Ethio A+
255 subscribers
211 photos
10 videos
203 files
98 links
A+ is Possible!
Feel free to ask and give any suggestion!
@EthioAplus_admin

https://youtube.com/@ethioa_plus?si=DekKjJasKzd5Oaq-
Download Telegram
#FYI
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት  መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

መንግሥት ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከጸጥታ አካላት እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር እየሠራ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ተናግረዋል።

የፈተና ጥያቄዎች እና የመሰረተ ልማት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ኩረጃን ለማስቀረት ፈተናዎች በከፍተኛ ስብጥር እንዲዘጋጁ መደረጉን ገልፀዋል።

በፈተና ወቅት ስልክን ጨምሮ ኤሌክትሮኒክስ ነገሮችን መያዝ መከልከሉንና ይዘው የተገኙ ተፈታኞች ውጤታቸው እንደሚሰረዝ አስገንዝበዋል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል። ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።


@ethioaplus
"ጀግናው 💪

የዛሬው ምስል ነው!

ጀግናው ልጇ ለትምህርቱ ከሰል ሸጣ ለለፋችለት እናቱ ያሳየው ክብርና ምስጋና ድንቅ ነው።

ይሄ ነው እውነተኛ ፍቅር! በክሰል ሽያጭ ልጇን አስተምራ ለዚህ ያበቃች እናት፣ በምርቃቱ ቀን ደግሞ ከሰል በመሸከም የእናቱን ውለታ በአደባባይ ያመሰገነ ምርጥ ልጅ!

እንኳን ደስ አላችሁ!
እናትህን እንዲህ በክብር እንድታኖር ያደረገህ
ፈጣሪ ይመስገን!

@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል ፈተናን በበይነ መረብ ለሚወስዱ ተማሪዎች  የሙከራ ፈተና ተሰጠ

የዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ ይታወቃል ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፈተናው  በበይነ መረብ እና በተለመደው የወረቀት ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በመሆኑም ፈተናቸውን በበይነ መረብ ለሚወስዱ ተማሪዎች የሙከራ ፈተና ሰኔ 17/2017 ዓ.ም እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ይህም ተፈታኞች በበይነ መረብ መፈተንን እንዲለማመዱ እና  ምንም አይነት ችግር ሳይገጥማቸው ፈተናቸውን በተሳካ ሁኔታ ለመውሰድ የሚያችላቸውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲው በበይነ መረብ የመፈተን አቅም ዝግጅት የሚገመገምበት መሆኑ ተገልጿል፡፡


@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅትና አፈጻጸም በክልሎች | 2017 E.C.

• ሀረሪ: 2292 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ። 1931 በኦንላይን፣ 361 በወረቀት። ክልሉ ከተማሪዎች ጋር የማጠናከሪያ ትምህርትና የስነ-ልቦና ዝግጅት ሲሰራ ቆይቷል።

• አፋር: 4893 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ። 794 በኦንላይን፣ 4099 በወረቀት። ተማሪዎች በወረቀት እና በኦንላይን ተከታታይ የሞዴል ፈተናዎችን ወስደዋል።

• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ: 35,246 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ። 7211 በኦንላይን፣ 28035 በወረቀት።

ፈተናው ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይሰጣል። መልካም ፈተና ለሁሉም ተፈታኞች!


https://t.me/ethioaplus
1
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት/ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ሀገር አቀፍ ፈተናው ሰኞ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጡ ፈተናዎች ይጀመራል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቹን እየተቀበሉ ሲሆን፤ በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠውን ፈተና በብቃት ለመስጠት ዝግጁ እንደሆኑ ገልፀዋል። 

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ምስል፦ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እና ቦረና ዩኒቨርሲቲ

@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያ በሚሰጠው የፈተና ገለጻ/Orientation/ ላይ መገኘት እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት በቂ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን እንዲሁም ፈተናው ከሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ የገለጹ ሲሆን ተማሪዎች በፈተና መስጫ ጣቢያዎች በወጣው መርሀ ግብር መሰረት በመገኘት ፈተናዉን ሊወስዱ ይገባል ብለዋል፡፡

አቶ ዲናኦል አክለዉም የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ ገለጻ በፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት የሚሰጠውን የፈተና ገለጻ/Orientation/ መከታተልና የመፈተኛ ቦታቸዉንና ክፍላቸዉን ማየት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡


https://t.me/ethioaplus
በ2017 ዓ.ም የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ እና አጠቃላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ለተፈታኝ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት አዕምሮ ታደሰ(ዶ/ር) ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በሚቆዩባቸው የፈተና ቀናት በፈተና ቦታ፣በማደሪያ እና ከፈተና ውጭ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሰለማዊ በመሆን እና የግቢውን ህግ እና ደንብ በማክበር መፈተን እንደሚገባቸው ገልጸው በራስ አቅም እና ዕውቀት ከኩረጃ እራስን በማራቅ በተቀመጠው የፈተና ህግና ደንብ መሰረት በአግባቡ እንዲፈተኑ አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር አዕምሮ አያይዘውም ተፈታኝ ተማሪዎች መፈተኛ ክፍል በሰዓቱ በመገኘት ፈተናውን እንዲወስዱ አሳስበው መልካም ውጤት እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡

ገለጻው በየመፈተኛ ክፍላቸው የተሠጠ ሲሆን ተፈታኞችም በፈተና ቦታ ማድረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች  ዝርዝር ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

@ethioaplus
#NationalExam 🇪🇹

ነገ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መሠጠት ይጀምራል።

ፈተናውን ለመውሰድ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችም ዛሬ የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ሲሰጥ ውሏል።

ተፈታኞቹ በዩኒቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ ስለሚያገኙት አገልግሎቶች (ምግብ፣ መኝታ፣ ጤና...) እና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል።

በተጨማሪም በፈተና ወቅት ስለሚከተሏቸው ህግና ደንቦች እንዲሁም ተያያዥ ስለሆኑ የፈተና ሂደቶችና አተገባበሮችን በሚመለከት ገለጻ ተሰጥቷቸዋል።

ነገ የሚጀመረው የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚወስዱት ፈተና ይጀምራል።

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።

ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@ethioaplus