Ethio con Tender
4.72K subscribers
2.66K photos
68 videos
752 files
498 links
የግንባታ ጨረታዎችን የምታገኙበት ቻናል ነው። የቻናሉ ቤተሰብ ይሁኑ!
Download Telegram
👉 ከ1447ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
***
1447ኛውን የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል ያለ ምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን በዓሉን ምክንያት በማድረግ ነገ ዓርብ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ የሚከናወነው የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎ ዝግ ይደረጋሉ፡፡

በመሆኑም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች የተገለፁት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ተገንዝበው ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
👉ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች (ቅዱስ ዑራኤል  አደባባይ ላይ እና ታች በተመሣሣይ ከቦሌ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ፣
👉ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
👉ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ለውስጥ ወደ ጋዜቦ አደባባይ ለሚመጡ (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)
👉ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ ሳንጆሴፍ መብራት ለሚመጡ ለከባድ ተሽከርካሪዎች (አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ) ሲሆን ለሌሎች ተሽከርካሪዎች (ጥላሁን አደባባይ ላይ)
👉ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ  ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች (ቡልጋሪያ መብራት ላይ)
👉ከልደታ ፀበል ውስጥ ለውስጥ ወደ አሹ ስጋ ቤት የሚያስወጣው (ልደታ ፀበል ላይ)
👉ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ)
👉ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ  መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት  (ፈረሰኛ ፖሊስ ካምፕ መብራት ላይ)
👉ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ (ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ)
👉ከበርበሬ በረንዳ ወደ ድሮ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች (ቃና ዘገሊላ ዳቦ ቤት መስቀለኛ ላይ)
👉ከመርካቶ አካባቢ በተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለሚሄዱ (ተክለ ሃይማኖት አደባባይ ላይ)
👉ከቴዎድሮስ አደባባይ በቸርችል ወደ አገር አስተዳድር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ)
👉ከ4 ኪሎ አደባባይ ወደ ውጭ ጉዳይ ለሚሄዱ (4 ኪሎ አደባባይ ላይ)
👉ከሲግናል አካባቢ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች (ሴቶች አደባባይ ላይ)
በበዓሉ ማለትም ዓርብ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ/ም ዕለት ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ የሚሆኑ ሲሆኑ ከበዓሉ ዋዜማ ምሽቱ ጀምሮ በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ህብረተሰቡ አውቆ ከዚህ ውጭ ባሉ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እያሳሰበ ማንኛውም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም ጥሪውን ያስተላልፋል። 


https://t.me/ethioconradio
1👍1
🔲 የነዳጅ ዋጋ ንረትን ለመቋቋም መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው

በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ የተፈጠረውን የነዳጅ ዋጋ ንረት ለመቋቋም መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ሲሆን፤ ከእርምጃዎች መካከል የነዳጅ ድጎማ እና ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን መቆጣጠር ይገኝበታል፡፡

ይህንን ተፅዕኖ ለመቋቋም የኢትዮጵያ መንግሥት በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚያደርገውን የድጎማ መጠን አሳድጓል።

በዚህም መሠረት በዓለም ገበያ አንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ 238 ብር ከ13 ሳንቲም እየተሸጠ ቢሆንም፣ መንግሥት ለአንድ ሊትር 98 ብር ከ33 ሳንቲም ድጎማ በማድረግ ለህዝብ በ139 ብር ከ84 ሳንቲም እንዲቀርብ እያደረገ ይገኛል።

ይህም ቀደም ሲል ከነበረው የ53 ብር ከ68 ሳንቲም የድጎማ መጠን ከፍተኛ ጭማሪ የታየበት ነው።

በተመሳሳይ ሁኔታ በዓለም ገበያ 205 ብር ከ74 ሳንቲም የሚሸጠው አንድ ሊትር ቤንዚን፣ መንግሥት የድጎማ መጠኑን በ155 በመቶ በማሳደግ በሊትር 73 ብር ከ56 ሳንቲም እየደጎመ ይገኛል።

በዚህም ምክንያት ቤንዚን ለህብረተሰቡ በሊትር 132 ብር ከ18 ሳንቲም እየቀረበ መሆኑ ታውቋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር አዳዲስ የነዳጅ ማከማቻዎች በፍጥነት ወደ ገበያ እንዲገቡና በመጠባበቂያነት ተይዞ የነበረው ነዳጅ ለስርጭት እንዲውል እየተደረገ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ከስርጭት ሰንሰለቱ ውጭ ነዳጅን በጥቁር ገበያ በሚያዘዋውሩና በህገ-ወጥ ተግባር ላይ በሚሳተፉ አካላት ላይ መንግሥት ጥብቅ የቁጥጥርና የህግ እርምጃዎችን እንደሚወስድ መግለፃቸው ይታወቃል ።

ባለፉት ቀናት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ታዲያ በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል በመሆኑም ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል። ሲሉ መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤም የከተማዋ ነዋሪዎችም አጫጭር መንገዶችን ፣በእግር በመጓዝ፣ እንዲሁም የብስክሌት አማራጮችን እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እንዲጠቀም ጥሪ አቅረበዋል ።

መንግሥት በየዓመቱ ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ በጀት በመመደብ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚያስገባ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡

(AMN)
1🙏1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 5 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
👍1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 5 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
👍1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 5 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
👍1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 9 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
1👍1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 9 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
1👍1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 10 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
1👍1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 10 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
👍1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 6 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
👍1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 6 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
2👍1
🏗 🏢የኮንስትራክሽን ሥራ አመራር ስልቶች (Construction Management Techniques)

▪️▪️▪️▪️▪️▪️

​➀ እቅድ እና የጊዜ ሰሌዳ (Planning & Scheduling)

▪️▪️▪️▪️▪️▪️

▶️ ​የሥራ ክፍፍል መዋቅር (WBS): ፕሮጀክቱን ወደ ትናንሽና ሊተገበሩ ወደሚችሉ ክፍሎች መከፋፈል።

▶️ ​ጋንት ቻርት (Gantt Charts): የሥራ ሂደትን በግራፍ ማሳያ።

📌​ክሪቲካል ፓዝ ሜተድ (CPM): ወሳኝ የሆኑ የሥራ መስመሮችን መለየት።

▶️ ​የማይልስቶን እቅድ (Milestone Planning): ዋና ዋና ግቦችን ማቀድ።
📌 ጥቅሙ: ፕሮጀክቱ በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል።

​⓶ የወጪ አስተዳደር (Cost Management)

▪️▪️▪️▪️▪️

​ዝርዝር የወጪ ግምት: እያንዳንዱ ሥራ ምን ያህል ወጪ እንደሚጠይቅ ማስላት።
▶️ የበጀት መድብ: ለተለያዩ የሥራ ክፍሎች በጀት መመደብ።

▶️ የገንዘብ ፍሰት ትንበያ (Cash flow): የገንዘብ ገቢና ወጪን መገመት።

▶️​ የወጪ ልዩነት ትንተና: ከበጀት በላይ እንዳይወጣ መቆጣጠር።

🔘 ጥቅሙ: ካልተገባ ብክነትና ከመጠን ያለፈ ወጪ ይከላከላል።

​➂ የጥራት አስተዳደር (Quality Management)

▪️▪️▪️▪️▪️

▶️​ የጥራት ማረጋገጫ (QA): ሂደቱ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ።

▶️ ​የጥራት ቁጥጥር (QC): ውጤቱ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን መፈተሽ።

▶️ ​የጥሬ ዕቃ ፍተሻና ምርመራ: ጥራታቸው የተረጋገጠ ግብዓቶችን መጠቀም።

▶️ ደረጃዎችን ማክበር: የግንባታ ሕጎችንና ዝርዝር መመሪያዎችን መከተል።

🔘 ጥቅሙ: ጠንካራና ደህንነቱ የተጠበቀ ግንባታ እንዲኖር ያደርጋል።

​⓸ የጊዜ አስተዳደር (Time Management)

▪️▪️▪️▪️▪️

▶️ የሥራዎች ቅደም ተከተል: የትኛው ሥራ ቀድሞ መከናወን እንዳለበት መለየት።

▶️ የሀብት ማመጣጠን (Resource leveling): የሰው ኃይልና መሣሪያን በጊዜው ማከፋፈል።

▶️ የሂደት ክትትል: ሥራው በምን ደረጃ ላይ እንዳለ መከታተል።

▶️​ የመዘግየት ትንተና: ለምን እንደዘገየ መለየትና መፍትሔ መፈለግ።

🔘 ጥቅሙ: ከጊዜ ሰሌዳ መውጣትን (Overrun) ያስቀራል።

​⓹ የአደጋ ስጋት አስተዳደር (Risk Management)

▪️▪️▪️▪️▪️

▶️ አደጋን መለየት: ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ ማወቅ።

▶️ አደጋን መገምገም: የችግሩን ክብደትና የመከሰት ዕድል መመዘን።

▶️ የመቀነሻ እቅድ: ችግሩን ለመቀነስ ወይም ለማስወገድ ማቀድ።

▶️ ​የመጠባበቂያ ክምችት: ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ገንዘብ ወይም ጊዜ መያዝ።

🔘 ጥቅሙ: ያልተጠበቁ እንቅፋቶችን ይቀንሳል።

​⓺ የሀብት አስተዳደር (Resource Management)

▪️▪️▪️▪️▪️
▶️​ የሰው ኃይል እቅድ: አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞችን ማደራጀት።

▶️​ የማሽነሪዎች መድብ: መሣሪያዎችን ለሚፈለገው ሥራ ማከፋፈል።

▶️ የቁሳቁስ አቅርቦት እቅድ: የግንባታ ዕቃዎች የሚገዙበትን ጊዜ መወሰን።

▶️ ​የምርታማነት ክትትል: የሥራ ቅልጥፍናን መለካት።

🔘 ጥቅሙ በግንባታ ቦታ ላይ ያለውን ብክነት ይቀንሳል።
​⓻ የግንኙነት አስተዳደር (Communication Management)
▪️▪️▪️▪️▪️
▶️ መደበኛ የጣቢያ ስብሰባዎች: ከባለሙያዎች ጋር መወያየት።
▶️ ​የሂደት ሪፖርቶች: የሥራውን ውጤት በጽሑፍ ማሳወቅ።
▶️ ባለድርሻ አካላትን ማስተናበር: ከባለቤቱና ከባለሙያዎች ጋር መናበብ።
▶️ የሰነድ ቁጥጥር: መረጃዎችንና ፕላኖችን በአግባቡ መያዝ።
🔘 ጥቅሙ: ግልጽነትንና የቡድን ሥራን ያጠናክራል።
​➇ የደህንነት አስተዳደር (Safety Management)

▪️▪️▪️▪️▪️
▶️ ​የደህንነት እቅድና ገለጻ (Toolbox talks): ለሠራተኞች የደህንነት ትምህርት መስጠት።
▶️​ የመከላከያ መሣሪያዎች (PPE): ቆብ፣ ጫማና ልብስ መጠቀምን ማረጋገጥ።
▶️ የአደጋ ትንተና: የግንባታ ቦታውን አደ ገኝነት መፈተሽ።

▶️የአደጋ ሪፖርት: አደጋ ሲከሰት በአግባቡ መመዝገብና መማር።
🔘 ጥቅሙ: ሠራተኞችንና ንብረትን ከአደጋ ይጠብቃል።
​⓽ የግዥ አስተዳደር (Procurement Management)

▪️▪️▪️▪️▪️
▶️ የአቅራቢዎች ምርጫ: ጥራት ያለው ዕቃ የሚያቀርቡ ድርጅቶችን መለየት።

▶️​ የውል አስተዳደር: ስምምነቶችንና ኮንትራቶችን መቆጣጠር።

▶️​ የዕቃዎች አቅርቦት ሰሌዳ: ዕቃዎች በሰዓቱ ጣቢያው እንዲደርሱ ማድረግ።

▶️ የመጋዘን ቁጥጥር (Inventory): ያሉትን ዕቃዎች መቆጣጠር።

📌 ጥቅሙ: በዕቃ እጥረት ምክንያት ሥራ እንዳይቆም ይረዳል።

​➉ ክትትል እና ቁጥጥር (Monitoring & Control)

▪️▪️▪️▪️▪️
👉​የአፈጻጸም መለኪያዎች (KPIs): ውጤታማነትን መለካት።

👉​የተከናወነ ሥራ ዋጋ (EVM): ከወጪ አንጻር የተሠራውን ሥራ መመዘን።

👉​የጣቢያ ኦዲት: ሥራው በትክክል መከናወኑን መፈተሽ።

👉​የማስተካከያ እርምጃዎች: ስህተት ሲኖር ወዲያውኑ ማረም።

🔘 ጥቅሙ: ፕሮጀክቱ በታለመለት መስመር እንዲሄድ ያደርጋል።

https://t.me/ethioconradio
3
ምሽት 2:00 - 3:30 በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ይጠብቁን!
👏1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 13 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
2
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 13 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
1
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 13 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
2
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 12 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
2
✴️ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 11 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ethioconbid
2
የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲቲውት እና ዓለም አቀፍ የፕሮጃክት አስተዳደር በኢትዮጵያ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዴኤታ የትምጌታ አስራት(ዶ/ር)  የኢትዮጵያ የፕሮጃክት አፈጻጸም በየጊዜው በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣቱን ገልጸው ለዓብነትም በአዲስ አበባ ከተማ አለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟሉ ፕሮጀክቶች ተሰርተው በመጠናቀቃቸው የሚታይ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ተናግረዋል።

ዓለም አቀፍ የፕሮጃክት አስተዳደር በኢትዮጵያ (PMI Ethiopia Chapter) እንዲሁም በ2026 በተመሳሳይ ከአፍሪካ ከተወከሉ ተቋማት ጋር በተጠናከረ መልኩ አብሮ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡

የስምምነት ሰነዱ (MOU) በዋናነት በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋና ዋና ሁነቶችን በጋራ ማዘጋጀት፣ ሁለቱ ተቋማት ተደራሽነታቸውን በተለያዩ ሴክተር ተቋማት ላይ ማስፋት፣ በሚሰሩ የፕሮጀክት ስራዎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዞ መስራት ላይ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት (CMI) እና ዓለም አቀፍ የፕሮጀክት አስተዳደር በኢትዮጵያ (PMI Ethiopia Chapter) በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት  ሰነድ ተፈራርመዋል።

ተቋማቱ የተፈራረሙት የስምምነት ሰነድ የስልጠናና የልምድ፣ የዕውቀትና የትብብር ስራዎችን  በቅንጅት በመስራት በቀጣይ ሀገራዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል፡፡

በ2026 በአለም አቀፍ ፕሮጀክት አስተዳደር የተወከሉ የየቻርተሩ ፕሬዝዳንቶች አዲስ አበባ ከተማን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት እጅግ የሚያስደስት እና ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት የሆኑ ስራዎች እንደተሰሩ እና ከተማዋን በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

(ከመልሚ)
2