Ethio A+
255 subscribers
211 photos
10 videos
203 files
98 links
A+ is Possible!
Feel free to ask and give any suggestion!
@EthioAplus_admin

https://youtube.com/@ethioa_plus?si=DekKjJasKzd5Oaq-
Download Telegram
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት/ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ሀገር አቀፍ ፈተናው ሰኞ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጡ ፈተናዎች ይጀመራል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቹን እየተቀበሉ ሲሆን፤ በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠውን ፈተና በብቃት ለመስጠት ዝግጁ እንደሆኑ ገልፀዋል። 

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ምስል፦ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እና ቦረና ዩኒቨርሲቲ

@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያ በሚሰጠው የፈተና ገለጻ/Orientation/ ላይ መገኘት እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት በቂ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን እንዲሁም ፈተናው ከሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ የገለጹ ሲሆን ተማሪዎች በፈተና መስጫ ጣቢያዎች በወጣው መርሀ ግብር መሰረት በመገኘት ፈተናዉን ሊወስዱ ይገባል ብለዋል፡፡

አቶ ዲናኦል አክለዉም የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ ገለጻ በፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት የሚሰጠውን የፈተና ገለጻ/Orientation/ መከታተልና የመፈተኛ ቦታቸዉንና ክፍላቸዉን ማየት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡


https://t.me/ethioaplus
በ2017 ዓ.ም የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ እና አጠቃላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ለተፈታኝ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት አዕምሮ ታደሰ(ዶ/ር) ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በሚቆዩባቸው የፈተና ቀናት በፈተና ቦታ፣በማደሪያ እና ከፈተና ውጭ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሰለማዊ በመሆን እና የግቢውን ህግ እና ደንብ በማክበር መፈተን እንደሚገባቸው ገልጸው በራስ አቅም እና ዕውቀት ከኩረጃ እራስን በማራቅ በተቀመጠው የፈተና ህግና ደንብ መሰረት በአግባቡ እንዲፈተኑ አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር አዕምሮ አያይዘውም ተፈታኝ ተማሪዎች መፈተኛ ክፍል በሰዓቱ በመገኘት ፈተናውን እንዲወስዱ አሳስበው መልካም ውጤት እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡

ገለጻው በየመፈተኛ ክፍላቸው የተሠጠ ሲሆን ተፈታኞችም በፈተና ቦታ ማድረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች  ዝርዝር ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

@ethioaplus
#NationalExam 🇪🇹

ነገ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መሠጠት ይጀምራል።

ፈተናውን ለመውሰድ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችም ዛሬ የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ሲሰጥ ውሏል።

ተፈታኞቹ በዩኒቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ ስለሚያገኙት አገልግሎቶች (ምግብ፣ መኝታ፣ ጤና...) እና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል።

በተጨማሪም በፈተና ወቅት ስለሚከተሏቸው ህግና ደንቦች እንዲሁም ተያያዥ ስለሆኑ የፈተና ሂደቶችና አተገባበሮችን በሚመለከት ገለጻ ተሰጥቷቸዋል።

ነገ የሚጀመረው የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚወስዱት ፈተና ይጀምራል።

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።

ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@ethioaplus
የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና መሰጠት ተጀመረ

የዘንድሮ አመት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም መሰጠት መጀመሩ ተገለጸ፤ የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በዛሬው እለት በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

ዘንድሮ በ2017 ዓ.ም በወረቀትና በበየነ መረብ ከ608 ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሃምሌ 08/2017ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የሚኒስቴሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ከሾጌ የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተናን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀምረዋል።

@ethioaplus
#FYI
Open Public Libraries in Addis (Excluding Abrehot )

Abrehot Library, Ethiopia’s largest and most advanced library located near the Ethiopian Parliament in Arat Kilo, is temporarily closed to the public as it is being used for national examinations you are encouraged to visit the many other accessible libraries located across the city.


Subcity Public Libraries (Open and Operating)

Addis Ababa has many operational subcity-level public libraries that provide free access to reading and study spaces. Below are some of the key ones with their known locations:

1.Kolfe Keranio Subcity Public Library
   Location: Kolfe Keranio Subcity, around Ayer Tena
   Coordinates: [Link](https://map.et/place/kolfe-keranio-subcity-public-library/2425113)

2. Lideta Subcity Public Library
   Location: Lideta Subcity, near Lideta Church and Lideta Court
   Coordinates: [Link](https://www.addismap.com/p6357223185/lideta-subcity-public-library)

3. Gulele Subcity Library (Kebele 07/17)
   Location: Gulele Subcity, near Semien Hotel area

4. Bole Subcity Public Library
   Location: Bole Subcity, around Wollo Sefer to Rwanda area
   Coordinates: [Link](https://map.et/addis-ababa/libraries)

5. Akaki Kality Woreda 01 Public Library
   Location: Akaki Kality Subcity, around Akaki St. Gabriel Church

6. Yeka Subcity Public Library
   Location: Yeka Subcity, commonly found around Megenagna or CMC area
   Coordinates: [Link](https://map.et/addis-ababa/libraries)

7. Addis Ababa Culture and Tourism Bureau Library Archives and Information Center
   Location: Around Arada Subcity, near Ras Mekonnen Street, close to Tewodros Square

These libraries offer book borrowing, quiet reading rooms, youth reading programs, and in some cases, limited internet access. Most operate from 8:30 AM to 5:00 PM, Monday to Friday.


Community Libraries

In addition to public sector libraries, several community-led libraries support local reading culture and offer free study spaces:

1. Mekerez Public Library
   Location: Around Arat Kilo, behind the National Theatre
   Map: [Wikimapia Link](http://wikimapia.org/4164972/Mekerez-Public-Library)

2. Senay Public Library
   Location: Around Gurd Shola area (specific map details limited, but locally known for youth engagement)

Sources

1. Abrehot Library Announcement (Closure): [https://www.facebook.com/100087948140607/photos/706289552312643/](https://www.facebook.com/100087948140607/photos/706289552312643/)
2. Public Library Directory – Rentech Digital: [https://rentechdigital.com/smartscraper/business-report-details/ethiopia/addis-ababa/list-of-public-libraries-in-addis-ababa](https://rentechdigital.com/smartscraper/business-report-details/ethiopia/addis-ababa/list-of-public-libraries-in-addis-ababa)
3. Interactive Library Map – Map.et: [https://map.et/addis-ababa/libraries](https://map.et/addis-ababa/libraries)
4. Mekerez Public Library Map: [http://wikimapia.org/4164972/Mekerez-Public-Library](http://wikimapia.org/4164972/Mekerez-Public-Library)

5. #ወመዘክር  National Archives and Library Agency #NALA:

📍 Around Tikur Anbesa Near National Bank


@ethioaplus
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአለም ምርጥ የትምህርት ተቋም ዝርዝር ወስጥ በ808ኛ ደረጃ ተቀመጠ

- ጎንደር እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ተከታዩን ደረጃ አግኝተዋል፣

የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አሰጣጥ ማዕከል በዘንድሮ እትሙ 21,462 የትምህርት ተቋማትን ደረጃ የሰጠ ሲሆን  ከነሱ መካከል ከፍተኛ ደረጃ ላይ የወጡት ግሎባል 2000 ዝርዝር ውስጥ አካቷል።

በዚህ ዝርዝር ወስጥ ስድስት የኢትየጵያ ዩንቨርስቲዎች ተካተዋል።

ማዕከሉ  ዩኒቨርሲቲዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ለመመዘን 74 ሚሊዮን የዳታ ነጥቦችን በአራት ዋና ዋና መለኪያዎች ላይ ተመስርቶ ገምግሟል፤ እነርሱም፡-
👉የትምህርት ጥራት (25%)
👉ቅጥር (ተቀጣሪነት) (25%)
👉የፋኩልቲዎች ጥራት (10%)
👉የምርምር አፈጻጸም (40%) ናቸው።

በዚህ ደረጃ የኢትዮጵያዎቹ;

⭐️አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከኢትዮጵያ አንደኛ ከአለም በ808ኛ

⭐️ጎንደር  ዩንቨርስቲ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ከአለም 1607ኛ

⭐️ጅማ ዩንቨርስቲ  ከኢትዮጵያ 3ተኛ ከአለም 1701ኛ

ለአስራ አራተኛ ተከታታይ ዓመት፣ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ደረጃነቱን አስጠብቋል።  ማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም  እና ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል ። ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

ፕሪንስተን፣ የፔንስልቬኒያ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሎምቢያ፣ ዬል እና የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ከ ስድስት አስከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘዋል።  እነዚህም ሁሉም የግል የአሜሪካ ተቋማት ናቸው። በሌላ በኩል ቻይና  346 ዩኒቨርሲቲዎችን በ2000 ዝርዝር ወስጥ በማካታት ብዛት ያለው ተቋም በማካታት አንደኛ ሆናለች

ከአፍሪካ የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ዩንቨርስቲ ከአለም 271ኛ ደረጃ ከአፍሪካ ደግሞ የአንደኛ ደረጃን አግኝቷል።

@ethioaplus
የ12 ኛ ክፍል ፈተና ሂደት ላይ በእንግሊዘኛ ፈተና ወቅት የኔት ወርክ መቆራረጥና የመጥፋት ችግር አጋጥሞ ነበር ተባለ

👉 134 ሺህ 828 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ወስደዋል


የ2017 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ የ12 ኛ ክፍል ፈተና ሂደት ላይ በእንግሊዘኛ ፈተና ላይ የኔት ወርክ መቆራረጥና የመጥፋት ችግር አጋጥሞ እንደነበር ተነግሯል።

ይህም በተወሰነ የመፈተኛ ጣቢያ ያጋጠመ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ማስታወቁን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

በዚህ ምክንያት 2 ሺህ 7 መቶ ተማሪዎች ይህ አይነቱ ችግር አጋጥሞ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ከኢትዮ ቴሌኮምና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ችግሩን ማስተካከል ተችሏል።

በ2017 የትምህርት ዘመን 134 ሺህ 828 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ወስደዋል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በትናንትናው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 608 ሺህ 742 ተማሪዎች መውሰዳቸው ተመላክቷል፡፡

ይህም አጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 23 ነጥብ 2 በመቶውን እንደሚሸፍን አብራርተው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በወረቀት እንደተፈተኑ ጠቁመዋል።

በበይነ መረብ በአራት ዙር እንዲሁም በወረቀት በሁለት ዙር የተሰጠው ፈተና ከስርቆት እና ኩረጃ ነጻ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን አንስተዋል፡፡

ፈተናው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተቋቋሙ 216 የመፈተኛ ማዕከላት ተሰጥቷል።

@ethioaplus
1