Ethio A+
255 subscribers
211 photos
10 videos
203 files
98 links
A+ is Possible!
Feel free to ask and give any suggestion!
@EthioAplus_admin

https://youtube.com/@ethioa_plus?si=DekKjJasKzd5Oaq-
Download Telegram
የሚኮርጅ ሰው ያለእውቀት እና ክህሎት የሚጓዝ በመሆኑ አዲስ ነገር መፍጠር አይችልም፡-ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ተክለማርያም
****

የሚኮርጅ ሰው ያለእውቀት እና ክህሎት የሚጓዝ  በመሆኑ አዲስ ነገር መፍጠር እንደማይችል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና  ተማራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ተክለማርያም ተናገሩ።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅትን በተመለከተ ከኤፍኤም አዲስ 97.1 ጋር ቆይታ ያደረጉት ፕሮፌሰሩ፥ ለተማሪ ፈተና ማለት ከክፍል ወደ ክፍል ማለፊያ ወይም መውደቂያ ሳይሆን የተማሪዎችን ጠንካራ እና ደካማ ጎን ለመለየት፤ እንዲሁም ደካማ ጎኑን ለመሙላት እና ጠንካራውን ይበልጥ ለማሻሻል አጋዥ ተግባር ነው ብለዋል።

የፈተና ዓላማ እውቅትን እና ክህሎትን ለማጠናከር ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ የተማሪዎች እውቀትን ከፍ ለማድረግ፣ የትምህርት ተገቢነትን ለማሳደግ እንዲሁም የልጆች ጥንካሬን ለማየትና ለመደገፍ የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ  ከዚህ ቀደም ከውጭ ተኮርጆ ሲተገበር የነበረው የትምህርት ፖሊሲ፤ የሀገሪቱን ችግር ከመፍታት ይልቅ ራሱ ችግር ሆኖ በመቆየቱ በትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ማድረግ አስፈላጊ  እርምጃ መሆኑንም አንስተዋል።

አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት ከ2013 ወዲህ መሰጠት ከተጀመረ በኋላ፤ ፈተና አብዛኛው ተማሪ በራሱ ሰርቶ ወደ ዩኒቨርስቲ መግባት አለመቻሉ የትምህርት ፖሊሲውን ክፍተት በደንብ ያሳያልም ብለዋል ፕሮፌሰሩ።

@ethioaplus
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በበይነ መረብ ለሚፈተኑ ተፈታኞች የቴክኒካል ድጋፍ የሚሰጥ ቡድን ተቋቁሟል።

በበይነ መረብ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጁ የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ማንኛውንም ድጋፍ በመጀመሪያ በትምህርት ቤታቸው ቀጥሎም በመፈተኛ ማዕከላት ካሉ የትምህርት አመራር እና ቴክኒክ ድጋፍ ሰጪዎች ማግኘት እንደሚችሉ ይታወቃል።

ተጨማሪ ድጋፍ ለተፈታኝ ተማሪዎቹ የሚሰጥ ቴክኒካል ቡድን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል።

ዘጠኝ አባላት በውስጡ የያዘው ቴክኒካል ቡድኑ፤ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተከፋፍሎ የተደራጀ ነው።

(የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ቡድኑን ድጋፍ ለማግኘት ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።)


@ethioaplus
በኢትዮጵያ ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ፈቃድ እንጂ እውቅና ያላቸው ተቋማት የሉም ተባለ

በኢትዮጵያ ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ፈቃድ እንጂ እውቅና ያላቸው ተቋማት አለመኖራቸውን የኢፌዲሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ሁለቱን ከተማ አስተዳደሮች እና 14 ቱንም ክልሎች አጠቃሎ 375 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ሲሆን፤ እነዚህ ተቋማት ፈቃዳቸውን ከኢፌዲሪ የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የሚወስዱ እና የሚያድሱ እንደሆነም ነው የተገለጸው።

ታዲያ እነዚህ ተቋማት የሚሰጡት ከዲግሪ ጀምሮ ያለው የትምህርት ደረጃ፤ በዓለም አቀፍ እውቅና ያለው እና በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ የትኛውም ሀገር ላይ ሄደው ድጋሚ የሄዱበትን ሀገር ትምህርት መማር ሳያስፈልጋቸው መስራት የሚያስችል አይደለም።

"ይህ ለምን ሆነ?፣ ተቋማቱን ዓለም አቀፋዊ እውቅና እንዲኖራቸው እና በእነዚህ ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎችም በዓለማቀፍ ደረጃ ተስተካካይ እንኳን ባይሆን ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችል የትምህርት ደረጃ እንዲኖራቸው ማድረግ ለምን አልተቻልም?" ሲል አሐዱ ጠይቋል።

የኢፌዲሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የተቋማት ቁጥጥር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ በሰጡት ምላሽም፤ ይህን እውቅና ለመስጠት በመጀመሪያ ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ሊያገኝ እንደሚገባው ገልጸው፤ እስካሁን ግን እውቅናውን አለማግኘቱን ተናግረዋል።

"በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፈቃድ እንጂ እውቅና ገና ያልተሰጣቸው ናቸው" ብለዋል።

ተቋሙም ከዓለም አቀፍ ደረጃ ሰጭ ተቋም ማለትም (አይሶ) ገና እውቅና እንዳልተሰጠውም ተናግረዋል። እሱን ለማድረግ እና እውቅና ያላቸው የትምህርት ተቋማትን ለማፍራት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተናን የሚሰጡ ከ28 ሺህ በላይ #ፈታኞች መመልመላቸው ተገለፀ፡፡

ፈታኞቹ በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጠውን ፈተና በብቃት ለመስጠት ዝግጅት ያደረጉ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ መልቀቂያ ፈተናውን በበይነመረብ የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች አስፈላጊውን ልምምድ እያደረጉ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

በፈተናው ወቅት የኢንተርኔት እና የመብራት መቆራረጥ እንዲሁም ሌሎች ችግሮች እንዳይፈጠሩ፤ ከ10 ተቋማት የተወጣጣ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ እየሠራ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

@ethioaplus
በኢትዮጵያ ፈተና ሳያጠኑ ማለፍ እንደማይቻል ግልፅ እየሆነ ነው - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
****

በኢትዮጵያ እንደከዚህ ቀደሙ ፈተና ሳያጠኑ እና ሳይረዱ ማለፍ እንደማይቻል  ግልፅ እየሆነ በመምጣቱ አብዛኛው የትምህርት ማህበረሰብ  በትኩረት ልጆችን ለማብቃት ርብርብ ማድረግ መጀመሩን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅትን በተመለከተ ለኢቲቪ 57 የዜና መሰናዶ በሰጡት ማብራሪያ፤ ሀገር አቀፍ ፈተናውን ያለምንም እክል ለመስጠት በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

እንደ ሀገር በወረቀትም ሆነ በበይነ መረብ ፈተናውን ያለምንም ችግር ለመስጠት፤ ከ28ሺህ በላይ ፈታኞች ተመልምለዋልም ነው ያሉት።

ባለፉት ጊዜያት ብዙ ተማሪዎችን ማሳለፍ ያልቻሉ ትምህርተ ቤቶች ላይ ትኩረት በማድረግ፤  የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትሩ በዘድሮው ፈተና ብዙ ተማሪዎችን የማሳለፍ እድል እንዳላቸውም ጠቁመዋል።

ሀገራዊ ፈተናውን በበይነመረብ የሚፈተኑ 150ሺህ ተፈታኞችም አስፈላጊውን ልምምድ እያደረጉ መሆናቸውንም አንስተዋል።

ያነበቡ ተማሪዎች እንዲሁም ተማሪዎቻቸውን በደንብ ያዘጋጁ ትምህርት ቤቶች ጥሩ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

በፈተናው ወቅት የኢንተርኔትና የመብራት መቆራረጥ እንዲሁም ሌሎች ችግሮች እንዳይፈጠሩ፤ ከ10 ተቋማት የተወጣጣ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

@ethioaplus
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ተኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ !


ኢድ ሙባረክ 💜

Join us➔ @ethioaplus
3
ለ22 ሴት አይነስውራን ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ።

ጸሐይ ዘውዴ መታሰቢያ የስኮላርሺፕ ፈንድ ለ22 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  ሴት አይነስውራን ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ።

ፈንዱ የቀድሞዋ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ተ/ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት  ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በዘንድሮው ዓመት ለሚመረቁ 22 ሴት አይነስውራን ተማሪዎች የስማርት ስልኮችን ድጋፍ አድርጓል።

ጸሐይ ዘውዴ መታሰቢያ የስኮላርሺፕ ፈንድ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 14 ዓመታት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አይነስራውን ተማሪዎች የመማሪያ ቴክኖሎጂ ግባአቶችን ጨምሮ የገንዘብና የተለያዩ ድጋፎችን እንዲሁም ስልጠናዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካል ጉዳተኞችን  የትምህርት ስኬት ለማረጋገጥ የልዩ ድጋፍ ቢሮ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡

@ethioaplus
እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው ከማየት በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም” ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የመምህራን ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

"እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው፣ መኪናቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤታቸው በር ላይ አቁመው ሲያስተምሩ ከማየት በላይ ለኔ ደስታ የለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ውስጥ ውስጡን እየተሠሩ ያሉት ሥራዎች ሲሳኩ የመምህራን ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ ብለዋል።

የመምህራን ጥያቄ በደመወዝ ጭማሪ ብቻ የማይመለስ መሆኑን አንስተው፣ የደመወዝ ጭማሪው ላይ ብቻ ትኩረት ከተደረገ ያለችው ተበልታ ታልቃለች ብሏል።

@Ethioaplus
ፈተናውን ከስርቆት በጸዳ መልኩ እንዲሰጥ በማድረግ ውጤታማና ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ይገባል – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ የጸጥታ ዕቅድና ኦሬንቴሽን መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የክልልና ከተማ መስተዳድሮች ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተወካዮች እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት፤ የ12ኛ ክፍል ፈተና በአግባቡ እንዲሰጥ ትኩረት የተሰጠው የተሻለ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር መሆኑን ገልጸው፤ ፈተናውን ከስርቆት በጸዳ መልኩ እንዲሰጥ በማድረግ ውጤታማና ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ይገባል ብለዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ችግሮችን በማረም ፈተናውን በተሻለ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም የጸጥታ አካላት ሚና ትልቅ መሆኑን ጠቁመው፤ 12ኛ ክፍል ፈተና ከነበረበት ችግሮች ተላቆ በተሻለ መልኩ እንዲሰጥ የጸጥታ ተቋማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ዘንድሮ ፈተናው ለ150 ሺህ ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ ፈተና አሰጣጡ ወደ ዲጂታል እንዲሸጋገር እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው፤ ፖሊስ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም እንዲካሄድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቁመዋል።

@ethioaplus
2
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄዷል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስተር በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ተማሪዎች ከፈተና ስርቆትና ኩረጃ በመውጣት አጥንቼ አውቄ ፈተናውን ማለፍ አለብኝ የሚል አስተሳሰብ ያለው ምክንያታዊ የሆነ ትውልድ መፍጠር አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከመከላከያ ሠራዊት እና ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር ለአራት ዓመታት የ12ኛ ከፍል መልቀቂያ ፈተና ስርዓት እንዲይዝ እና ተማሪዎች የለፉበትን ውጤት እንዲያገኙ በማድረግ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል።

ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ቀደም ባሉት ጊዜያት በስርቆትና በኩረጃ ይታወቅ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ስርዓት እንዲይዝ የለውጡ መንግስታችን በወሰደው ቁርጠኝነት የፖሊስ ለውጥ በማድረግ አሁን ላይ ተማሪዎች ስርዓት ይዘው በመፈተን ያጠኑትን፣ ያነበቡትንና የለፉበትን ውጤት እንዲያገኙ ከማስቻልም በላይ በዩኒቨርስቲዎች በተመሳሳይ ሰዎች ለፍተው ጥረው አንብበው የሚበቁበት ሀገር የሚገነባበት ሥርዓት እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ትውልዱ በእውቀቱና በችሎታው መድረስ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ትውልድን መቅረፅ ለሀገር እድገትና ለፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት በተሻለ መልኩ የጸጥታ መዋቅሩ አስቀድሞ መዘጋጀት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡


@ethioaplus
#FYI
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት  መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

መንግሥት ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከጸጥታ አካላት እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር እየሠራ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ተናግረዋል።

የፈተና ጥያቄዎች እና የመሰረተ ልማት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ኩረጃን ለማስቀረት ፈተናዎች በከፍተኛ ስብጥር እንዲዘጋጁ መደረጉን ገልፀዋል።

በፈተና ወቅት ስልክን ጨምሮ ኤሌክትሮኒክስ ነገሮችን መያዝ መከልከሉንና ይዘው የተገኙ ተፈታኞች ውጤታቸው እንደሚሰረዝ አስገንዝበዋል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል። ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።


@ethioaplus