የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁሶች እሸጋ መርሀ ግብርን ለመገናኛ ብዙኃን አባላት አስጎበኘ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ተኛውን ሀገራዊ ምርጫንና በተለይም የመራጮች ምዝገባን ለማካሄድ አስፈላጊ የሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶችን የእሸጋ መርሃ ግብር በመጪዉ እሁድ እንደሚያጠናቅቅ ገለጸ።
ቦርዱ ዛሬ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በየኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነትና የሎጂስቲክስ አገልገሎት ቅጥር ግቢ በሚገኘዉ መጋዘን የሚካሄደውን የምርጫ ቁሳቁሶች እሸጋ መርሀ ግብርን ለመገናኛ ብዙኃን አባላት አስጎብኝቷል፡፡ ዝርዝሩን ለማንበብ 👉 https://bit.ly/3Mku4b1
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection

የፖለቲካ ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክት ይፋ ማድረጊያ ሥነ ስርዓት ላይ ዕጩዎች የሥነ ምግባር ደንብ ፈረሙ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ለመወዳደር የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክት ማስተዋወቂያና የዕጩዎች ሥነ ምግባር ደንብ መፈራረሚያ መርሐ ግብርን ዛሬ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም አካሄደ።
በመርሐ ግብሩ የመክፈቻ ንግግራቸው የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንዳሉት የዕለቱ ትልቅ ሁነት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚወዳደሩባቸውን ምልክቶች ይፋ ማድረግና ለሕዝብ ማስተዋወቅ እንደሆነ ገልጸዋል። የምርጫ ምልክት ይፋ የማድረግያ መርሐ ግብሩ ዋና ዓላማ መራጩ ሕዝብ የሚመርጠውን ለይቶ ማወቅ እንዲችል ከምርጫ ምልክቱ ጀምሮ መረዳትና ማወቅ ስላለበት መሆኑንም ሜላትወርቅ ገልጸዋል። “በተለይም ሚዲያዎች የፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት አካታችና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንድታስተዋውቁና እንድታሳዩ ይጠበቅባቹሃል” ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በመርሐ ግብሩም ቦርዱ በ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የሚካፈሉና እጩዎቻቸውን ያስመዘገቡ 48 የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመወዳደሪያ ምልክትና ስያሜን በቅደም ተከተል በተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም የዕጩዎች ሥነ ምግባር ደንብ መፈራረሚያ መርሐ ግብር ተያይዞ ተካሄዷል፡፡ ይህንን አስመልክቶ ሜላትወርቅ “የሠለጠነ ምርጫ ለማካሄድ ሥርዓትና ደንብ ያስፈልገናል፡፡ ስለዚህ በምርጫው የሚወዳደሩ ዕጩዎችና ፓርቲዎች የሥነ ምግባር ደንቡን መፈረማቸው አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
🟥ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ👉 https://ethioelections.com/የፖለቲካ-ፓርቲዎች-የመወዳደሪያ-ምልክት/

የኢዜማው መሪ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በመጪው ሀገራዊ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወንበር መጋራት አለባቸው ሲሉ አሳሰቡ።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ-ኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ሀገርን ለማሻገር መጪው 7ተኛ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች “ወንበር የሚጋሩበት እንጂ” እንደ በፊቱ ብልጽግና ፓርቲ “99 በመቶ አሸነፍኩ” የሚልበት መሆን እንደሌለበት አሳሰቡ።ኢዜማ ትላንት የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት የዘለቀ “ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ እና ምርጫ” በሚል ርዕስ የበይነመረብ ውይይት አካሄዷል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የውይይት መነሻ አቅራቢ የነበሩት የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ እንዳሉት ምርጫው በ5 ዓመት አንድ ጊዜ የሚደረግ የሐይማኖታዊ በዓል ክንውን ሳይሆን “ካለንበት የፖለቲካ ውጥንቅጥ የምንወጣበት” ብቸኛው መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም “በዚህ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወንበር ተጋርተው የሚሻገሩበት እንጂ እንደድሮው ብልፀግና ፓርቲ 99 በመቶ አሸነፍኩ ብሎ መቀጠል ሀገርን ወደ ሚፈለገው እድገት አያሻግርም” በማለት አሳስበዋል።
ኢዜማ ለህዝብ ክፍት ባደረገው የበይነመረብ (የዙም) ውይይት ከደጋፊዎቹና ከተሳታፊዎች ለተነሱት በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የድርጅቱ መሪና የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
🟥ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ👉https://ethioelections.com/የኢዜማው-መሪ-ፕ-ር-ብርሀኑ-ነጋ-በመጪው-ሀ/

በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል “አከራካሪ ሆነው” የቆዩ የተባሉ አምስት የምርጫ ክልሎች፤ “የይገባኛል ጥያቄው እስከሚፈታ” ድረስ ከትግራይ ክልል ውጪ ሆነው ለፓርላማ “በቀጥታ” ምርጫ እንዲደረግባቸው ውሳኔ ተላለፈ። ውሳኔ የተላለፈባቸው የምርጫ ክልሎች፤ ሁመራ፣ አዲ ረመጽ፣ ጠለምት፣ ኮረም ኦፍላ እና ራያ አላማጣ ናቸው።
እነዚህ ምርጫ ክልሎች ከሁለቱ ክልሎች ውጭ ሆነው ምርጫ እንዲካሄድባቸው ውሳኔ ያሳለፈው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው። ለምክር ቤቱ ውሳኔ መንስኤ የሆነው፤ ጥር 22፤ 2018 ይፋ የተደረገው የምርጫ ክልሎች እና ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በዚህ ዝርዝር ላይ በሁመራ ምርጫ ክልል የሚገኙ ጣቢያዎች፤ በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን፣ በሰቲት ሁመራ፣ ቃፍታ ሁመራ እና ወልቃይት ወረዳዎች የሚገኙ እንደሆነ ተጠቅሶ ነበር። በአዲ ረመጽ የምርጫ ክልል የሚገኙ ጣቢያዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ በትግራይ ክልል፣ ምዕራባዊ ዞን፣ በወልቃይት እና ፀገዴ ወረዳዎች ውስጥ ያሉ መሆናቸው በዝርዝሩ ላይ ሰፍሯል።
በዚሁ ክልል፣ በተመሳሳይ ዞን ውስጥ እንደሚገኝ በምርጫ ቦርድ ዝርዝር ተጠቅሶ የነበረው የፀለምቲ ምርጫ ክልል፣ በፀለምቲ ወረዳ የሚገኝ መሆኑ በሰነዱ ተመልክቷል። በትግራይ ክልል፣ ደቡብ ዞን ስር ያሉ የምርጫ ክልሎች ሆነው የተጠቀሱት ደግሞ ኦፍላ ኮረም እና አላማጣ ናቸው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/በትግራይ-ክልል-ስር-የነበሩ-አምስት-የምር/

እናት ፓርቲ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች ዕጩዎችን ባያቀርብም በ“ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት (ለኢትዮጵያ)” ስር ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን መዘጋጀቱን አስታወቀ።
በመጪው 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ በአማራና ትግራይ ክልሎች ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት እጩዎቹን ማስመዝገብ ያልፈለገው እናት ፓርቲ፤ "ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" በተሰኘው አዲስ የፓርቲዎች ቅንጅት ውስጥ በመካተት ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን ግን እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
ፓርቲው ይህን ስትራቴጂካዊ ውሳኔ ያሳለፈው፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች መከፋፈልን እና መብዛትን በመቀነስ፣ እንዲሁም የተበታተነውን የፖለቲካ ኃይል በማዋሃድ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተሻለና አንድ ወጥ አማራጭ ለማቅረብ በማለም መሆኑን የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አቶ ጌትነት ወርቁ አብራርተዋል።
ከዚህ ጎን ለጎንም፣ እናት ፓርቲ ወደ አዲሱ ጥምረት ለመቀላቀል ባደረገው ሂደት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ውክልና እና ስንብት አለመግባባት በውይይት መፍታት መቻሉ ተገልጿል። ቦርዱ ባስቀመጠው የቁጥጥር መስፈርት መሠረት ማስተካከያዎችን በማድረግና አስፈላጊውን ሂደት በማሟላት፣ ፓርቲው ከየካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ወደ ትብብሩ መመለሱ ተረጋግጧል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️https://ethioelections.com/እናት-ፓርቲ-በአማራ-እና-ትግራይ-ክልሎች-ዕ/
[ምርጫ 2018 - በኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
#ምርጫ2018 #እናትፓርቲ #ኢትዮጵያ #ምርጫቦርድ #EthiopiaElection

ኢዜማ ብልጽግና ፓርቲ በግዳጅ ከባለሀብቶች ገንዘብ እየሰበሰበ ነው ሲል ከሰሰ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ ብልጽግና ፓርቲ ለ7ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የፓርቲው አባል ካልሆኑ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች በአስገዳጅነት ገንዘብ እየሰበሰበ መሆኑን አስታወቀ። ብልጽግና ፓርቲ የመንግሥትን መዋቅር በመጠቀም በየክፍለ ከተማውና በወረዳዎች በአካል በመሄድ እና በስልክ በማስፈራራት አባል ካልሆኑ ባለሀብቶች ገንዘብ እየሰበሰበ መሆኑ በኢዜማ መግለጫ ተገልጿል። ይህ ተግባር የምርጫ ህግን የሚጥስ እና ከሞራል ያፈነገጠ መሆኑን ኢዜማ አመልክቷል።
ኢዜማ ገዢው ፓርቲ ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እንዲያሳይ እና ከኢ-ዴሞክራሲያዊ አካሂዶች እንዲቆጠብ ጠይቋል። በተጨማሪም ኢዜማ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይህን ህገወጥ ተግባር በትኩረት በመከታተል እንዲያስቆመው እና የመንግሥት ሀብት ለፓርቲ ዓላማ መዋልን በፅኑ እንዲያወግዝ አሳስቧል። ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሁሉም ፓርቲዎች በእኩልነት የሚጠቀሙበት የምርጫ ፈንድ እንዲቋቋምም ሀሳብ አቅርቧል።
[ምርጫ 2018 - በኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
#ምርጫ2018 #ኢዜማ #ኢትዮጵያ #ብልጽግና_ፓርቲ #EthiopiaElection

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ አምስት የምርጫ ክልሎች ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው በቀጥታ የፓርላማ ምርጫ እንዲካሄድባቸው በተላለፈው ውሳኔ ላይ ጊዜያዊ የእግድ ውሳኔ አስተላለፈ። ፍርድ ቤቱ እግዱን ያስተላለፈው ከዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ የቀረበውን የእግድ አቤቱታ ተከትሎ ነው።
ስምረት ፓርቲ አቤቱታውን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው በፕሬዝዳንቱ አቶ ጌታቸው ረዳ በኩል ነው። ዛሬ ሐሙስ የካቲት 19፤ 2018 ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ለቀረበው አቤቱታ ተከሳሽ ወይም ተጠሪ የተደረገው ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሆኑን አቶ ጌታቸው በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ያጋሩት የፍርድ ቤት ሰነድ አመልክቷል።
ምርጫ ቦርድ በፍርድ ቤት አቤቱታ የቀረበበት፤ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል “አከራካሪ ሆነው” የቆዩ የተባሉ አምስት የምርጫ ክልሎችን በተመለከተ ባለፈው ሰኞ ይፋ ባደረገው ውሳኔ ነው። እነዚህ የምርጫ ክልሎች ሁመራ፣ አዲ ረመጽ፣ ጠለምት፣ ኮረም ኦፍላ እና ራያ አላማጣ ናቸው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/የምርጫ-ቦርድ-ውሳኔ-በፍርድ-ቤት-ጊዜያዊ-እ/

የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ተስፋና ስጋት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጪው 7ተኛ ሀገራዊ ምርጫ የዲጂታል መራጮች ምዝገባ ስርዓት ሊተገበር መሆኑን ማስታወቁን ተከትሎ፣ ይህ አዲስ አሰራር ከሚሰጠው ተስፋ ጎን ለጎን ስጋትንም ፈጥሯል። ቦርዱ ቴክኖሎጂው ሂደቱን ለማቀላጠፍ፣ ጊዜና ጉልበት ለመቆጠብ እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳ ይፋ ቢያደርግም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን በቅርቡ ባጠናቀቁት የዕጩዎች ዲጂታል ምዝገባ ላይ ያጋጠሟቸውን ችግሮች በመጥቀስ ስጋት እንዳላቸው ይገልጻሉ።
ፓርቲዎቹ እንደሚሉት፣ የዕጩዎች ምዝገባ ላይ የነበረው የሲስተም እና የኢንተርኔት ተደራሽነት ችግር እንዲሁም የማጽደቅ ሂደቱ መዘግየት ከፍተኛ የጊዜና የሀብት ብክነት አስከትሏል። በመሆኑም በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮችን በዲጂታል ለመመዝገብ መታቀዱ ተመሳሳይ እንቅፋቶች እንዳይፈጠሩ ሰፊ ዝግጅትና የሙከራ ስራዎች መከናወን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል። በዓለም አቀፍ ተሞክሮ መሰረትም የዲጂታል ምዝገባ ማጭበርበርን ለመከላከል ቢረዳም፣ ከሳይበር እና የግል መረጃ ደህንነት ጋር የተያያዙ ስጋቶችን በአግባቡ ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባ ጥናቶች ያሳስባሉ።
🔴ሙሉ ትንታኔውን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/የዲጂታል-የመራጮች-ምዝገባ-ተስፋና-ስጋት/
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection #digitalregistration

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በዋትስአፕ መተግበሪያ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የተቀናጁ የጠለፋ ጥቃቶች አሉ በማለት የጥንቃቄ መልዕክት አስተላለፈ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም 7ተኛውን ሀገራዊ የምርጫ ሂደትን ተገን በማድረግ፣ ዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረጉ ጠላፊዎች ሰፊ የሳይበር ጥቃት እየፈጸሙ እንደሚገኙ አስተዳደሩ በሚደርሱት መረጃዎችና የሳይበር ደህንነት ትንተናዎች ማረጋገጥ መቻሉን ገልጿል፡፡
ይህ ጥቃት በተለይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ተማሪዎችን፣ በርቀት ሆነዉ በዲጂታል አማራጮች የሚማሩ ግለሰቦችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ዒላማ ያደረገ በመሆኑ፣ መላው የዋትሳፕ ተጠቃሚ ማህበረሰብ የጥቃት ስልቶችና የመከላከያ መንገዶች በማወቅ እንዲጠነቀቅ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የባለ 6-አሃዝ ኮድ ለዋትስአፕ ተጠቃሚዎች በመላክ የምርጫ ደጋፊ በመምሰል፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደጋፊ በሚመስል መልኩ የፓርቲዎችን አርማ (Logo) በመጠቀም፣ የምርጫ መረጃ አቅራቢ በመምሰል፣
▶️ "ለፓርቲያችን ድጋፍዎን እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ይግለጹ" ፣
▶️"የምርጫ ቅስቀሳ ቡድናችንን ይቀላቀሉ" ፣
▶️ "የምርጫ ጣቢያዎትን ለማወቅ"፣
▶️ "የዕጩዎችን ዝርዝር ለማየት" ወይም
▶️ "የምርጫ ውጤቶችን በቅድሚያ ለማግኘት" የሚሉ አሳሳች ማስፈንጠሪያዎችን (Links) በመጠቀም የተጠቃሚዎችን የዋትስአፕ አካውንት በቁጥጥራቸው ስር እያዋሉ እንደሚገኙም አስተዳደሩ ገልጿል።

😁1
የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በመጪው ሀገራዊ ምርጫ ራሱን እንደ "ዕጩ መንግሥት" አድርጎ እንደሚቆጥር የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነቢሃ መሐመድ ገለጹ። ፓርቲው ለፌደራልና ለክልል ምክር ቤቶች ወደ 1,500 የሚጠጉ ዕጩዎችን ማስመዝገቡንና ዝርዝር የምርጫ ስትራቴጂ ማዘጋጀቱንም አስታውቀዋል። የምርጫ ስትራቴጂው ፓርቲው በምርጫው ውጤታማ ለመሆን የሚከተለውን አጠቃላይ ፍኖተ ካርታ እንደያዘም ገልጸዋል።
ነእፓ ለዘብተኛ ሊበራሊዝም ርዕዮተ ዓለምን የሚከተል ሲሆን፣ ከሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት ለመፍጠር ጥናት እያካሄደ መሆኑን የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም በቅርቡ አስታውቀዋል።
🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/ነእፓ-ራሱን-ዕጩ-መንግሥት-አድርጎ-እን/
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
ነእፓ ለዘብተኛ ሊበራሊዝም ርዕዮተ ዓለምን የሚከተል ሲሆን፣ ከሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት ለመፍጠር ጥናት እያካሄደ መሆኑን የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም በቅርቡ አስታውቀዋል።
🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/ነእፓ-ራሱን-ዕጩ-መንግሥት-አድርጎ-እን/
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 28፣ 2018 ዓ.ም የሚጀመረውን የመራጮች ምዝገባን ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ቦርዱ ትላንት የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም. በምርጫ ሂደት የዜጎችን ተሣትፎን ለማበረታታት “ምርጫችን ነው -ሀገር ያለኛ” የተሰኘ አዲስ የምርጫ ኅብረ ዝማሬን በይፋ ባስመረቀበት ሥነ ስርዓት ወቅት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ መራጮች ባሉበት ቦታ ሆነው "ምርጫዬ" በተሰኘውን የሞባይል መተግበሪያ መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በምርጫ ጣቢያ በመገኘት በዲጂታል እንዲሁም ከዚህ በፊት በተለመደው መልኩ መመዝገብ እንደሚችሉም ገልጸዋል። ቦርዱ ከዚህ በፊት ይፋ ባደረገው የመራጮች ምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምዝገባው እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 የሚቀጥል ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባን ከየካቲት 28 ቀን ጀምሮ እንደሚካሄድ ቢያስታውቅም፣ በሀገሪቱ በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል፣ እንዲሁም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ችግር የምርጫው ሂደት ላይ ጥላ አጥልቷል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚጠቁሙት በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ አካታች እና ፍትሃዊ ምርጫን ለማካሄድ እንቅፋት ሆኗል። ቦርዱ ከክልል መስተዳደሮችና ጸጥታ ኃይሎች ባገኘው መረጃ መሰረት በምርጫ ክልሎች ያለውን የጸጥታ ሁኔታን በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ በመመደብ ምርጫው ሊካሄድ የሚቻልባቸውን እና የማይቻልባቸውን ለይቷል። ሆኖም መረጃውም ሆነ ምደባው እስከ ምርጫው ቀን ድረስ ተቀያያሪ ሊሆን ስለሚችል ሙሉ ለሙሉ ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።
🔴ዝርዝር ትንታኔውን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/7ኛው-ጠቅላላ-ሀገራዊ-ምርጫ-ላይ-ጥላ-ያጠላው/

👍2
የ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ነገ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀምራል። ምዝገባው በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ መስተዳደሮች እንዲሁም በሐረሪ ክልል ሙሉ በሙሉ በዲጂታል የሚከናወን ሲሆን በአፋር ክልል ደግሞ ከዚህ በፊት በተለመደው በእጅ ወይም በማኑዋል የሚከናወን ይሆናል። በተቀሩት ክልሎች የመራጮች ምዝገባው በዲጂታል እና በማኑዋል አማራጮች ይካሄዳል።
የዲጂታል ምዝገባው በሁለት አይነት አማራጭ የሚከናወን እንደሆነ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። አንደኛው “ምርጫዬ” የተሰኘውን የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም መራጮች በራሳቸው ምዝገባውን የሚያከናውኑበት ነው ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ መራጮች አቅራቢያቸው በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት በምርጫ አስፈጻሚዎች እገዛ በታብሌት የሚያከናወን ነው።
ምርጫ ቦርድ ባወጣው የግዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የተመዘገቡ የዕጩዎች ቁጥር 10 ሺህ 934 እነደሆነ አሳውቋል። ቦርዱ ይህንን የዕጩዎች ቁጥር የመዘገበዉ ከ47 የፖለቲካ ፖርቲዎች እና 73 የግል ተወዳዳሪዎች መሆኑንም አሳውቋል።
ከዚህ ውስጥ 2 ሺህ 198 ዕጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ ሲሆኑ የተቀሩት 8 ሺህ 736 ደግሞ ለክልል ምክር ቤቶች የሚፎካከሩ ይሆናሉ። ዕጩዎቹ በፆታም የተገለፁ ሲሆን በዚህ መሠረት 2ሺህ 760 ሴቶች ሲሆኑ 8ሺህ 174 የሚሆኑት ደግሞ ወንዶች ናቸዉ።
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
ከዚህ ውስጥ 2 ሺህ 198 ዕጩዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ ሲሆኑ የተቀሩት 8 ሺህ 736 ደግሞ ለክልል ምክር ቤቶች የሚፎካከሩ ይሆናሉ። ዕጩዎቹ በፆታም የተገለፁ ሲሆን በዚህ መሠረት 2ሺህ 760 ሴቶች ሲሆኑ 8ሺህ 174 የሚሆኑት ደግሞ ወንዶች ናቸዉ።
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ትላንት የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ተጀምሯል። መራጮች “ምርጫዬ” በተሰኘው መተግበሪያ ለመመዝገብ የሚከተሉትን ሂደቶች መከተል አለባቸው፦
1. “ምርጫዬ” የተሰኘውን መተግበሪያ ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር በማውረድ ተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው ላይ መጫን
2. መተግበሪያውን በመክፈት ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ይመዝገቡ የሚለውን መጫን
3. የመራጭ መታወቂያቸውን ለማግኘት የፋይዳ መታወቂያ መለያቸውን በመጠቀም መግባት
4. በተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው በጸሑፍ መልዕክት የሚደርሳቸውን የፋይዳ ኮድ ወይም OTP በማስገባት የፋይዳ መረጃዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ መፍቀድ
5. የአካል ጉዳት ሁኔታን መምረጥ
6. የግል መረጃን (ሙለ ስም ከነአያት፣ የመኖርያ አድራሻና የመሳሰሉትን) መሙላት
7. በአካባቢው ካሉ የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር በመምረጥ መመዝገብ
8. በመጨተሻም በአካባቢው በነዋሪነት ያሳለፉትን ግዜ ርዝማኔ በመሙላትና የመታውቂያ ዓይነት መርጠው በመጫን የመራጭነት መታወቂያን ማግኘት ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ራስን በራስ ለመመዝገብ በተዘጋጀውና “ምርጫዬ” በተሰኘው የመራጮች ምዝገባ መተግበሪያ የሚመዘገቡ “የተወሰኑ መራጮች ቋሚ የመራጮች ቁጥር እንዳገኙ ምዝገባው የተጠናቀቀ አድርገው በመውሰድ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጭነት ካርድ” አለመውሰዳቸውን አሳወቀ።
ዛሬ የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ቦርዱ ባወጣው መግለጫ “አብዛኛው “ምርጫዬ” መተግበሪያን በመጠቀም ራስን በራስ በመመዝገብ ሂደት ቋሚ የመራጭነት ቁጥር ያገኙ መራጮች፤ የምዝገባውን ሂደት በመቀጠል” እንዲሁም በሲስተሙ አማካኝነት “ምርጫ ጣቢያቸውን መርጠው ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚያገለግለውን ካርድ” እንዳገኙ ገልጿል።
ሆኖም “የተወሰኑ መራጮች ግን ቋሚ የመራጮች ቁጥር እንዳገኙ ምዝገባው የተጠናቀቀ አድርገው በመውሰድ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጭነት ካርድ ከሲስተሙ ላይ አለመውሰዳቸውን ለመረዳት ተችሏል” ሲል ቦርዱ በመግለጫው አሳውቋል።
🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/ምርጫ-ቦርድ-በምርጫዬ-መተግበሪያ-የሚ/

የትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመመካከር፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ልዩ የምርጫ ጣቢያ የማቋቋም አሠራር እንዲቀር መወሰኑ ቅሬታ አስነሳ። ተማሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በየመኖሪያ አካባቢያቸው ሄደው እንዲሳተፉ ያስተላለፈው መመሪያ፣ ለትግበራ አዳጋችና የተማሪዎችን ተሳትፎ የሚቀንስ እንደሆነ የተለያዩ አካላት ገልጸዋል።
ሚኒስቴሩ “ተማሪዎች መርጠው ለመመለስ የሚያስፈልጋቸው ቀናት ብቻ ታስቦ እንዲፈቀድላቸው” ሲል ያሰራጨው መመሪያ፣ በተለይ በማኑዋል የመራጮች ምዝገባ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ተማሪዎች አመቺ እንዳልሆነ ተመልክቷል።
ተማሪዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ባልደረቦች እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በሰጡት አስተያየት፤ ለመመዝገብና ድምፅ ለመስጠት ሁለት ጊዜ መመላለስ በፀጥታ፣ በሎጂስቲክስ እና በኢኮኖሚክ ምክንያቶች እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም በምርጫው የመሳተፍ ዕድላቸውን በእጅጉ እንደሚቀንስ ተናግረዋል።
🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/ልዩ-የምርጫ-ጣቢያ-ዩኒቨርሲቲዎች-ውስጥ-የ/

“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) ከጥር 16 እስከ የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በምሽት ሁለት ሰዓት ዜናዎቹ ያቀረባቸውን የቅድመ ምርጫ ዘገባዎች የተመለከተ ዳሰሳ አካሄዷል። በዚህም መሰረት በመንግሥት በጀት የሚተዳደረው ይህ መገናኛ ብዙኃን ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ተመጣጣኝ እና ፍትሓዊ የዘገባ ሽፋን እንዳልሰጠ ማረጋገጥ ችሏል።
በዳሰሳው መሠረት ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ የአየር ሰዓት ከተሰጣቸው አምስት ዘገባዎች ውስጥ ሁለቱን አግኝቷል። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብልፅግና ፓርቲ ስብሰባ ላይ ምርጫን በተመለከተ ያቀረቡት ንግግር ላይ ያተኮረ ዜና ብቻውን 10 ደቂቃ በመውሰድ ከፍተኛ የአየር ሰዓት ሽፋን ሲያገኝ፣ ለፓርቲው ማኒፌስቶ እና አርማ ማስተዋወቂያ የተዘጋጀው ፕሮግራም ደግሞ 4 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በመውሰድ አራተኛ ከፍተኛ የአየር ሰዓት ሽፋን አግኝቷል።
በአንፃሩ “የመገናኛ ብዙኃንና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ ሥነ-ምግባር እና አሠራር መመሪያ ቁጥር 02/2013” በአንቀጽ 16(1) ላይ የመንግሥት ሚዲያዎች “ሁሉም ተወዳዳሪ ፓርቲዎች አቋማቸውን ለመራጭ ሕዝቡ ለማቅረብ ፍትሓዊ ዕድል እንዲያገኙ” የማድረግ ግዴታ ጥሎባቸዋል። እንዲሁም በአንቀጽ 16(6) መሠረት በምርጫ ወቅት ለሚዘጋጁ የውይይት፣ የክርክር እና የቃለ-መጠይቅ ፕሮግራሞች ተገቢ የዜና ሽፋን መስጠት እንዳለባቸው ይደነግጋል።
ሙሉ የዳሰሳውን ውጤት የሚመለከተውን ዘገባ እዚህ ያንብቡ:- https://ethioelections.com/የኢትዮጵያ-ቴሌቪዥን-የቅድመ-ምርጫ-2018-አዘጋ/
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection #EBCNews

“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ባደረገው የሚዲያ ዳሰሳ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) ከጥር 16/2018 እስከ የካቲት 15/2018 ባሉት ቀናት ውስጥ የቀረቡ የምሽት 2፡00 ሰዓት ምርጫ ነክ ዜናዎች የተሰጣቸውን አጠቃላይ ሽፋን ተመልክቷል።
ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ የአየር ሰዓት ከተሰጣቸው አምስት ዘገባዎች ውስጥ ሁለቱን አግኝቷል። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብልፅግና ፓርቲ ስብሰባ ላይ ምርጫን በተመለከተ ያቀረቡት ንግግር ላይ ያተኮረ ዜና ብቻውን 10 ደቂቃ በመውሰድ ከፍተኛ የአየር ሰዓት ሽፋን ሲያገኝ፣ ለፓርቲው ማኒፌስቶ እና አርማ ማስተዋወቂያ የተዘጋጀው ፕሮግራም ደግሞ 4 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በመውሰድ አራተኛ ከፍተኛ የአየር ሰዓት ሽፋን አግኝቷል። ከአምስቱ ከፍተኛ የአየር ሰዓት ከተሰጣቸው ዜናዎች ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚመለከት አንድም ዜና የለም።
በአንፃሩ ከአምስቱ ከፍተኛ የአየር ሰዓት ከተሰጣቸው የምርጫ ነክ ዜናዎች ውስጥ ባይገባም፣ ሕብር ኢትዮጵያ የምርጫ ማኒፌስቶ ማዘጋጀቱን የሚገልጸው ዜና 3 ደቂቃ ከ46 ሰከንድ የወሰደ የአየር ሰዓት ያገኘ እና የተናጠል የዜና ሽፋን ያገኘ ብቸኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ሆኗል። 2ኛ ከፍተኛ የአየር ሰዓት የወሰደው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምርጫ ነክ ትንታኔ ቢሆንም በፓርላማ መንግሥትን በመወከል ያደረጉት ንግግር መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለብልፅግና ፓርቲ የተሰጠ የአየር ሰዐት ተደርጎ በዳሰሳው አልተወሰደም።
ሙሉውን የዳሰሳውን ዘገባ ለመመልከት፣ የ"ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ደረገጽ ላይ ይመልከቱ፤ https://ethioelections.com/የኢትዮጵያ-ቴሌቪዥን-የቅድመ-ምርጫ-2018-አዘጋ/

“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ባደረገው የሚዲያ ዳሰሳ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) ከጥር 16/2018 እስከ የካቲት 15/2018 ባሉት ቀናት ውስጥ የቀረቡ የምሽት 2፡00 ሰዓት ምርጫ ነክ ዜናዎች ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተጠቀሱባቸውን ድግግሞሽ ተመልክቷል።
በዚህም በዜናዎቹ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተናጠል ወይም በቡድን በተጠቀሱበት ድግግሞሽ መሠረት ሲታዩ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) 6 ዘገባዎች ላይ ሥሙ በተደጋጋሚ የተጠቀሰ ቀዳሚው ፓርቲ ሆኖ ተገኝቷል። ከኢዜማ በመቀጠል ብልፅግና ፓርቲ 5 ጊዜ፣ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) 3 ጊዜ ቢጠቀሱም፣ ሌሎቹ ሰባት ፓርቲዎች ከአንድ ጊዜ በላይ አልተጠቀሱም።
ተቃዋሚዎቹ ፓርቲዎች ምንም እንኳን ሥማቸው እና እነርሱን የሚመለከቱ ጉዳዮች በዜና ዘገባዎች ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አንድ ላይ በጋራ ቢጠቀሱም፣ “ሕብር ኢትዮጵያ” የተባለ የፓርቲዎች ቅንጅት የምርጫ ማኒፌስቶ እያዘጋጀ መሆኑን የሚገልጽ የዜና ትንታኔ ከማግኘቱ በቀር የተናጠል ሽፋን ዘገባ ያገኘ ሌላ ተቃዋሚ ፓርቲ በዳሰሳው በተቃኙ ዘገባዎች ውስጥ አልታየም። ሆኖም፣ በዜና እወጃዎች ሰዓት መካከል በተደጋጋሚ ይለቀቁ በነበሩ ማስታወቂያዎች ብልፅግና ፓርቲ፣ ኢዜማ፣ እና ነእፓ የፓርቲዎቻቸውን ዝግጅት የሚመለከቱ ቃለ መጠይቆች እንደተደረጉላቸው መገንዘብ ይቻላል።
ሙሉውን የዳሰሳውን ዘገባ ለመመልከት፣ የ"ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ደረገጽ ላይ ይመልከቱ፤https://ethioelections.com/የኢትዮጵያ-ቴሌቪዥን-የቅድመ-ምርጫ-2018-አዘጋ/