Ethio Fm 107.8
20.2K subscribers
7.22K photos
16 videos
4 files
2.29K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
የዩክሬን ጦርነት እስከ 2030 ድረስ ሊዘልቅ ይችላል ተባለ፡፡

የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት እስከ 2030 ሊዘልቅ ይችላል ሲሉ የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ፡፡
የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቨክቶር ኦርባን ለራዲዮ ዩሮፕ እንደተናገሩት አሁን ባለው ሁኔታ ጦርነቱ በጥቂት ጊዜያቶች የሚጠናቀቅ አይደለም::
ጠቅላይ ሚኒስትር ኦርባን ከፓርቲያቸው ጋር በዝግ ባደረጉት ውይይት፣ ጦርነቱ ለሃንጋሪም እንደተረፈ ተናግረው ጊዜ የሚፈጅ አደገኛ ጦርነት ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ዩክሬን በዚህ ጦርነት ግማሽ ያህል ግዛቷን በሩስያ መወሰዱን ተናግረዉ በዚህ የሚያበቃ አይደለም ሲሉም አክለዋል፡፡

በአውሮፓ ህብረት እና በአሜሪካ ድጋፍ የቀጠለው የዩክሬን ጦርነት፣ አስቸኳይ መፍትሄ የማይገኝለት ከሆነ ከታሰበው በላይ ኪሳራ አሳድሮ የሚያልበት አጋጣሚም ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

አሜሪካ እና አንዳንድ የአውሮፓ ሀጋራት አሁንም ድረስ ለዩክሬን የጦር መሳርዎችን እየለገሱ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጦርነቱን ከማፋፋም ውጪ ምንም ለውጥ አላመጣም ብለዋል፡፡
ጦርነቱን ተከትሎ በሩስያ ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች ዳፋው ያረፈው እኛን በመሳሰሉ ሃገራት ነው ሲሉ ቪክቶር ኦርባን መናገራቸዉን አርቲ ኒውስ
ዘግቧል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መስከረም 09 ቀን 2015 ዓ.ም
አቶ ወርቁ አይተነው የአቪዬሽን ኩባንያ አቋቋሙ፡፡

ታዋቂው ባለሀብት አቶ ወርቁ አይተነው "ጎልድ ስታር አቪዬሽን " የተሰኘ የአየር ትራንስፖርት ኩባንያ በማቋቋም ላይ እንደሆኑ ተሰማ፡፡

አቶ ወርቁ ቤል 407 የተሰኘች ሄሊኮፕተር መግዛታቸው የሚታወስ ሲሆን ሄሊኮፕተሯን ወደ ኮሜርሺያል አቪዬሽን እንዳስገቧት ታውቋል፡፡

ባለሀብቱ "ጎልድ ስታር አቪዬሽን " በሚል ስያሜ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ የመሰረቱ ሲሆን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ፈቃድ (Air operator certificate) ከኢትዮጲያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ለማግኘት በሂደት ላይ እንደሆኑም ተነግሯል፡፡

አዲስ የተመሰረተው ኩባንያ ተጨማሪ አነስተኛ የአየር ትራንስፖርት አውሮፕላን አስገብቶ የመስራት እቅድ እንዳለው ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
ዘግቧል፡፡

አቶ ወርቁ አይተነው ግዙፍ የሆነውን የደብሊው ኤ የምግብ ዘይት ፋብሪካ የገነቡ ሲሆን በቅርቡ በአንድ ቢሊየን ዶላር ወጪ የሲሚንቶ ፋብሪካ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመራቸው መነገሩ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 09 ቀን 2015 ዓ.ም
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 10-01-15

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለ
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ለዩክሬን የ2.63 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡

አዲሷ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ሊዝ ትረስ ለዩክሬን ጦርነት ድጋፍ የሚሆን የ2.63 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

ይህ ገንዘብ አገሪቱ ከዚህ በፊት ኪየቭ ከሩሲያ ጋር ለምታርገዉ ጦርነት ከመደበችዉ የገንዘብ መጠን እንደሚበልጥ ተነግሯል፡፡

ሊዝ ትረስ እንግሊዝ በእያንዳንዱ እርምጃ ከዩክሬን ጎን ሆና ትቀጥላለች ሲሉ ቃል አቀባይ መናገራቸዉን ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል፡፡

ለንደን አ.ኤ.አ በ2022 ለኪየቭ ካደረገችዉ የ2.63 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አኳያ ለዩክሬን ትልቅ ወታደራዊ ድጋፍ ያደረገች አገር መሆኗን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በቤዛዊት አራጌ
መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም
ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች መስፋፋት ምክንያት ከ 31 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱ ተገለፀ፡፡


ኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች አምራች ዜጎቿን እያጣችና የኢኮኖሚ እድገቷ እየተገታ ከመሆኑም በላይ ለነዚህ ህመሞችም በዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር እንደምታወጣ የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር አስታዉቋል።


ማህበሩ ለኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ በላከው መግለጫ ላይ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች አንዱና ዋነኛ አጋላጭ መሆኑን ገልጿል።

በኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ብዙ ሰዎች በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን ገዝተው በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ የገለፀው ማህበሩ እነዚህም የምግብ አይነቶች በፍጥነት ወደ ገበያ እየገቡ መሆኑን አመላክቷል።


እ.ኤ.አ. በ 2019 በሀገሪቱ የተመዘገበው 39.2% አጠቃላይ ሞት ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች እንደ ልብ ድካም ፣ ስትሮክ ፣ የስኳር በሽታ እና ካንሰር ባሉ ሥር በሰደዱ በሽታዎች ምክንያት ነው መባሉን ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡


በ2017 ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች አጠቃላይ የመንግስት ወጪ 4.4 ቢሊዮን ብር ነበር። በ2014ዓ.ም ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች መስፋፋት ምክንያት (ቀጥታ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ወጪ) 31.3 ቢሊዮን ብር የኢኮኖሚ ኪሳራ አጋጥሟል ።

ይህም ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 1.84 በመቶ አካባቢ እንደሚይዝ የማህበሩ መግለጫ ያስረዳል፡፡


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም
ሩሲያ የአፈር ማዳበሪያ ለአፍሪካ በነጻ አቀርባለሁ ብላለች፡፡


የሩሲያ የማዕድንና የፖታሽ ማዳበሪያዎች አምራች ዩራልቼም ነዉ ምርቶቹን ለአፍሪካ በነጻ ለማቅረብ መወሰኑን ያስታወቀዉ፡፡


የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዲሚትሪ ኮኒያዬቭ እንዳሉት፣የመጀመሪያው 25 ሺህ ቶን ማዳበሪያ ወደ ቶጎ ይላካል መባሉን አር ቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡


ከዚህ ቀደም የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሃገራቸዉ በምዕራቡ ዓለም በተጣለባት ማዕቀብ ሳቢያ በወደቦች ከተጠራቀመዉ ዉስጥ 300 ሺህ ቶን ማዳበሪያን ለታዳጊ ሀገራት በነፃ ልታቀርብ እንደምትችል ፍንጭ ሰጥተዉ ነበር፡፡


በመሳይ ገ/መድህን

መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 21 እና መስከረም 22 ቀን ይከበራል፡፡


የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት እንዳስታወቀዉ የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 21 እና መስከረም 22 ቀን ይከበራል፡፡


በዓሉ መስከረም 21 ቀን ሆራ ፊንፊኔ በአዲስ አበባ እንዲሁም መስከረም 22 ቀን ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ እንደሚከበርም ነው የተገለጸዉ።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 11-01-15

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የማዕድን ሚኒስቴር የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ የማፈላለግ ስራ ላይ ከተሰማራው ፖሊ ጂ ሲ ኤ ል ከተሰኘው ኩባንያ ጋር የገባውን ውል አቋረጠ።


የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ከኩባንያው ጋር የነበረው ውል ከትናንት ጀምሮ የተቋረጠው ከረጅም ጊዜ ትእግስት እና ማስጠንቀቂያዎች በኋላ ነው ብለዋል።

በቀጣይም የነዳጅ ሀብቱን ወደ ስራ የሚያስገቡ አፋጣኝ ስራዎችን እንሰራለን ሲሉ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ለሚያካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የ541 ሚሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ አቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ ማስፈጸሚያ የሚያስፈልገውን የ541 ሚሊዮን ብር
ተገማች በጀት ያቀረበው ለኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።

ቦርዱ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር የሚገኙ ስድስት ዞኖች ማለትም የጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ጌዲዮ፣ ኮንሶና፣ ደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም አምስት ልዩ ወረዳዎችን እነዚሁም የቡርጂ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ባስኬቶ፣ አሌ ልዩ ልዩ ወረዳዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንደሚያካሄድ ይታወቃል።

ቦርዱ በተጠቀሱት ዞኖችና ልዪ ወረዳዎች ላይ ሕዝበ ውሣኔ በማደራጀት ውጤቱን እንዲያሳወቅ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተጠየቀው ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ሲሆን፤ በዚህም መሠረት ቦርዱ የሕዝብ ውሣኔውን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ዝርዝር ተግባራትን በማካተት የድርጊት መርኅ ግብር አዘጋጅቶ አቅርቧል።

በሕዝበ ውሣኔው የድርጊት መርኅ ግብሩ ላይ የተጠቀሱትን አጠቃላይ ተግባራት ተፈጻሚ ለማድረግም የሚያስፈልገውን በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም
“ ይፈለጋል “ ፊልም ከ15 ዓመት በኋላ ዳግም ለእይታ ሊቀርብ ነው።

በሰይፉ ፋንታሁን የተዘጋጀው ይህ ፊልም ከ15 ዓመት በሗላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ሲኒማ ሊታይ ነው ተብሏል::

በእይታው የሚገኛውን ገቢ ደግሞ ለአዘጋጅና ተዋናይ ስዩም ተፈራ ለህክምና የሚውለው ይሆናል::
ተዋንያን :- ሠራዊት ፍቅሬ
:- ሰይፉ ፋንታሁን
:- አምለሰት ሙጪ
:- ደረጀ ሀይሌ
:- ቶማስ ቶራ
:- ሳምሶን ቤቢ
:- ፍቃዱ ከበደ
:- በላይነሽ አመዴ እና ሌሎችም አንጋፋ ተዋንያኖች የተሳተፉበት

በአለም ሲኒማ የሚታይባቸው ቀናቶች
⁃ መስከረም 12 ሀሙስ በ11:00 ሰአት
⁃ መስከረም 13 አርብ በ10:00 ሰአት
⁃ መስከረም 14 ቅዳሜ በ10:00 ሰአት ይታያል እንዲሁም
⁃ መስከረም 15 እሁድ ከቀኑ በ10:00 ሰአት በአለም ሲኒማ በልዩ ፕሮግራም ይታያል

የፊልሙ ሙሉ ገቢው ለአዘጋጅና ተዋናይ ስዩም ተፈራ ለህክምና እንደሚውል ተገልጿል።
ዛሬ ምሽት ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ምሽቱን ከዲጄ ሔኒኬ ጋር ፕሮግራማችን ከተወዳጇ ድምጻዊት ሃሌሉያ ገ/ጻዲቅ ጋር “ተወዳጅ” ስለተሰኘዉ አዲስ አልበሟ እና ስለ አጠቃላይ የሙዚቃ ህይወቷ እንጨዋወታለን፡፡
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 12-01-15

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ ተገደሉ::


የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ እንዳስታወቀው በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ የነሩት ኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸዉ አልፏል።

ኮማንደሩ በፀጥታ በማስከበር ስራ ላይ በነበሩበት ወቅት ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት አካባቢ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ተመትተዉ ለህዝብና ለሀገር ሲሰሩ መስዕዋት ሆነዋል ሲል የክልልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

ፖሊስ ኮሚሽኑ በኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉን ሀዘን ገልጾ ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ረፋድ መፈፀሙን እስታውቋል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም