Ethio A+
255 subscribers
211 photos
10 videos
203 files
98 links
A+ is Possible!
Feel free to ask and give any suggestion!
@EthioAplus_admin

https://youtube.com/@ethioa_plus?si=DekKjJasKzd5Oaq-
Download Telegram
በኢትዮጵያ ፈተና ሳያጠኑ ማለፍ እንደማይቻል ግልፅ እየሆነ ነው - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
****

በኢትዮጵያ እንደከዚህ ቀደሙ ፈተና ሳያጠኑ እና ሳይረዱ ማለፍ እንደማይቻል  ግልፅ እየሆነ በመምጣቱ አብዛኛው የትምህርት ማህበረሰብ  በትኩረት ልጆችን ለማብቃት ርብርብ ማድረግ መጀመሩን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅትን በተመለከተ ለኢቲቪ 57 የዜና መሰናዶ በሰጡት ማብራሪያ፤ ሀገር አቀፍ ፈተናውን ያለምንም እክል ለመስጠት በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

እንደ ሀገር በወረቀትም ሆነ በበይነ መረብ ፈተናውን ያለምንም ችግር ለመስጠት፤ ከ28ሺህ በላይ ፈታኞች ተመልምለዋልም ነው ያሉት።

ባለፉት ጊዜያት ብዙ ተማሪዎችን ማሳለፍ ያልቻሉ ትምህርተ ቤቶች ላይ ትኩረት በማድረግ፤  የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትሩ በዘድሮው ፈተና ብዙ ተማሪዎችን የማሳለፍ እድል እንዳላቸውም ጠቁመዋል።

ሀገራዊ ፈተናውን በበይነመረብ የሚፈተኑ 150ሺህ ተፈታኞችም አስፈላጊውን ልምምድ እያደረጉ መሆናቸውንም አንስተዋል።

ያነበቡ ተማሪዎች እንዲሁም ተማሪዎቻቸውን በደንብ ያዘጋጁ ትምህርት ቤቶች ጥሩ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

በፈተናው ወቅት የኢንተርኔትና የመብራት መቆራረጥ እንዲሁም ሌሎች ችግሮች እንዳይፈጠሩ፤ ከ10 ተቋማት የተወጣጣ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

@ethioaplus
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ተኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ !


ኢድ ሙባረክ 💜

Join us➔ @ethioaplus
3
ለ22 ሴት አይነስውራን ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ።

ጸሐይ ዘውዴ መታሰቢያ የስኮላርሺፕ ፈንድ ለ22 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  ሴት አይነስውራን ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ።

ፈንዱ የቀድሞዋ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ተ/ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት  ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በዘንድሮው ዓመት ለሚመረቁ 22 ሴት አይነስውራን ተማሪዎች የስማርት ስልኮችን ድጋፍ አድርጓል።

ጸሐይ ዘውዴ መታሰቢያ የስኮላርሺፕ ፈንድ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 14 ዓመታት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አይነስራውን ተማሪዎች የመማሪያ ቴክኖሎጂ ግባአቶችን ጨምሮ የገንዘብና የተለያዩ ድጋፎችን እንዲሁም ስልጠናዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካል ጉዳተኞችን  የትምህርት ስኬት ለማረጋገጥ የልዩ ድጋፍ ቢሮ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡

@ethioaplus
እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው ከማየት በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም” ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የመምህራን ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

"እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው፣ መኪናቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤታቸው በር ላይ አቁመው ሲያስተምሩ ከማየት በላይ ለኔ ደስታ የለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ውስጥ ውስጡን እየተሠሩ ያሉት ሥራዎች ሲሳኩ የመምህራን ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ ብለዋል።

የመምህራን ጥያቄ በደመወዝ ጭማሪ ብቻ የማይመለስ መሆኑን አንስተው፣ የደመወዝ ጭማሪው ላይ ብቻ ትኩረት ከተደረገ ያለችው ተበልታ ታልቃለች ብሏል።

@Ethioaplus
ፈተናውን ከስርቆት በጸዳ መልኩ እንዲሰጥ በማድረግ ውጤታማና ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ይገባል – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ የጸጥታ ዕቅድና ኦሬንቴሽን መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የክልልና ከተማ መስተዳድሮች ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተወካዮች እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት፤ የ12ኛ ክፍል ፈተና በአግባቡ እንዲሰጥ ትኩረት የተሰጠው የተሻለ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር መሆኑን ገልጸው፤ ፈተናውን ከስርቆት በጸዳ መልኩ እንዲሰጥ በማድረግ ውጤታማና ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ይገባል ብለዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ችግሮችን በማረም ፈተናውን በተሻለ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም የጸጥታ አካላት ሚና ትልቅ መሆኑን ጠቁመው፤ 12ኛ ክፍል ፈተና ከነበረበት ችግሮች ተላቆ በተሻለ መልኩ እንዲሰጥ የጸጥታ ተቋማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ዘንድሮ ፈተናው ለ150 ሺህ ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ ፈተና አሰጣጡ ወደ ዲጂታል እንዲሸጋገር እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው፤ ፖሊስ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም እንዲካሄድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቁመዋል።

@ethioaplus
2
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄዷል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስተር በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ተማሪዎች ከፈተና ስርቆትና ኩረጃ በመውጣት አጥንቼ አውቄ ፈተናውን ማለፍ አለብኝ የሚል አስተሳሰብ ያለው ምክንያታዊ የሆነ ትውልድ መፍጠር አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከመከላከያ ሠራዊት እና ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ለአራት ዓመታት የ12ኛ ከፍል መልቀቂያ ፈተና ስርዓት እንዲይዝ እና ተማሪዎች የለፉበትን ውጤት እንዲያገኙ በማድረግ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል።

ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ቀደም ባሉት ጊዜያት በስርቆትና በኩረጃ ይታወቅ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስርዓት እንዲይዝ የለውጡ መንግስታችን በወሰደው ቁርጠኝነት የፖሊስ ለውጥ በማድረግ አሁን ላይ ተማሪዎች ስርዓት ይዘው በመፈተን ያጠኑትን፣ ያነበቡትንና የለፉበትን ውጤት እንዲያገኙ ከማስቻልም በላይ በዩኒቨርስቲዎች በተመሳሳይ ሰዎች ለፍተው ጥረው አንብበው የሚበቁበት ሀገር የሚገነባበት ሥርዓት እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ትውልዱ በእውቀቱና በችሎታው መድረስ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ትውልድን መቅረፅ ለሀገር እድገትና ለፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት በተሻለ መልኩ የጸጥታ መዋቅሩ አስቀድሞ መዘጋጀት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡


@ethioaplus
#FYI
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት  መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

መንግሥት ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከጸጥታ አካላት እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር እየሠራ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ተናግረዋል።

የፈተና ጥያቄዎች እና የመሰረተ ልማት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ኩረጃን ለማስቀረት ፈተናዎች በከፍተኛ ስብጥር እንዲዘጋጁ መደረጉን ገልፀዋል።

በፈተና ወቅት ስልክን ጨምሮ ኤሌክትሮኒክስ ነገሮችን መያዝ መከልከሉንና ይዘው የተገኙ ተፈታኞች ውጤታቸው እንደሚሰረዝ አስገንዝበዋል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል። ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።


@ethioaplus
"ጀግናው 💪

የዛሬው ምስል ነው!

ጀግናው ልጇ ለትምህርቱ ከሰል ሸጣ ለለፋችለት እናቱ ያሳየው ክብርና ምስጋና ድንቅ ነው።

ይሄ ነው እውነተኛ ፍቅር! በክሰል ሽያጭ ልጇን አስተምራ ለዚህ ያበቃች እናት፣ በምርቃቱ ቀን ደግሞ ከሰል በመሸከም የእናቱን ውለታ በአደባባይ ያመሰገነ ምርጥ ልጅ!

እንኳን ደስ አላችሁ!
እናትህን እንዲህ በክብር እንድታኖር ያደረገህ
ፈጣሪ ይመስገን!

@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል ፈተናን በበይነ መረብ ለሚወስዱ ተማሪዎች  የሙከራ ፈተና ተሰጠ

የዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ ይታወቃል ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፈተናው  በበይነ መረብ እና በተለመደው የወረቀት ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በመሆኑም ፈተናቸውን በበይነ መረብ ለሚወስዱ ተማሪዎች የሙከራ ፈተና ሰኔ 17/2017 ዓ.ም እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ይህም ተፈታኞች በበይነ መረብ መፈተንን እንዲለማመዱ እና  ምንም አይነት ችግር ሳይገጥማቸው ፈተናቸውን በተሳካ ሁኔታ ለመውሰድ የሚያችላቸውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲው በበይነ መረብ የመፈተን አቅም ዝግጅት የሚገመገምበት መሆኑ ተገልጿል፡፡


@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅትና አፈጻጸም በክልሎች | 2017 E.C.

• ሀረሪ: 2292 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ። 1931 በኦንላይን፣ 361 በወረቀት። ክልሉ ከተማሪዎች ጋር የማጠናከሪያ ትምህርትና የስነ-ልቦና ዝግጅት ሲሰራ ቆይቷል።

• አፋር: 4893 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ። 794 በኦንላይን፣ 4099 በወረቀት። ተማሪዎች በወረቀት እና በኦንላይን ተከታታይ የሞዴል ፈተናዎችን ወስደዋል።

• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ: 35,246 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ። 7211 በኦንላይን፣ 28035 በወረቀት።

ፈተናው ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይሰጣል። መልካም ፈተና ለሁሉም ተፈታኞች!


https://t.me/ethioaplus
1
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት/ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ሀገር አቀፍ ፈተናው ሰኞ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጡ ፈተናዎች ይጀመራል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቹን እየተቀበሉ ሲሆን፤ በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠውን ፈተና በብቃት ለመስጠት ዝግጁ እንደሆኑ ገልፀዋል። 

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ምስል፦ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እና ቦረና ዩኒቨርሲቲ

@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያ በሚሰጠው የፈተና ገለጻ/Orientation/ ላይ መገኘት እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት በቂ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን እንዲሁም ፈተናው ከሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ የገለጹ ሲሆን ተማሪዎች በፈተና መስጫ ጣቢያዎች በወጣው መርሀ ግብር መሰረት በመገኘት ፈተናዉን ሊወስዱ ይገባል ብለዋል፡፡

አቶ ዲናኦል አክለዉም የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ ገለጻ በፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ22/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ የሁለተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት የሚሰጠውን የፈተና ገለጻ/Orientation/ መከታተልና የመፈተኛ ቦታቸዉንና ክፍላቸዉን ማየት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡


https://t.me/ethioaplus