ኦሜጋ መጻሕፍት- Omega Books
354 subscribers
486 photos
9 videos
7 files
42 links
Download Telegram
The church of Ethiopia

0941555550
የተክለ ጻድቅ መኩሪያ
#ሦስተኛ_እትም
በአንባብያን ዘንድ እጅግ የተወደደው #ኦርቶዶክሳዊ_ተዋሥኦ ሦስተኛ እትም ታትሞ ዛሬ ወጥቷል።መጽሐፉን ስትፈልጉ የነበራችሁ በ 0941555550 በመደወል ማግኜት ትችላላችሁ።
Forwarded from Omega Books
የማምሻ ዕድሜ ወግ
መርሐ ቤቴ በታሪክ፣ትዝታዎቸና ገጠመኞች
ይህን ድንቅ መጽሐፍ ሳያልቅብዎ የራስዎ ያድርጉ

ኦሜጋ መጽሐፍ መደብር ያገኙታል

0941555550
ትምህርተ ጽድቅን በመደብራችን ያገኙታል።
0941555550
በመምህር በትረ ማርያም አበባው የተዘጋጀው "ኦርቶዶክሳዊ ተዋሥኦ ቅጽ 2 ከነገ ጀምሮ ወደ መጽሐፍ መደብሮች ይሰራጫል።

ስልክ 0941555550 ወይም 0911456866
አዲስ መጽሐፍ እነሆ
(መጻሕፍተ ሊቃውንት ላይና መጻሕፍተ መነኰሳት ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው በእግዚአብሔር ቸርነት ታተመ)

መጽሐፉ ከነገ ማለትም ከየካቲት 21 ጀምሮ በሚከተለው አድራሻ ይከፋፈላል።

የመጽሐፉ ገጽ ብዛት=በA5 paper size 500
የወረቀት ዓይነት= ሽሮ መልክ
የመጽሐፉ የሽፋን ዋጋ= 850 ብር
ማከፋፈያ= ኦሜጋ መጻሕፍት መደብር
(አዲስ አበባ አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ ሕንፃ ሥር)
ስልክ ቁጥር= 0941555550
0911456866
©ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል አስናቀ (የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር እንደጻፉት)

በዚህ የሚድያ ጫጫታ በበዛበት እና ትውልዱ በብዙ የጥያቄ ማዕበል በሚናወጥበት ዘመን የቤተክርስቲያንን ረቂቅ ምስጢር በነገረ መለኮት አመክንዮ አብራርቶ የሚያስረዳ እና የሚያመለክት መሪ ማግኘት ለዘመኑ ትውልድ ታላቅ ዕድል ነው። ይህ መጽሐፍ በቤተክርስቲያኒቱ ትምህርት በብዙ የደከሙ እና አሁንም በዕውቀት ማዕድ ላይ የሚገኙት በማኅበራዊ ሚድያውም በጎ ተጽዕኖ ያላቸው የመምህር በትረ ማርያም የተዋሥኦ ሥራ ነው። መምህሩ በጥንታውያን ሊቃውንት ዘንድ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ እና ትምህርተ ሃይማኖትን ለማጽናት ይሠራበት የነበረውን ጥልቅ እና ረቂቅ የተዋሥኦ ጥበብን በመከተል በመጻሕፍተ ሊቃውንት እና በመጻሕፍተ መነኮሳት ላይ ለተነሡላቸው የነገረ ሃይማኖት ጥያቄዎች በመረጃ እና በአመክንዮ የተደገፈ ምላሽ ሰጥተዋል። በእነዚህ ረቂቅ መጻሕፍት ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ብርቱ ድካምንና ትጋትን የሚጠይቅ ቢሆንም መምህሩ የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል ይህንን የመሰለ ድንቅ መጽሐፍ በማዘጋጀት አንባብያን ጥልቅ የሆነውን የሃይማኖት ምስጢር በቀላሉ እንዲረዱ መንገድ ከፍተዋል። መጽሐፉንም ተራ ክርክር ሳይሆን የአባቶችን የተዋሥዖ መንገድ ተከትሎ ጥያቄ የሚመልስ የዘመኑን አንባቢ ከመረጃ ከንባብ ወደ ጥልቅ ምስጢር የሚያሸጋግር ድልድይ ኾኖ አግኝቼዋለሁ። ሃይማኖቱን ለማወቅ የሚሻ ሁሉ ይህን ቢያነብ በብዙ እንደሚያተርፍበት አምናለሁ።

ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል አስናቀ
(የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት መምህር)
ኦርቶዶክሳዊ ተዋስኦ በዋናነት ሰባት የመረዳት መሠረቶችን የያዘ የሕይወት ሀሳብ ነው።
(©መምህር ገብረመድኅን እንየው)

እነዚህም የተዋስኦ መሠረቶች፦ምሉዕ ንባብ፣ርቱዕ ትርጉም፣ቅብብሎሻዊ አረዳድ፣ኅብረትታዊነት፣ክሡት ምሥጢር፣የሕይወት ምሥክርነት እና ዘለዓለማዊ ተስፋ ናቸው።የቅዱሳት መጻሕፍት ተዋስኦዋዊ አረዳድ ከእነዚህ ጉዳዮች የወጣ ወይም የተለየ አይደለም።በእነዚህ ጥልቅ የተዋስኦ መሠረቶች ሦስት ሚዛኖች ተጠብቀው ይኖራሉ።
አንደኛው፦እግዚአብሔር ወደ ሰው ልጆች ያዘነበለባቸው የሕግ፣የመንፈሰ ረድኤት፣የኩረነት እና የቸርነት መገለጫ መንገዶቹ መታጎል ሳይኖርባቸው በርቱዓዊነት ተጠብቀውና ማደሪያ አግኝተው በሥራ መገለጽ አለባቸው።እንዲሁም ክቡሩ ፍጥረት ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚሄድባቸው፦የሕግ፣የአምልኮት፣የመገዛት፣የተስፋ፣የኅብረት፣የቅብብሎሽ መንገዶቹ በርቱዓዊነት ተጠብቀው መቀጠል መቻል አለባቸው።
ሁለተኛው ሰው ከሰው ጋራ ሊያደርጋቸው የሚገቡ አምላካዊ ፍጽምናዎች ናቸው።ሕገ እግዚአብሔር እና ሕገ ተፈጥሮ የሚገለጠው አንዱ ለአንዱ በሚያደርገው የቸርነት ግብር ነውና የተዋሥኦ አረዳዶቻችን የተፈጥሮና የሕግ ሚዛናቸውን እንደጠበቁ ለመኖር ህሊናን ማቅናት ልቡናን ማስፋት አለባቸው።
ሦስተኛው ከሰማይ በታይ ከምድር በላይ እንዲመግብ የተሾመው የሰው ልጅና መላው ሥነ-ፍጥረት የተፈጠሉለት የተፈጥሮ ሚዛናቸው እንዳለ ሳይቃወስ ወደ ትውልድ እየተላለፈ መኖር አለበት።
በዚህ ሁሉ የኑሮ ውጣውረድ ሂደት ውስጥ ደግሞ ተዋሥኦዋችን በተስፋ የሚጠበቀውን የመዳንን መንገድን ወደ ፍጽምና ሕይወት ማድረስ መቻል ነው።በመምህር በትረ ማርያም አበባው የተዘጋጀው መጽሐፍም ይሄንን ሚዛን ለመጠበቅ የተደረገ የተዋሥኦ ዕቅበት ነው።ከባለቤቱ የተገለጠውን፣በኦርቶዶክሳዊት ጉባኤ የተቀበልነውን፣የምንጠብቀውና ለትውልድ የምንሰጠውን ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ለመጠበቅ የተጻፈ ተዋሥኦ የህሊና ማረፊያ የልቡና መደገፊያ ነው።ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን አረዳድና ኅብረት ሊነጥል ከሚችል ማንኛውም ነገር፦አረዳድ፣ጥያቄ፣ኑፋቄ፣ፈቃደ ሥጋ፣ፈቃደ ሰይጣን፣ፍልስፍና፣ደርጅት፣ርዕዮተ ዓለም ጋር እንደ አመጣጡ ለመመለስ የሚደረግ ተዋሥኦ የወንጌላዊነት መገለጫ ነው።
ከዚህ ቀደም በርካታ መጻሕፍትን አዘጋጅተው ባስነበቡን በመምህር በትረ ማርያም አበባው የተዘጋጀልን ይሄ መጽሐፍም ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮን ለመጠበቅ የተደረገ ተዋሥኦ ነውና አንብበን ለወንጌላዊ ኑሮ እና ለድኅነት ጉዞ እንድንጠቀምበት እግዚአብሔር ይርዳን።

©መምህር ገብረመድኅን እንየው
1
በብዙ ድካም የኅትመት ብርሃን እንዲያይ የተደረገው ይህ የታሪክ ሰነድ እጅዎ ገብቶ ይሆን!?
ከማለቁ በፊት እጅዎ ያስገቡ!!
#OmegaBooks
0941555550