Ethiopia Election
42 subscribers
34 photos
2 videos
26 links
የኢትዮጵያ ኢንሳይደር የምርጫ ዘገባዎች - #ምርጫ2018 | Ethiopia Insider's dedicated platform for election coverage
Download Telegram
Channel created
Channel photo updated
#ምርጫ2018፤ በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎች እና መራጮች በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ የሚችሉበት መተግበሪያ እና የድረ ገጽ አማራጭ ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የዲጂታል አማራጮቹ፤ በስድስት የሀገሪቱ ቋንቋዎች ምዝገባ ለማከናወን እንዲችሉ ተደርገው መዘጋጀታቸውም ተገልጿል።

ምርጫ ቦርድ ይህን የገለጸው፤ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 27፤ 2018 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደ የዲጂታል ምዝገባ ስርዓት ይፋ ማድረጊያ ስነ-ሥርዓት ላይ ነው።

የዲጂታል ምዝገባ ሥርዓቱ የሚያገለግለው ለመመዝገብ ብቻ መሆኑን በስነ-ሥርዓቱ ላይ የገለጹት የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ድምጽ ለመስጠት ግን ሁሉም መራጭ እንደወትሮው የተመዘገበበት የምርጫ ጣቢያ መሄድ እንደሚጠበቅበት አስረድተዋል።

ምርጫ ቦርድ ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ይፋ ባደረገው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፤ የዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጪያ ዕለት ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ነው።

ይኸው የጊዜ ሰሌዳ፤ የዕጩዎች ምዝገባ ከፊታችን አርብ ጥር 1 እስከ የካቲት 1 ድረስ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወን አስቀምጧል።

በቴክኖሎጂ የሚደረገው የመራጮች ምዝገባ ከመጪው ጥር ወር አጋማሽ እስከ መጋቢት 7 ድረስ እንደሚደረግም በጊዜ ሰሌዳው ላይ ተዘርዝሯል።

ይህንን ምዘገባ ለማድረግ መራጮች “ምርጫዬ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን መተግበሪያ በሞባይል ስልካቸው ወይም በሌሎች መተግበሪያ በሚቀበሉ የኤሌክትሮኒክስ አማራጮች አውርደው መጠቀም እንደሚችሉ ገልጿል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17050/

@EthiopiaInsiderNews
Channel photo removed
#ምርጫ2018፤ በመጪው ሀገር አቀፍ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎችን ለመመዝገብ የተዘጋጀው የዲጂታል ስርዓት፤ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን “ከፉክክር ሜዳው በማውጣት ህዝብን አማራጭ አሳጥቶ ለመግዛት የታሰበ የፖለቲካ ሴራ ነው” የሚል ነቀፋ ቀረበበት።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ የምርጫ ሂደቱን “ለመጉዳት” በመስሪያ ቤቱ “ሆን ተብሎ የሚደረግ ተግባር የለም” ሲል አስተባብሏል።

ዛሬ አርብ ጥር 15፤ 2018 ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ በዲጂታል ሥርዓቱ እና በምርጫ ቦርድ የዕጩዎች ምዝገባ መስፈርቶች ላይ ተቃውሞ ያቀረቡት ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ የፓርቲዎች ስብስብ ናቸው።

ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በዚሁ መግለጫቸው “ግልጽነት በጎደለው” እና “በተድበሰበሰ የምዝገባ አሠራርና ሂደት”፤ በመጪው ግንቦት መጨረሻ የሚካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ “አሳታፊ፣ ሃቀኛ፣ ተዓማኒ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሊሆን አይችልም” ሲሉም አቋማቸውን አስታውቀዋል።

ሀገር አቀፉ ምርጫ ሊካሄድ ወራት በቀሩበት በአሁኑ ወቅት፤ በዕጩዎች ምዝገባ ጅማሮ ላይ “በርካታ ተግዳሮቶች አጋጥመውናል” ብለዋል ፓርቲዎቹ።

ከቅሬታ አቅራቢ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም ኃይማኖት፤ በዲጂታሉ አማራጭ አንድ ዕጩ መታወቂያው ከተመዘገበበት አካባቢ ውጭ ባለ የምርጫ ክልል ለተወዳዳሪነት የመመዝገብ ዕድል እንደሌለው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ማስተባበርያ ክፍል ኃላፊ ቀነኒ እንሰርሙ፤ የዕጩዎች የሰነድ ማረጋገጫ በልደት ሰርተፍኬት እና በመታወቂያ ላይ ብቻ የተመሰረተ እንዳልሆነ ምላሽ ሰጥተዋል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17213/

@EthiopiaInsiderNews
የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ክልላዊ ውክልና 👇🏿 https://bit.ly/3Md2s7q
#ምርጫ2018'ን የሚመለከቱ ወቅታዊ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን ለመከታተል ይህንን ገጽ ( @ethioelections ) ይከታተሉ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቪዲዮ፦ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚኖረውን ተጽዕኖ በተመለከተ የተለያዩ ባለድርሻዎች የተሳተፉበት ውይይት ዛሬ ሰኞ ጥር 25፤ 2018 በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው በዚህ ውይይት ላይ የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ርዕሰ መስተዳድሮችና ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የጸጥታ አካላት ተገኝተዋል።

ውይይቱ በተለያዩ ስፍራዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ ለቀጣዩ ምርጫ “አስቻይ” መሆን ወይም አለመሆኑ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ገልጸዋል።

ከቦርዱ ሰብሳቢ የመክፈቻ ንግግር በኋላ ባለው ውይይት ላይ የመገናኛ ብዙሃን እንዲታደሙ አልተፈቀደም።

በዛሬው ውይይት ላይ የ11 ክልሎች እንዲሁም የድሬዳዋ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮች የጸጥታ ሁኔታን የሚመለከት ሪፖርት እንደሚቀርብ በቦርዱ የተዘጋጀው መርሃ-ግብር ያመለክታል። ሪፖርቱ በትግራይ ክልል ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አላካተተም። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@EthiopiaElections / @EthiopiaInsiderNews
በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻ ለሚደረገው ሀገር አቀፍ #ምርጫ ወደ 17 ሺህ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ በዲጂታል መንገድ እንደሚካሔድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ይሔን ያስታወቀው ዛሬ ሰኞ ጥር 25፤ 2018 ለቀጣዩ ምርጫ የጸጥታ ሁኔታን ለመገምገም ባዘጋጀው ውይይት ላይ ነው።

በዚሁ ውይይት መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ፤ የመራጮች ምዝገባ በሶስት አይነት መንገድ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

የመጀመሪያው የተለመደው "የማኑዋል" ምዝገባ ሲሆን ሌሎቹ አሁን ቦርዱ በሚያስጀምረው አዲሱ የዲጂታል ምዝገባ የሚከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል።

የዲጂታል ምዘገባው "ምርጫዬ" በተሰኘ መተግበሪያ የሚከናወን እና በራስ የሚካሄደውን (self-registration) እና በምርጫ አካላት ድጋፍ የሚካሄደውን (assisted-voter registration) የሚያጠቃልል መሆኑን የቦርድ ሰብሳቢዋ ገልጸዋል፡፡

“የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚናከናወን በመሆኑ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በሁሉም የምርጫ ክልል መተግበር አይቻልም” ብለዋል የቦርድ ሰብሳቢዋ።

“ከመሠረተ ልማት፣ በጀትና የሰው ኃይል አቅርቦት አንጻር በተለዩ ወደ 17 ሺህ የሚጠጉ የምርጫ ክልሎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገናል” ሲሉ ሜላትወርቅ ለስብሰባው ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

ለዚህም እንዲያመች ቦርዱ ለምርጫ አስፈጻሚዎች ሥልጠና በመስጠት ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ (ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🟥 ይህን ጉዳይ በተመለከተ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የሰጡትን ማብራሪያ ይህን የቪዲዮ ሊንክ https://youtu.be/lg9jfSJfH2E ተጭነው ይመልከቱ።

@ethioelections / @EthiopiaInsiderNews
የፌደራል መንግስት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 26፤ 2018 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የፓርላማ አባላትን ጥያቄዎችን አድምጠዋል።

ከእነዚህ የፓርላማ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ተመራጭ ዶ/ር አብርሃም በርታ፤ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ ተከታታይ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።

የፓርላማ አባሉ ጥያቄ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

“የምርጫ ወቅት በንጽጽር ከቅድመ ምርጫ በተሻለ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚዲያ እድል የሚያገኙበት እንደሆነ ይታወቃል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ይህንን ሁኔታ በሚያሳጣ መልኩ የህዝብ መገናኛ ብዙኃን በዝምታ ውሰጥ ሆነው፤ የምርጫ ድባብ እንዳይኖር እና ሂደቱ በተቀዛቀዘ ሁኔታ የቀጠለበት ሁኔታ ስላለ ይህ የሆነበት ምክንያት ማብራሪያ ቢሰጥ?

በተጨማሪም መንግስት በግልጽ የፓርቲና የመንግስት ሥራ ልዩነትን ባለማስመሩ፤ እነዚህ ሚዲያዎች የገዢው ፓርቲ አገልጋይ ሆነዋል እስከሚባል ድረስ የገለልተኝነት ጥያቄ ይነሳባቸዋል። ስለዚህ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበት እኩል ሜዳ በሌለበት ሁኔታ የምርጫው ውድድር እንዴት ጤነኛ ሊሆን ይችላል?”

🟥 የፓርላማ አባሉን ሙሉ ጥያቄ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://www.facebook.com/ethioelections/posts/pfbid0du2ZLX5266ZDeDXeZ78WKjcrdX7nxnirTfWHQGiW6LBAGZ34fFfnHPhsM3Zq3X24l

[በ“ምርጫ 2018-ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተጠናቀረ]

@ethioelections/ @EthiopiaInsiderNews
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለፓርላማ አባልነት በድጋሚ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን በመወከል በባህር ዳር ከተማ ምርጫ ክልል ተመርጠው ላለፈው አራት ዓመት ተኩል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቆዩት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ በመጪው ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ። ዶ/ር ደሳለኝ ራሳቸውን ለምርጫ በዕጩነት ላለማቅረብ የወሰኑት ነጻ፣ ሰላማዊ እና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል “ምቹ መደላድል ባለመኖሩ” ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።

የፓርላማ አባሉ ይህን የገለጹት፤ የመጪው ምርጫ ተሳትፏቸውን በተመለከተ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጻቸው ዛሬ አርብ ጥር 29፤ 2018 ባሰራጩት መግለጫ ነው። ዶ/ር ደሳለኝ ባለፉት ዓመታት የባህር ዳር ከተማ በመወከል፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህዝቡ “ሀቀኛ ድምጽ” በመሆን ማገልገላቸውን በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል።

በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻ ለሚካሄደው ሰባተኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በዕጩነት መመዝገብ አለመመዝገባቸውን በተመለከተ “ተደጋጋሚ” ጥያቄዎች ሲቀርብላቸው እንደቆየ ዶ/ር ደሳለኝ በመግለጫቸው ላይ አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው ይፋዊ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፤ ጥር 1 የተጀመረው የዕጩዎች ምዝገባ ከነገ በስቲያ እሁድ ይጠናቀቃል።

ዶ/ር ደሳለኝ በመጪው ምርጫ ለመወዳደር በባህር ዳር አሊያም በአዲስ አበባ በዕጩነት እንዲቀርቡ ከ“አንዳንድ ፓርቲዎች” ዕድሉ ተሰጥቷቸው እንደነበር በዛሬው መግለጫቸው ላይ አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) ከሚመሩት አመራሮች ጋር ቅራኔ ያላቸው የፓርላማ አባሉ፤ ዕድሉን የሰጧቸውን ፓርቲዎች በስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል። 🔴ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://bit.ly/4qFiyVP
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ግንቦት መጨረሻ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚወዳደሩ ዕጩዎች ምዝገባ የሚያከናወኑበትን ጊዜ እስከ የካቲት 16፤ 2018 አራዘመ። ቦርዱ የምዝገባ ጊዜውን ያራዘመው፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቋሙ ባዘጋጃቸው የተለያዩ መድረኮች ላይ እና በጽሁፍ ጭምር ባቀረቡት ጥያቄ መሆኑን አስታውቋል።
ምርጫ ቦርድ ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ይፋ ባደረገው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ፤ የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወነው ከጥር 1 እስከ የካቲት 1 ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ነበር። በዚህ መሰረት ምዝገባው የሚጠናቀቀው ከነገ በስቲያ እሁድ ቢሆንም፤ ቦርዱ ዛሬ አርብ ጥር 29 ምሽት ባወጣው መግለጫ ለዕጩዎች የተሰጠው ጊዜ በሁለት ሳምንት መራዘሙን አመልክቷል።
ቦርዱ በዛሬው መግለጫው፤ ከዚህ ወር መጀመሪያ አንስቶ ሲካሄድ በቆየው የዕጩዎች ምዝገባ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች በተናጠል፤ 15 የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ በሁለት የተለያዩ ቅንጅቶች እና በአንድ ግንባር ስር ሆነው ተወዳዳሪዎችን ማስመዘገባቸውን ገልጿል። የግል ዕጩዎችም በተመሳሳይ መልኩ ምዝገባ እያከናወኑ መሆኑንም ጠቁሟል።
የዕጩዎቹ ምዝገባ ሲከናወን የቆየው፤ ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ባደረገው የዲጂታል ምዝገባ ስርዓት ነው። ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ ይፋ ይተደረገው ይህ ስርዓት “ለአካታችነት” እና “ተደራሽነት” ከሚኖረው ፋይዳ በተጨማሪ “የዕጩዎችን እና የመራጮችን ጊዜ እንደሚቆጥብ”፤ “አላስፈላጊ ምልልሶችን እንደሚያስቀር” እና “ወጪ ቆጣቢ” እንደሆነ ምርጫ ቦርዱ በወቅቱ አስታውቆ ነበር። #ምርጫ2018

🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://bit.ly/46qcw3P
በሰኔ 2013 ዓ.ም በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን ወክለው የፓርላማ አባል የሆኑት ዶ/ር አበባው ደሳለው፤ በመጪው ምርጫ ኢሕአፓን ወክለው ሊወዳደሩ ነው።

የአብን የአዲስ አበባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት ዶ/ር ይህዓለም ታምሩም በተመሳሳይ መልኩ የፓርቲ ለውጥ አድርገው በመጪው ምርጫ እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዛሬ ማክሰኞ ጥር 3፤ 2018 ማምሻውን በበይነ መረብ በሰጠው መግለጫ ሁለቱ ቀድሞ የአብን አባላት ፓርቲውን መቀላቀላቸውን ይፋ አድርጓል። በበይነ መረብ የተካሄደውን መግለጫ ከሁለቱ የምርጫ ተወዳዳሪዎች ጋር በመሆን የሰጡት፤ የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ሚስጥረስላሴ ታምራት ናቸው።

ሁለቱ የቀድሞ የአብን አባላት ለዘንድሮው ምርጫ በእጩነት የተመዘገቡት፤ ኢሕአፓ አባል በሆነበት “ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት” በተሰኘው የፓርቲዎች ቅንጅት በኩል መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ባለፈው መስከረም ወር የተመሰረተው ይህ የፓርቲዎች ቅንጅት፤ ከኢሕአፓ በተጨማሪ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ አባል የሆኑበት ነው።

በቅንጅቱ ተካትቶ የነበረው እናት ፓርቲ፤ በዚህ የፓርቲዎች ስብስብ ውስጥ አባል መሆኑን በተመለከተ በፓርቲው ጉባኤው ከማስጸደቅ አንጻር ያላሟላው ሂደት በመኖሩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እግድ ተጥሎበታል።

እናት ፓርቲ ሂደቱን ሲያሟላ የስብስቡ አምስተኛ አባል መሆን እንደሚችል ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል። #ምርጫ2018

🟥ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/የአብን-የፓርላማ-አባሉ-ዶ-ር-አበባው-ደሳለ-2/

@ethioelections / @EthiopiaInsiderNews
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ለመጪው ምርጫ ያዘጋጀው ማኒፌስቶ በዋናነት ትኩረት ያደረገው፤ “በመግባባት፣ በመፍታት፣ በማስፋት እና በመገንባት” ላይ መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ። የምርጫ ማኒፌስቶዉ ዋነኛ እሳቤ “ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር መትጋት” እንደሆነም ገልጸዋል።

አቶ አደም ይህን የገለጹት፤ የሰባተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ባደረገበት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 3፤ 2018 በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ ከፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች አንዱ የሆኑት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተገኝተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ እና ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት እንዲሁም የፓርቲው የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን አመራሮች በታደሙበት በዚህ መድረክ፤ ገዢው ፓርቲ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱ “የስንዴ ነዶ” መሆኑን ይፋ አድርጓል። ፓርቲው በባለፈው ምርጫ የተጠቀመበት ምልክት አምፖል እንደነበር ይታወሳል።

በስድስተኛው ዙር ምርጫ ወቅት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የሚያቀርቡበት እና የሚያስወስኑበት ጊዜ በምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ተካትቶ ነበር። ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ይፋ የተደረገው የዘንድሮው ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ግን ይህ ተግባር አልተካተተም። #ምርጫ2018

🟥ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/ብልጽግና-ፓርቲ-በመጪው-ምርጫ-የሚጠቀምበ/

@ethioelections / @EthiopiaInsiderNews
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ለቀጣዩ ምርጫ በዕጩነት ካዘጋጃቸው ተወዳዳሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ቀን እስር በኋላ ተፈቱ። አቶ የሺዋስ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 4፤ 2018 ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ ተፈትተው በስልክ እንዳነጋገሯቸው የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም ሃይማኖት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
በተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ለረዥም ጊዜ የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸው አቶ የሺዋስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፤ ትላንት ማክሰኞ ከቀኑ 8 ሰዓት ገደማ እንደነበር የኢሕአፓ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስሀቅ ወልዳይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ገልጸዋል። አቶ የሺዋስ የተያዙት ከመኖሪያ ቤታቸው ውጭ ባለ ስፍራ መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል።
ፖሊስ ፖለቲከኛውን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ወደሚገኘው ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዳቸው ማረጋገጣቸውን ጉዳዩን ሲከታተሉ የቆዩት አቶ ይስሀቅ ተናግረዋል። ኢሕአፓ ዛሬ ረፋድ ላይ ባወጣው አጭር መግለጫ፤ በቅርቡ ፓርቲውን በተቀላቀሉት በአቶ የሺዋስ ላይ የተወሰደውን የእስር እርምጃ ተችቷል።
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
🟥ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️https://bit.ly/4aIPRCh
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁሶች እሸጋ መርሀ ግብርን ለመገናኛ ብዙኃን አባላት አስጎበኘ
‎የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ተኛውን ሀገራዊ ምርጫንና በተለይም የመራጮች ምዝገባን ለማካሄድ አስፈላጊ የሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶችን የእሸጋ መርሃ ግብር በመጪዉ እሁድ እንደሚያጠናቅቅ ገለጸ።
‎ቦርዱ ዛሬ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በየኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነትና የሎጂስቲክስ አገልገሎት ቅጥር ግቢ በሚገኘዉ መጋዘን የሚካሄደውን የምርጫ ቁሳቁሶች እሸጋ መርሀ ግብርን ለመገናኛ ብዙኃን አባላት አስጎብኝቷል፡፡ ዝርዝሩን ለማንበብ 👉 https://bit.ly/3Mku4b1

#ምርጫ2018 #EthiopiaElection