ኦሜጋ መጻሕፍት- Omega Books
351 subscribers
483 photos
9 videos
7 files
41 links
Download Telegram
ዛሬ በገበያ ላይ ይውላል! ለአከፋፋዮችና ለአንባቢዎች በሙሉ!!!

የሮሜ መልእክት ማብራሪያ - ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተረጎመው

በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከታላላቅ አስተማሪዎች አንዱ የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሮሜ መልእክትን የተጎረመው በመምህር ሽመልስ መርጊያ በአማርኛ ተተርጉመው ለእርስዎ ዝግጁ ሆነዋል!

ይህ መጽሐፍ የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ የሚያስችል ታላቅ ሥራ ነው። የቅዱሳን አባቶች ትምህርት በቀጥታ ከምንጩ ወደ እጅዎ ይመጣል።


#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!

💎 Telegram: https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ!

አሁን ይዘዙ!
“በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ኹሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን
የሌላው ብልቶች ነን።” (ቁ. ፬—፭)

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንዳደረገው እንደ እነርሱ በተመሳሳይ ደዌ ተይዘው የነበሩትን ለማዳን ሲል ተመሳሳይ ምሣሌን በዚህም ተጠቀመ። ይህን የትዕቢት ደዌ ለማከም ይህ መድኀኒት ታላቅ ሲሆን ምሣሌውም ብርቱ ነው። ለምን ራስህን እንዲህ ታስታብያለህ? ወይም ሌላው ሰው ስለምን ራሱን ፈጽሞ ያዋርዳል? ታላላቆችም ሆናችሁ ታናናሾች የአንድ አካል ሕዋሳት አይደላችሁምን? እንግዲህ ኹላችሁም አንድ አካልና እርስ በርሳችንም ሕዋሳት ከሆናችሁ፥ ስለምን በትዕቢት ራሳችሁን ከፍ ከፍ ታደርጋላችሁ? ወንድምህንስ ለምን ታሳፍረዋለህ? እርሱ ያንተ ሕዋስ እንደኾነ ኹሉ፥ አንተም የእርሱ ሕዋስ ነህና። አንድ አካል በመሆናችሁም ክብራችሁም አንድ ነው።

ሐዋርያው የእነርሱን የትዕቢት መንፈስ ሊያዋርዱ የሚችሉ ኹለት አመክንዮዎችን በዚህ ተጠቀመ፤ አንደኛው አንዱ ለአንዱ ሕዋስ መሆናቸውን በመግለጽ ሲሆን ይህም
ታናሹ የታላቁ ብቻ ሳይሆን፥ ታላቁም የታናሹ ሕዋስ መሆናቸው ሲሆን፤ ኹለተኛው ኹሉም በክርስቶስ አንድ አካል መሆናቸው ነው። ሦስተኛም አምክንዮ አለ፤ እርሱም የጸጋ ስጦታው ነው። ስለዚህ አትታበዩ። እነዚህን ከእግዚአብሔር የተሰጣችሁ እንጂ በምርጫቹህ ያገኛችኋቸው አይደለምና፤ ወይም ፈልጋችሁ ያገኛችኋቸው አይደሉም።
ስለዚህ ሐዋርያው ስለ ስጦታ ሲያነሣ አንዱ ይበልጥ ተቀበለ ሌላው ደግሞ ያነሰ አላለም፤ ምንድን ነው ታዲያ ያለው? “ልዩ ልዩ” አለ። ቃሉም፡- “እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤” (ሮሜ ፲፪፥፮) የሚል ነው እንጂ “ያነሰና የበለጠ” የሚል አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ በተመሳሳይ አገልግሎት ላይ የተሾምን ባንሆን እንኳ የምናገለግለው አንዱን አካል ነው።

ሐዋርያው በዚህ መልክ ትምህርቱን በጸጋ ስጦታዎች ጀምሮ በመልካም ሥራ ይፈጽማል። እርሱ ትንቢትን፥ አገልግሎትንና ሌሎችንም የጸጋ ስጦታዎች ካነሣ በኋላ፥ በምሕረት፥ በትጋትና በረድኤት ይደመድማል። አንዳንዶች ግን ቅዱሳን በመሆናችን የሚሰጡን ናቸው፤ ነገር ግን ትንቢት መናገር አይደለም፤ እንዲያም ኾኖ ይህ ከእግዚአብሔር ጸጋዎች አንዱ እንደኾነና ከሌሎች ጸጋዎች እንደሚበልጥ ገልጾልናል፤ (በቆሮንቶስ መልእክቱ ይህን አስፍሮልናል) ከእነዚህም አንዱ ዋጋን የሚያሰጠት ሲሆን ሌላኛው ግን ምንም ዓይነት ብድራት የሌለው ነው። በአጠቃላይ ግን ኹሉም የእግዚአብሔር የጸጋው ስጦታዎች ናቸው።

ድርሳን ሃያ አንድ
የሮሜ መልእክት ማብራሪያ - መምህር ሽመልስ መርጊያ እንደተረጎመው

መጽሐፉን 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ በሚገኘው ሱቃችን መውሰድ ይችላሉ። ኦሜጋ መጻሕፍት ነን!!!


#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!

💎 Telegram: https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ!

አሁን ይዘዙ!
3
መጽሐፉን 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ በሚገኘው ሱቃችን መውሰድ ይችላሉ። ኦሜጋ መጻሕፍት ነን!!!


#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!

💎 Telegram: https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ!

አሁን ይዘዙ!
ሥለ ምታገባው ሰው ጸልይ
ጸሎት ለተዘጉ ብዙ በሮች ሁሉ ቁልፍ ነው:: ካላንኳኳን የሚከፈትልን በር የለም:: ጋብቻ ወደ ተባለ ትልቅ ተቋም ከመግባትህ በፊት፣ ነገሮችን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ የሚሰራው ፈጣሪ ነውና:: መክ 3-11 ነገሮች በጊዜአቸው መልካም እንዲሆኑልህ በጉዳዩ ላይ ትኩረት በመስጠት መንገዱንም ይመራሃልና ደጋግመህ ጸልይ:: መልካም ሚስት በሒሳብ ስሌትና ቀመር አትገኝም::

“ረዳቱ ናትና ፅኑ መጠጊያውም ናትና ልባም ሴትን ያገባ ሰው ተድላ ደስታውን አገኘ” ሲራክ 36-29 ከምታውቃት በላይ፣ የምታፈቅራትን፣ ከምታፈቅራትም በላይ ዘርህን ተቀብላ ስለ ምታስቀጥልልህ አጋርህ፣ እስከ ሽምግልና ለምትቆዩት ውዷ ሚስትህ አብዝተህ ጸልይ::
ይህ ማለት “ከፊት ይልቅ ትጋ" ለማለት እንጂ፣ አንድ ክርስቲያን ይብዛም ይንስም ከጸሎት የተለየ ሕይወት ኖሮት አይደለም:: “ሳታቋርጡ ጸልዩ" እንዲል 1ተሰ 5-17 ጸሎት ከማግባትህ በፊትም፣ በኋለም ፈጣሪ ካንተ ጋርመሆኑን የምታረጋግጥበት፣ ተገዢነትህን የምትገልጽበት፣ ከእጁም በረከት የምታገኝበት የአምልኮህ መገለጫህ ነው::

ስለዚህ አንዳንዴ ሳይሆን ሁልጊዜ ጸልይ:: ምን ዓይነት ትዳር ውስጥ ገባው እያልክ ከማዘንህ በፊት ጸልይ:: በጸሎት ባሕርን ትሻገርበታለህ፣ ድቅድቁን ጨለማ ታቋርጥበታለህ፣ ከጠላትም ታመልጥበታለህና "ጋሻህ" ነው:: ልታገባትም ላታገባትም ትችላለህ፣ አብራችሁ ላትኖሩም፣ ልትወልዱም፣ ላትወልዱም ትችላላቹ:: ይቅርና ሀዘኑን ብቻ ሳይሆን ከአቅም በላይ የሆነን ደስታን መቋቋም የሚቻለው “በጸሎት" ነው::

ስትጸልይ ቅዱሱ መንፈስ ካንተ ጋር ይሆናል:: ይህ መንፈስ እንዳይወሰድብህ አብዝተህ ጸልይ:: ቅዱስ መንፈስ ያለበት ሰው ለሌላም ይተርፋል:: መንፈሱ አለኝ ተብሎም ተምታቶበት፣ትዳር እንዳይምታታም መጠንቀቅ ያስፈልጋል:: በገዛ ሚስትህ በጋብቻህ ውስጥ ለሚፈጠሩ ማንኛውም ጉዳይመፍትሔው እጅህ ላይ ነው:: ያ የሚሆነው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ሲረዳህ ነው:: ቅዱሱ መንፈስ ካልረዳን በቀርየሚረዳንና የሚረዳንን አጋር ማግኘት ይቸግረናል:: መዝ 50-11 የሚጸልዩ ስዎች በሚስቶቻቸው ላይአሲድ አይደፉም:: ያደላቸውማ በትር ቀርቶ የከፋ ቁጣ እንኳ የላቸውም:: ሁሌ በመነጋገር ያምናሉ:: ከዚህም በላይ ደግሞ የጋብቻን ዓላማ ስለሚገነዘቡ ለተጋቡለት ዓላማ ይኖራሉ:: አይሆንም እንጂ ባይሳካ እንኳን ሁሉን “ ለበጎ ነው “ እያሉ ያልፋሉ:: የጸሎት ጥቅሙም ለፈተናዎች ሁሉ መውጫ መንገድ መሆኑም ጭምር ነው:: የምናመልከው ጌታ አሳልፎ አይሰጠንምና::

የሚጸልዩ ሰዎች ከምድርም ያልፋሉ:: እይታቸው ይቀየራል ስማያዊ ነው:: አይደለም ለሚስት ለሌሎችም ይተርፋሉ:: በጸሎት መጽሐፍ እየጸለዩ ሚስታቸውን በፊክሽን መጽሐፍ አይፈቱም:: ለሚሻግት፣ ለሚቆሽሽ፣ ለእዳሪ ነገርበትንሽ ትልቁ አይጋጩም:: የሚጸልዩ መንፈሳቸው ይሰክናል:: ሊጣሉ፣ ሊደባደቡ፣ ሊሰዳደቡ፣ ሊተዛዘቡ፣ ቂም ሊያያዙ፣ ሊጨቃጨቁና፣ “ልሞክረው” በሚል ሊፋቱ አይጋቡም:: ምክንያቱ ለጸሎት የሚቆሙት ሁሉን በሚያውቅ አምላክ ፊት እንደሆነ ያውቃሉና፣ ምን ይዘው ይቆማሉ?
የሀገሬ ሰው “ባልና ሚስት ከአንድ ምንጭ ይቀዳሉ“ እንዲል የሚጸልዩ ሰዎች የሚስማማቸውን ያገባሉ:: ስትጸልይየምትጸልየዋን ታገኛለህ:: ምናልባት እርሷ ባትጸልይ ባንተ የተነሳ የተባረከቺው ትመጣለች:: ደግሞም ደክመህና ሰንፈህ ባትጸልይ እንኳ የምታበረታታህና የምትጸልይልህን አጋርታገኛለህ:: ጸሎት ለሚመጡ ልጆችም ይጠቅማል:: በትዳርሁሉ ነገር የሚሆነውም፣ የሚታለፈውም፣ “በጸሎት” ነው::

ሁሉ ብቻ በጸሎት ያገኘኸውን ሁሌም ስታከብረው ትኖራለህ:: አብሶ ሚስትህን ተባርካ ካገኘኻት ዘመዴ፣ ዘመንህ ይባረካል:: የተባረከቺውን አገባህ ማለት በደስታህ ሳይሆን በሀዘንህም ውስጥ በረከት ታያለህ:: ብዙ ሀዘኖችህን “እርሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት አልፈው ነበር" ያስብልሃል:: የእርሷ መባረክ ለልጆችህ፣ ለጤናህ፣ ለሥራህ ጠቅላላ ለማህበራዊ ኑሮህ ዋስትና ስለ አለው:: ቅድሚያ ሳይታክቱ መጸለይ::
ከዚህ አውነት ተነስተን፣ ከስኬቶችህ ጎን የእርሷ ድጋፍና ጸሎት ወሳኝ ስለሆነ ጋብቻህ የማትጸጸትበት ሊሆን እንዲገባ ቀድመህ ጸልይ:: ስለምታገባው ጸለይክ ማለት ስለ ሀገርም ስለ ምትወልደው ልጅም፤ ስለ ወደፊትህም እየጸለይክ ነው::
ከመጽሐፉ ገጽ 52 - 54 የተወሰደ

መጽሐፉን 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ በሚገኘው ሱቃችን መውሰድ ይችላሉ። ኦሜጋ መጻሕፍት ነን!!!


#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!

💎 Telegram: https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ!

አሁን ይዘዙ!
1
ርዕስ፦ ፍኖት መንፈሳዊት (The Way of Pilgrim)

አዘጋጅ ፦ ክብረ ሃይማኖት የትርጉም ክፍል
◄◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆►

ኒሴሮረስ ባሕታዊ

በልብህ ውስጥ ሰማያዊውን እሳት በሙቀት ልትረዳውና በውስጥህ ስላለችው መንግሥተ ሰማያት ከልምድ ልታውቅ ብትሻ፥ ስለ ሰማያዊ ሕይወት ኹኔታ ወይም ያለ ድካምና ላብ የሚተገብረውን ወደ ፍትወት አልባነት መሸሸጊያ የሚመራውን ጥበብ እነግርህ ዘንድ ወደእኔ ና።

አንድ ጊዜ በውድቀታችን ስለ ገባንበት አሁን ፍላጎታችንን በመተው ወደ ራሳችን እንመለስ። አስቀድመን ወደ ራሳችን ካልተመለስንና ወደ ጥልቀታችን ካልገባን ከእግዚአብሔር ጋራ መታረቅና ከእርሱ ጋራ መቀራረብ አንችልም፡፡

የውስጥ ሕይወት ብቸኛና እውነተኛ የክርስትና ሕይወት ነው። ለዚህም ሁሉም አባቶች ይመሰክራሉ።

በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ አጋቶንን፥ “ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው አፍኣዊ ሥራ ወይስ ልብን መጠበቅ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ እርሱም “ጠቢቡ ሰው ከዛፍ ጋራ ይመሳሰላል!” ሲል መለሰ፤ አፍኣዊ ሥራው ቅጠሎች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ፍራፍሬዎች ደግሞ የልብ ጥበቃ ናቸው፤ ስለዚህ በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት “መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ ወደ እሳት ይጣላል።” (ማቴ ፫፥፲)። ስለዚህ ትኩረታችሁን በፍሬው ላይ ልታተኩሩ እንደሚገባ ግልጽ ነው። ይህም የልብ ጥበቃ ነው።

እንዴትም ቢሆን የቅጠሎቹ ጌጣጌጥ ወይም አፍኣዊ ሥራ ያስፈልገናል። ይህን አስመልክቶ ዮሐንስ ዘሰዋስው ሲናገር፥ “ሰውነት ውስጥ ያሉ የሕዋሶችህን በሮች ዝጋ፤ የከንፈሮችን በር ለንግግር፤ የነፍስህንም የውስጥ በር ለርኲሳን መናፍስት ዝጋ። በከፍታ ተቀምጠህ ማለትም ትኩረትህን በልብህ ላይአድርገህ ቃኝ፤ ከተፈተንህ ብዙ ዐይነት ዘራፊዎች ይመጣሉ፤ ወደ ልብህ አትክልትም ገበተው ወይን ይሰርቃሉ። ጠባቂው ሲደክም ለመጸለይ ተነሣና እንደገና ተቀመጠ፤ ደግሞም በዐዲስ ድፍረት ወደ ልቡ በማተኮር ጸሎትን ይጀምራል።” ይላል።

ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ እንደሚያስተምረን በትሕርምት ውስጥ በጣም አስፈላጊው ሥራ ልብን ከክፉ ሐሳቡ ጠብቆ ከሰይጣን ጋራ መዋጋት ነው፡፡

ቅዱስ ይሥሐቅ ሶርያዊ (ማር ይሥሐቅ)፥ “ወደ ውስጥ ለመግባት ጥረት አድርግ፤ በዚያም ሰማያዊ ሀብትን ታያለህ። ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚያስገባው መሰላል በአንተ፣ በልብህ ውስጥ ተደብቋል። ከኀጢአትም ራስህን አንጻና ወደ ልብህ ግባ፤ እዚያም ወደ ከፍታዎች መውጣት የምትችልበት የመወጣጫ ደረጃዎችን ታገኛለህ።” ይላል።

ዮሐንስ ዘቃርፋጦስም፥ “የአእምሮና የሐሳብ ሰላማዊ ኑሮን ለማግኘት በጸሎት ብዙ መድከምና መጣር ያስፈልጋል፤ ይህም ክርስቶስ የሚኖርባትን የልብ መንግሥተ ሰማያትን ለማግኘት ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው፥ “ኢየሱስ፡ ክርስቶስ: በእናዓተ፡ ውስጥ፡ እንዳዕ፡ አታስተውሉምን?” (፪ቆሮ. ፲፫፥፭)።” ......

ከመጽሐፉ ገጽ 240 - 241 የተወሰደ

መጽሐፉን 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ በሚገኘው ሱቃችን መውሰድ ይችላሉ። ኦሜጋ መጻሕፍት ነን!!!


#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!

💎 Telegram: https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ!

አሁን ይዘዙ!
2
ርዕስ፦ ዝርዝር ግሶች በመዝሙረ ዳዊት

አዘጋጅ ፦ ግዛቸው ደጀኑ መኰንን - የግእዝ ቋንቋ መምህር
◄◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆►

መጽሐፉን 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ በሚገኘው ሱቃችን መውሰድ ይችላሉ። ኦሜጋ መጻሕፍት ነን!!!


#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!

💎 Telegram: https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ!

አሁን ይዘዙ!