Ethio A+
255 subscribers
211 photos
10 videos
203 files
98 links
A+ is Possible!
Feel free to ask and give any suggestion!
@EthioAplus_admin

https://youtube.com/@ethioa_plus?si=DekKjJasKzd5Oaq-
Download Telegram
በ2017 ዓ.ም የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚፈተኑ ተማሪዎች የኦንላይን መለማመጃ ፈተና መስጠት ተጀምሯል፡፡

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጅ ስራ አስፈጻሚ በተሰራው ሶፍትዌር አማካኝነት ከእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና በኦንላይን ለሚፈተኑ ተማሪዎች የመለማመጃ ፈተና በመሰጠት ላይ ነው።

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጅ ስራ አስፈፃሚ አዱኛው አለበል እንደገለጹት የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ኢንተርኔት ባለባቸው አካባቢዎች የሚማሩ ተማሪዎች በበይነ መረብ እንደሚሰጥ ከትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ሶስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1,670 ለሚሆኑ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የአይሲቲ ባለሙያዎች በተሰራው ሶፍትዌር የበየነ መረብ የመለመጃ ፈተና ከትናንት ጀምሮ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ስራ አስፈጻሚው አያይዘውም የመለማጃ ፈተናው አስፋላጊነት ተፈታኝ ተማሪዎች ቴክኖሎጅው ጋር አንዲግባቡና ለቀጣይ ለዋናው ፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የመለማመጃ ፈተናው  ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 07/2017ዓ.ም እንደሚሰጥ ጠቅሰው በቀጣይ የአዊ ብሄረሰብ ትምህርት መምሪያ በሚያወጣው መርሀ ግብር መሰረት የበየነ መረብ (ኦንላይን) ሞዴል ፈተና እንደሚፈትኑም ገልፀዋል።

@ethioaplus
#EthiopianDefenceUniversity

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ምልመላ ማድረግ ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን መልምሎ ለማስተማር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን በማካሔድ ላይ ይገኛል።

በዚህም ከመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሒዷል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ቅበላና ምልመላ ዙሪያ ገለጻ ከተደረገላቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ይጠቀሳሉ።

በወታደራዊ  ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በፈጠራ ክህሎት ልዩ አቅም ያላቸው ተማሪዎች በውድድር ዩኒቨርሲቲውን መቀላቀል እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በጤና፣ በኢንጅነሪግ እና ሌሎችም የሙያ ዘርፎች ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት መገለፁ ይታወሳል።

©️tikvahuniversity

@ethioaplus
#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀምሯል፡፡

አስተዳደሩ በመላ ሀገሪቱ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ የሆኑ ልዩ ታለንት ያላቸውን በመመልመል ለማሰልጠን ዝግጅት ማጠናቀቁን ግልጿል።

በመሆኑም በሳይበር ደህንነት፣ በዴቨሎፕመንት፣ በኢምቤድድ ሲስተም እና በኤሮስፔስ መስኮች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

ለመመዝገብ 👇
https://talent.insa.gov.et

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎች በመመለመለና በማሰልጠን ወደ ተቋሙ እና ወደ ሳይበር ኢንዱስትሪው እንዲቀላቀሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

©️tikvahuniversity

@ethioaplus
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈታና ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተና በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።

በትምህርት ሚኒሰቴር የተዘጋጁ የሁሉም ትምህርት አይነቶች የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides

@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?

➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 26 ፣ ሰኔ 27 እና ሰኔ 30/2017 ዓ/ም

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?

➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 4 ፣ ሐምሌ 7 እና ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም


@ethioaplus
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈታናዎች አገልግሎት አስትውቋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኤፍ ኤም ሲ እንደተናገሩት በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በሁለት ዙር ይፈተናሉ።

ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን ለመጨመር እና ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፈተናው በ2 ዙር በበይነ መረብ መሰጠቱ ከመኖሪያ ቤታቸው እየተመላለሱ በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ቁጥር ይጨምራል ብለዋል፡፡

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ በዩኒቨርሲቲዎች የሚፈተኑ ይሆናል።

ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣ በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። #ኤፍኤፍምሲ

@ethioaplus
@ethioaplus
#FYI

ትምህርት ሚኒስቴር ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች አጋዥ portal ይፋ አድርጓል።

እዚህ Portal ላይ
ለተለያዩ የትምህርት አይነቶች የቪዲዬ tutorial ታገኛላችሁ።
የተለያዩ ወቅታዊ ዜናዎችን ታገኛላችሁ።
የonline መፈተኛ ጣቢያችሁን ማየት ትችላላችሁ።
https://examinfo.moe.gov.et/guides

የመፈተኛ Portal
https://exam8.ethernet.edu.et

@ethioaplus
#FYI
⚡️የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምን ያህል ተማሪዎች ይወስዳሉ?

👉በአገር አቀፍ ደረጃ 608 ሺህ 588 ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል

👉309 ሺህ 547 የተፈጥሮ ሳይጓስ ተፈታኞች

👉299 ሺህ 41 የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች

👉150 ሺህ ተማሪዎች በኦላይን (በይነ መረብ) ፈተናቸውን ይወስዳሉ

@ethioaplus
በTelegram scam ለተደረጋቹ!

በተለያየ መንገድ Telegram ላይ scam ከተረጋችሁ ወደዚህ bot በመሄድ ማመልከት ትችላላችሁ።
Scam ያደረጋችሁን ሰው ስልክ ቁጥር፣ username፣ እንዲሁም ማስረጃ የሚሆናችሁን screenshot በማያያዝ
#report ማድረግ ትችላላችሁ።
@notoscam
©bighabesha_softwares

@Ethioaplus
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችለንን ቅድመ ዝግጅት እያደረገን ነው ሲሉ ተፈታኝ ተማሪዎች ገለጹ።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በመላ ሀገሪቱም ከ600 ሺህ በላይ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን በወረቀት እና በበይነ መረብ እንደሚወስዱ የወጣው ፕሮግራም ያሳያል።

ኢዜአ ለሀገር አቀፍ ፈተናው እየተደረጉ ያሉ ቅድመ ዝግጅቶችን አስመልክቶ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እና የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን አነጋግሯል።

በኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ አብርሃም ሠላምነህ በብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ወደ አዲስ የትምህርት ምዕራፍ ለመሻገር ሰፋ ያለ ዝግጅት እያደረኩ ነው ብሏል።

በተለይም ለፈተናው የሚረዱትን መጽሀፍት እንዲሁም በበይነ መረብ አማካኝነት አጋዥ የሆኑ ግብዓቶችን በማንበብ ላይ እንደሚገኝ ነው ያብራረው።

ሀገር አቀፍ ፈተናው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማርናቸውን ርዕሰ ጉዳዮች የሚሸፍን በመሆኑ ይህን ታሳቢ ያደረገ የአጠናን ዘዴ በመጠቀም እየተዘጋጀሁ እገኛለሁ ያለችው ደግሞ በዚሁ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪ የሆነችው ዳናት ባህሩ ናት።

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ሼርድ ካምፓስ የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አማኑኤል ታሪኩ በበኩሉ፥ ውጤታማ በመሆን ህልሙን እውን ለማድረግ በትምህርቱ ላይ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል።
ይህንን ጥረት ከግብ ለማድረስም በቀጣይ ወር በሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ከዚህ ቀደም የተማራቸውን ትምህርቶች ወደ ኋላ መለስ  ብሎ በመከለስ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።

ሌላኛዋ የካምፓሱ ተማሪ ሰሎሜ ታደሰ በፈተናው ውጤታማ እንድንሆን መምህራኖቻችን ጥያቄዎችን እንድንሰራ በማድረግና በሌሎች በሚያስፈልጉን ነገሮች  እየደገፉን ይገኛሉ ብላለች።

ፈተናው እየተቃረበ በመምጣቱ በእውቀትም በስነ-ልቦናም ብቁ ለመሆን ጥረቷን እንደምታጎለብት ገልፃለች።

ተማሪ አማኑኤል በበኩሉ፥ተፈታኞች ራሳቸውን በሚገባው ልክ በማዘጋጀትና በመፈተሽ ለላቀ ውጤት ዝግጁ መሆን አለባቸው ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

የኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ደለለኝ አስማረ  በበኩላቸው፥ ትምህርት ቤቱ በዘንድሮ ዓመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 632 የቀን 63 የማታ ተማሪዎችን ያስፈትናል ብለዋል።

ትምህርት ቤቱም ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው በሚፈለገው ደረጃ እንዲዘጋጁ ለማድረግ የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲወስዱ እና ተፈታኞች በግቢው እያደሩ ማጥናት የሚችሉበት ሁኔታ ማመቻቸቱን ተናግረዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎቹ በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚፈተኑ መሆናቸውን  በማንሳት በተለይም በበይነ መረብ ለሚፈተኑ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በኮምፕዩተር ልምምድ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ምክትል ርዕሰ መምህር አብርሃም ድሪባ፥ ካምፓሱ በሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ፈተና 80 ተማሪዎችን እንደሚያስፈትን አስታውቀዋል።

ተማሪዎቹም ለረጅም ዓመታት በትምህርት ዓለም ያደረጉት ጉዞ ፍሬያማ እንዲሆን የተለያዩ ሞዴል ፈተናዎችን እየወሰዱ እንደሚገኙ አንስተው፥ ይህም እስከ ፈተናው መዳረሻ ይቀጥላል ነው ያሉት።

@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከ608 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ!

በ2017 የትምህርት ዘመን ከ608 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ መልቀቂያ ፈተና የፈተና ስርቆትና ኩረጃ በሚቀንስ መልኩ በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።

በወረቀት የሚፈተኑት መሰረተ ልማት ያልተሟላባቸው፤ ኮምፒውተር እና ኢንተርኔት ኮኔክሽን በበቂ ባላገኙ አካባቢዎች የሚገኙ ተፈታኞች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ዋና ዳይሬክተሩ፤ በበየነ መረብ የሚሰጠው ፈተና እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ ወደፊት ሙሉ በሙሉ ፈተናውን በበየነ መረብ ለመስጠት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የፈተና ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን በመግለጽ፤ ፈታኞችን የመመልመል፤ የተመለመሉት ወደዬመፈተኛ ጣቢያው እንዲሰማሩ የማድረግ ዝግጅት እየተካሄደ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡በአማራ ክልል ባለው ግጭት ሳቢያ በርካታ ት/ቤቶች የዘንደሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደማያስፈትኑ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግሥቱ በቅርቡ ገልጸዋል።

በክልሉ በአጠቃላይ 685 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊዋ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የዘንድሮውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶች 470 ብቻ ናቸው ብለዋል።

ክልሉ ቀደም ባሉት ዓመታት በየዓመቱ ከ150 ሺህ እስከ 180ሺህ ተማሪዎችን የማስፈተን አቅም እንደነበረው የገለጹት ኃላፊዋ ሰላም ባለባቸው አከባቢዎች በሚገኙ ት/ቤቶች የሚገኙ 99ሺህ 880 ተማሪዎች የዘንድሮን ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል ሲሉ ተናግረዋል።


@ethioaplus
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወሰዱ ተማሪዎች ለቅድመ ዝግጅት የሞዴል ፈተና እየተሠጠ መሆኑ ተገለጸ

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወሰዱ ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት ሥራ እንዲሰሩ እና ተማሪዎች 'ምን ያህል ተዘጋጅተዋል?'የሚለውን ለማወቅ፤ በክልል እና በሀገር ደረጃ የሞዴል ፈተና እየተሠጠ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይልቃል ወንድሜነህ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤የሞዴል ፈተናው የሚሰጠው ተማሪዎች ከዋናው ፈተና በፊት የዝግጅት ደረጃቸውን እንዲገመግሙ ለመርዳት ነው።

"ፈተናው ተማሪዎች ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን እንዲለዩ፣ ጊዜያቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲቆጣጠሩ እና ከፈተና ጋር የተያያዘ ጭንቀትን እንዲቀንስ ያስችላቸዋል" ሲሉም ተናግረዋል።

እንዲሁም ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉት ጥያቄዎች አወቃቀር እና አስቸጋሪነት እራሳቸውን እንዲያውቁ ጠቃሚ ዕድል ይሰጣቸዋል።

ሞዴል ፈተናው በክልልም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጥ ሲሆን፤ ይህም ተማሪዋቹ ምን ያህል ብቁ ናቸው የሚለውን ትክክለኛ ግምገማ እያስገኘ ነው ተብሏል።

እንዲህ ያለው ሁሉን አቀፍ የዝግጅት ስልት በሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎችን አጠቃላይ ውጤት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የ2017 ትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ከሰኔ 23 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ በወረቀት የሚፈተኑ እና በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች እንደሚያካትት ተገልጿል።

የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ፤ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ሊዘጋጅ እንደሚገባ አስተላልፏል።
የ2017ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቶች  ተጠናቀዋል - የትምህርት ፈተናና ምዘና  አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
****

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የትምህርት ፈተናና ምዘና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ ተናገሩ።

አብዛኛውን ጊዜ ፈተና ሲነሳ የፈተና ስርቆትና ኩረጃ አብሮ የሚነሳ ሲሆን፤ ይህን ለማስቀረት መንግስት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ሀገረ አቀፍ ፈተናን ተማሪዎች ከተማሩበት ት/ቤት ወደ  ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው እንዲፈተኑ አድርጓል።

ለፈተና ስረቆትና ኩረጃ የሚያግዙ  ድምፅን ምስልን የሚወስዱ ማንኛውንም  መሳሪያዎችን ተማሪዎች እንዳይጠቀሙና ይዘውም እንዳይገኙ  በመከልከል፤ ጥብቅ ፈተሻ  እንደሚደረገ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ  ተይዘው ሲገኙም እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ተማሪዎች ፈተናን ለመስረቅና ለመኮረጅ የሚያባክኑትን ጊዜ ትምህርቱን በሚገባ ቢያጠኑበት መልካም ነው፤ ውጤታማም ብለዋል።

በብይነ-መረብና በወረቀት የሚሰጠው የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በተሳካ መንገድ ለመስጠት፤  የትምህርት ተቋማት የቁሳቁስና የተለያዩ ዝግጅቶችን አጠናቀው ተማሪዎችን በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ፈተናውን በብይነ መረብ የሚፈተኑ ተማሪዎች በየትምህርተ ቤታቸው ልምምድ በማድረግ ላይ እንዳሉ የጠቆሙት ዶ/ር እሸቱ፤ ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎችም ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኙ እየተደረገም ይገኛል ነው ያሉት።

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ግብአቶች ዝግጁ መሆናቸውን መፈተሸና ለሰው ሀይል ስልጠናዎችን መስጠት፤ እንዲሁም ከክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ከዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሮች ጋር በቅርበት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።