#ወላይታሊቃ
ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ያስፈተናቸውን ሁሉንም ተማሪዎች በከፍተኛ ውጤት በማሳለፍ ውጤታማነቱን አስቀጥሏል፡፡
የትምርት ቤቱ የዓመቱ ከፍተኛ ውጤት 560/600 (93%) ላይ ሲሆን ይህም በትምህርት ቤቱ ታሪክ ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል::
እንኳን ደስ አላችሁ!
@ethioaplus

👏3
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቆ እየጠበቀ መሆኑን ገልጿል፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ መመዘኛና መስፈርት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩ ይታወቃል።
በመሆኑም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመስከረም 05-09/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በዩኒቨርሲቲው ፖርታል (https://portal.aau.edu.et) አማካኝነት መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡
በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፣ ሰዓት እና የፈተና ማዕከላት በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ መገናኛ ገፆች እና በተቋሙ ይፋዊ ድረገፅ እንደሚገለፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡

Write all ur critical questions here in comment section, I will tryna help u!
@ethioaplus
#Attention
📣በ2018 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብታችሁ መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች ግልጽ እና አጠቃላይ መረጃ:-
📍መስከረም 9- Apply የማድረጊያ የመጨረሻ ቀን (በሾላርሺፕ ሚመዘገቡትን ጨምሮ)
📍 መስከረም 10 - የመፈተኛ ቦታ ምደባ
📍ከመስከረም 12- 14 - UAT ፈተና ይሰጣል
📍መስከረም 16 - የUAT ፈተና ውጤት ይለቀቃል
📍 መስከረም 19 - የተማሪዎች campus ምደባ ይለቀቃል
📍 መስከረም 22 - ለሁሉም Freshman ኦረንቴሽን ይሰጣል
📍መስከረም 22-23 - የአዲስ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ይካሔዳል
📍 መስከረም 24 - የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ
📍 መስከረም 26 - የሁሉም አዲስ የመጀሪያ አመት Class ይጀመራል።
በዚህ መሰረት ራሳቹህን አዘጋጁ::

👏2
"የኦሽዊትዝ ሚስጢር" እና ዶክተር ሜንጌሌ
"የኦሽዊትዝ ሚስጢር" በሚል ርእስ የሚጠራ መጽሐፍ ታስታውሳላችሁን? አዎን! በሕይወቴ እየዘገነነኝና ሰውነቴን እየነዘረኝ ካነበብኳቸው መጻሕፍት አንዱ በዚህ ርእስ የተሰየመ ነው። መጽሐፉ የጀርመኖቹ የናዚ መንግሥት "ኦሽዊትዝ" (Auschwitz) በሚባለው የማጎሪያ ካምፕ በሰው ልጆች ላይ የሰራውን የተለያዩ የስቃይ ዓይነቶችና ድርጊቶች በዝርዝር የሚተርክ ኢ-ልብወለድ ድርሰት ነው።
----
ያንን መጽሐፍ ያነበበ ሁሉ በደንብ የሚያስታውሰው አንድ ጨካኝ ግለሰብ አለ። ይህም ከላይ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ሰው ነው። ዶክተር ጆሴፍ ሜንጌሌ ይባላል። በእርሱ እጅ ወድቀው ልዩ ልዩ ስቃዮችን የተቀበሉና ከኦሽዊትዝ ግድያ የተረፉ ህያዋን "መልአከ ሞት" የሚል ቅጽል ስም አውጥተውለታል።
ዶክተር ሜንጌሌ በኦፊሴል የተሰጠው የስራ መደብ "በኦሽዊትዝ ያለውን ማህበረሰብ ጤና ማስተባበር" የሚል ነበር። እርሱ ግን የሚታወቀው በዚህ ሙያው አይደለም። በካምፑ በቆየበት የሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ በኦሽዊትዝ በታጎሩ የስቃይ ሰላባዎች ላይ አሰቃቂ እና አጸያፊ የጤና ምርምር (experiment) ሲሰራ ነው የኖረው።
የዶክተር ሜንጌሌ ምርምር የሳይንስንም ሆነ የጤና ህግጋትን የተከተለ አይደለም። ሰዎችን በቁማቸው እያሉ ቆዳቸውን እየገፈፈና ሰውነታቸውን እየበለተ ምርምር ያካሄድባቸዋል። የትኩስ ሬሳዎችን አንገት እየቀነጠሰ እና የሆድ እቃ እየቆራረጠ እንደ ታክሲደርሚ ይደረድራቸዋል።
በሌላ በኩል ዶክተር ሜንጌሌ "ያገኘሁት አዲስ ክትባት የሚሰራ መሆኑን ልሞክር" እያለ በኦሽዊትዝ የታጎሩ ሰዎችን ከብዙ ኬሚካሎች የተቀመመ ነገር በመርፌ ይወጋቸዋል። በዚህም ብዙዎች ሞተዋል። ታዲያ ሜንጌሌ " መድሃኒቱ አይሰራም" ብሎ መተውን አያውቅም።
" ኬሚካሉን በመጠንና በዓይነት እየቀያየረ በሌሎች ጤነኛ ሰዎች ላይ ይሞክራል። በዚህም በርካታ ተጨማሪ ሰዎች ይሞቱ ነበር።
የዶክተር ሜንጌሌ ምርምር አዲስ መድሃኒት በመሞከር ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። ጤነኛ ሰዎችን በበሽታ አምጪ ተውሳኮች ጭምር እየበከለ ምርምር ያካሂድባቸው ነበር። ለምሳሌ የታይፎድ ወይንም የሳባ ነቀርሳ ወረርሽኝ በጀርመን ግዛቶች ውስጥ ከተከሰተ ሜንጌሌ "ለበሽታው መድሀኒት መፈለግ አለብኝ" ይልና ወደ ኦሽዊትዝ የሚመጡ ጤነኞችን በበሽታው እየበከለ ምርምር ያካሂድባቸዋል። በዚህም እጅግ ብዙ ሰዎች አልቀዋል።
የዶክተር ሜንጌሌ ዋነኛ ምርምር ግን ከላይ የተገለጸውም አይደለም። የምርምሩ ዋነኛ ዘርፍ በመንትዮች ላይ ያተኮረ ነው። ይህንንም የሚያደርገው "የጀርመን ዝርያ ያላቸው ሰዎችን አብዝተን አውሮጳን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አለብን" በሚል ሐሳብ ነው። በዚህም የተነሳ ወደ ኦሽዊትዝ የሚደርሱ መንትያዎች ከፍተኛ ስቃይ ይደርስባቸው ነበር።
በኦሽዊትዝ ካምፕ በሜንጌሌ እጅ ከፍተኛ ከፍተኛ ስቃይ የተቀበሉት አይሁዶች፣ የጂፕሲ (ሮማኒ) ተወላጆች፣ ስላቮች፣ ኮሚኒስቶች፣ የግራ ፖለቲካ አቀንቃኞች፣ የናዚ ተቃዋሚ የሆኑ የጀርመን ዜጎች እና የጦር ምርኮኞች (POW) ነበሩ።
እዚህ ላይ ሁለት አስገራሚ ነጥቦችን መጨመር ያሻል። ዶክተር ሜንጌሌ ዲግሪውን በስርቆት ያገኘ ግለሰብ አይደለም። በተማረበት ዩኒቨርሲቲ genius ተብሎ የተሸለመ የጤና ሳይንስ ምሩቅ ነበር። በተጨማሪ ደግሞ በአንትሮፖሎጂ የዶክትሬት ዲግሪ የነበረው ምሁር ነበር። የናዚ ፓርቲን በ1937 እስኪቀላቀል ድረስ በታካሚዎች የተደነቀና የተከበረ ሃኪም ሆኖ ሰርቷል። እብደቱም ሆነ ጭካኔው የመጣበት የናዚ አባል ከሆነ በኋላ ነበር።
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ እርሱ አባባል የሆነበት SS (Shzestaffell) የተባለው የናዚ ፓርቲ ቅርንጫፍ ሜንጌሌ የሰራቸውን አሰቃቂ የምርምር ስራዎች በማሞገስ "ሀገሩን በሚገባ ያገለገለ ጀግና ዶክተር" በማለት የከፍተኛ ደረጃ ሜዳሊያ ሸልሞታል።
-----
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ በኑረንበርግ ከተማ የተሰየመው ዓለም አቀፍ ችሎት የሁለተኛ ደረጃ ተከሳሽ ካደረጋቸው የናዚ ወንጀለኞች መካከል አንዱ ዶክተር ጆሴፍ ሜንጌሌ ነበር። ይሁን እንጂ ሜንጌሌ ዱካው ሊገኘ አልቻለም። በኦሽዊትዝ የነበሩትና ለእርሱ ረዳት ሆነው በግዴታ የሰሩት ሁሉ ለፍለጋ ቢሰማሩም ሊያገኙት አልቻሉም።
ሜንጌሌ ከጦርነቱ በኋላ ራሱንና ስሙን ደብቆ በአርጀንቲና፣ በፓራጓይ እና በኮሎምቢያ ይኖር ነበር። በስተመጨረሻው ግን የብራዚልም ሆነ የላቲን አሜሪካ ትልቅ ከተማ በሆነችው ሳኦ ፓውሎ እየኖረ በ1979 በስትሮክ ተመትቶ ሕይወቱ አልፏል። ታዲያ ሰውዬው በላቲን አሜሪካ ይኖር እንደነበረ የታወቀው እርሱ ከሞተ ከአስራ ሶስት ዓመታት በኋላ በ1992 ነበር።
©ተጻፈ በአፈንዲ ሙተቂ!!

#Update
ከፊዚክስ ትምህርት ፈተና ጋር በተያያዘ በውጤት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ተስተካከለ።
በሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለተኛው ዙር የፊዚክስ ፈተና 60ው ወደ 100 ሳይየቀር በመቀመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው መውረዱን ጠቁመው መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር።
የውጤት ችግሩ ዛሬ መስተካከሉን እና ከ100 ተቀይሮ መቀመጡን ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ችግሩ መስተካከሉን ከክልል ትምህርት ቢሮዎችም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በሌላ በኩል ፤ መጀመሪያው ዙር የማሕበራዊ ሳይንስ የኢኮኖሚክስ ፈተና ውጤትም ችግር ያለበት እንደሆነ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።
በርካታ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች የሌሎች ትምህርታቸው ውጤታቸው ከፍተኛ ሆኑ የኢኮኖሚክስ ውጤታቸው እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ መቀመጡን ገልጸዋል።
ከማህበራዊ ሳይንስ ሒሳብ ፈተና ጋር በተያያዘ ውጤት ላይ ችግር እንዳለ ተማሪዎች ገልጸዋል። እሱም እንዲታይላቸው አመልክተዋል።

#MoE
300 ነጥብ የነበረው የየኒቨርሲቲ መግቢያ ወደ 297 ተጠጋጋ
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በአማካይ ውጤታቸው 49.50 - 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ የሚጠጋጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
በዚህም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፥ ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ ያሟሉ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን መስከረም 20/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል።
በመሆኑም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስተሩ ገልፀዋል።
ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ያረጋገጠ ሲሆን፤ በዚህ ውሳኔ መሠረት 300 ነጥብ የነበረው የየኒቨርሲቲ መግቢያ ወደ 297 የተጠጋጋ መሆኑን ተረድተናል።

የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ።
ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የRemedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን አሳውቋል።
1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።
2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ።
የመቁረጫ ነጥብ ፦
➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216
➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204
➡️ ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198
➡️ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198
➡️ ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165

የዩኒቨርሲቲ ምደባ‼️
የዩኒቨርስቲ ምደባ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
የዩኒቨርስቲ ምደባችሁን በእነዚህ ሊንኮች ማየት ትችላላችሁ👇👇
Website: https://student.ethernet.edu.et
Telegram bot: @moestudentbot

Welcome to Ethio A+ tutoring
🧑🎓 Students / Parents:
➡️ Find your tutor here: https://forms.gle/cXyMrvfhe8VpYeqS7
🧑🏫 Tutors:
➡️ Register here: https://forms.gle/8gsPGR4zSrRySHpE6
📞 Questions? Message us on Telegram @karl_u7

❤1
" በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ ይቆማል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።
ይህ ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነስርዓት ባከናወነበት ወቅት ነው።
በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጠንካራ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደገለፁት፤ በሚቀጥሉት ዓመታት የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ምደባ እንደሚያቆምና የማለፊያ ነጥብ የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች በሚፈልጓቸው ዩኒቨርሲቲዎችና የትምህርት መስኮች እንዲያመለክቱ ይደረጋል፡፡
" የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደከዚህ ቀደሙ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ ሳይሆን በተማሪዎቹ ምርጫ ይሆናል " ብለዋል።
" ተማሪዎች የሚማሩበትን ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡም ምክንያታዊ በመሆን በዬትኛው ዩኒቨርሲቲ የተሻለ የትምህርት መስክ፣ እውቀትና የስራ እድል ላገኝ እችላለሁ በማለት ይመርዝታሉ " ሲሉ ገልጸዋል። #ኢፕድ

የቴክኒክና ሙያ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።
የኢፌዲሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባደረሰን መረጃ መሠረት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው መስፈርቱን የሚያሟሉ በሙሉ ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በመሄድ መሰልጠን እንደሚችሉ አሳውቋል።
የመግቢያ ነጥቦቹ:-
ለደረጃ 5 ወንዶች179 እና ከዚያ በላይ
ሴቶች 168 እና ከዚያ በላይ
ለደረጃ 3እና4 ወንዶች135 እና ከዚያ በላይ
ሴቶች 122 እና ከዚያ በላይ
ለደረጃ 1እና2 ወንዶች134 እና ከዚያ በታች
ሴቶች 121 እና ከዚያ በታች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።
የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።
ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ፣ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ ላይ ተቃዉሞ እያሰሙ ነዉ
የትምህርት ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ፣ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን መናገራቸውን ተከትሎ፣ ትናንት ሰኞ ኅዳር 8 ባንዳንድ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ዋዜማ ሰምቻለሁ ስትል ዘግባለች።
የተማሪዎች ተቃውሞ ከተቀሰቀሰባቸው ከፍተኛ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት መካከል አምቦ፣ አርሲ፣ ቡሌ ሆራ፣ ሰላሌ፣ መደ ወላቡ እና ድሬዳዋ ዪኒቨርሲቲዎች እንደሚገኙበት ዋዜማ ከደረሷት መረጃዎች ተረድቻለሁ ብላለች።
ተቃውሞ ያሰሙት ተማሪዎች ካስተጋቧቸው መፈክሮች መካከል፣ "የመምህርነት ሙያ ሥልጠና ያልወሰዱ ተማሪዎችን የማስተማር ብሄራዊ አገልግሎት ስጡ ማለት ተቀባይነት የለውም" የሚለው እንደሚገኝበት ምንጮች ነግረውኛል ብሏል ዘገባው።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከሰሞኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በአዲሱ መመሪያ ዙሪያ ባደረጉት ገለጻ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ተመራቂዎች የአንድ ዓመት የማስተማር ስነ ዘዴ ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ጠቁመው ነበር።

አዲስ የትምህርት ደንብ‼️ እስከ 150,000 ብር የሚደርስ ቅጣት እና የባህል ጥበቃ‼️
የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታወቀ።
ይህ ደንብ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች እና ዓላማዎች:
* የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እስከ 150,000 ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተመላክቷል።
ደንቡ እየጨመሩ የመጡትን አዋኪ ጉዳዮች ከመግታት ባሻገር፣ ከኢትዮጵያውያን ወግና ልማድ ጋር ይቃረናሉ ተብለው የተለዩ የውጭ ባህላዊ ልማዶችን በትምህርት ተቋማት አካባቢ መፈጸም ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።
ዋንኛው ዓላማ በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ጉዳዮችን በመከላከል፣ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀና ግብረ-ገብነትን የተላበሰ ብቁ ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል ነው።
የተከለከሉ የውጭ ባህላዊ ድርጊቶች ምሳሌዎች:
አዲሱ ደንብ የሀገሪቷን ባህልና ወግ ይቃረናሉ ተብለው በግልጽ የዘረዘራቸውን አሉታዊ መጤ ድርጊቶችንና ክብረ በዓላትን ይከለክላል።
ከእነዚህም መካከል:
* Crazy Day
* Gentle Day
* Olds Day
* Valentine Day
* Color Day
* Pyjama Day የሚሉት ይገኙበታል።
@Ethioaplus

የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በሌላ በኩል ፦
- የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም
- የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም
- የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም
- የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ይሰጣል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም
@ethioplus

Adobe Photoshop 2023 v24.0 Multilingual.part2.rar
1.2 GB
Adobe Photoshop 2023