም ኮስትር ተሽከርካሪ እና መነሻውን ከምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ያደረገ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ጋር ግጭት ተፈጥሮ በተሳፋሪዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው በአምስት ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከፈተናው የሚያግዳቸው አይደለም ተብሏል።

የሰሜን ሜጫ ወረዳ ትራንስፖርት ፅ/ቤት ግጭቱ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት መፈጠሩን ገልጿል።

በዚህ ወቅት ከአገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር ተያይዞ የትራፊክ መጨናነቅ ስላለ አሽከርካሪዎች በተገቢው ፍጥነት በማሽከርከር እራሳቸውን እና ተሳፋሪውን ከትራፊክ አደጋ እንዲታደጉ የሰሜን ሜጫ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አሳስቧል።
ወቅታዊ መረጃ

በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሰላም ንግግር ከሀገር ሉዓላዊነትና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓት አንፃር መታረም የሚገባቸው ጉዳዮች፡-
የቃላት አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲደረጉ….የኢትዮጵያ መንግስት
የኢትዮጵያ መንግስት፤ የኢትዮጵያ ወዳጆች ወይም " የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ህገመንግስት እናከብራለን " የሚሉ ወገኖች ከሰላም ንግግሩ ጋር በተያያዘ የቃላት አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲደረጉ አሳሰበ።
ፌዴራል መንግስት ማሳሰቢያውን ያወጣው በስሩ ባለው የ " ወቅታዊ ሁኔታዎች መረጃ ማጣሪያ " በኩል ነው።
የመረጃ ማጣሪያው እንደ " የትግራይ መንግስት (Government of / state of Tigray " ወይም ፣ " የትግራይ የውጭ አገልግሎት / Tigray External Service " የመሳሰሉ አገላለጾች ተራ ስህተቶች ሳይሆኑ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥሉ በመሆናቸው ሊፈተሹ ይገባል ብሏል።
የኢትዮጵያ ወዳጆች ወይም " የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና ሕገ መንግሥት እናከብራለን " የሚሉ ወገኖች ሁሉ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት በቅርቡ በሚደረገው የሰላም ንግግር ሕገ-ወጥ ቃላትን / አገላለፅን ከመጠቀም ይቆጠቡ ሲል አስገንዝቧል።
" ከዚህ የሰላም ንግግር አንፃር ወዳጆቻችን እና አጋሮቻችን ማስታወስ ያለባቸው ሁለቱ ወገኖች በመሰረታዊነት ልዩነት ያላቸው መሆኑን ነው " ያለው ይኸው የመረጃ ማጣሪያ ፤ " አንዱ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ፣ ህጋዊ መንግስት እና ሌላኛው ' ህወሓት ' የታጠቀ ቡድን ነው " ብሏል።
እንደዚሁም እንደ " የትግራይ አስተዳደር / Tigray Administration " ወይም " የትግራይ ክልል መንግስት / Regional Government of Tigray " የመሳሰሉ አገላለፆችም ተቀባይነት የላቸውም ሲል አሳውቋል።
ምክንያት ያለውም ፤ " በትግራይ ክልል ውስጥ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት የተመረጠ አካል ስለሌለ ነው " ሲል አስረድቷል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
1 ሺሕ 497ተኛው የነብዩ ሙሐመድ (ሰዓወ) የልደት በዓል (መውሊድ) ነገ ይከበራል፡፡

የዘንድሮው የመውሊድ በዓል ነብዩ ሙሐመድ ( ሰዓወ ) ለመላው ዓለም የተላኩ በመሆናቸው የእሳቸውን ልህቀት በሚገልፅ መልኩ “የእዝነቱ ነቢይ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍኤም 107.8 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺሕ 497ተኛው የነብዩ ሙሐመድ (ሰዓወ) የልደት በዓል (መውሊድ) አደረሳችሁ ይላል፡፡

መልካም በዓል