ኦሜጋ መጻሕፍት- Omega Books
354 subscribers
486 photos
9 videos
7 files
42 links
Download Telegram
༒ የመልክአ ሕማማት ንባቡና አንድምታ ትርጓሜው በመጽሐፍ ተዘጋጅቶ በዐቢይ ጾም ለአንባቢው ቀርቧል ༒
መልክአ ሕማማት ስለ ጌታችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሕማም፥ መከራ፥ ስቃይ፥ የሚናገር መጽሐፍ ሲሆን፤ ደራሲው ታላቁ ሊቅና የደብረ ባሕርይ ጋሥጫ መምህር አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ነው፡፡
መልክአ ሕማማት በባለ 3ት መስመር አርኬ የተደረሰ ግጥማዊ ድርሰት ሲሆን፤ የተደረሰውም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት አንጻር በመሆኑ ‹‹ጸሎት ዘሰባዐቱ ጊዜያት›› በሚል መጠሪያም ይጠራል፡፡ የእያንዳንዱ ጊዜ ድርሰትም በዋነኛነት 3ት ክፍሎችን የያዘ ነው፤ እነርሱም፤

1ኛ) ስብሐተ እግዝእትነ ማርያም /የእመቤታችን ምስጋና/
2ኛ) ስበሐተ ኢየሱስ ክርስቶስ /የኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና/
3ኛ) ስብሐተ ሥሉስ ቅዱስ /የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና/

ይህ ታላቅ ጸሎት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስር ባሉ በሁሉም ገዳማትና አድባራት በሰሙነ ሕማማት የሚደርስ ሲሆን፤ በአንዳንድ ትላልቅ ገዳማት (እንደ ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ወደብረ ጎል አቡነ በጸሎተ ሚካኤል) ያሉ መነኰሳትና መናንያን ግን ከዓመት እስከ ዓመት ጸሎቱን በዜማ /በንባብ/ ያደርሱታል፡፡

የጎልማሳነት ዕድሜያቸውን በአግባቡ የተጠቀሙባት መጋቤ ሐዲስ ወብሉይ አባ ጸጋ ዘአብ {ቆሞስ} በጎልማሳነት ዘመናቸው ከተማሩባቸው ጉባኤ ቤቶች መካከል ፤ የኔታ መዝገቡ ዘዝቋላ፣ የኔታ አባ ኃይለ ሚካኤል ዘዝቋላ፣ የኔታ አባ ክፍለ ጊዮርጊስ ዘበዓታ፣ የኔታ አባ ሳሙኤል ዘበዓታ፣ የኔታ አባ ፍቅረ ዮሐንስ ዘሐይቅ፣ የኔታ አባ ፍቅረ ማርያም ዘሐይቅ፣ የኔታ አባ ገብረ መድኅን ዘዲማ፣ የኔታ ብዙአየሁ ዘበዓታና የኔታ ኪ/ወልድ ዘዲማ ይገኙባቸዋል። በጉባኤ ቤት ሳይለዩ ከእነዚህ ንዑዳን ሊቃውንት ከጸዋትወ ዜማ እስከ ትርጓሜ መጻሐፍት ድረስ ጠንቅቀው ምስጢር አደላድለዋል። በሰሙነ ሕማማት በቀጥታ ስርጭት ከጥልቁ ትርጓሜያቸው በማንኪያ ጨልፈው ሲያሰሙን እንደነበረ የሁላችንም ትውስታ ነው።

ጸጋ ዘአብ የአብ ስጦታ ማለት ነው። በጎልማሳነት ዘመናቸው ከማስተማር ጎን ለጎን ድርሰት መድረስ፣ ያልተተረጎሙ መጻሕፍትን በአንድምታ ትርጓሜ የማዘጋጀት ሀብትም አላቸው ይህም ከአብ የተሰጠ ጸጋ ነው። ካህኑ ጸጋ ዘአብ የሐይማኖት ፍሬ የተባለውን ተክል በማፍራቱ ፍሬውምው ያማረና ያበበ ሆኗል። የእሳቸውም የትምህርት ቆይታቸው እንደዚህ አይነት ትርጓሜ መጽሐፍን በማዘጋጀት አብበዋል። አንድም ጸጋ ማለት ምርቃት፣ በረከት ፣ ባለው ላይ ተጨማሪ ሥጦታ፣ መክሊት ማለት ነው። ክቡር አባታችን መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ነገረ ክርስቶስ በሚታሰብባት በዚህ በወርኅ ጾም በተለይም የጌታ የሕማሙና የሞቱ መታሰቢያ በሆነው በታላቁ ሰሙነ ሕማማት በረከተ ነፍስ ወሥጋ እናገኝ ዘንድ {መልክአ ሕማማት}ን ንባቡና አንድምታ ትርጓሜውን አዘጋጅተውልናል። የኔታ ጸጋ ዘአብ {አባ} እንኳን ለዚህ ክብር አበቃዎት።

ዕድሜና ጤና ሰጥቶ ይጻፉልን።
ለቀደሙት ሐዋርያት "ከዋው እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ዜና ሠናየ። ዘእግዚአብሔር ፈነዎ ይነግር ቃለ እግዚአብሔር" እንደተባለ የዘመናችን ሐዋርያ ሊቁ አባታችን መንገድዎ የተቃና ይሁን። ከዚህ በላይ ይጻፉልን።

ጸጋ ዘአብ ሂሩት ዘወልድ ሱታፌ ዘመንፈስ ቅዱስ ዘኀደረ ላዕለ ሐዋርያት ከማሁ ይኅድር በላዕሌነ።

መልክአ ሕማማት ንባቡና አንድምታ ትርጓሜው
አሳታሚና አከፋፋይ: ኢትዮ ፋጎስ
አድራሻ: ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ቢሮ ቁጥር 003
ስልክ ቁጥር: 📲 +𝟮𝟱𝟭𝟵𝟰𝟭𝟱𝟱𝟱𝟱𝟱𝟬
☎️ +𝟮𝟱𝟭𝟭𝟭𝟭𝟰𝟲𝟭𝟭𝟮𝟲

ፖስታ ሣጥን ቁጥር: 📫 𝟯𝟯𝟲𝟬𝟬

Petros Ashenafi Kebede
አዲሲቷ ኢየሩሳሌም
(የነፃነት ከተማ)
መጻሕፍት ከእሳት ሊያወጡን የተላኩ መላእክት ናቸው!
_
በተማሪነት ዘመኔ በጣም የጸናብኝ ድህነት የመጻሕፍት ማጣት ነበር፤ የኔ ብቻ ሳይሆን በእኔ ዘመን የነበሩ ተማሪዎች ሁሉ ችግር ነው ማለት እችላለሁ። ከእኛ በፊት የነበሩት በታላላቅ ገዳማትና አድባራት ዕቃ ቤቶች ገብቶ የማንበብ ዕድሉ ስለነበራቸው መጻሕፍትን ለማግኘት አይቸገሩም ነበር። እኛ የደረሰንበት ዘመን ዕቃ ቤቶች በሌባ ስጋት ተዘግተው አሁን ያለው የሕትመት ዘመንም ሳይደርስ መካከል ላይ ነበርና የመጻሕፍት ዕጥረት በጣም ፈትኖናል።

በዚህ ዘመን ደግሞ በስም ብቻ እናውቃቸው የነበሩ መጻሕፍትን ታትመው ወደ እጃችን እየገቡ ያሉበት ዘመን በመሆኑ እግዚአብሔር ሊመሰገን ይገባዋል። ለሎጥ መላእክትን እንደላከ ለእኛ መጻሕፍትን ልኮልናልና። እንዲያውም ከሎጥ የበለጠ የማዳን ሥራ የተሠራልን ይመስለኛል፤ ለሎጥ የተላኩ መላእክት ያዳኑት ሎጥንና ቤተ ሰቡን ብቻ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት ግን ሕዝቡን ሁሉ የሚያድኑ መላእክት ናቸው። ሎጥ የዳነው ከምድራዊ እሳት ነው፤ እኛ ግን በመጻሕፍት ከዘለዓለም እሳት እንድንባቸዋለን።

ይህ መጽሐፈ ሐዊ ለእኛ ከተላኩ መላእክት መካከል አንዱ ሲሆን ተሰውሮ ከሚኖርበት ቦታ ለሕዝቡ ልትገለጥ ይገባሃል ብለው ያመጡት ሊቀ ጠበብት መሠረት ናቸው። ዜማን ከዜማ መሣሪያ ጋር ማስማማት የማይሳናቸው የአቁቋሙ ሊቅ የትርጓሜው መምህር ሊቀ ጠበብት መሠረት የተሰወረ የፊቱን መልክ እንድናየው የቋንቋ መጋረጃውን አንስተው ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ እያሉን ነው።

በቀኖና ቤተ ክርስቲያን በሥርዐተ ሃይማኖት ጸንቶ ለመኖር ለሚፈልግ ክርስቲያን ሁሉ እጅግ ጠቃሚ መጽሐፍ ነው። የምዕመናን፣ የመምህራን፣ የመነኮሳት ሕይወት በዚህ መጽሐፍ ተዳሷል። የጥንት አባቶቻችን ምን ብለው አስተማሩ? ብሎ የሚጠይቅ ሰው ካለ አንዱ የአባቶቻችንን ትምህርት ከያዙ መጻሕፍት አንዱ ይህ መጽሐፈ ሐዊ ስለሆነ መመልከት ይገባዋል።

ክቡር ሊቀጠበብት መሠረት ምሕረቱ በክፍል አንድ መጽሐፍዎ የጀመሩትን በጎሥራ በክፍል ሁለት ስላስቀጠሉልን እጅግ እያመሰገንን እኛም የመምህራኑን ትምህርት አንብበን የመምህራንን እግር ተከትለን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ ያብቃን እላለሁ። አሳትማ ያቀረበችልን ኢትዮ ፋጎስን ግሪክ ድረስ ሳንወርድ ያገኘናት አርዮስፋጎሳችን {መካነ ጥበባችን} ነሽ ብለናታል።

መልካም ንባብ!!

©ሊቀሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ
በቅርቡ የተመረቀው የፕ/ር ኃይሉ ሀብቱ የምርምር ውጤት በመደብራችን ይገኛል።

አዲሱ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
https://t.me/ethiofagos

ስልክ +251941555550
መጻሕፍት የነፍስ ምግቦች ናቸው!
0941555550
ድልድይ
[ዮሐንስ ተመስገን]
ተንከተም ማለት ድልድይ ማለት ነው። ድልድይ ደግሞ አገልግሎቱ መሻገሪያ ነው። ድልድይ ካለ ማዕበል አይነካም፤ የሚናውጠውን አይነካም። ጎርፍም ይሁን ቆሻሻ ቁልቁል እየተመለከቱ ያለ ፍርሃት ይሻገሩበታል።

<ተንከተም> ሊቀሊቃውንት ስምዐኮነ የኒቂያ ጉባኤን ውሳኔ ጸሎተ ሃይማኖትን ያብራሩበት መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ በተለያዩ ዘመናት የተነሡና ወደ ፊትም የሚነሡ የንስጥሮስ፤ የአርዮስ፤ የመቅዶንዮስ ... የክህደት ማዕበል አነዋውጾ እንዳያስቀር ድልድይ ሁኖ ያሻግራል። በምስጢረ ሥጋዌና በምስጢረ ሥላሴ ላይ የሚነሡ የኑ*ፋ*ቄ ጎርፎችን ከአእምሮ በታች እያሳየ በትርጓሜ ድልድይነት ያመላልሳል።

ሊቁ በክፍል ሁለት በአንቀጽ አንድ (ገጽ 62) <ነአምን በአሐዱ አምላክ> ብለው ጀመረው ገጽ 494 ላይ በአንቀጽ 12 <ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም> በማለት ጸሎተ ሃይማኖትን በ12 አናቅጽ ከፍለው አብራርተውታል።

ተንከተም ማንበብ ከምስጢር ጋር መዋል ነው። ምስጢረ ሥላሴንና ምስጢረ ሥጋዌን ላይ ሃይማኖተ አበውን ከኢትዮጵያውያን አበው ማብራርያ ጽሑፎች ጋራ እያዋደደ በጸሎተ ሃይማኖት ዙሪያ የማያዳግም መጽሐፍ ሁኖ ወጥቱዋል። ጸሐፊውን የማሳስበው ሌሎች እንዲህ ማብራሪያ የሚፈልጉ መጻሕፍትን እያዘጋጁ እንዲያቀርቡልን ነው። ለአሁኑ የኑፋ*ቄ ማዕበሉን በተንከተም እንድትሻገሩ ለማለት እወዳለሁ።
ይህ ቅጂ የሌላችሁ 15 ቅጂዎች ስላሉን በ0941555550 ደውለው መያዝ ይችላሉ።

በዚሁ አጋጣሚ በቀድሞው ከቅጽ 7 - 13 አንድ ላይ አጠቃልሎ የያዘው #ቅጽ_2 በቅርቡ ታትሞ ገበያ ላይ ይውላል።
እነዚህንና ሌሎቹን እዚህ ያገኛሉ!!
በቅርቡ ታትሞ በስርጭት ላይ ያለው ይህ መጽሐፍ ጥቂት ቅጂዎች ብቻ ቀርተውናል። ከማለቁ በፊት ገዝተው በሰሙነ ሕማማት የሚዜመውን ዜማ ትርጉም በአንድምታ ይወቁ።
0941555550
#ሰላም በብዝኀ ሃይማኖት

አከፋፋይ
ኢትዮፋጎስ የመጽሐፍ ማእከል
0941555550
#ርጢን
በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ
+251941555550