ኦሜጋ መጻሕፍት- Omega Books
354 subscribers
486 photos
9 videos
7 files
42 links
Download Telegram
ቀዳማዊ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ
(የ2ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ የሕይወት ታሪክ)
ሦስቱ የመነኮሳት መጻሕፍት በከፍተኛ ጥራት ታትሞ ለገበያ ቀርቧል። በመደብራችን ያገኙታል።
ይህ የአማርኛ የቤተክርስቲያን መዝገበ ቃላት ዛሬ ከሰዓት ከሕትመት ወጥቶ ወደ ገበያ ይቀርባል።
አድራሻ ቁ1 ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻ
ቁ2 አብርሆት ቤተ መጻሕፍት አጠገብ
ስልክ 0941555550 ወይም 0911456866
ግብር እና ማዕድ መዝገበ ቃላትን እኛ ጋር ያገኙታል!!
የአሳታሚው ማስታወሻ
ኢትዮፋጎስ ትሬዲንግ ሓላ/የተ/የግ/ማ እና የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዕውቀትን ለማስፋፋት በጋራ የሚሠሩበት የመግባቢያ ስምምነት አላቸው። ይህ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት የዚህ ስምምነትን መሠረት ያደረገ የጋራ ጥረት ውጤት ነው። የዚህን መዝገበ ቃላት ረቂቅ ከሥልሳ ዓመታት በፊት ያዘጋጁት ነፍስ ኄር ፕ/ር ሥርግው ሐብለሥላሴ ናቸው። ኢትዮፋጎስ መጽሐፍ ማእከል ይህ በብዙ ድካም የተዘጋጀን ታሪካዊ መጽሐፍ የኅትመት ብርሃን ቢያይ ለአዲሱ ትውልድ፣ ለቤተ ክርስቲያን እና ለሀገርም ጉልህ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት በማመን እንዲታተም አድርጓል።

ከሥልሳ ዓመታት በፊት የተዘጋጀው የአማርኛ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት በአሥራ ሦስት ቅጾች የተዋቀረና ጽሑፉም በታይፕ የተመታ ነበር። ኢትዮፋጎስ መጽሐፍ ማእከል በታይፕ የነበረው በኮምፒተር በማስጻፍ እንዲሁም አሥራ ሦስቱን ቅጾች በሁለት ጥራዝ በማዋቀር አዘጋጅቶታል። እንዲሁም በረቂቁ ያልነበረ ማውጫና ሌሎች የሌይአውት ሥራዎችን አክሎበታል። ከዚህ በተጨማሪም በርካታ ምሁራንን በማሳተፍ ከሕትመት በፊት እንዲያዩት ተደርጓል።
ከረጅም ዓመት በፊት የተዘጋጁት ቅጂዎች በተለያየ ምክንያት ለሕትመት ሥራው አዳጋች በመሆናቸው አንዳንድ ክፍተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ እንገምታለን። አንባቢ ጉድለቶች ቢያጋጥሙት በቀጣዩ ኅትመት ለማረም እንዲረዳ ያገኛቸውን ግድፈቶች በሚቀጥለው የኅትመት ጊዜ እንዲስተካከሉ በኢሜይል አድራሻችን
ethiofagos@gmail.com ጥቆማ ቢልክልን የምንቀበልና የምናስተካክል መሆኑን እናሳስባለን።
መልካም ንባብ
ኢትዮፋጎስ መጽሐፍ ማእከል
❝በወጉ ያልተዘከሩት ምሁር መጽሐፍ
( ዶ/ር ሥርግው ሐብለሥላሴ)
[ጸጋው ማሞ እንዳሰናዳው]

"ሥርግው ምን አልባትም በ20ኛው ክፍለ ዘመን ካሉት ብቸኛው የኢትዮጵያ የጥንታዊ ታሪክ ሊቅ ነው" ይላሉ ኤርትራዊው የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር "ባህሩ ተፍላ" ስለ ጥረታቸውና ሀቃዊ የታሪክ ትንተናቸው ፕሮፌሰር መስፍን ወልተማሪያምም "በመክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ " መጽሐፋቸው ላይም ምሥክርነታቸውን በአድናቆት ሰጥተዋል። ተቀዳሚ ምሁር ፕሮፌሰር ሥርግው ሐብለሥላሴ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ተምረው ባካበቱት ሰፊ እውቀት ላይ ተንተርሰው አያሌ የታሪክ ጥናቶችን እንዳካፈሉን ይታወቃል። ከሁሉም በላይ ግን " የኢትዮጵያ የብራና ጽሑፎች ማይክሮ ፊልም ድርጅት " ዳይሬክተር ሆነው በሰሩት ዘመን ተሻጋሪ ሥራ የዓለም ሕዝብ ሁሉ ሲዘክራቸውም ይኖራል ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የእርሳቸውን የድካም ሥራዎች ተገንዝቦ ተገቢውን ክብር ሊቸራቸው ይገባል።

ከእርሳቸው የበዙ ሥራዎች መካከል አንዱ እና ግዙፍ የሆነው "አማርኛ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት " ሲሆን ይኸውም በብርቱ ያላሰለሰ ጥረት እና ድካም የተሰራ፤ ዘመን የማይሽረው ከወረት የተሻገረ እጅግ ድንቅ ሥራ ነው። ይኸ ግዙፍ መዝገበ ቃላት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ የታላላቅ ሊቃውንትን ፣ ቅዱሳንን ፣ ገዳማትን እና አድባራትን ታሪክ በመረጃ የሰነደ ድንቅ ሥራ ነው ።

ይኸ ታሪካዊ መዝገበ ቃላት ለታሪክ ተመራማሪዎች ፣ ለሥነ ጽሑፍ ሰዎች ፣ ለሥነ መለኮት አጥኝዎች ፣ ለሥነ ሰብእ መርማሪዎች እንደዚሁም ታሪክ ለሚወዱ ሰዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ መጽሐፍ ነው ። ለምሳሌ በገጽ 662 ላይ "ገላኔ"ን እንዲህ ያብራራልናል " /እመት/ በ19ኛው ምእት ዓመት የኖረች የጉድሩ ሴት። ባሉዋ ዋቅጅራ ይባላል። ከእነዚህ አብራክ የተገኘው ወንድ ልጅ ነገሮ ይባላል...ይኸውም ተክለ ኢየሱስ የተባለው የኢትዮጵያን ታሪክን ጽፎ ያቆየን ነው " በማለት ይገልጽና መረጃውን ከታች ያስቀምጥልናል።

ሌላው የሚያሳስቱ ተመሳሳይ ስም ያላቸውን የተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችን እና የቦታ ስሞች በወጉ እንድንለይም ይጠቀመናል ።ለምሳሌ በዚህ መጽሐፍ ላይ ከ35 በላይ ዮሐንስ የሚባሉ ታላላቅ ታሪካዊ ሰዎች በግልጽ ተብራርተዋል ። ጀርመኖች ታላቁን "Encyclopedia of Aethiopica " ከመስራታቸው በፊት የተሰራ ምናልባትም ለዚህ ስራ ታላቅ ግብአት የሆነ መጽሐፍ ነው።

እነዚያ ፊደል የቀረጹ ፣ ገድል ፣ ተአምራት ፣ ዜና መዋዕል ፣ ታሪከ ነገሥት የጻፉ ፤ ወንጌል ፣ ቁርአን ፣ ፍልስፍና እና ታሪክ የተረጎሙ ቀደምት አባቶቻችን ድርሰትን እና ንባብን የምታበረታታ እንዲህ የምትል ቡራኬ በየድርሳናቱ ላይ ያስቀምጡ ነበር " ይኸንን መጽሐፍ የጻፈውን ፣ ያጻፈውን ፣ ያነበበውን ...እግዚአብሔር ዕድል ፈንታውን ጽዋ ተርታውን በቅዱሳኑ ወገን ያሳርፍልን " በማለት ጽሁፍን እና ንባብን ያበረታቱ ነበር ።

አሁንም የፕሮፌሰር ሥርግው ሐብለሥላሴን የድካም ውጤት "ኢትዮፋጎስ የመጽሐፍ ማእከል"ከኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት " ጋር በመተባበር በእጅ ጽሁፍ የነበረውን 13 ቅጽ አርትኦት በመሥራት በሁለት ግዙፍ መጽሐፍት በማሳተማቸው ከፍተኛ ክብር እና ምሥጋና ይገባቸዋል። ከእኛ የሚጠበቀው በከፍተኛ ልፋት ተጋጅቶ የቀረበልንን ጥሩ ማዕድ መመገብ ብቻ ነው ።

ዶ/ር እጓለ ገብረዮሐንስ "ከመጽሐፍ የሚደገሙት ጥሩዎቹ ናቸው " ይላሉ ። እንደዚሁም 'ማርክ ትዋይን' የተባለ ሊቅ ደግሞ "ጥሩ መጽሐፍትን የማያነብ ሰው ማንበብ ከማይችል ሰው አይሻልም " ይላል ። ይኸ መጽሐፍ ደግሞ ከጥሩዎቹ አንዱ ስለሆነ በእያንዳንዱ ቤተ መጻሕፍት እና መደርደሪያ ውስጥ ሊገኝ የሚገባ ግሩም መጽሐፍት ነው ።
እሁድ በዐውደ ፋጎስ ይቀርባል
~~~~
ርእስ:- ቅድመ ውሳኔን (predestination) ከነጻ ፈቃድ (freewil) ጋር ማስታረቅ : ከትምህርተ መለኮት እይታ

( Reconciling predestination with freewil:
A theological perspective)

አቅራቢ:- "ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሳ" (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ የነገረ መለኮት መምህር)

ቀን :- እሁድ መስከረም 4 /2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00

ቦታ :- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት( ወመዘክር)
የዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ዜና መዋዕል

ትርጉም፦ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ
የሀገራችን ነገሥታት ዜና መዋዕሎች (Chronicles) የተጻፉት በግእዝ ቋንቋ ነው። የኢትዮጵያን ታሪክ ያለግእዝ ቋንቋ ዕውቀት አጠናለሁ ብሎ የሚነሣ አካል ካለ በጨለማ እንደመሄድ ይሆንበታል። ቋንቋው መሰጠቱ በሀገራችን የታሪክ ዕውቀት ላይ የሚጨምርልን ብዙ ጉዳዮች አሉት። ታሪክን ከሥር መሠረቱ ማወቅ ደግሞ ትላንትን በትክክል ተረድተን ዛሬን ለመሻገርና ነገን ለመሥራት ይጠቅመናል።

የግእዝ ቋንቋን ሁሉም በቀላሉ መረዳት እንዲችል በማሰብ ይህንን መጽሐፍ አዘጋጅቻለሁ። መጽሐፉን የምትፈልጉ አዲስ አበባ፣ አራት ኪሎ፣ ኢትዮ ፋጎስ መጽሐፍ ማከፋፈያ በስልክ ቁጥር 0941555550 ታገኙታላችሁ።

ቋንቋው ላይ ያለን ዕውቀት እንዲዳብር በመፈለግ ለብዙ ጊዜ በተከታታይ ያስተማርኳቸው የግእዝ ትምህርቶች በPDF በቴሌግራም ቻናሌ ደግሜ ዛሬ ለቅቄያቸዋለሁ ገብታችሁ ማውረድ ትችላላችሁ።

© በትረ ማርያም አበባው

✝️የቴሌግራም ቻናሌ በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw https://t.me/betremariyamabebaw ነው።

✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- We belong to Christ ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
1
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና የውጭ ግንኙነት