" በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ ይቆማል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።
ይህ ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነስርዓት ባከናወነበት ወቅት ነው።
በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጠንካራ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደገለፁት፤ በሚቀጥሉት ዓመታት የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ምደባ እንደሚያቆምና የማለፊያ ነጥብ የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች በሚፈልጓቸው ዩኒቨርሲቲዎችና የትምህርት መስኮች እንዲያመለክቱ ይደረጋል፡፡
" የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደከዚህ ቀደሙ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ ሳይሆን በተማሪዎቹ ምርጫ ይሆናል " ብለዋል።
" ተማሪዎች የሚማሩበትን ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡም ምክንያታዊ በመሆን በዬትኛው ዩኒቨርሲቲ የተሻለ የትምህርት መስክ፣ እውቀትና የስራ እድል ላገኝ እችላለሁ በማለት ይመርዝታሉ " ሲሉ ገልጸዋል። #ኢፕድ
@ethioaplus

የቴክኒክና ሙያ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።
የኢፌዲሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባደረሰን መረጃ መሠረት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው መስፈርቱን የሚያሟሉ በሙሉ ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በመሄድ መሰልጠን እንደሚችሉ አሳውቋል።
የመግቢያ ነጥቦቹ:-
ለደረጃ 5 ወንዶች179 እና ከዚያ በላይ
ሴቶች 168 እና ከዚያ በላይ
ለደረጃ 3እና4 ወንዶች135 እና ከዚያ በላይ
ሴቶች 122 እና ከዚያ በላይ
ለደረጃ 1እና2 ወንዶች134 እና ከዚያ በታች
ሴቶች 121 እና ከዚያ በታች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።
የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።
ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ፣ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ ላይ ተቃዉሞ እያሰሙ ነዉ
የትምህርት ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ፣ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን መናገራቸውን ተከትሎ፣ ትናንት ሰኞ ኅዳር 8 ባንዳንድ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ዋዜማ ሰምቻለሁ ስትል ዘግባለች።
የተማሪዎች ተቃውሞ ከተቀሰቀሰባቸው ከፍተኛ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት መካከል አምቦ፣ አርሲ፣ ቡሌ ሆራ፣ ሰላሌ፣ መደ ወላቡ እና ድሬዳዋ ዪኒቨርሲቲዎች እንደሚገኙበት ዋዜማ ከደረሷት መረጃዎች ተረድቻለሁ ብላለች።
ተቃውሞ ያሰሙት ተማሪዎች ካስተጋቧቸው መፈክሮች መካከል፣ "የመምህርነት ሙያ ሥልጠና ያልወሰዱ ተማሪዎችን የማስተማር ብሄራዊ አገልግሎት ስጡ ማለት ተቀባይነት የለውም" የሚለው እንደሚገኝበት ምንጮች ነግረውኛል ብሏል ዘገባው።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከሰሞኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በአዲሱ መመሪያ ዙሪያ ባደረጉት ገለጻ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ተመራቂዎች የአንድ ዓመት የማስተማር ስነ ዘዴ ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ጠቁመው ነበር።

አዲስ የትምህርት ደንብ‼️ እስከ 150,000 ብር የሚደርስ ቅጣት እና የባህል ጥበቃ‼️
የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታወቀ።
ይህ ደንብ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች እና ዓላማዎች:
* የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እስከ 150,000 ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተመላክቷል።
ደንቡ እየጨመሩ የመጡትን አዋኪ ጉዳዮች ከመግታት ባሻገር፣ ከኢትዮጵያውያን ወግና ልማድ ጋር ይቃረናሉ ተብለው የተለዩ የውጭ ባህላዊ ልማዶችን በትምህርት ተቋማት አካባቢ መፈጸም ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።
ዋንኛው ዓላማ በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ጉዳዮችን በመከላከል፣ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀና ግብረ-ገብነትን የተላበሰ ብቁ ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል ነው።
የተከለከሉ የውጭ ባህላዊ ድርጊቶች ምሳሌዎች:
አዲሱ ደንብ የሀገሪቷን ባህልና ወግ ይቃረናሉ ተብለው በግልጽ የዘረዘራቸውን አሉታዊ መጤ ድርጊቶችንና ክብረ በዓላትን ይከለክላል።
ከእነዚህም መካከል:
* Crazy Day
* Gentle Day
* Olds Day
* Valentine Day
* Color Day
* Pyjama Day የሚሉት ይገኙበታል።
@Ethioaplus

❤1
የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በሌላ በኩል ፦
- የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም
- የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም
- የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም
- የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ይሰጣል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም
@ethioplus

Adobe Photoshop 2023 v24.0 Multilingual.part2.rar
1.2 GB
Adobe Photoshop 2023
Forwarded from Ethio A+
✅መሳሳትህን አትጥላው ፣መውደቅም መሸነፍ አይደለም፤ ግን አንድ ነገር አስታውስ የተሸነፍከው ያቆምክ እለት ነው!
⚡ማርቲን ሉተርም በአስገራሚ ንግግሩ እንዲህ ብሏል "መሮጥ ቢያቅትህ ተራመድ መራመድ ቢያቅትህ ዳዴ በል ዳዴ ማለት ቢያቅትህ ተንፏቀቅ ግን በፍፁም #እንዳታቆም!"
@ethioaplus
⚡ማርቲን ሉተርም በአስገራሚ ንግግሩ እንዲህ ብሏል "መሮጥ ቢያቅትህ ተራመድ መራመድ ቢያቅትህ ዳዴ በል ዳዴ ማለት ቢያቅትህ ተንፏቀቅ ግን በፍፁም #እንዳታቆም!"
@ethioaplus
Forwarded from Ethio A+
✳️ በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች! 😊
🔰 ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው ። ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለመድረግ ያስችለናል። ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያረገናል ። ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ:
•📌 አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ።
•📌 በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ።
•📌 የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ።
📌• ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት። እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው። ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤
🙌🏾 ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤
🎯• ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።
🎯• ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ። እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ።
🎯 • ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል። ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
🎯• ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።
🎯• የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።
🔰 ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤
🍁 • ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
🍁• አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።
🍁• ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።
🍁 • በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ።
ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር፡፡ ለምሳሌ ;አሁን ደህና ነኝ ፥ ጥሩ ሆኛለሁ ወይም በምናምነው ሀይማኖት ጊዜ የማይወስድብንን አጭር ፀሎት በልባችን መፀለይ። ከዛም መልሰን በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን መጀመር።
🍁• ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤
🍁 • በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።
🍁• ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
🍁• በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት።
https://t.me/ethioaplus

A compound that produces hydrogen ions in solution is a (an)
Anonymous Quiz
78%
Acid
1%
Salt
13%
Base
7%
Polymer
ሕልም ሲኖርህ፣ መንገዱ ራሱ ይከፈታል።
ለረጅም ጊዜ ሲዘጋጅ የነበረው ነገር አሁን እውን ሊሆን ነው።
ምትጠብቀው ላይሆን ይችላል — ግን የሚፈልገው ነው።
👉 @ethioaplus
ለረጅም ጊዜ ሲዘጋጅ የነበረው ነገር አሁን እውን ሊሆን ነው።
ምትጠብቀው ላይሆን ይችላል — ግን የሚፈልገው ነው።
👉 @ethioaplus
#ExitExam
በ2018 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ በድጋሚ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የምትፈተኑ ተማሪዎች፤ ከዚህ በታች በተገለጸው ሊንክ (Link) በመጠቀም፣ የ750 ብር ክፍያ በቴሌብር በመፈጸም ቁጥሩን (Transaction Number) በማስገባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
http://exam.ethernet.edu.et/

exam.ethernet.edu.et
Ministry of Education
Ministry of Education | National GAT
Exit Exam
የዳግም ተፈታኞች ምዝገባ ጀምሯል
http://exam.ethernet.edu.et/
ለምዝገባ የባለፈው ፈተና ላይ ከትምህርት ቤት የወሰዳቹት username ያስፈልጋል

#Update
ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በሚሰጥባቸው የጊዜ መርሐግብር ላይ ማሻሻያ መደረጉን ሰምተናል።
በዚህም፥
➫ የሪሚዲያል ፈተና ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም
➫ የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም
➫ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም የሚሰጡ መሆኑ ተገልጿል።
ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የመርሐግብር ለውጡን ከዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ለማረጋገጥ ችሏል። የመርሐግብር ለውጥ መደረጉን የተወሰኑ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻቸው እያጋሩ ይገኛሉ።