Ethio A+
255 subscribers
211 photos
10 videos
203 files
98 links
A+ is Possible!
Feel free to ask and give any suggestion!
@EthioAplus_admin

https://youtube.com/@ethioa_plus?si=DekKjJasKzd5Oaq-
Download Telegram
#Update

ከፊዚክስ ትምህርት ፈተና  ጋር በተያያዘ በውጤት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ተስተካከለ።

በሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለተኛው ዙር የፊዚክስ ፈተና 60ው ወደ 100 ሳይየቀር በመቀመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው መውረዱን ጠቁመው መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር።

የውጤት ችግሩ ዛሬ መስተካከሉን እና ከ100 ተቀይሮ መቀመጡን ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ችግሩ መስተካከሉን ከክልል ትምህርት ቢሮዎችም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሌላ በኩል ፤ መጀመሪያው ዙር የማሕበራዊ ሳይንስ የኢኮኖሚክስ ፈተና ውጤትም ችግር ያለበት እንደሆነ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

በርካታ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች የሌሎች ትምህርታቸው ውጤታቸው ከፍተኛ ሆኑ የኢኮኖሚክስ ውጤታቸው እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ መቀመጡን ገልጸዋል።

ከማህበራዊ ሳይንስ ሒሳብ ፈተና ጋር በተያያዘ ውጤት ላይ ችግር እንዳለ ተማሪዎች ገልጸዋል። እሱም እንዲታይላቸው አመልክተዋል።

@ethioaplus
#MoE

300 ነጥብ የነበረው የየኒቨርሲቲ መግቢያ ወደ 297 ተጠጋጋ

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በአማካይ ውጤታቸው 49.50 - 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ የሚጠጋጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፥ ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ ያሟሉ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን መስከረም 20/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል። 

በመሆኑም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስተሩ ገልፀዋል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ያረጋገጠ ሲሆን፤ በዚህ ውሳኔ መሠረት 300 ነጥብ የነበረው የየኒቨርሲቲ መግቢያ ወደ 297 የተጠጋጋ መሆኑን ተረድተናል።

@ethioaplus
የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የRemedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን አሳውቋል።

1.  በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ።

የመቁረጫ ነጥብ ፦

➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216

➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204

➡️ ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

➡️ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

➡️ ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165

#MoE

@ethioaplus
የዩኒቨርሲቲ ምደባ‼️
የዩኒቨርስቲ ምደባ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
የዩኒቨርስቲ ምደባችሁን በእነዚህ ሊንኮች ማየት ትችላላችሁ👇👇
Website:  https://student.ethernet.edu.et
Telegram bot: @moestudentbot


@ethioaplus
Welcome to Ethio A+ tutoring
🧑‍🎓 Students / Parents:
➡️ Find your tutor here: https://forms.gle/cXyMrvfhe8VpYeqS7

🧑‍🏫 Tutors:
➡️ Register here: https://forms.gle/8gsPGR4zSrRySHpE6

📞 Questions? Message us on Telegram @karl_u7
1
" በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ ይቆማል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።

ይህ ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነስርዓት ባከናወነበት ወቅት ነው።

በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጠንካራ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደገለፁት፤ በሚቀጥሉት ዓመታት የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ምደባ እንደሚያቆምና የማለፊያ ነጥብ የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች በሚፈልጓቸው ዩኒቨርሲቲዎችና የትምህርት መስኮች እንዲያመለክቱ ይደረጋል፡፡

" የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደከዚህ ቀደሙ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ ሳይሆን በተማሪዎቹ ምርጫ ይሆናል " ብለዋል።

" ተማሪዎች የሚማሩበትን ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡም ምክንያታዊ በመሆን በዬትኛው ዩኒቨርሲቲ የተሻለ የትምህርት መስክ፣ እውቀትና የስራ እድል ላገኝ እችላለሁ በማለት ይመርዝታሉ " ሲሉ ገልጸዋል። #ኢፕድ

@ethioaplus
Forwarded from Ethio A+
Order of adjective with rules
የቴክኒክና ሙያ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የኢፌዲሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባደረሰን መረጃ መሠረት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው መስፈርቱን የሚያሟሉ በሙሉ ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በመሄድ መሰልጠን እንደሚችሉ አሳውቋል።

የመግቢያ ነጥቦቹ:-

ለደረጃ 5           ወንዶች179 እና ከዚያ በላይ
                        ሴቶች 168 እና ከዚያ በላይ

ለደረጃ 3እና4    ወንዶች135 እና ከዚያ በላይ
                        ሴቶች 122 እና ከዚያ በላይ

ለደረጃ 1እና2    ወንዶች134 እና ከዚያ በታች
                        ሴቶች 121 እና ከዚያ በታች

@ethioaplus
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

@ethioaplus
ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ፣ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ ላይ ተቃዉሞ እያሰሙ ነዉ

የትምህርት ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ፣ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን መናገራቸውን ተከትሎ፣ ትናንት ሰኞ ኅዳር 8 ባንዳንድ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ዋዜማ ሰምቻለሁ ስትል ዘግባለች።

የተማሪዎች ተቃውሞ ከተቀሰቀሰባቸው ከፍተኛ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት መካከል አምቦ፣ አርሲ፣ ቡሌ ሆራ፣ ሰላሌ፣ መደ ወላቡ እና ድሬዳዋ ዪኒቨርሲቲዎች እንደሚገኙበት ዋዜማ ከደረሷት መረጃዎች ተረድቻለሁ ብላለች።

ተቃውሞ ያሰሙት ተማሪዎች ካስተጋቧቸው መፈክሮች መካከል፣ "የመምህርነት ሙያ ሥልጠና ያልወሰዱ ተማሪዎችን የማስተማር ብሄራዊ አገልግሎት ስጡ ማለት ተቀባይነት የለውም" የሚለው እንደሚገኝበት ምንጮች ነግረውኛል ብሏል ዘገባው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከሰሞኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በአዲሱ መመሪያ ዙሪያ ባደረጉት ገለጻ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ተመራቂዎች የአንድ ዓመት የማስተማር ስነ ዘዴ ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ጠቁመው ነበር።

@ethioaplus
አዲስ የትምህርት ደንብ‼️ እስከ 150,000 ብር የሚደርስ ቅጣት እና የባህል ጥበቃ‼️

የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታወቀ።

ይህ ደንብ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።

ዋና ዋና ነጥቦች እና ዓላማዎች:
* የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እስከ 150,000 ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተመላክቷል።

ደንቡ እየጨመሩ የመጡትን አዋኪ ጉዳዮች ከመግታት ባሻገር፣ ከኢትዮጵያውያን ወግና ልማድ ጋር ይቃረናሉ ተብለው የተለዩ የውጭ ባህላዊ ልማዶችን በትምህርት ተቋማት አካባቢ መፈጸም ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።

ዋንኛው ዓላማ በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ጉዳዮችን በመከላከል፣ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀና ግብረ-ገብነትን የተላበሰ ብቁ ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል ነው።

የተከለከሉ የውጭ ባህላዊ ድርጊቶች ምሳሌዎች:
አዲሱ ደንብ የሀገሪቷን ባህልና ወግ ይቃረናሉ ተብለው በግልጽ የዘረዘራቸውን አሉታዊ መጤ ድርጊቶችንና ክብረ በዓላትን ይከለክላል።

ከእነዚህም መካከል:
* Crazy Day
* Gentle Day
* Olds Day
* Valentine Day
* Color Day
* Pyjama Day የሚሉት ይገኙበታል።

@Ethioaplus
1
የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፦

- የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም

- የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም

- የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም

- የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ይሰጣል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም

@ethioplus
Forwarded from Ethio A+
መሳሳትህን አትጥላው ፣መውደቅም መሸነፍ አይደለም፤ ግን አንድ ነገር አስታውስ የተሸነፍከው ያቆምክ እለት ነው!

ማርቲን ሉተርም በአስገራሚ ንግግሩ እንዲህ ብሏል "መሮጥ ቢያቅትህ ተራመድ መራመድ ቢያቅትህ ዳዴ በል ዳዴ ማለት ቢያቅትህ ተንፏቀቅ ግን በፍፁም #እንዳታቆም!"

@ethioaplus
Forwarded from Ethio A+
✳️ በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች! 😊

🔰 ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው ። ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለመድረግ ያስችለናል።  ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያረገናል ።  ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ: 
📌 አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ።

📌 በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ። 

📌 የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ።

📌• ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት።  እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው።  ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤

🙌🏾 ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤

🎯• ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። 

🎯• ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ።  እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ።

🎯 • ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል።   ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። 

🎯• ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። 

🎯• የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።

🔰 ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤

🍁 • ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።  

🍁• አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። 

🍁• ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።

🍁 • በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ።
ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር፡፡ ለምሳሌ ;አሁን ደህና ነኝ ፥ ጥሩ ሆኛለሁ ወይም በምናምነው ሀይማኖት ጊዜ የማይወስድብንን አጭር ፀሎት በልባችን መፀለይ። ከዛም መልሰን በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን መጀመር። 

🍁• ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤

🍁  • በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።

🍁• ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። 

🍁• በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን  መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት።


https://t.me/ethioaplus
1
Forwarded from Ethio A+
A compound that produces hydrogen ions in solution is a (an)
Anonymous Quiz
78%
Acid
1%
Salt
13%
Base
7%
Polymer
Happy Monday!
መልካም የትምህርት ሳምንት ይሁንልዎ🙏

@ethioaplus