Forwarded from Omega Books ኦሜጋ መጻሕፍት
1.2. የሰሎሞን ልጅነት
ሰሎሞን የተወለደው በኢየሩሳሌም ነው። ንጉሥ ዳዊት ሕግን ተላልፎ ከኦርዮ ሚስት ከቤርሳቤህ ጋራ በዝሙት በወደቀ ጊዜ ባሏን በማስገደሉ፤ ከእርሷም ጋራ በደል በመፈጸሙ እግዚአብሔር ነቢዩን ልኮ ከገሠጸው በኋላ ንስሓ ገብቶ መሪር ልቅሶን አለቀሰ። እግዚአብሔርም ንስሓውን ተቀብሎ ኀጢአቱን ይቅር አለው። ዳዊትም ቤርሳቤህን አጽናና፤ ኋላም በእግዚአብሔር ፈቃድ ሚስቱ አደረጋት። የመጀመሪያ ልጃቸው በሕፃንነቱ ከሞተ በኋላ የወለዱትን ኹለተኛ ልጃቸውን እናቱ ሰሎሞን ብላ ጠራችው፤ ትርጉሙም የሰላም ሰው ወይም ሰላማዊ ማለት ነው፤ በዘመኑ ሰላም ይነግሣልና። ሰሎሞን ሲያድግ በዙፋኑ እንደሚተካው ንጉሥ ዳዊት ለቤርሳቤህ ቃል ገባላት።
በዘመኑ እንደነበረው ኹሉ፣ “እግዚአብሔር ለእሥራኤል ሰላምንና ጸጥታን ሰጠ።”7
#ሲሎንዲስ ገጽ 15
_______
መጽሐፉን ከሐሙስ ጀምሮ በመደብራችን ያገኙታል
አድራሻ:- ቁጥር 1 ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻ
ቁጥር 2 አብርሆት ቤተመጻሕፍት አጠገብ
ስልክ፦0941555550 ወይም 0911456866

ከገበያ ጠፍቶ የነበረው በረ/ፕ መ/ር ግርማ ባቱ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ 5ተኛ እትም ዛሬ ከሰዓት ከሕትመት ይወጣል። መጽሐፉን የምትፈልጉ በ 0941555550 መደወል ትችላላችሁ።
#ዋና_አከፋፋይ= ኦሜጋ መጻሕፍት
#ዋና_አከፋፋይ= ኦሜጋ መጻሕፍት
👍1
#ማኅትው
አእምሮ፡ ርእስነ፡ ለርእስነ፡ በርእስነ፡ ይትገሐድ
_____
“እከሌ የተባለው የእከሌ ሀገር ሊቅ እንደጻፈው፣ ኢትዮጵያ ወይም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን …” ብሎ ራስን ከውጭ ወደ ውስጥ ለማየት መሞከር ሙሉ ለሙሉ የሚነቀፍ ባይሆን እንኳ እንደ መደበኛ እይታ መለመዱ ያስጨንቃል። እኛ ማን ነን? ማለትን ለመዳኘት አስቀድሞ ስለራሳችን የሚሰማንንና የምናውቀውን አንብሮ ከመነሣት ይልቅ ሰዎች ማን ይሉናል? ብሎ ራስን በሰዎች ብይን ብቻ ወስኖ መጓዝ የማይጨበጥ፣ ከውጭ የተጫነ ማንነትን በምናብ ማሳደድን ሲጋብዝ ይታያል። በመጽሐፍ እንደምናነብ ክርስቶስም በቂሳርያ ሳለ “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” ብሎ ጠይቋል። መልሱ ልዩ ልዩ ነበረ። ኤልያስም፣ ኤርምያስም፣ ዮሐንስ መጥምቅም፣ ከነቢያት አንዱ ነው ያሉትም ነበሩ። ውስጥን የሚያውቀው የሰማዩ አባት ከገለጠለት ከቅዱስ ጴጥሮስ በቀር ማንነቱን ያወቀ አልነበረም። 'ቦ እለ ይብሉከ ...” እያለ ቅዱስ ወንጌል እንደ ደረደራቸው የጌታን ማንነት ሁሉም እናውቃለን ብለው የመሰላቸውን ተናግረዋል። የመሰላቸውና የሆነው አንድ እንዳልሆነ ግን የባለቤቱ ምላሽ ያረጋግጥልናል።
እንዲህ ያለው አጋጣሚ በታሪክ ንባብም ያለ ነው። አንድ ሀገር ወይም ቤተ እምነት በራሱ ነዋሪ ወይም አማኝና በውጫዊ ተመልካች እይታ ሲታይና ሲገለጥ ተመሳሳይ ምስል ይኖረዋል ተብሎ አይጠበቅም። ውጫዊ ተመልካች ማሰላሰያው ማንጸሪያው አስቀድሞ የሚያውቀው የራሱ ኑሮና ምስል፣ ዛሬና ነገ እንዲሆንለት የሚመኘው ምኞት ነው። ያየውን ለመግለጥ ቢደፍርም መግለጫው የሚገልጠውን ነገር ማንነት በመበየን ረገድ ከቶውንም ምሉዕ ሊሆን አይችልም። በአንጻሩ በሚገለጠው ታሪክና ሕይወት ውስጥ ያለው አካል ደግሞ ኑሮውን ከመበየን ይልቅ መኖሩ ይቀለዋልና ያንን ኑሮ ግለጥልን ሲባል ገላጭ ቋንቋና ስሜት ይቸገራል፤ የቱን አንስቶ የቱን እንደሚተው ይጨንቀዋል።
ወደያዝነው ርእስ ስንንደረደር፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ ሀገራችን ኢትዮጵያን እንዲህ ብሎ ከመግለጥ ይልቅ ሕይወቱን መኖር፣ በዚያ ውስጥ ያለ ማንነትን እንዲሁ በኑሮ መግለጥ ይቀላል። ለእኛ ለነዋሪዎቿ ይህ ነው ቀላል። ቤተ ክርስቲያን በዐይነ ካህን፣ በዐይነ ምዕመናን፣ በቤተ መንግሥት ወገኖች፣ በፖለቲከኞች፣ በውጭአሳሾችና ሚሲዮናውያን ስትታይ እርሷ አንዲት ብትሆንም መገለጫዋ እንደ ተመልካቹ ዐይን፣ አንዳንዴም እንደ ተመልካቹ ዐላማ ይለያያል። ለካህናትና ምዕመናኗ በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ናት። ፖለቲከኞች በበኩላቸው ኢትዮጵያ ካሏት የሃይማኖት ተቋማት እንደ አንዷ ያዩአታል። ለአሳሾችና ሚሲዮናውያን ብዙ ጊዜ ታድሳና ተከልላ በተፈለገው መንገድ ልትሠራ የምትችል ተራ ግብዓት፣ ነባር እርሾ እየተደረገች ስትወሰድና ስትገለጥ ይታያል።
ለምዕመንና ካህናቷ የቤተ ክርስቲያን ሕይወት፡- ትናንት፣ ዛሬና ነገ የሚዋሐዱበት አማናዊና ቀጣይነት ያለው ሕያው ህላዌ ሲሆን ለአሳሾች ደግሞ አንድ ትርዒት ወይም ሙዚየም የመጎብኘት ያህል ሆኖ ይቀርባል። እንዲህ ያለው እይታ አለመገራቱ ጉዳቱ ብዙ ነው። ምዕመናንና ካህናት ሳይተረጕሙ በገቢር የሚኖሩትን ሕይወት ድንገት አሳሽና ሚሲዮን በውጫዊ እይታ ምን እንደሚለው ሰምተው ቃሉን እንደ ወረደ የወሰዱት እንደሆነ ራስን በራስ የማወቅ ዕድላቸው ተላልፎ ይሰጣል፤ ለራሳቸው ያላቸው ግምትና በራስ መተማመን ይናወጻል። ራስን መሸሽ ይመጣል። ከዚያም አልፎ ያልተስተባበለው ውጫዊው እይታ እንደ ቤተ ክርስቲያን አማናዊ መገለጫ ተደርጎ በመደበኛ ተረክነት ይገንናል። ተረኩ ለፖለቲከኛውም፣ ለቀሊል ብሔርተኛውም፣ ሌላው ቀርቶ ቤተ ክርስቲያንን በጥልቀት ላልተረዳው ኦርቶዶክሳዊ ትውልድም ቀላል ሸቀጥና ፖሊሲ መቅረጫ ግብዓት ተደርጎ ይቀርባል።
ከ1950ዎቹ የ“ዘመናዊ”ው ትምህርት ጅማሮ ወዲህ እንዲህ ያለው የቤተ ክርስቲያንንና የሀገርን ታሪክ በውጫዊ እይታ በባዕዳን ቅኝት የመረዳት ቀሊል አካሄድ መደበኛውን ዐውድ መያዙ፣ ሀገራዊ ፖሊሲና የፖለቲካ “ማኒፌስቶ”ነትን ተላብሶ መታየቱ ተደጋግሞ የተነገረ ነው። አካሄዱ ያሰጋቸውና ያስቆጫቸው ቀደም ያሉት አበው እነ ብላቴን ጌታ ኅሩይ፣ እነ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ፣ እነ አለቃ አያሌው ታምሩ፣ እነ ሊቀ ሥልጣናት አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ በጠዋቱ ትውልዱን ከመባዘን ለመታደግ ሞክረዋል። አረሙ ስር ሰድዶ ነበርና የተገኘው ፍሬ የደከሙትን ያህል አይመስልም።
የመምህራችን አቀራረብ የዚያ ቁጭት ቀጣይ ክፍል ይመስለኛል። ልዩነቱ እነዚያኞቹ የሚሆነውን ገምተው በፍርሃትና በጭንቀት የጻፉ ሲሆኑ መምህር ግርማ ባቱ ግን ከራስ የመራቅ ጣጣ ያመጣውን ድቀት ዐይቶና ተረድቶ መጻፉ ነው። ሀገራችን የመጽሐፍ ሀገር ናት። ቤተ መንግሥቱም ቤተ ክህነቱም በጽሕፈት የበለጸገ ነው፤ የሁሉም አስተጋባኢት ቤተ መዘግብት ደግሞ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት። ከዚህ የተነሣ ኢትዮጵያን
ለመረዳት ወደእርሷ መገስገስ ግድ በግድ ይሆናል።
መዛግብቱ ብዙኃን የሩቅ ተመልካቾች እንደሚሉት የቤተ መንግሥቱንና የቤተ ክህነቱን ሹማምንት ብቻ ሳይሆን የ“ተራ”ውን ሕዝብ አኗኗር፣ መተዳደሪያውን፣ የየወቅቱን ዐቢይ ክስተት፣ የቋንቋና የባህል ይዘት፣ ወዘተ. በቀጥታም በተዘዋዋሪም ይነግሩናል። እንደ እውነቱ ዘመናውያን ሊቃውንት በተዐብዮ ይኂሱት እንጂ እንደ ፕ/ር ታደሰ ታምራት ያሉ ሊቃውንት የጻፉት Church and State፣ የስቴፈን ካፕላን Beta Esrael: The Jewish of Ethiopia and Beyond: Ancient and Medieval Ethiopian History የመሳሰሉ በምዕራብ ጸሐፍት የተደነቁ ሥራዎች ምንጭ የቤተ ክርስቲያን መዛግብት ናቸው። እነዚህ ሥራዎች በአፈ እንግሊዝ እየተተነተኑ ሲቀርቡ እንደ ዘመናዊ ንጥርጥናት፣ በብሔራውያን ሊቃውንትና የአብነት መምህራን ሲቀርቡ ደግሞ እንደ “ተረት” የሚታዩበት አቀራረብ ግን የአሳዛኙ ውጫዊ እይታ መገለጫና በብሔራውያን ሊቃውንት ላይ የተካሄደው የምሁራዊ ሰብእና ግድያ ኣካል ነው። የያዝነው የመምህር ግርማ መጽሐፍ ይህን አካሄድ ለመግራትና ለመወደር ከቤተ ክህነቱ ወገን ከተጻፉ መጻሕፍት ጎልቶ ሊጠቀስ የሚችል ሆኖ ታይቶኛል።
መሣሪያነት ሳይሆን በራሳቸው ግርማ ገድላቱን እንደ “ዘመናውያኑ” አጥኚዎች ለሆነ ግብ መዳረሻ መሆናቸውንም ተቀብሎ፣ ያ የተኖረ የቅድስና ሕይወት ዛሬም መዓዛ የተኖሩ አማናውያን ህላዌያት ያለውና የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ሕያው አካል መሆኑን አምኖና ተቀብሎ ስለሆነ የሚጠቅሳቸው እንደኔ ላሉ አማኝ አንባብያን ኅሊናን አይገፋም። ቤተ ክርስቲያንን በውስጧ እየኖሩ በውጭ እያዩ እንዲያ ናት ለሚሏት ውስጧን ባታውቁ እንጂ እርሷ እንዲያ ሳትሆን እንዲህ ናት የሚል አፈ ጉባኤ ሲገኝ ደስ ያሰኛል። በዚህ መጽሐፍ ፕ/ር ጌታቸው እንዳሉት ስለራሳችን የነቃፊዎቻችንን ያህል እንኳ ባለማወቃችን ሊቃና ሲገባው እንደ መደበኛ እይታ የተቈጠረው የታሪክ ተፋልሶ ክርስትናው ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት እስከ ዘመኑ የተዛባ የታሪክ አተራረክ /ትርክት/ተዳስሷል።

ክርስትና የገባው በጃንደረባው አማካይነት መሆኑ ቢነገርም አሁን ድረስ በርካታ ጸሐፍት የክርስትና ዘመናችንን ወደ 4ኛው ክፍለ ዘመን መሳባቸው፣ በብዙ ጸሐፍት ማረጋገጫ የሚሰጠው የወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ በኢትዮጵያ የማስተማር ታሪክ እንዳይነገር ታሪኩ መጨቆኑ፣ የዘመነ ብሉይ የአንድ አምላክ አምልኮታችን ላይ የሚፈጠረው ብዥታ፣ የክብረ ነገሥትና የንግሥተ አዜብ ተአማኒነት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች፣ የሚሲዮናውያንና የግብፃውያን ጫና፣ የቤተ ክርስቲያን የቀደሙ ወርቃማ የሥነ ጽሑፍ፣ የሕይወተ ገዳምና የሥነ አምልኮ ጊዜያት፣ የታሪካችን አጻጻፍ በአውሮፓዊ ሥዕለ ኅሊና የተቃኘ መሆን ያመጣው ራስን የማጣት ችግር፣ ወዘተ. በራሳችን ሰው የራሳችንን እንድናውቅ ተደርገው በማዕከላዊ ቋንቋና ሁሉም ተደራሲ በሚረዳው አቀራረብ በዚህ መጽሐፍ ተዳስሰዋል። የባለቅኔውን ቃል ተውሰን “አእምሮ፡ ርእስነ፣ ለርእስነ፡ በርእስነ፡ ይትገሐድ - ራሳችንን ማወቅ በራሳችን ለራሳችን ይገለጥ” ማለታችንም ለዚህ ነው። አንዱ ራስን ማወቂያ እንዲህ ያለ ከራስ ሰው: ከቤት ልጅ የወጣ መጽሐፍ ነውና። መልካም ንባብ!
በአማን ነጸረ
ደብተራና የሕግ ባለሙያ
በአማን ነጸረ
ደብተራና የሕግ ባለሙያ
ይህ በጠቢቡ ሰሎሞን ሕይወትና ሥራዎች ላይ ተመሥርቶ የተጻፈው #ሲሎንዲስ የተሰኜ ድንቅ መጽሐፍ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በገበያ ላይ ይውላል። ጸሐፊው ዲያቆን ኤልያስ ደፋልኝ ከዚህ በፊትበዳዊት ታሪክ ላይ ተመሥርቶ "ዳዊት ከእረኝነት እስከ ንግሥና" የተሰኘ መጽሐፍ አስነብቦን እንደነበር ይታወቃል። መልካም ንባብ!!
አካሳታሚ እና አከፋፋይ፦ #ኦሜጋ_መጻሕፍት
ስልክ፦ +251941555550 ወይም +251911456866
አካሳታሚ እና አከፋፋይ፦ #ኦሜጋ_መጻሕፍት
ስልክ፦ +251941555550 ወይም +251911456866
Forwarded from Omega Books
ሲሎንዲስ የሚለው የስሙ ትርጉም ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን? ይህን መጽሐፍ ከፈለጋችሁ እንሆ ብለናል።በተጨማሪ የእስራኤል ሦስተኛ ንጉሥ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን መጻሕፍት ጥበብና ታሪክ የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነው
ይህ መጽሐፍ በኦሜጋ መጽሐፍ መደብር ያገኙታል።
አድራሻችን፡-ቁ1,ቅድስት ሥላሴ ዮንቨርሲቲ ግራውንድ ላይ
ቁ2,አብርሆት ቤተመጻሕፍት አጠገብ
0941555550
ይህ መጽሐፍ በኦሜጋ መጽሐፍ መደብር ያገኙታል።
አድራሻችን፡-ቁ1,ቅድስት ሥላሴ ዮንቨርሲቲ ግራውንድ ላይ
ቁ2,አብርሆት ቤተመጻሕፍት አጠገብ
0941555550
❤1