Ethio Fm 107.8
20.2K subscribers
7.22K photos
16 videos
4 files
2.29K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
ሰበር ዜና

ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ወጥተዋል

ታሪካዊቷ የደሴ ከተማና የንግድና የኢንዱስትሪ ኮሪደር የሆነችው ኮምቦልቻ ከተማ፣ በጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ወጥተዋል።

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ ከደሴና ኮምቦልቻ በተጨማሪ በምሥራቅ ግንባር ባቲን፣ቀርሳን፣ ገርባንና ደጋንን ነጻ ያወጣ ሲሆን በሐርቡ ግንባር ደግሞ ቃሉ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመላው ዓለም ወደ ኢትዮጵያ ለሚደረገው "ታላቅ ጉዞ ወደ አገር ቤት" የ30% ቅናሽ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች “የ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት ጥሪ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ለማክበር ይፋ የሆነውን 1 ሚሊየን ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የማድረግ ጥሪን እንዲቀበሉ ጠይቀዋል፡፡

አየር መንገዱም ይህን ተከትሎ በዛሬው ዕለት "ከአሁን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 11 2014 ተመዝግበው ትኬትዎን ይግዙ።

ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 2014 ይጓዙ" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም
ከሸዋሮቢት እስከ ካራቆሬ ባሉ ከተሞች የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመሮችን የመጠገን ሥራ መስራት ተገለጸ

በሽብርተኛውና የህወኃት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው ከሸዋ ሮቢት እስከ ካራቆሬ ባሉት ከተሞች የሚገኙ የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ተጠግነው ተጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሸዋሮቢት፣ በጀውሀ፣ በሰንበቴ፣ በአጣዬና ካራቆሬ ከተሞች የሚያልፈውን የከፍተኛ መስመር በመጠገን ለስርጭት መስመሮች ኃይል መስጠት እንዲችሉ ዝግጁ የማድረግ ሥራ አጠናቋል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጀመረው የሥርጭት መስመሮች የጥገና ሥራ እንደተጠናቀቀ የተጠቀሱት ከተሞችና አጎራባች የገጠር ቀበሌዎች በፍጥነት የኤሌክትሪክ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቀጣዮቹ ቀናት ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው መስመር የመጠገን ሥራ እንደሚሰራ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም
የህወሃት ቡድን በቅርሶች ላይ ያደረሰውን ውድመትን ለማወቅ የአጥኚ ቡድን ተላከ

በተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት በተፈረጀው ህወሃት ተይዘው አሁን ነፃ የወጡት አካባቢዎች ላይ በቅርሶች ላይ የደረሰው ጉዳት ለማወቅ የአጥኚ ቡድን ወደተለያየ አካባቢ መላኩን የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተናገሩ።

ቡድኑ በተለያዩ ቅርሶች ላይ ፣ ብሄራዊ ፓርክ ፣ ሆቴሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።

ሚኒስቴ መስርያ ቤቱ ቅድመ ጥናት ማድረጉን የገለፁት አምባሳደር ናሲሴ ትክክለኛውን ውድመት ለማወቅ የአጥኚ ቡድን ወደተለያየ አካባቢ መላኩን ዛሬ በሰጡት መግለጫ አንስተዋል።

ትላንት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታዋ ሰላማዊት ካሳ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህወሓት ቡድን ወርሯቸው በነበሩ አካባቢዎች በሚገኙ ቅርሶች፣ የቱሪስት መዳረሻዎች እና ጥብቅ የማህበረሰብ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ማሳወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሚኒስትር ዴዔታዋ ጨምረው እንዳሉት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በቅርስና የቱሪስት መዳረሻ በሆኑ 6 የሃይማኖት ተቋማት፣ 2 የቱሪዝም ድርጅቶች እና በ22 የቱሪዝም አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት፤ ባለሙያዎች ወደስፍራው አቅንተው ባደረጉት ምልከታ ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙም ተረጋግጧል፡፡

ረድኤት ገበየሁ
ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም
እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ 400ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል ወደ ሀገር ቤት ይገባል ተባለ፡፡

ለተፈናቃይ ወገኖች እየተደረገ ባለው ድጋፍ ላይ እጥረት እንዳይፈጠር መንግስት ከውጪ እህል ገዝቶ እያስገባ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች እየተደረገ ባለው ድጋፍ እጥርት እንዳይፈጠር 400ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል ተገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ እንደሆነ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

የተገዛው እህልም እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም 300ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል ግዢ ለማከናንም በሂደት ላይ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት የተፈናቃች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር በተያያዘም ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቁጥርም ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

ለተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረግ የሚሹ ድርጅቶች ግለሰቦች እና ረጂ ድርጅቶች ለተፈናቃይ ዜጎች በአግባቡ እንዲደርስ በኮሚሽኑ በኩል ቢያደርጉ የተሸለ ይሆናል ሲሉ አቶ ደበበ ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም
ወሊድ እና እርግዝና ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዳይመለሱ ከፍተኛ እንቅፋት የሆነባቸዉ የኡጋንዳ ሴት ተማሪዎች፡-

የኮቪድ 19 መከሰቱን ተከትሎ ትምህርት እንዲቋረጥ ካደረጉ ሃገራት መካከል ኡጋንዳ አንዷ ናት፡፡

እነዚህ ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎች በቀጣዩ የፈረንጆች አመት 2022 ትምህርት እንዲጀምሩ ጥሪ የተደረገላቸዉ ሲሆን አብዛኞቹ በማርገዛቸው እና በመውለዳቸው ምክንያት ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ እንደማይችሉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ባሳለፍነው ወር ትምህርት ቤቶች በፈረንጆቹ አዲስ አመት ጥር 2022 እንደሚከፈት አስታውቀው ነበር፡፡

ነገር ግን በብዛኞቹ ተማሪዎች ትምህርት መዘጋቱን ተከትሎ ማግባታቸውን እና መውለዳቸውን እንዲሁም የእርግዝና ጊዜን እያሳለፉ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከፈረንጆቹ መጋቢት 2020 ጀምሮ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም የትምህርት ተቋማት ተዘግተው ቆይተዋል፡፡

እንደ የሃገሪቱ እቅድ እና ትግበራ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ ትምህርት ተዘግቶ በመቆየቱ ሳቢያ እስከ 30 በመቶ የሚደርሱ ተማሪዎች እርግዝና ፣ ያለ እድሜ ጋብቻ በለጋ እድሜያቸው ስራ በመጀመራቸው ምክንያት በጥር ወር በሚጀመረው ትምህርት ላይ አይመለሱም ተብሎ ይጠበቃል ብሏል።

ዩኒሴፍ ከፈረንጆቹ መጋቢት 2020 እስከ ያዝነው ወር ያለውን ሁኔታ ባመላከተዉ ሪፖርቱ በኮቪድ 19 ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው በቤታቸው ከተቀመጡት ውስጥ 22. 5 በመቶ የሚሆኑትና እድሜያቸዉ ከ10 አመት እስከ 24 የእድሜ ክልል የሚገኙት ተማሪዎች ማርገዛቸውን በሪፖርቱ ማመልከቱን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም
በበጀት አመቱ ባለፉት አምስት ወራት ከ7 መቶ 33 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማሰባሰቡን የአዲስ አበባ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በ2014 በጀት አመት 875 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማሰባሰብ አቅዶ ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 733 ሚሊዮን 875ሺ 5 መቶ19 ብር ገቢ በማሰባሰብ የእቅዱን 83 በመቶ ማሳካት መቻሉን የአዲስ አበባ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገቢውን ከመንጃ ፍቃድ ፤ ከሰሌዳ ፤ ከቦሎ ፤ ከተሸከርካሪ ስም ዝውውርና ከተያያዥ አገልግሎቶች በማሰባሰብ በግማሽ በጀት አመት ውስጥ እቅዱን በላቀ ሁኔታ ማሳካቱን ገልጿል፡፡

በቀጣይም ተቋሙ የሚሰጣቸውን የአገልግሎት ዘርፎች በማስፋትና የገቢ አሰባሰብ ዘርፎቹን በማዘመን እቅዱን በእጥፍ ለማሳካት እንሚሰራም አስታውቋል።

ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
የኢትዮጵያን ስም ከማድመቅ የበለጠ ዕድል የለምና የዚህ ታሪክ አካል ለመሆን ፈጣሪ ዕድሉን የሰጣችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ!! ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

“በድል የታጀበው የመጀመሪያው ምእራፍ”
ውድ የሀገሬ ልጆች፣
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣
ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ትከበራለች፤ ትታፈራለች። ኢትዮጵያን መገዳደር ይሞከር ይሆናል። ተገዳድሮ ማሸነፍ ግን ትናንትም አልተቻለም፤ ዛሬም አይሆንም፤ ነገም አይቻልም።

ኢትዮጵያ የሚለው ስም ሁሌም ከአሸናፊነት ጋር የተያያዘ ነው። ከጥቂት ጊዜያት በፊት ኢትዮጵያን ሊወጋ የተነሳውን ጠላት በጋራ ሆነን እንድንመክት ጦር ግንባር ላይ የያዝነው ቀጠሮ ጠላትን አንገት ሲያስደፋ ኢትዮጵያን ቀና አድርጓታል። ሀገራችን ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ለማድረግ በጦር ግንባር እየተከፈለ ያለው መስዕዋትነት የኢትዮጵያን የአሸናፊነት ስም የሚመልስ መሆኑን እያበሰርኩ፣ ያቀረብኩትን ጥሪ ተቀብላችሁ ሕይወታችሁን፣ ጉልበታችሁን፣ ሀብታችሁን፣ ዕውቀታችሁን፣ ጊዜያችሁንና ሞያችሁን ለሠጣችሁ ሁሉ በኢትዮጵያ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

በዚሁ አጋጣሚ፣ የመጀመሪያውን ምእራፍ አጠናቅቄ ለተወሰኑ ጊዜያት ወደ ቢሮ መመለሴን እየገለጽኩ፣ ዛሬም ሆነ ወደፊት ጠላቶቻችን ጉልበታቸው ዝሎ፣ የጥላቻና የጠበኝነትን መንገድ ጥለው፣ የፍቅርና የሰላምን መንገድ እስኪመርጡ ትግላችን ይቀጥላል።

የእኛ ፍላጎት ሁሌም ሰላምና ፍቅር ነው። ኢትዮጵያ ሕብረ ብሔራዊ አንድነቷ ተጠብቆ የብልጽግና ጉዞዋ የተቃና እንዲሆን ያለንን ፍላጎት ከጅምሩ አሳውቀን ለተግባራዊነቱ ስንተጋ ቆይተናል። ነገር ግን በተደጋጋሚ ያቀረብነውን የሰላም አማራጭ ባለመቀበል፤ አሳታፊና አካታች የሆነውን አዲሱን የፖለቲካ ባህላችንን ረግጦ በመውጣት፤ ጥፋትንና እልቂትን ለማስቀረት ሲባል የተደረገውን ትዕግሥት ከቁብ ባለመቁጠር፤ የአንዳንድ የውጭ ጠላቶችን አፍና ድጋፍ በመተማመን፤ አሸባሪው ሕወሓት ከግብር አምሳሎቹ ጋር ሆኖ በሀገራችን ላይ አደጋ ደቅኖ ነበር።

ነገሮች ያለቁና የተጠናቀቁ እስኪመስሉ ድረስ ኢትዮጵያን የማያውቁ ሁሉ በሥጋትና በፍርሐት ተውጠው ነበር። ሠግተው ሊያሠጉን፤ ፈርተው ሊያስፈራሩን የሞከሩ የውስጥና የውጭ አካላትም ነበሩ። ልጣችን የተራሰ፣ ጉድጓዳችን የተማሰ መስሎ የተሰማቸው ነበሩ። የኢትዮጵያን የአሸናፊነት ምሥጢር የሚያውቁት ብቻ በጽናት እስከ መጨረሻው የቆሙበት አጋጣሚም ተፈጥሮ ነበር።

ወደ ትግል የገባነው ሐቅን ይዘን ነውና የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር። ድካማችንን አበርትቷል። ሕዝባችንን ከዳር እስከ ዳር አነቃንቋል። የሠራዊታችንን ቁጥርና ዐቅም ጨምሮልናል። ልባችንን አጀግኖ የኢትዮጵያን አሸናፊነት በዓይናችን አሳይቶናል። ውድቀታችንን ሲመኙ የነበሩትን ሁሉ አሳፍሮ ዳግም የኢትዮጵያን ስም በወርቅ ቀለም እንድንጽፍ አስችሎናል። የዚህ ታሪክ አካል ለመሆን ፈጣሪ ዕድሉን የሰጣችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። የኢትዮጵያን ስም ከማድመቅ የበለጠ ዕድል የለምና!!

በዕቅዳችን መሠረት የመጀመሪያውን ምዕራፍ፣ “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነትን” በሁለት ሣምንት ውስጥ አሳክተናል። የመከላከያ ሠራዊት፣ የየክልሎቹ ልዩ ኃይሎች፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላት እና የየአካባቢዎቹ ሚሊሻዎችና ታጣቂዎች በከፈላችሁት መሥዋዕትነት ለልጆቻችን የምንነግረው ድንቅ ታሪክ ሠርታችኋል። በሁሉም መስክ በደጀንነት የተሰለፋችሁ ሁሉ የኢትዮጵያ ውድ ሀብቶች መሆናችሁን በዓይናችሁ አይታችኋል።

ትግሉ ገና አልተጠናቀቀም። ነጻ ያልወጡ አካባቢዎች አሉን። አሁን የፈተነን ኃይል ዳግመኛ የኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ እንዳይመጣ የሚያስችል ዘላቂ መፍትሔ ልንሰጠው ይገባል። ለዚህኛው ችግር በምንሰጠው መፍትሔ ወደፊት ለክፉ ያሰቡን ሁሉ እጃቸውን እንዲሰበስቡ ማድረግ አለብን። ላለፈው የምናመሰግንበት እንጂ ጨርሰናል ብለን እፎይ የምንልበት ወቅት ላይ አይደለንም። የተበተነው ጠላት እንዲማረክ ማድረግ አለብን። አካባቢያችንን ከበፊቱ በበለጠ ነቅተን የመጠበቂያ ጊዜው አሁን ነው። ፍተሻና አሰሳዎችን አጠንክረን መቀጠል ይገባናል።

ጠላት ያፈረሰውን መልሰን መገንባት፣ የተፈናቀሉትን መመለስ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎቻችንንም ከበፊቱ በበለጠና በፈጠነ መንገድ ማሳለጥ ይጠበቅብናል።
ለሠራዊታችን የምንሰጠውን ሁለንተናዊ ድጋፍ በዓይነትም በብዛትም አጠናክረን የምንቀጥልበት ወቅት ነው። ያልዘመቱ ወገኖች ግማሽ ያህል ጊዜና ጉልበታቸውን ለዘማች ቤተሰቦች መስጠት ይጠበቅባቸዋል፤ እነሱ ለእኛ ሕይወታቸውን ሲገብሩ እኛ ለእነሱ ገንዘብና ጉልበታችንን መስጠታችን ቢያንስ እንጂ አይበዛም። እናም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የዘማች ቤተሰቦችን መደገፍና ማበርታት አለብን።

ትግሉ በጦር ግንባር ብቻ አይደለም፤ በሁሉም መስክ መፋለም ይገባናል። የገበሬውን እህል አንዲት ፍሬ እንዳትባክን አድገን ወገባችን አሥረን መሰብሰብ አለብን። በዲፕሎማሲውና በፖለቲካው ዘርፍ የምንሠራቸውን ሥራዎች በአዳዲስ መንገዶች እያከናወንን መቀጠል ይገባል። ወጭ ቆጥበን፣ ጊዜና ጉልበት ጨምረን፣ ለሀገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መሥራት ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል።

በተለይ በተለይ በህልውና ዘመቻው ወቅት ያየነውን የኢትዮጵያውያንን አንድነት እስከ ዓለም ፍጻሜ ሀብታችን አድርገነው መቀጠል አለብን። በገጠርና በከተማ፣ በሀገር ቤትና በውጭ፣ በግንባርና በደጀን፣ ያለን ሁላችን ለአንድ ዓላማ ተሰልፈን አንድ ግብ እያሳካን ነው። ማንም ተነስቶ ኢትዮጵያን ማውረድ ከማይችልበት ማማ ላይ እየሰቀልናት ነው። ይህ አንድነታችን እንዲዘልቅ ከፋፋይ ሐሳቦችን እንመክት። የድል አጥቢያ አርበኞችን እንቃወም። በተጋድሏችን ያገኘነውን ነገር ለማቅለል የሚፈልጉትን ፊት እንንሣቸው። በጋራ ታግለን በጋራ ያስገኘነውን ድል፣ እንደ ቅርጫ ሥጋ ሊመድቡ የሚነሡትን አቃራጮች እናነውራቸው። ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ናት። ከዚህ የወረደ ነገር አንቀበልም።

የገጠመን ፈተና ብዙ መከራና ችግር ያስከተለብን ቢሆንም በምንም መንገድ የማናገኛቸውን ዕድሎችም ይዞልን መጥቷል። ከገጠመን ፈተና ይልቅ በዕድሎቻችን ላይ አተኩረን ከሠራን ኢትዮጵያን ኃያልና ራሷን በሁሉም መስክ የቻለች ሀገር እናደርጋታለን። ከፈጣሪ ቀጥሎ በፈተናችን ጊዜ አብረውን ለቆሙ እና በዓለም አደባባይ ለተማገቱልን ሁሉ ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ምስጋና ታቀርባለች። የጀመርነው ህልውናችንን የማስከበርና ኢትዮጵያን በጽኑ መሠረት ላይ የመትከል ተጋድሏችንን በፍጥነት አጠናቅቀን ወደ ብልጽግና አጀንዳችን በሙሉ ጉልበት በቅርቡ እንደምንመለስ እምነቴ ነው።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሕዳር 29፣ 2014 ዓ.ም
ሰበር ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጦር ግንባር የነበራቸውን የመጀመሪያውን ምእራፍ አጠናቅቀው ወደ ቢሮ መመለሳቸውን አስታወቁ
ኦላፍ ሾልስ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሆነው ዛሬ ተመረጡ።

የቀድሞው የሀምቡርግ ከተማ ከንቲባ የ63 ዓመቱ ኦላፍ ሾልስ በፖለቲካ አቋማቸው ሶሻል ዴሞክራት ሲሆኑ፤ በምርጫው ከፍተኛ ድምፅ ካገኙት ከአረንጓዴ ፓርቲ እና ከነጻ ዴሞክራቶች ፓርቲዎች ጋር በመቀናጀት ሀገራቸውን ለመምራት ተስማምተዋል።

ሾልስ ዛሬ በጀርመን ምክር ቤት በተካሄደው ምሥጢራዊ የድምፅ አሰጣጥ ሂደትም ከ707 አባላት የ395ቱን በማግኘት ኦላፍ ሾልስ አዲሱ የጀርመን መሪ ሆነው ተመርጠዋል።

እንዲያም ሆኖ የተጣማሪ ፓርቲዎቹን አባላት ሙሉ ድምፅ አላገኙም።

በምርጫው ሂደትም 303 አባላት ተቃውመዋል፤ ስድስት የምክር ቤት አባላት ደግሞ ድምፅ አልሰጡም። ከድምፅ አሰጣጡ ሥርዓት በኋላ ወደ ፕሬዝደንቱ መኖሪያ በመሄድ የሹመት ደብዳቤያቸውን ተቀብለዋል።

በዛሬው ዕለት ከጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በይፋ የመራኄ መንግሥትነት ሥልጣናቸውን የተቀበሉት ሾልስ ወደ ምክር ቤት በመሄድ ቃለመሃላ ፈጽመዋል።

በመቀጠልም የካቢኔ አባሎቻቸውን በማቅረብ አዲስ ሚኒስትሮቻቸውን በይፋ ሰይመዋል።

ላለፉት 16 ዓመታት የጀርመን መራኂተ መንግሥት የነበሩት አንጌላ ሜርክል የምክር ቤቱ አባል ባለመሆናቸው የአዲሱን መራኄ መንግሥት ምርጫ እና የቃለ መሃላ ሂደት ተመልካቾች በሚቀመጡበት ስፍራ በመሆን ተከታትለዋል።

ላለፉት በርካታ ዓመታት ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦም የአዲሱ ምክር ቤት አባላት ከመቀመጫቸው በመነሳት አክብሮታቸውን ለሜርክል ገልጸዋል።

ኦላፍ ሾልስ በይፋ የጀርመን መራኄ መንግሥት መሆናቸውን ተከትሎም ከተለያዩ ሃገራት የደስታ እና አብሮ ለመሥራት ፈቃደኝነት ያካተተ መልእክት እየተላከ ነው።

ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
1.3 ቢሊዮን ህዝብ ያላት አፍሪካ በተመድ የጸጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል - ጠ/ሚ ዐቢይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 1.3 ቢሊዮን ህዝብ ያላት አፍሪካ በተመድ የጸጥታው ም/ቤት ቋሚ ድምጽና ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚፈልጉ የአፍሪካ ሀገራትን መቀላቀላቸውን በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል፡፡

የአፍሪካን አህጉር የሚመለከቱ ሀሳቦችና ውሳኔዎች ያለ አህጉራዊ ውክልና ሊፈታ እንደማይችል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናረዋaል፡፡

ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
“ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቅድሚያ ሰጥታ እየሠራች ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ።

ዛሬ ከጅቡቲ፣ ከኬንያ፣ ከዩጋንዳ፣ ከሶማልያ፣ ከኤርትራ እና ከደቡብ ሱዳን መሪዎች ጋር ጥልቅ የስልክ ውይይት ማድርጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገልፀዋል።

በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም
ሰበር ዜና

በአሸባሪው ሕወሐት ተወርረው የነበሩት ቀሪ ከተሞች፣ የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በወሰዱት ማጥቃት ነጻ እየወጡ ነው።

ጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ባደረጉት ማጥቃት በደሴ ግንባር ሐይቅ፣ ቢስቲማ፣ ባሶሚሌ እና ውጫሌ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል። ሠራዊቱም ወደ መርሳ እየገሠገሠ ነው።

በተንታ ግንባር በተካሄደው ማጥቃት ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽሜዳ ከአሸባሪው የሕወሐት ወራሪ ነጻ ወጥተዋል።

በሁሉም ግንባሮች የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወደውስጥ ዘልቀው በመግባት የተበታተነውን አሸባሪ ኃይል ቀለበት ውስጥ አስገብተው በመደምሰስ ፣ ወራሪው ኃይል የዘረፈውን ንብረት እንዲሁም የያዘውን መሣሪያና ትጥቅ ይዞ እንዳይወጣ እያደረጉት ይገኛሉ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

 ሚኒስቴሩ በላከው መግለጫ፥ እንዳለው የዓለም አቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ጉድለት ያስከተለ መሆኑን አስታውቋል።

በተጨማሪም የአገር ውስጥ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከጎረቤት አገራት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እስከ አንድ መቶ ፐርሰንት በማደጉ እና ምርቱ ለከፍተኛ ኮንትሮባንድ የተጋለጠ በመሆኑ እንዲሁም አገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን መከለስ አስፈላጊ በመሆኑ አዲስ የመሸጫ ዋጋ ተዘጋጅቷል ብሏል።

በዚህም መሰረት ቤንዚን ላይ በተደረገ የዋጋ ማስተካከያ ባለፈው ወር ሲሸጥበት ከነበረው ዋጋ ጭማሪ በማድረግ በሊትር 31 ብር ከ74 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

 እንዲሁም ነጭ ናፍጣ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ ነጭ ጋዝ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ73 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ29 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ 58 ብር ከ77 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል በመግለጫው።

ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም
የጦር መሣሪያ ምዝገባው ለ15 ተከታታይ ቀናት እንዲቀጥል ተወሰነ

የጦር መሣሪያ ምዝገባው በሁሉም የሀገሪቱ የገጠርና የከተማ አካባቢዎች ከኅዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እንዲቀጥል ተየአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ውሳኔ አስተላልፏል ።

የኅብረተሰቡን የተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ከዚህ በፊት የወጣው ትእዛዝ የገጠር አካባቢዎችን ባለማካተቱ የተነሣ፣ የምዝገባውን ጊዜ ማራዘም እንደሚያስፈልግ ዕዙ አምኗል።

በመሆኑም በሁሉም የሀገሪቱ የገጠርና የከተማ አካባቢዎች ከኅዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጦር መሣሪያ ምዝገባው እንዲቀጥል ተወስኗል።

በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስ ጽ/ቤቶችም ይሄንን መመሪያ እንዲያስፈጽሙ ታዝዟል።

ይህ መመሪያ በጦር ግንባር የዘመቱና የሚታወቅ የጸጥታ ኃይል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላትን አይመለከትም ሲል የአስቸኳይ_ጊዜ_አዋጅ_ዕዝ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም
ጆ ባይደን ለጉብኝት በሄዱበት ካንሳስ ከተማ ከኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ገጠማቸው

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለጉብኝት በመጡበት ካንሳስ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ፕሬዚዳንት ባይደን ሚዙሪ ግዛት በምትገኘው ካንሳስ ከተማ ረቡዕ ከሰዓት የስራ ጉብኝት አካሂደዋል።

ተቃዋሚዎቹ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር በሚያካሂደው እንቅስቃሴ ቁጣቸውን እንዳሰሙ የዘገበው ኬኤምቢሲ “በኢትዮጵያ ላይ የሚካሄደውን የውክልና ጦርነት እና ጣልቃ ገብነት እኛ በቃ፣ በቃ እንላለን” ማለታቸውን አስነብቧል።

ተቃዋሚዎች “የጆ ባይድን አስተዳደር አሸባሪው ህወሃትን የመደገፍ እንቅስቃሴውን ሊያቆም ይገባል፣ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ለማጥፋት የሚያካሄደው ጣልቃ ገብነትም ሊቆብ ይገባል” ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም
ባለፉት ሶስት አመታት በስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የተከለከሉ መድሀኒቶች ተጠቅመው የተገኙ 16 አትሌቶች መታገዳቸው ተገለጸ፡፡

ከተቋቋመ ሶስት አመታት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት እስካሁን ድረስ የተቀመጡትን ህጎች ተላልፈው የተገኙ አትሌቶች ከውድድር ማገዱን አስታውቋል፡፡

የጽፈት ቤቱ ዋና ዳሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከውድድር የታገዱት አትሌቶች ከአራት አመት አንስቶ እስከ አስራ ስድስት አመት በየትኛውም ውድድር እንዳይሳተፉ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በውድድር እንዳይሳተፉ እግድ የተጣለባቸው አትሌቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚ የሚሆን ነውም ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችንና ሌሎች ተዛማጅ ቅመሞችን ከቦታ ቦታ ማዘዋወር ከአራት ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ የሚያስቀጣ ሲሆን አትሌቶች የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችንና መድኃኒቶችን እንዲጠቀሙ ማገዝ በተመሳሳይ ከአራት ዓመት ጀምሮ እስከ ዕድሜ ልክ ቅጣት እንደሚያስቀጣ ጽፈት ቤቱ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅህፈት ቤት በቀጣይም የምርመራና ቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና አካታች ሀገራዊ ምክክር አስፈላጊነት ላይ ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ኅዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የሀገርን ህልውና ለማጽናትና ዴሞክራሲን ለማጎልበት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ማሰቀመጡን የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገልፀዋል።

እንደ አቶ አደመ ፋራህ ገለፃ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታውን የገመገመ ሲሆን የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ በተደረገው ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት የተገኘውን ውጤት አድንቋል።

በዘመቻው አመርቂ ውጤት እንዲገኝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልል የጸጥታ ኃይሎች፣ ደጀኑ ሕዝብና በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ላደረጉት ርብርብና ከፍተኛ አስተዋጽዖ ኮሚቴው ምስጋና አቅርቧል።

ኅብረተሰቡ ያሳየው ርብርብና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ይበልጥ እንዲጎለብትና በቀጣይም ሌሎች ድሎች እንዲመዘገቡ በሚያደርግ ሁኔታ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሥራ አስፈጻሚው ጥሪ ማቅረቡን ኃላፊው ገልፀዋል።

እንደ አቶ አደም ፋራህ ገለፃ ከአሸባሪው ወራሪ ነጻ የወጡ አካባቢዎችን መልሶ ለማደራጀትና ለማቋቋም የተጀመረው ሥራ በመልካም ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው የገመገመ ሲሆን ሥራው በተቀናጀ አግባብ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አምኖበታል።

ለመልሶ ማቋቋምና ማደራጀት ሕዝቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ሥራ አስፈጻሚው ጥሪ ማቅረቡንም ነው ኃላፊው የገለፁት።

የፓርቲው አመራሮችና አባላትም ለተጀመረው የማደራጀትና መልሶ ማቋቋም እንቅስቃሴ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በመጨረሻም አቶ አደም ሥራ አስፈጻሚው በሀገራችን የተጀመረውን የፖለቲካ ሽግግር ሂደት ስለሚጠናከርበት ሁኔታም መምከሩን ገልፀዋል።

በዚሁ መሰረተ አካታችነትና ሁሉን አቀፍ ምክክር ከለውጡ መነሻ ጀምሮ ሲቀነቀን የነበረ ሐሳብ መሆኑ የታየ ሲሆን በሀገራችን አካታች ሀገራዊ ምክክር አስፈላጊ መሆኑን አምኖበታል ብለዋል።

አካታች ሀገራዊ ምክክሩም ሀገር በቀል የሆነ፣ በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚያግዝ፣ ከሕዝባችን ባህልና ዕሴት ጋር የሚጣጣም፣ የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በዘላቂነት ለማስከበር የሚረዳ መሆን እንዳለበት አጽንዖት ተሰጥቶታል ብለዋል።

የታሰበው ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካም በገለልተኛ የሆነ ብቃት ያለው ሀገራዊ ተቋም መመራት እንዳለበት ሥራ አስፈጻሚው አምኖበታል ብለዋል።

አካታች ምክክሩ እንዲሳካና የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣም ብልጽግና ፓርቲ እንደመሪ ፓርቲ የሚጠበቀበተን ኃላፊነት እንደሚወጣ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ማረጋገጡንም ኃላፊው አክለው ገልፀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን ማሻሻያ እንደሚደረግ ተገለፀ

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን ማሻሻይ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

የዓለም አቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናቱን በማጠናቀቅ ላይ ሲሆን፥ በቀጣይ ቀናት ይፋ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም የታሪፍ ማሻሻያው ተጠናቆ ይፋ እስኪሆን ድረስ ቀደም ሲል በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል፡፡

በከተማዋ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎችም የታሪፍ መጠኑ ይፋ ሳይሆን ምንም ዓይነት ዋጋ ባለመጨመር አገልግሎቱን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ታህሳስ 01 ቀን 2014 ዓ.ም
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

መንግስት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ይሁኝታ አግኝቶ ሲመረጥ ቃል ከገባባቸው አገራዊ ጉዳዮች መካከል ሁሉን አካታች የሆነ አገራዊ ምክክርና ውይይት በማካሄድ አገራዊ መግባባት እና በአገር ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲኖር የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት መሠረታዊ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች በተለያየ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ልሂቃንም ሆኑ ምልዓተ ህዝቡ ተቀራራቢና በአገራዊ አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ አካታች አገራዊ ምክክሩን ተግባራዊ ለማድረግ በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ቀርቧል።

ምክር ቤቱም በቀረበው የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ታህሳስ 01 ቀን 2014 ዓ.ም
ሰበር ዜና
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ዋናውን የወልድያ መቀሌ ጎዳና ቆርጦታል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመሩት የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በአሸባሪው ወራሪ ላይ በሰነዘሩት ክንደ ብርቱ ማጥቃት፣ በምሥራቅ ግንባር ስትራቴጂያዊ የሆኑትንና ወራሪው በፍጻሜ ዋዜማ ላይ መሆኑን የሚያሳዩትን የዞብል ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርጆ፣ ፎኪሳ እና ቦረን ከተሞችን ተቆጣጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን በመቆጣጠር የወልድያ መቀሌ ዋናውን አውራ ጎዳና በመቁረጥ ጠላት መውጫ አጥቶ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ግንባር የድሬ ሮቃና የሶዶማ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከተሞችና ተራሮች በመቆጣጠር ጥምር ጦሩ ወደ ሐራ ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል፡፡

በውጫሌ ግንባር ደግሞ የአምባሰል ከፍተኛ ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ የሮቢትና የጎልቦን፣ በወረባቦ ወረዳ የሚሌ ኮትቻን፣ በሐብሩ ወረዳ የኮልቦን፣ የመርካታና የፋጂን አካባቢዎችን በመቆጣጣር ወደ መርሳ ከተማ እየገሠገሠ ነው፡፡
በእነዚህ ግንባሮች በተደረገው ኦፐሬሽን በአሸባሪው የጠላት ኃይል ላይ በተሠነዘረበት ማጥቃት ጠላት ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆኗል፡፡
የወገን የመካናይዝድ ኃይልና ንሥሮቹ የአየር ኃይሉ በጥምረት ባካሄዱት ኦፐሬሽን የጠላት ኃይል ምንም ዓይነት ተሸከርካሪ እና ከባድ መሣሪያዎችን ይዞ እንዳይንቀሳቀስ ስላደረጉት፣ ጠላት በየአቅጣጫው ጥሎ ለመፈርጥጥ ተገድዷል፡፡

ነጻነታችንን የምናረጋግጠው በተባበረ ክንዳችን ነው!
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ታህሳስ 02 ቀን 2014 ዓ.ም