ኦሜጋ መጻሕፍት- Omega Books
351 subscribers
486 photos
9 videos
7 files
42 links
Download Telegram
ርዕስ፦ ብርህይት ዐይን
አዘጋጅ፦ ዲያቆን ኅሊና በለጠ
የገጽ ብዛት፦ ከ298 ገጾች በላይ

👉 የምናየው ዓለም እና የማይታየው መንፈሳዊ ምስጢር እንዴት ይገናኛሉ? ለዚህ ጥያቄ ጥልቅ ምላሽ የሚሰጠውና በመንፈሳዊ እውቀት የሚያጠግባው „ብርሃነ ዓይን“ የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ አሁን በገበያ ላይ ይገኛል።

🤲 ይህ መጽሐፍ በውስጡ በዋና ዋና ምዕራፎች የተከፋፈሉ፣ ለሕይወታችን እጅግ አስፈላጊ የሆኑ አበይት ጉዳዮችን አካቷል፦

✍️ መግቢያ እና የትርጓሜ ሥራ፦ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት አቀራረብ፣ ስለ ሕይወት እና ስርአት ጥልቅ ግንዛቤ ይሰጣል።

✍️ የምስጢራት መግለጫ፦ የብርሃነ ዓይን ምንነት፣ የመጀመርያው ምስል፣ የሥርዓተ አምልኮ መገለጫዎች እና የንዋያተ ቅድሳት ምስጢር።

✍️ የክህነት እና የጥንታውያን ልብሶች (Primordial Robe)፦ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የልብሶች እና የሥርዓቶች መሠረት።

✍️ ምስጢረ ሥጋዌ እና ነገረ ቅዱሳን፦ ሥጋዌ እና ምስጢረ ኤጲክሌሲስ (Incarnation and Epiclesis) እንዲሁም የቅዱሳን አባቶች መንፈሳዊ ትውፊት።

ይህ መጽሐፍ ለአንባቢያን አዳዲስ መንፈሳዊ እይታዎችን የሚከፍት፣ ለጥናቶችም እንደ ዋቢ መጽሐፍ የሚያገለግል ብስል ሥራ ነው።

#ይዘዙን_እናቀርባለን!!!!!!!!
ኦሜጋ መጻሕፍት - Omega Books
💎 telegram : https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia.
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ
የመጽሐፉ ርዕስ፦ ቅድመ መተጫጨት
ተርጓሚ፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
የገጽ ብዛት፦ ከ 260 በላይ ገጾች

ትዳር የሕይወት ትልቅ ውሳኔ ነው። ነገር ግን ወደ ትዳር ከመገባቱ በፊት ያለው „የመጠበቅ እና የመጠናናት“ ጊዜ እንዴት ማለፍ እንዳለበት ብዙዎቻችን እንቸገራለን። ለዚህ ይረዳ ዘንድ በኦሜጋ መጻሕፍት ቤት የታተመው „ቅድመ መተጫጨት“ የተሰኘው መጽሐፍ መፍትሔ ይዞልን መጥቷል።

ይህ መጽሐፍ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች የተዘጋጀ ጥልቅ መመሪያ ነው፦

👉 ክፍል 1፡ ድንግልና ወይስ ትዳር? ስለ ነጠላነት በረከት፣ የብቸኝነትን ጊዜ ትርጉም ባለው መልኩ ስለመጠቀም እና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለመጠበቅ በስፋት ይተነትናል።

👉 ክፍል 2፡ ለመተጫጨት መዘጋጀት፦ ከእግዚአብሔር፣ ከራሳችንና ከሰዎች ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ጤናማ ግንኙነት፤ እንዲሁም ስለ ፍቅር፣ እምነትና በስሜት ስለመገፋፋት ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ያርማል።

👉 ክፍል 3፡ መተጫጨት፤ መጠናናት እና ዕቅድ ማውጣት፦ ክርስቲያናዊ መጠናናት እንዴት ይጀምራል? የአምልኮ እና የተግባቦት ሚና ምንድነው? ንጽሕናን ጠብቆ እስከ ጋብቻ ለመድረስ ምን መደረግ አለበት? የሚሉትን ምስጢራት ደረጃ በደረጃ ያሳያል።


👉 የመጽሐፍ መደርደሪያዎ ላይ ሊኖር የሚገባ ድንቅ መጽሐፍ!

ኦሜጋ መጻሕፍት - Omega Books
💎 telegram : https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia.
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ!
1
ርዕስ፦ መሠረታዊ የግእዝ ቋንቋ መማሪያ
አዘጋጅ፦ መምህር በትረማርያም አበባው
የታተመበት ዘመን፦ 2015 ዓ.ም.
አከፋፋይ ፦ ኦሜጋ መጻሕፍት
የገጽ ብዛት፦ ከ 373 ገጾች በላይ

👉 ግእዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ማዕድና የቅዱሳት መጻሕፍት መዛግብት የተከፈቱበት ታላቅ ልሳን ብቻ አይደለም፤ የሀገራችን ታሪክ፣ ስልጣኔ፣ ፍልስፍና እና ጥልቅ እውቀቶች የተቀመጡበት የጥበብ ምንጭም ጭምር ነው።

👉 ዜማው፣ ቅኔው የሚቀነቀንበት፣ ማኅሌቱ የሚቆምበት፣ በዋናነት ቅዱሳት መጻሕፍት የሚተረጎሙበት በግእዝ ቋንቋ ስለሆነ፤ ቅዳሴ ሲቀደስ፣ ዜማ ሲዜም፣ ማኅሌት ሲቆም የዜማውን ሥርዓት ብቻ ሳይሆን ሥርዓተ አምልኮውን በእውቀት የተመሠረተ ለማድረግ የግእዝ ቋንቋን ማወቅና መረዳት ይጠበቅበታል።

👉 ይህን ታላቅ ቋንቋ ከፊደላት መነሻ ጀምሮ እስከ ጥልቅ ሰዋስው ድረስ በቀላሉ መማርና ማወቅ እንዲችሉ የሚያግዝ "#መሠረታዊ_የግእዝ_ቋንቋ_መማሪያ" የተሰኘው ድንቅ መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል!

📖 መጽሐፉ በውስጡ የያዛቸው ዋና ዋና የትምህርት ይዘቶች፦

ምዕራፍ 1 - 4፦ የግእዝ ፊደላት፣ ቁጥሮች፣ ሥርዓተ ንባብ እና የባለቤትና አመለካከት ቅጽሎች።

ምዕራፍ 5 - 7፦ የግስ አወቃቀር፣ ዝርዝር የግስ እርባታእና በጥልቀት የተተነተኑ የአንቀጽ አወጣጥ ሥርዓቶች ከነሙሉ ዝርዝሩ።

ምዕራፍ 8፦ የቅጽል ዓይነቶች (ሣልስ፣ ሳድስ፣ ባዕድ ቅጽሎች) እና አጠቃቀማቸው።

ምዕራፍ 9፦ ሰፊ የግዕዝ ስሞች ዝርዝር (የእፀዋት፣ የእንስሳት፣ የአራዊት፣ የአዕዋፋት፣ በውኃ የሚኖሩና በልባቸው የሚሳቡ፣ ሌሎች ጥቃቅን ፍጥረታት፣ ዝምድና ተኮር ስሞች፣ የቤት ዕቃዎች፣ የምግብ እና የሰውና የእንስሳት አካል ክፍሎች በግእዝና በአማርኛ ትርጉም)።

ምዕራፍ 10 - 11፦ የዓረፍተ ነገር ማያያዣዎች (ዐቢይ፣ ደቂቅ እና ንዑስ አገባቦች) እንዲሁም ነጠላ ግሶች ከ "ሀ" እስከ "ፐ"

#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!
ኦሜጋ መጻሕፍት - Omega Books
💎 telegram : https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia.
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ
🐑 "እረኛ ወይስ ምንደኛ?“ — በአገልግሎት መስመር ላይ ያሉ ሁሉ ሊያነቡት የሚገባ ታላቅ መጽሐፍ! 🐑

ርዕስ፦ እረኛ ወይስ ምንደኛ
አዘጋጅ፦ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ
አከፋፋይ ፦ ኦሜጋ መጻሕፍት
የገጽ ብዛት፦ ከ 100 ገጾች በላይ

"እውነተኛው እረኛ ማነው? ምንደኛውስ?“ በአሁኑ ዘመን በአገልግሎት ውስጥ የሚታዩትን እውነተኛ እረኝነትና ጥቅምን ብቻ ማሳደድን በግልጽና በስዉር የሚለየው ምንድነው?

በዕውቀታቸውና በምርምራቸው ለሚታወቁት ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ የተዘጋጀውና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው „እረኛ ወይስ ምንደኛ?“ (፩ኛ ዕትም) መጽሐፍ አሁን በገበያ ላይ ውሏል!

ይህ መጽሐፍ በመንፈሳዊ አገልግሎት፣ በቤተሰብ መሪነት እንዲሁም በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ያሉ መሪዎችና አገልጋዮች ራሳቸውን እንዲፈትሹ የሚያደርግ እጅግ ጥልቅ መመሪያ ነው።

📖 መጽሐፉ በውስጡ የያዛቸው አበይት ርዕሰ-ጉዳዮች፦

ክፍል አንድ፦ አበው እረኞች ማን ናቸው?

* የአበው መግለጫዎች፣ ስለ ትሕትናቸውና ስለ እውነተኛ እረኝነታቸው።

* ከዓውደ ምሕረት ውጭ መስበክ፣ መምህራንን የመለየት ዕውቀት እና የታዛዥነት በረከት።

ክፍል ሁለት፦ በጥንቱ ዘመን የነበሩ እረኞችና ሁኔታቸው

* በአቤል፣ በቃየን፣ በኖኅ እና በሌሎችም አባቶች ሕይወት የተገለጠው የእረኝነት ምሳሌ።

* ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኙባቸው ሦስት መንገዶች (ቃል በቃል፣ በሕልምና በራዕይ)።

ክፍል ሦስት እና አራት፦ የፍኖተ አበው ባህርያትና ማንነት

* አበው እግዚአብሔርን በቅንነት ለመታዘዝ የሄዱባቸው መንገዶች (ስደት፣ መራቆት እና ረሃብ)።

* "አበው ማንን ይመስላሉ?“ በሚል ርዕስ ራስን ከገንዘብ ወዳድነት፣ ከቃላት ስርቆትና ከጊዜ ሌባነት ስለመጠበቅ የተጻፉ እውነታዎች።

ክፍል አምስት እና ስድስት፦ በአገልግሎት ጉዞ ውስጥ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች

* በበረከት መሻት፣ በመስቀል አጠገብ መቆም እና ሐሳባችን ሰማያዊ እንዲሆን ስለማድረግ።

* የአበው እውነተኛ ባህርያት (የዋህነት፣ ታማኝነት፣ ቅንነትና ራስን አለማስቀደም)።

#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!
ኦሜጋ መጻሕፍት - Omega Books
💎 telegram : https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia.
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ
ርዕስ፦ ትወደኛለህን ?
አዘጋጅ፦ ቀሲስ ተአምራት ዉቤ
የታተመበት ዘመን፦ 2018 ዓ.ም.
የገጽ ብዛት፦ ከ 209 ገጾች በላይ

🔥 „ትወደኛለህን?“ — ከክርስቶስ የቀረበልህ የሕይወትህ ትልቁ ጥያቄ! 🔥

"ጌታ ሆይ፤ ካንተ ይልቅ የምወደው... ከቀን ውሎዬ ይልቅ የማስቀድመው... በውስጤ የነገሠ ሌላ ማን አለ?“

ይህንን ጥያቄ ጌታችን ለቅዱስ ጴጥሮስ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ለእያንዳንዳችን ይጠይቀናል። ጌታን እውነት እንወደዋለን? ወይስ ስማችን ብቻ ክርስቲያን ተብሎ በስመ-ክርስቲያንነት እየኖርን ነው?

በቀሲስ ታምራት ውቤ የተዘጋጀውና በብዙዎች ሕይወት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረው #ትወደኛለህን? የተሰኘው መጽሐፍ በጉጉት በሚጠባበቁት አንባቢያን ጥያቄ መሠረት በ3ኛ ዕትም በድጋሚ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል!

ይህ መጽሐፍ የራስህን ክርስትና ከመሠረቱ እንድትመረምርና ከጌታህ ጋር እውነተኛውን የፍቅር ቃል-ኪዳን እንድታድስ የሚያደርግህ ድንቅ የንስሐ መነሻ ነው።

📖 በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱ አስገራሚና ልብ የሚነኩ ርዕሶች በጥቂቱ፦

ኖላዊና እረኛ፦ ጌታችን እረኛችን ሆኖ ሳለ እኛ የበረቱ በጎች ነን?

#ትወደኛለህን?፦ የፍቅር ጥያቄና መልሱ።

እሰረኞቹ እና መሣሪያው፦ በሕይወትህ ውስጥ ጌታን እንዳታገለግል ያሰሩህ ሰንሰለቶች እና መፍቻዎቻቸው።

"At least“ ክርስትና፦ በታይታና በይመስልኝነት ውስጥ የምትኖርበትን „ለስሙ ክርስቲያን“ የመሆንን ሰነፍ አካሄድ ያጋልጣል።

ከገሃነም እንዴት እመልጣለሁ?፦ የዘለአለም ሕይወትን ለማግኘትና ከፍርድ ለመዳን የሚጠቅሙ የቅዱሳን አባቶች ምክሮች።

"ነገ እንደ ዛሬው ወደ አንተ እመጣለሁና ተዘጋጅ!“፦ ሞትና የጌታን ዳግም ምጽአት የመጠበቅ ዝግጁነት።

ሚጡት እና ቀይ እረኛ፦ ለመንፈሳዊ ዕድገት መነቃቃትን የሚፈጥሩ ምሳሌያዊና እውነተኛ አስተማሪ ታሪኮች።

#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!
ኦሜጋ መጻሕፍት - Omega Books
💎 telegram : https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia.
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ
3
ርዕስ፦ ኢትዮጵያዊው ሱራፊ
አዘጋጅ፦ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
የታተመበት ዘመን፦ 2011 ዓ.ም.
የገጽ ብዛት፦ ከ 1082 ገጾች በላይ

✍️ ስለ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ምን ያህል ያውቃሉ? ገድላቸውስ በስንት ዓይነት መንገድና መቼ ተጻፈ? የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንና መንግሥት ታሪክ ከአባታችን ተጋድሎ ጋር እንዴት ይያያዛል?

✍️ እነዚህንና ሌሎችንም እጅግ ጥልቅ የሆኑ ታሪካዊና መንፈሳዊ እውነታዎችን በማስረጃ አስደግፎ የያዘውና ለንባብ የበቃው ታላቁ „ኢትዮጵያዊው ሱራፌል“ መጽሐፍ አሁን በገበያ ላይ ውሏል!

✍️ ይህ መጽሐፍ ከተራ ታሪክ ትረካ ባለፈ፣ ከ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩ የብራና መጻሕፍትን፣ የታሪክ ድርሳናትን፣ የተለያዩ ነገሥታት የዜና መዋዕሎችንና የውጭ አገር ጸሐፊዎችን ምስክርነት በማመሳከር የተዘጋጀ እውነተኛ የምርምርና የበረከት ሥራ ነው።

📖 በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱ ዋና ዋና የጥናት ክፍሎችና ርዕሶች በጥቂቱ፦

🏅 ክፍል አንድ፦ ማስረጃ እና ታሪካዊ ዐውድ

* ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚነሱ ልዩ ልዩ ሐሳቦች (የአልመይዳ፣ የኪዳነ ወልደ ክፍሌ እና የዛሬዎቹ ሊቃውንት ትንተናዎች)።

* የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት መመለስና የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የማይተካ ሚና።

* የገድላት ታሪክ በአገራችን፦ የገድል ትርጉም፣ ዓይነቶችና ከ25 በላይ የተለያዩ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድላት የብራና ቅጂዎች ዝርዝር ጥናት (የአፄ ዮሐንስ፣ የደብረ ሊባኖስ፣ የኢየሩሳሌም፣ ወዘተ)።

* በአራቱ ወንጌላት አጻጻፍ ስልት የተዘጋጁት ልዩ ልዩ የስንክሳርና የድርሳናት ታሪኮች።

* ልዩ ልዩ የታሪክ ጸሐፊዎች ምስክርነት (የአውሮፓውያን፣ የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን መረጃዎችና ጥንታውያን ሥዕላት)።

🏅 ክፍል ሁለት፦ የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማንነትና ሕይወት

* ከጽንሰታቸውና ከልደታቸው ጀምሮ እስከ ዕረፍታቸው ድረስ ያለው ሙሉ መንፈሳዊ ጉዞ።

* ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ያደረጉት መንፈሳዊ ጉዞ፣ በሐይቅ እስጢፋኖስና በደብረ ዳሞ የነበራቸው የምንኩስና ሥርዓትና ሕይወት።

* ወደ ደብረ አስቦ (ደብረ ሊባኖስ) መመለስና የጸሎት ተጋድሎአቸው (በአንድ እግራቸው መቆማቸውና የክንፍ መበቀል ምስጢር)።

* የታምራት መጽሐፍ ምስክርነቶች።

🏅 ክፍል ሦስት፦ ተክለ ሃይማኖታውያን ከጥንት እስከ ዛሬ

* የደብረ ሊባኖስ እጨጌዎች ታሪክ፣ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ሥርዓት፣ ዜማና የቅኔ ምስጢር።

* የነገሥታትና የቤተ ክህነት ግንኙነት ከአባታችን ዘመን በኋላ የነበረው ታሪካዊ ገጽታ።

🏅 ክፍል አራት፦ አባሪ ታሪኮችና ጥንታውያን ዋቢ መጻሕፍት

አባታችንን የሚመለከቱ የብራና፣ የዕደ-ክንውን (Manuscript) መረጃዎች እና የኢትዮጵያ ታሪክ ሰነዶች ስብስብ።


#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!
ኦሜጋ መጻሕፍት - Omega Books
💎 telegram : https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia.
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ
3
ርዕስ፦ ዳዊት፤ ከእረኝነት እስከ ንግሥና
አዘጋጅ፦ ዲያቆን ኤልያስ ደፋልኝ
የታተመበት ዘመን፦ 2015 ዓ.ም.
የገጽ ብዛት፦ ከ 335 ገጾች በላይ

👑 እግዚአብሔር ሰውን እንደ ውጫዊ መልኩ ሳይሆን ልቡን ያያል...👑

📖 በወንድሞቹ ዘንድ ተንቆ በገደልና በበረሃ በጎችን ይጠብቅ የነበረው እረኛ፣ እንዴት በሳሙኤል እጅ ተቀብቶ የእስራኤል ታላቅ ንጉሥ ሊሆን ቻለ? ከጎልያድ ፊት ከመቆም ጀምሮ በሳኦል የቅናት ሰይፍ እስከ መሰደድ፣ ከታላላቅ ድሎች እስከ ከባዱ የንስሐ ሕይወት ድረስ ዳዊት ያለፈበት መንገድ ምን ያስተምረናል?

📖 ከመጽሐፉ ሰፊ የትምህርት ማዕድ በጥቂቱ፦

🔥 ምዕራፍ አንድና ሁለት፦ የቅዱስ ዳዊት ቀደሞ ሕይወት
👉 የዳዊት የልጅነት አደረጃጀትና ቤተሰባዊ ዐውድ።
👉 በነቢዩ ሳሙኤል እጅ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀባቱ።
👉 የጎልያድ መውደቅና የእስራኤል ነፃ መውጣት ታሪካዊና መንፈሳዊ ምስጢር።

🔥 ምዕራፍ ሦስት፦ የስደትና የፈተና ዘመን
👉 በሳኦል ዘንድ የነበረው የምቀኝነትና የቅናት ጦርነት።
👉 የዳዊት ስደት፣ በምድረ በዳ ያደረጋቸው ተጋድሎዎችና የፈተና ጊዜያት።

🔥 ምዕራፍ አራት፦ የንግሥና እና የክብር ዘመን
👉 ዳዊት በኬብሮንና በኢየሩሳሌም በሙሉ እስራኤል ላይ መንገሡ።
👉 የታቦተ ሕጉ ወደ ኢየሩሳሌም መምጣትና የዳዊት ታላቅ ሐሴት።
👉 ፈተናዎችና ጦርነቶች፦ ከአሴር፣ ከአሞን፣ ከፍልስጥኤማውያንና ከታላላቅ ነገሥታት ጋር የተደረጉ ጦርነቶችና የተገኙ ታላላቅ ድሎች።
👉 የቤተሰብ ፈተና፣ የአቤሴሎም ማመፅና የዳዊት ልብ የሚነካ ሐዘን።

🔥 ምዕራፍ አምስት፦ የመጨረሻው ዘመንና መንፈሳዊ ቅርስ
👉 የዳዊት እርጅና፣ የአዶንያስና የሰሎሞን የንግሥና ሽኩቻ ምስጢር።
👉 የዳዊት የመጨረሻ ኑዛዜ፣ መዝሙራቱና ትንቢታዊ መልእክቶቹ።

📖 የዳዊት መዝሙር በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቶች እና የአምልኮት ሥርዓታችን ውስጥ በሚከናወኑ የአምልኮ ሥነ ሥርዓቶች በቅዳሴው፣ በሰዓታቱ፣ በማኅሌቱ፣ በተክሊል ጸሎት እንዲሁም በጸሎተ ፍትሐቱ ሰፊውን ቦታ ይይዛል።

📖 በአጠቃላይ መጽሐፉ ንጉሥ ዳዊት በንግሥና ዘመኑ ያገኛቸውን ድሎች ፤ መውደቁ ፤ መነሳቱ ፤ በእግዚአብሔር መታመኑ ፤ መቶ ሃምሳውን መዝሙራትን የዘመረባቸው የሕይወቱ ምዕራፎች በዝርዝር ያቀርባል።


#ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!
ኦሜጋ መጻሕፍት - Omega Books
💎 telegram : https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia.
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ
1
አዲስ የመጽሐፍ ግብዣ በኦሜጋ መጻሕፍት!

📖 “ፈላስፋው ሰማዕት ቅዱስ ዮስጢኖስ — ሕይወቱና ሥራዎቹ”
በዲያቆን መስፍን ተከሥተ የተዘጋጀ
[፻-፻፷፭ / 100-165 ዓ.ም.]

በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የነበረውን የታላቁ አባት፣ ፈላስፋና ሰማዕት የቅዱስ ዮስጢኖስን መንፈሳዊ ሕይወት፣ የፍልስፍና ጉዞ፣ ነገረ-መለኮታዊ ድርሳናት እና ለክርስቲያናዊ እውነት ያደረገውን ተጋድሎ በጥልቀት የሚያብራራ ድንቅ መጽሐፍ አሁን በእጃችን ይገኛል!

📌 ለመንፈሳዊ እና ታሪካዊ እውቀቶት የሚጨምረው፦

✝️ የቅዱስ ዮስጢኖስ ከፈላስፋነት ወደ ክርስቲያናዊ እውነት ያደረገው መንፈሳዊ ሽግግር

📜 በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው የቤተ ክርስቲያን ተጋድሎና የሃይማኖት መከላከያ (Apologetics)

📚 ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች እና በቅዱሳን አበው ታሪክ ላይ ማጥናት ለሚፈልጉ ሁሉ ተመራጭ መጽሐፍ

🚚 #ይዘዙን_ያሉበት_ድረስ_እናደርሳለን!!!!!!!!

📍 አድራሻችን፦ 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል። (አዲስ አበባ)

📞 ስልክ ቁጥር፦ 0941555550

✈️ ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiofagos
🔥1