Ethio A+
255 subscribers
211 photos
10 videos
203 files
98 links
A+ is Possible!
Feel free to ask and give any suggestion!
@EthioAplus_admin

https://youtube.com/@ethioa_plus?si=DekKjJasKzd5Oaq-
Download Telegram
#EthiopianDefenceUniversity

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ምልመላ ማድረግ ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን መልምሎ ለማስተማር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን በማካሔድ ላይ ይገኛል።

በዚህም ከመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሒዷል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ቅበላና ምልመላ ዙሪያ ገለጻ ከተደረገላቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ይጠቀሳሉ።

በወታደራዊ  ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በፈጠራ ክህሎት ልዩ አቅም ያላቸው ተማሪዎች በውድድር ዩኒቨርሲቲውን መቀላቀል እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በጤና፣ በኢንጅነሪግ እና ሌሎችም የሙያ ዘርፎች ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት መገለፁ ይታወሳል።

©️tikvahuniversity

@ethioaplus
#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀምሯል፡፡

አስተዳደሩ በመላ ሀገሪቱ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ የሆኑ ልዩ ታለንት ያላቸውን በመመልመል ለማሰልጠን ዝግጅት ማጠናቀቁን ግልጿል።

በመሆኑም በሳይበር ደህንነት፣ በዴቨሎፕመንት፣ በኢምቤድድ ሲስተም እና በኤሮስፔስ መስኮች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

ለመመዝገብ 👇
https://talent.insa.gov.et

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎች በመመለመለና በማሰልጠን ወደ ተቋሙ እና ወደ ሳይበር ኢንዱስትሪው እንዲቀላቀሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

©️tikvahuniversity

@ethioaplus
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈታና ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተና በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።

በትምህርት ሚኒሰቴር የተዘጋጁ የሁሉም ትምህርት አይነቶች የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides

@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?

➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 26 ፣ ሰኔ 27 እና ሰኔ 30/2017 ዓ/ም

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?

➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 4 ፣ ሐምሌ 7 እና ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም


@ethioaplus
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈታናዎች አገልግሎት አስትውቋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኤፍ ኤም ሲ እንደተናገሩት በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በሁለት ዙር ይፈተናሉ።

ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን ለመጨመር እና ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፈተናው በ2 ዙር በበይነ መረብ መሰጠቱ ከመኖሪያ ቤታቸው እየተመላለሱ በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ቁጥር ይጨምራል ብለዋል፡፡

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ በዩኒቨርሲቲዎች የሚፈተኑ ይሆናል።

ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣ በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። #ኤፍኤፍምሲ

@ethioaplus
@ethioaplus
#FYI

ትምህርት ሚኒስቴር ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች አጋዥ portal ይፋ አድርጓል።

እዚህ Portal ላይ
ለተለያዩ የትምህርት አይነቶች የቪዲዬ tutorial ታገኛላችሁ።
የተለያዩ ወቅታዊ ዜናዎችን ታገኛላችሁ።
የonline መፈተኛ ጣቢያችሁን ማየት ትችላላችሁ።
https://examinfo.moe.gov.et/guides

የመፈተኛ Portal
https://exam8.ethernet.edu.et

@ethioaplus
#FYI
⚡️የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምን ያህል ተማሪዎች ይወስዳሉ?

👉በአገር አቀፍ ደረጃ 608 ሺህ 588 ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል

👉309 ሺህ 547 የተፈጥሮ ሳይጓስ ተፈታኞች

👉299 ሺህ 41 የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች

👉150 ሺህ ተማሪዎች በኦላይን (በይነ መረብ) ፈተናቸውን ይወስዳሉ

@ethioaplus
በTelegram scam ለተደረጋቹ!

በተለያየ መንገድ Telegram ላይ scam ከተረጋችሁ ወደዚህ bot በመሄድ ማመልከት ትችላላችሁ።
Scam ያደረጋችሁን ሰው ስልክ ቁጥር፣ username፣ እንዲሁም ማስረጃ የሚሆናችሁን screenshot በማያያዝ
#report ማድረግ ትችላላችሁ።
@notoscam
©bighabesha_softwares

@Ethioaplus
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችለንን ቅድመ ዝግጅት እያደረገን ነው ሲሉ ተፈታኝ ተማሪዎች ገለጹ።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በመላ ሀገሪቱም ከ600 ሺህ በላይ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን በወረቀት እና በበይነ መረብ እንደሚወስዱ የወጣው ፕሮግራም ያሳያል።

ኢዜአ ለሀገር አቀፍ ፈተናው እየተደረጉ ያሉ ቅድመ ዝግጅቶችን አስመልክቶ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እና የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን አነጋግሯል።

በኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ አብርሃም ሠላምነህ በብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ወደ አዲስ የትምህርት ምዕራፍ ለመሻገር ሰፋ ያለ ዝግጅት እያደረኩ ነው ብሏል።

በተለይም ለፈተናው የሚረዱትን መጽሀፍት እንዲሁም በበይነ መረብ አማካኝነት አጋዥ የሆኑ ግብዓቶችን በማንበብ ላይ እንደሚገኝ ነው ያብራረው።

ሀገር አቀፍ ፈተናው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማርናቸውን ርዕሰ ጉዳዮች የሚሸፍን በመሆኑ ይህን ታሳቢ ያደረገ የአጠናን ዘዴ በመጠቀም እየተዘጋጀሁ እገኛለሁ ያለችው ደግሞ በዚሁ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪ የሆነችው ዳናት ባህሩ ናት።

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ሼርድ ካምፓስ የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አማኑኤል ታሪኩ በበኩሉ፥ ውጤታማ በመሆን ህልሙን እውን ለማድረግ በትምህርቱ ላይ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል።
ይህንን ጥረት ከግብ ለማድረስም በቀጣይ ወር በሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ከዚህ ቀደም የተማራቸውን ትምህርቶች ወደ ኋላ መለስ  ብሎ በመከለስ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።

ሌላኛዋ የካምፓሱ ተማሪ ሰሎሜ ታደሰ በፈተናው ውጤታማ እንድንሆን መምህራኖቻችን ጥያቄዎችን እንድንሰራ በማድረግና በሌሎች በሚያስፈልጉን ነገሮች  እየደገፉን ይገኛሉ ብላለች።

ፈተናው እየተቃረበ በመምጣቱ በእውቀትም በስነ-ልቦናም ብቁ ለመሆን ጥረቷን እንደምታጎለብት ገልፃለች።

ተማሪ አማኑኤል በበኩሉ፥ተፈታኞች ራሳቸውን በሚገባው ልክ በማዘጋጀትና በመፈተሽ ለላቀ ውጤት ዝግጁ መሆን አለባቸው ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

የኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ደለለኝ አስማረ  በበኩላቸው፥ ትምህርት ቤቱ በዘንድሮ ዓመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 632 የቀን 63 የማታ ተማሪዎችን ያስፈትናል ብለዋል።

ትምህርት ቤቱም ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው በሚፈለገው ደረጃ እንዲዘጋጁ ለማድረግ የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲወስዱ እና ተፈታኞች በግቢው እያደሩ ማጥናት የሚችሉበት ሁኔታ ማመቻቸቱን ተናግረዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎቹ በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚፈተኑ መሆናቸውን  በማንሳት በተለይም በበይነ መረብ ለሚፈተኑ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በኮምፕዩተር ልምምድ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ምክትል ርዕሰ መምህር አብርሃም ድሪባ፥ ካምፓሱ በሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ፈተና 80 ተማሪዎችን እንደሚያስፈትን አስታውቀዋል።

ተማሪዎቹም ለረጅም ዓመታት በትምህርት ዓለም ያደረጉት ጉዞ ፍሬያማ እንዲሆን የተለያዩ ሞዴል ፈተናዎችን እየወሰዱ እንደሚገኙ አንስተው፥ ይህም እስከ ፈተናው መዳረሻ ይቀጥላል ነው ያሉት።

@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከ608 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ!

በ2017 የትምህርት ዘመን ከ608 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ መልቀቂያ ፈተና የፈተና ስርቆትና ኩረጃ በሚቀንስ መልኩ በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።

በወረቀት የሚፈተኑት መሰረተ ልማት ያልተሟላባቸው፤ ኮምፒውተር እና ኢንተርኔት ኮኔክሽን በበቂ ባላገኙ አካባቢዎች የሚገኙ ተፈታኞች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ዋና ዳይሬክተሩ፤ በበየነ መረብ የሚሰጠው ፈተና እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ ወደፊት ሙሉ በሙሉ ፈተናውን በበየነ መረብ ለመስጠት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የፈተና ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን በመግለጽ፤ ፈታኞችን የመመልመል፤ የተመለመሉት ወደዬመፈተኛ ጣቢያው እንዲሰማሩ የማድረግ ዝግጅት እየተካሄደ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡በአማራ ክልል ባለው ግጭት ሳቢያ በርካታ ት/ቤቶች የዘንደሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደማያስፈትኑ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግሥቱ በቅርቡ ገልጸዋል።

በክልሉ በአጠቃላይ 685 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊዋ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የዘንድሮውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶች 470 ብቻ ናቸው ብለዋል።

ክልሉ ቀደም ባሉት ዓመታት በየዓመቱ ከ150 ሺህ እስከ 180ሺህ ተማሪዎችን የማስፈተን አቅም እንደነበረው የገለጹት ኃላፊዋ ሰላም ባለባቸው አከባቢዎች በሚገኙ ት/ቤቶች የሚገኙ 99ሺህ 880 ተማሪዎች የዘንድሮን ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል ሲሉ ተናግረዋል።


@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወሰዱ ተማሪዎች ለቅድመ ዝግጅት የሞዴል ፈተና እየተሠጠ መሆኑ ተገለጸ

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወሰዱ ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት ሥራ እንዲሰሩ እና ተማሪዎች 'ምን ያህል ተዘጋጅተዋል?'የሚለውን ለማወቅ፤ በክልል እና በሀገር ደረጃ የሞዴል ፈተና እየተሠጠ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይልቃል ወንድሜነህ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤የሞዴል ፈተናው የሚሰጠው ተማሪዎች ከዋናው ፈተና በፊት የዝግጅት ደረጃቸውን እንዲገመግሙ ለመርዳት ነው።

"ፈተናው ተማሪዎች ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን እንዲለዩ፣ ጊዜያቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲቆጣጠሩ እና ከፈተና ጋር የተያያዘ ጭንቀትን እንዲቀንስ ያስችላቸዋል" ሲሉም ተናግረዋል።

እንዲሁም ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉት ጥያቄዎች አወቃቀር እና አስቸጋሪነት እራሳቸውን እንዲያውቁ ጠቃሚ ዕድል ይሰጣቸዋል።

ሞዴል ፈተናው በክልልም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጥ ሲሆን፤ ይህም ተማሪዋቹ ምን ያህል ብቁ ናቸው የሚለውን ትክክለኛ ግምገማ እያስገኘ ነው ተብሏል።

እንዲህ ያለው ሁሉን አቀፍ የዝግጅት ስልት በሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎችን አጠቃላይ ውጤት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የ2017 ትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ከሰኔ 23 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ በወረቀት የሚፈተኑ እና በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች እንደሚያካትት ተገልጿል።

የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ፤ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ሊዘጋጅ እንደሚገባ አስተላልፏል።
የ2017ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቶች  ተጠናቀዋል - የትምህርት ፈተናና ምዘና  አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
****

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የትምህርት ፈተናና ምዘና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ ተናገሩ።

አብዛኛውን ጊዜ ፈተና ሲነሳ የፈተና ስርቆትና ኩረጃ አብሮ የሚነሳ ሲሆን፤ ይህን ለማስቀረት መንግስት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ሀገረ አቀፍ ፈተናን ተማሪዎች ከተማሩበት ት/ቤት ወደ  ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው እንዲፈተኑ አድርጓል።

ለፈተና ስረቆትና ኩረጃ የሚያግዙ  ድምፅን ምስልን የሚወስዱ ማንኛውንም  መሳሪያዎችን ተማሪዎች እንዳይጠቀሙና ይዘውም እንዳይገኙ  በመከልከል፤ ጥብቅ ፈተሻ  እንደሚደረገ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ  ተይዘው ሲገኙም እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ተማሪዎች ፈተናን ለመስረቅና ለመኮረጅ የሚያባክኑትን ጊዜ ትምህርቱን በሚገባ ቢያጠኑበት መልካም ነው፤ ውጤታማም ብለዋል።

በብይነ-መረብና በወረቀት የሚሰጠው የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በተሳካ መንገድ ለመስጠት፤  የትምህርት ተቋማት የቁሳቁስና የተለያዩ ዝግጅቶችን አጠናቀው ተማሪዎችን በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ፈተናውን በብይነ መረብ የሚፈተኑ ተማሪዎች በየትምህርተ ቤታቸው ልምምድ በማድረግ ላይ እንዳሉ የጠቆሙት ዶ/ር እሸቱ፤ ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎችም ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኙ እየተደረገም ይገኛል ነው ያሉት።

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ግብአቶች ዝግጁ መሆናቸውን መፈተሸና ለሰው ሀይል ስልጠናዎችን መስጠት፤ እንዲሁም ከክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ከዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሮች ጋር በቅርበት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
#FYI

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሞዴል ፈተና መሰጠት ጀምሯል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2017 ዓ.ም በበይነ መረብ ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለሁለት ቀናት የሚቆይ #ሞዴል ፈተና አዘጋጅቷል፡፡

ፈተናው ዛሬ መሰጠት የጀመረ ሲሆን፤ በጠዋት እና ከሰዓት መርሐግብር የሚከናወን ይሆናል፡፡

የትምህርት አመራርና መምህራን እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሳካ የሞዴል ፈተና እንዲኖርና በሂደቱም ተፈታኞቻችን ከሲሰተሙና ከፈተና ማዕከላቱ ጋር በአግባቡ እንዲተዋወቁ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ  አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ዘንድሮ 150 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናውን በብይነ መረብ ይወስዳሉ።

@ethioaplus
✳️ በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች! 😊

🔰 ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው ። ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለመድረግ ያስችለናል።  ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያረገናል ።  ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ: 
📌 አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ።

📌 በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ። 

📌 የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ።

📌• ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት።  እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው።  ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤

🙌🏾 ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤

🎯• ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። 

🎯• ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ።  እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ።

🎯 • ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል።   ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። 

🎯• ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። 

🎯• የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።

🔰 ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤

🍁 • ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።  

🍁• አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። 

🍁• ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።

🍁 • በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ።
ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር፡፡ ለምሳሌ ;አሁን ደህና ነኝ ፥ ጥሩ ሆኛለሁ ወይም በምናምነው ሀይማኖት ጊዜ የማይወስድብንን አጭር ፀሎት በልባችን መፀለይ። ከዛም መልሰን በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን መጀመር። 

🍁• ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤

🍁  • በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።

🍁• ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። 

🍁• በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን  መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት።


https://t.me/ethioaplus
😢1