Ethio A+
255 subscribers
211 photos
10 videos
203 files
98 links
A+ is Possible!
Feel free to ask and give any suggestion!
@EthioAplus_admin

https://youtube.com/@ethioa_plus?si=DekKjJasKzd5Oaq-
Download Telegram
#NationalExam 🇪🇹

ነገ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መሠጠት ይጀምራል።

ፈተናውን ለመውሰድ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችም ዛሬ የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ሲሰጥ ውሏል።

ተፈታኞቹ በዩኒቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ ስለሚያገኙት አገልግሎቶች (ምግብ፣ መኝታ፣ ጤና...) እና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል።

በተጨማሪም በፈተና ወቅት ስለሚከተሏቸው ህግና ደንቦች እንዲሁም ተያያዥ ስለሆኑ የፈተና ሂደቶችና አተገባበሮችን በሚመለከት ገለጻ ተሰጥቷቸዋል።

ነገ የሚጀመረው የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚወስዱት ፈተና ይጀምራል።

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።

ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@ethioaplus
የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና መሰጠት ተጀመረ

የዘንድሮ አመት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም መሰጠት መጀመሩ ተገለጸ፤ የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በዛሬው እለት በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

ዘንድሮ በ2017 ዓ.ም በወረቀትና በበየነ መረብ ከ608 ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሃምሌ 08/2017ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የሚኒስቴሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ከሾጌ የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተናን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀምረዋል።

@ethioaplus
#FYI
Open Public Libraries in Addis (Excluding Abrehot )

Abrehot Library, Ethiopia’s largest and most advanced library located near the Ethiopian Parliament in Arat Kilo, is temporarily closed to the public as it is being used for national examinations you are encouraged to visit the many other accessible libraries located across the city.


Subcity Public Libraries (Open and Operating)

Addis Ababa has many operational subcity-level public libraries that provide free access to reading and study spaces. Below are some of the key ones with their known locations:

1.Kolfe Keranio Subcity Public Library
   Location: Kolfe Keranio Subcity, around Ayer Tena
   Coordinates: [Link](https://map.et/place/kolfe-keranio-subcity-public-library/2425113)

2. Lideta Subcity Public Library
   Location: Lideta Subcity, near Lideta Church and Lideta Court
   Coordinates: [Link](https://www.addismap.com/p6357223185/lideta-subcity-public-library)

3. Gulele Subcity Library (Kebele 07/17)
   Location: Gulele Subcity, near Semien Hotel area

4. Bole Subcity Public Library
   Location: Bole Subcity, around Wollo Sefer to Rwanda area
   Coordinates: [Link](https://map.et/addis-ababa/libraries)

5. Akaki Kality Woreda 01 Public Library
   Location: Akaki Kality Subcity, around Akaki St. Gabriel Church

6. Yeka Subcity Public Library
   Location: Yeka Subcity, commonly found around Megenagna or CMC area
   Coordinates: [Link](https://map.et/addis-ababa/libraries)

7. Addis Ababa Culture and Tourism Bureau Library Archives and Information Center
   Location: Around Arada Subcity, near Ras Mekonnen Street, close to Tewodros Square

These libraries offer book borrowing, quiet reading rooms, youth reading programs, and in some cases, limited internet access. Most operate from 8:30 AM to 5:00 PM, Monday to Friday.


Community Libraries

In addition to public sector libraries, several community-led libraries support local reading culture and offer free study spaces:

1. Mekerez Public Library
   Location: Around Arat Kilo, behind the National Theatre
   Map: [Wikimapia Link](http://wikimapia.org/4164972/Mekerez-Public-Library)

2. Senay Public Library
   Location: Around Gurd Shola area (specific map details limited, but locally known for youth engagement)

Sources

1. Abrehot Library Announcement (Closure): [https://www.facebook.com/100087948140607/photos/706289552312643/](https://www.facebook.com/100087948140607/photos/706289552312643/)
2. Public Library Directory – Rentech Digital: [https://rentechdigital.com/smartscraper/business-report-details/ethiopia/addis-ababa/list-of-public-libraries-in-addis-ababa](https://rentechdigital.com/smartscraper/business-report-details/ethiopia/addis-ababa/list-of-public-libraries-in-addis-ababa)
3. Interactive Library Map – Map.et: [https://map.et/addis-ababa/libraries](https://map.et/addis-ababa/libraries)
4. Mekerez Public Library Map: [http://wikimapia.org/4164972/Mekerez-Public-Library](http://wikimapia.org/4164972/Mekerez-Public-Library)

5. #ወመዘክር  National Archives and Library Agency #NALA:

📍 Around Tikur Anbesa Near National Bank


@ethioaplus
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአለም ምርጥ የትምህርት ተቋም ዝርዝር ወስጥ በ808ኛ ደረጃ ተቀመጠ

- ጎንደር እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ተከታዩን ደረጃ አግኝተዋል፣

የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አሰጣጥ ማዕከል በዘንድሮ እትሙ 21,462 የትምህርት ተቋማትን ደረጃ የሰጠ ሲሆን  ከነሱ መካከል ከፍተኛ ደረጃ ላይ የወጡት ግሎባል 2000 ዝርዝር ውስጥ አካቷል።

በዚህ ዝርዝር ወስጥ ስድስት የኢትየጵያ ዩንቨርስቲዎች ተካተዋል።

ማዕከሉ  ዩኒቨርሲቲዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ለመመዘን 74 ሚሊዮን የዳታ ነጥቦችን በአራት ዋና ዋና መለኪያዎች ላይ ተመስርቶ ገምግሟል፤ እነርሱም፡-
👉የትምህርት ጥራት (25%)
👉ቅጥር (ተቀጣሪነት) (25%)
👉የፋኩልቲዎች ጥራት (10%)
👉የምርምር አፈጻጸም (40%) ናቸው።

በዚህ ደረጃ የኢትዮጵያዎቹ;

⭐️አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከኢትዮጵያ አንደኛ ከአለም በ808ኛ

⭐️ጎንደር  ዩንቨርስቲ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ከአለም 1607ኛ

⭐️ጅማ ዩንቨርስቲ  ከኢትዮጵያ 3ተኛ ከአለም 1701ኛ

ለአስራ አራተኛ ተከታታይ ዓመት፣ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ደረጃነቱን አስጠብቋል።  ማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም  እና ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል ። ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

ፕሪንስተን፣ የፔንስልቬኒያ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሎምቢያ፣ ዬል እና የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ከ ስድስት አስከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘዋል።  እነዚህም ሁሉም የግል የአሜሪካ ተቋማት ናቸው። በሌላ በኩል ቻይና  346 ዩኒቨርሲቲዎችን በ2000 ዝርዝር ወስጥ በማካታት ብዛት ያለው ተቋም በማካታት አንደኛ ሆናለች

ከአፍሪካ የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ዩንቨርስቲ ከአለም 271ኛ ደረጃ ከአፍሪካ ደግሞ የአንደኛ ደረጃን አግኝቷል።

@ethioaplus
የ12 ኛ ክፍል ፈተና ሂደት ላይ በእንግሊዘኛ ፈተና ወቅት የኔት ወርክ መቆራረጥና የመጥፋት ችግር አጋጥሞ ነበር ተባለ

👉 134 ሺህ 828 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ወስደዋል


የ2017 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ የ12 ኛ ክፍል ፈተና ሂደት ላይ በእንግሊዘኛ ፈተና ላይ የኔት ወርክ መቆራረጥና የመጥፋት ችግር አጋጥሞ እንደነበር ተነግሯል።

ይህም በተወሰነ የመፈተኛ ጣቢያ ያጋጠመ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ማስታወቁን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

በዚህ ምክንያት 2 ሺህ 7 መቶ ተማሪዎች ይህ አይነቱ ችግር አጋጥሞ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ከኢትዮ ቴሌኮምና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሩን ማስተካከል ተችሏል።

በ2017 የትምህርት ዘመን 134 ሺህ 828 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ወስደዋል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በትናንትናው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 608 ሺህ 742 ተማሪዎች መውሰዳቸው ተመላክቷል፡፡

ይህም አጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 23 ነጥብ 2 በመቶውን እንደሚሸፍን አብራርተው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በወረቀት እንደተፈተኑ ጠቁመዋል።

በበይነ መረብ በአራት ዙር እንዲሁም በወረቀት በሁለት ዙር የተሰጠው ፈተና ከስርቆት እና ኩረጃ ነጻ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን አንስተዋል፡፡

ፈተናው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተቋቋሙ 216 የመፈተኛ ማዕከላት ተሰጥቷል።

@ethioaplus
1
" የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር ላይ ይፋ ይደረጋል " -
ትምህርት ሚኒስቴር


" መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ይቀበላሉ ! "

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር 2017 ዓ/ም ላይ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ትላንት በሰጠው መግለጫ ላይ ለመስማት ተችሏል።

ትምህርታቸውን በሰላምና ደህንነት ምክንያት ዘግይተው በጀመሩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች እንዲሁም የተወሰኑ የህግ ታራሚዎች ፈተናውን ነሀሴ ወር ላይ እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳውቀዋል።

አጠቃላይ ፈተናውን የሚወስዱት 4,966 ተፈታኞች ሲሆኑ ፈተናውን ከነሐሴ 26 - 28/2017 ዓ/ም ድረስ በወረቀት እንደሚወስዱ ተገልጿል።

እንዚህ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከወሰዱ በኃላ አጠቃላይ የሁሉም የ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች እንደሚቀበሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@ethioaplus
ነጻ የትምህርት ዕድል!

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት (MfM) ስር የሚተዳደረው የሐረር አግሮ-ቴክኒካልና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ብቁ የሆኑ የቴክኖሎጂ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ ለማስተማር ዕድል ይሰጣል፡፡

ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የ12ኛ ክፍል አጠናቀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ወይም የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትለው ያለፉ ከሆነ የነጻ የትምህርት ዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ማመልከት ይችላሉ!

የሚሰጡ ፕሮግራሞች፦
► አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
► ማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ
► ኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ

📅 ምዝገባ የሚያበቃው፦
ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ትምህርት መስከረም 12/2018 ዓ.ም ይጀምራል።

የማመልከቻ አማራጮች፦

ኦንላይን ለማመልከት፦
ድረ-ገጽ፦ www.mfmattc.edu.et
ቴልግራም፦ https://t.me/ATTC_online

በአካል ለማመልከት፦
► ሀረር፦ ATTC ሬጅስትራር
► አዲስ አበባ፦ MfM ዋና ቢሮ፣ ቦሌ ቡልቡላ
► መቱ፦ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማዕከል
► አልቡኮ፣ አንኮበር፣ ቦረዳ፣ ቦረና/ዎግዲ፣ ዳኖ/ኢሉ ገላን፣ ኖኖ ቤንጃ፣ ካዎ ኮይሻ እና ጎፋ MfM ፕሮጀክት ጽ/ቤት በመቅረብ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

☎️  ለተጨማሪ መረጃ፦ 0256664577 / 0966772012 / 0911386973

@ethioaplus
1
#ጥቆማ
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቁ የሆኑ ተለማማጅ የማርኬቲንግ ባለሙያዎችን (School of Marketing Trainee) አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ School of Marketing Trainee
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ቢያንስ 300 ውጤት ያለው/ያላት
➤ ዕድሜ፦ ከ 18-25

የምዝገባ ቀናት፦ ከነሐሴ 05-09/2017 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታዎች፦

➫ አዲስ አበባ፦ በኦንላይን
➫ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ
➫ አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ አምቦ
➫ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ አርባ ምንጭ
➫ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ አሶሳ
➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ባህር ዳር
➫ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ወሎ
➫ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ
➫ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ ጋምቤላ
➫ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ጎንደር
➫ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረር ካምፓስ፣ ሐረር
➫ ሀዋሳ ኤርፖርት፣ ሀዋሳ
➫ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅግጅጋ
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ
➫ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ መቐለ
➫ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣ ሮቤ
➫ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ነቀምቴ
➫ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰመራ
➫ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ
➫ ሻሸመኔ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፦ ሻሸመኔ

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
አንድ ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ የ10ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣ የትምህርት ማስረጃ ዲግሪ፣ የልደት ሰርተፊኬት እና የቀበሌ መታወቂያ፡፡ የሰነዶችዎንና የትምህርት ማስረጃዎችዎን ዋናውንና ኮፒውን ስካን በማድረግ ማያያዝ ይጠበቅብዎታል፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ፣ አመልካቾች በተገለፁት ቦታዎች በአካል በመገኘት ማመልከት ይጠበቅባቸዋል፡፡

Via @ethioaplus
2
| የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የዩኒቨርሲቲዎች መረጃ አሰጣጥን በተመለከተ የተናገሩት፦

"ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸውና ስለሚሠሩት ሥራ ትክክለኛ መረጃ ስጡን ብለን ከጠየቅን ሦስት ዓመት አልፎናል፡፡ ሆኖም እስካሁን የተሟላ መረጃ ለማግኘት ችግር ሆኖብናል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ እውነተኛ መረጃ መስጠት አልተለመደም፡፡"

"ባለፈው ዓመት ከተማሪዎች ምገባ ጋር ተያይዞ የውሸት ሪፖርት ሲቀርብ ነበር፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ቁጥር በውሸት በመጨመር በጀት እንዲጨመርላቸው ያደርጉ ነበር። ዩኒቨርሲቲዎች አሉን የሚሏቸውን የተማሪዎች መረጃ ከእነፎቷቸው አምጡ ስንል ግን፣ አሉን ብለው ካስመዘገቧቸው ተማሪዎች 251 ሺህ ያህሉ የት እንደገቡ አያውቁም፥ ለማምጣትም አልቻሉም፡፡ አንድ ዕውቀት ላይ እሠራለሁ የሚል ተቋም በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ ከሆነና እውነተኛ መረጃ መስጠት የማይፈልግ ከሆነ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲመጣ የምንፈልገውን ለውጥ አዝጋሚ ያደርገዋል።"

@ethioaplus
1
#ETHIOPIA🇪🇹
#GERD💪

💧 ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአጠቃላይ ከ13 ተርባይኖች 5,150 ሜጋዋት ማመንጨት የሚችልበት አቅም ላይ ይገኛል።

💧እስካሁን ከ71 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ ተይዟል። ቀሪው 2.1 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በመጪዎቹ 7-10 ቀናት ውስጥ ይያዛል።


🔵 በግድቡ የተያዘው ውሃ ወደኋላ ከ246 ኪሎ ሜትር በላይ ይተኛል፤ እስካሁን ባለው 240 ኪሎ ሜትር ላይ ተደርሷል። ርቀቱ ከአዲስ አበባ እስከ ሻሸመኔ ይሆናል።

(#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ)

ኢትዮጵያ ገንብታ ባጠናቀቀችው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አማካኝነት ኃይል እያገኘች ትገኛለች። የኃይል ማመንጫ ግድቡ ነሐሴ 24/2017 ላይ 2530 ሜጋ ዋት በማመንጨት ኃይል መስጠት ችሏል።

ለመሆኑ ግድቡ ተጠናቋል ሲባል ምን ማለት ነው ?

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋናው ግድብ በ1.8 ኪሎ ሜትር እርዝማኔና 145 ሜትር ከፍታ ተገንብቶ ተጠናቋል። በአጠቃላይ ከ10 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር ያህል ኮንክሪት (RCC) ሙሌት ተካሂዷል።

የግድቡ የስረኛው ክፍል 150 ሜትር ስፋት አለው። የላይኛው ክፍል ደግሞ 11 ሜትር ስፋት ሲኖረው ሁለት መኪኖችን ጎን ለጎን ማሳለፍ ይችላል።

ኃይል ማመንጨት የሚችሉ 13 ተርባይኖች ተከላ የተጠናቀቀ ሲሆን ከእነዚህ ተርባይኖች 5150 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ይቻላል።

በግድቡ የውጨኛው ክፍል የሚታዩት የብረት አሸንዳዎች በግራ እና በቀኝ በኩል ላሉ ኃይል የሚያመነጩ ተርባይኖች ውኃ የሚተላለፍባቸው ሲሆን እያንዳንዳቸው 8.5 ሜትር ዲያሜትር ስፋት አላቸው። 300 ሜትር ኪዩብ በሰከንድ ማሳለፍ አቅም አላቸው።

በግራ የኃይል ማመንጫ 7 ተርባይኖች ሲኖሩ በቀኝ የኃይል ማመንጫ ደግሞ 6 ተርባይኖች ሙሉ ለሙሉ ተከላቸው ተጠናቋል።

@ethioaplus
🌙 ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ 1500ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!


@ethioaplus
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲሄዱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው እንዲሄዱ ገቢዎች ሚኒስቴር አሳሰበ።

የገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ክፍያ ለመሰብሰብ እያንዳንዱ የወጪ መጋራት ተጠቃሚ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማውጣት እንዳለበት አስታውሷል።
አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የፋይዳ ቁጥር በመያዝ በአካባቢያቸው በሚገኝ ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት (ገቢዎች) ወይም ቢሮ በመቅረብ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እንዲያወጡ ማሳሰቡን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ በሚገቡበት ወቅት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው እንዲቀርቡ አስገንዝቧል።

@ethioaplus
Ethio A+
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲሄዱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው እንዲሄዱ ገቢዎች ሚኒስቴር አሳሰበ። የገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ክፍያ ለመሰብሰብ እያንዳንዱ የወጪ መጋራት ተጠቃሚ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማውጣት እንዳለበት አስታውሷል። አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የፋይዳ ቁጥር በመያዝ በአካባቢያቸው በሚገኝ ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት (ገቢዎች)…
#TIN (Taxpayer Identification Number) — የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር

◽️ የዚህ ነገር አጠቃላይ ሀሳቡ ምንድነው

👉 የወደፊት የግብር ስርዓት:
▬ ተማሪዎች ይማራሉ ፣ ይመረቃሉ ፣ ስራ ይይዛሉ ከዚያም ገንዘብ ያገኛሉ። TIN ሲኖራቸው ወደፊት የሚያገኙትን ገቢ በቀላሉ በማግኘት ግብር የመሰብሰብ ስራን ቀላል ያደርጋል።

👉 የፋይናንስ መለያ(ID):
▬ TIN በሀገሪቱ የፋይናንስ ስርዓት ውስጥ ልክ እንደ መለያ ቁጥር ያገለግላል። ይህም የባንክ አካውንት ሲከፈት ፣ ነፃ የትምህርት እድል ሲገኝ እንዲሁም ከመንግሥት ጋር የተገናኙ ስራዎችን በሀገሪቱ የመረጃ ቋት ለማደራጀት ያግዛል።

👉 ምዝገባ እና ቁጥጥር:
▬ መንግስት የዜጎችን (ተማሪዎችን ጨምሮ) አጠቃላይ መረጃ መያዝ ይፈልጋል። ይሄም ምን ያክል ተመራቂዎች ፣ ሰራተኞች እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች እንዳሉት ለማወቅ ይረዳዋል።

#ማጠቃለያ
👉 ተማሪዎች አሁን TIN ያስፈልጋቸዋል ማለት አሁን ግብር ይከፍላሉ ማለት አይደለም። ይልቁንስ መንግስት የዜጎቹን (የተማሪዎችን ጨምሮ) መረጃ ለመሰብሰብ ፣ ለመመዝገብ ፣ ለመለየት እና ለወደፊቱ አጠናቅሮ ለማዘጋጀት የሚጠቀመው መንገድ ነው።
👉 ኢትዮጵያ የተማሪዎች የወጪ መጋራትን (Cost Sharing) መልሰው የሚከፍሉበትን "Student loan system" እየተገበረች መሆኑን ማሳያ ነው።
👉 TIN ማውጣት ያስፈለገው የዩኒቨርስቲ ቆይታን የወጪ መጋራት (Cost Sharing) ልክ ግብር በ TIN እንደሚከፈለው ስለሚከፈል ነው።
👉 ተማሪዎች ተምረው ፣ ተመርቀው ፣ ስራ ይዘው ገንዘብ ማግኘት ሲጀምሩ መንግስት የ TIN ቁጥርን በመጠቀም የወጪ መጋራት (Cost Sharing) ክፍያን እና ግብርን በቀላሉ እንዲሰበስብ ይረዳዋል።

@ethioaplus
"አንድ የሰፈራችን የተከበረ አባወራ ልጁን ፈረንሳይ አገር ወደሚገኘው “Jules Romania college” ህክምና እንዲያጠና ላከው። ከዛም ከዓመታት በኋላ ልጁን እዛው ፈረንሳይ አገር ሊጠይቀው ሲሄድ የተፈጠረው ነገር ትዝ አለኝ። ልጁ በኩራት ለአባቱ ፓሪስ ውስጥ ያሉትን ነገሮች እየጠቆመ እያስረዳው ነው፦“ይሄ መጠጥ ቤት ነው፤ ይህ የምሽት ክበብ ነው፤ ይሄኛው ደግሞ ምርጥ ፔንሲዮን ነው።”

እንዲህ እንዲህ እያለህ በመጨረሻም አንድ ትልቅ የተንጣለለ ሕንፃ ጋር ደረሱ። አባትየውም ከዚህ ሕንፃ አጠገብ እንደቆመ “ይሄኛውስ ምንድነው?” ብሎ ጠየቀ።

ልጁ፦“እኔንጃ ከዚህ በፊት አይቼው አላውቅም”

አባትየው እና ልጁ ስለዚህ ሕንፃ የማወቅ ጉጉት ፈጥሮባቸው ከአጠገባቸው የቆመውን አንድ ሰውዬ ጠየቁት።

ሰውዬው፦“ይህ የህክምና ትምህርት የሚሰጥበት
Jules Romania college ነው”🫣
ወዴት ወዴት 😂😅😭
😁2
ህዳሴ ተመረቀ!

ገበያ ሚዲያ ጳጉሜ 4፣ 2017 ዓ.ም

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ  የኢትዮጵያውያን ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ የሆነውን ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ በዛሬው ዕለት መርቀዋል።

የኢትዮጵያውያን የዘመናት ቁጭት የነበረው ታላቁ ኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ የምረቃ ሥነ ሥርዓት በጉባ እየተካሄደ ይገኛል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የቀድሞ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች ታድመዋል፡፡

@ethioaplus
2
ውጤት ዛሬ ለሊት ይለቀቃል የሚል ተስፋ እንዳይኖራችሁ ፤ cuz ዛሬ ከሰዓትም ምንም አልተባለም ።

መስከረም 2ን እንጠብቃለን ። በዓልን ደስ ብሏችሁ አሳልፉ ሁሉም ከልኩ አያልፍም።
#Grade12Result

የ 12ኛ ክፍል ውጤትን አስመልክቶ ነገ አዲስ ነገር ይጠበቃል።

የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት እስካሁን ያልተገለፀው የሁሉንም ተማሪዎች ውጤት በአንድ ላይ ለመግለፅ እንደሆነና በቅርቡ ፈተናቸውን የወሰዱ ተማሪዎች ፈተና እርማት ስላለቀ ነው ።

አሁን ግን ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉንም ነገር በጊዜ ለመጨረስ እና የተማሪዎችን ውጤት ለማሳወቅ እየሰራ እንደሆን ተገልጿል።

መረጃዎችን ተከታትለን ምናደርሳችሁ ይሆናል

@ethioaplus