ኦሜጋ መጻሕፍት- Omega Books
353 subscribers
486 photos
9 videos
7 files
42 links
Download Telegram
ኦርቶዶክሳዊ ተዋስኦ በዋናነት ሰባት የመረዳት መሠረቶችን የያዘ የሕይወት ሀሳብ ነው።
(©መምህር ገብረመድኅን እንየው)

እነዚህም የተዋስኦ መሠረቶች፦ምሉዕ ንባብ፣ርቱዕ ትርጉም፣ቅብብሎሻዊ አረዳድ፣ኅብረትታዊነት፣ክሡት ምሥጢር፣የሕይወት ምሥክርነት እና ዘለዓለማዊ ተስፋ ናቸው።የቅዱሳት መጻሕፍት ተዋስኦዋዊ አረዳድ ከእነዚህ ጉዳዮች የወጣ ወይም የተለየ አይደለም።በእነዚህ ጥልቅ የተዋስኦ መሠረቶች ሦስት ሚዛኖች ተጠብቀው ይኖራሉ።
አንደኛው፦እግዚአብሔር ወደ ሰው ልጆች ያዘነበለባቸው የሕግ፣የመንፈሰ ረድኤት፣የኩረነት እና የቸርነት መገለጫ መንገዶቹ መታጎል ሳይኖርባቸው በርቱዓዊነት ተጠብቀውና ማደሪያ አግኝተው በሥራ መገለጽ አለባቸው።እንዲሁም ክቡሩ ፍጥረት ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚሄድባቸው፦የሕግ፣የአምልኮት፣የመገዛት፣የተስፋ፣የኅብረት፣የቅብብሎሽ መንገዶቹ በርቱዓዊነት ተጠብቀው መቀጠል መቻል አለባቸው።
ሁለተኛው ሰው ከሰው ጋራ ሊያደርጋቸው የሚገቡ አምላካዊ ፍጽምናዎች ናቸው።ሕገ እግዚአብሔር እና ሕገ ተፈጥሮ የሚገለጠው አንዱ ለአንዱ በሚያደርገው የቸርነት ግብር ነውና የተዋሥኦ አረዳዶቻችን የተፈጥሮና የሕግ ሚዛናቸውን እንደጠበቁ ለመኖር ህሊናን ማቅናት ልቡናን ማስፋት አለባቸው።
ሦስተኛው ከሰማይ በታይ ከምድር በላይ እንዲመግብ የተሾመው የሰው ልጅና መላው ሥነ-ፍጥረት የተፈጠሉለት የተፈጥሮ ሚዛናቸው እንዳለ ሳይቃወስ ወደ ትውልድ እየተላለፈ መኖር አለበት።
በዚህ ሁሉ የኑሮ ውጣውረድ ሂደት ውስጥ ደግሞ ተዋሥኦዋችን በተስፋ የሚጠበቀውን የመዳንን መንገድን ወደ ፍጽምና ሕይወት ማድረስ መቻል ነው።በመምህር በትረ ማርያም አበባው የተዘጋጀው መጽሐፍም ይሄንን ሚዛን ለመጠበቅ የተደረገ የተዋሥኦ ዕቅበት ነው።ከባለቤቱ የተገለጠውን፣በኦርቶዶክሳዊት ጉባኤ የተቀበልነውን፣የምንጠብቀውና ለትውልድ የምንሰጠውን ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ለመጠበቅ የተጻፈ ተዋሥኦ የህሊና ማረፊያ የልቡና መደገፊያ ነው።ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን አረዳድና ኅብረት ሊነጥል ከሚችል ማንኛውም ነገር፦አረዳድ፣ጥያቄ፣ኑፋቄ፣ፈቃደ ሥጋ፣ፈቃደ ሰይጣን፣ፍልስፍና፣ደርጅት፣ርዕዮተ ዓለም ጋር እንደ አመጣጡ ለመመለስ የሚደረግ ተዋሥኦ የወንጌላዊነት መገለጫ ነው።
ከዚህ ቀደም በርካታ መጻሕፍትን አዘጋጅተው ባስነበቡን በመምህር በትረ ማርያም አበባው የተዘጋጀልን ይሄ መጽሐፍም ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮን ለመጠበቅ የተደረገ ተዋሥኦ ነውና አንብበን ለወንጌላዊ ኑሮ እና ለድኅነት ጉዞ እንድንጠቀምበት እግዚአብሔር ይርዳን።

©መምህር ገብረመድኅን እንየው
1
በብዙ ድካም የኅትመት ብርሃን እንዲያይ የተደረገው ይህ የታሪክ ሰነድ እጅዎ ገብቶ ይሆን!?
ከማለቁ በፊት እጅዎ ያስገቡ!!
#OmegaBooks
0941555550