Ethio A+
255 subscribers
211 photos
10 videos
203 files
98 links
A+ is Possible!
Feel free to ask and give any suggestion!
@EthioAplus_admin

https://youtube.com/@ethioa_plus?si=DekKjJasKzd5Oaq-
Download Telegram
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚያግዙ ብዙ የትምህርት material እንለቃለን እናንተ share share አድርጉ🙏

@ethioaplus
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እዉነት ወይስ ሀሰት?
መልሱን ኮሜንት ላይ
👇👇👇👇👇👇
👍1
‼️ነፃ የስኮላርሺፕ ዕድል‼️

Netherlands Scholarships 2025 at University of Twente, Netherlands for World Students!

No Agent - Direct Apply

👉Apply Link: https://scholarships365.info/netherlands-scholarships-2025-university-of-twente

Degree: Multiple Degree Programs

Benefits: Higly Funded Support upto 22000 Euro Yearly!

Deadline: Different Deadline for each programs

forward for your friends

Join us for more
👇👇👇👇👇👇
@ethioaplus
በሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በዲጂታል የመመዝገብ (School Mapping) ሥራ ጀምረናል። - ትምህርት ሚኒስቴር

ከሕዝብ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፤ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በሙሉ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማፕ የማድረግ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በዚህም ትምህርት ቤቶቹ በሚገኙባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ብዛትን በማየት የት ነው ትምህርት ቤት መገንባት የሚያስፈልገው የሚለውን በደረጃ ለይተናል ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በ School Mapping ፕሮጀክቱ አማካኝነት የተጎዱ እንዲሁም ትምህርት ቤት በጣም የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ተለይተው፥ ዝርዝር እየወጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ሲተገበር የትምህርት ቤት አቅርቦት ለሁሉም በእኩል ለማዳረስ ያስችላል ብለዋል።

@ethioaplus
የ2017 ማትሪክ ፈተና መቸ ይሰጣል ?

ትልልቅ ከተሞች ላይ በኦላይን እንደሚሠጥ በአጠቃላይ ከ600ሺህ በላይ ተማሪዎች የተመዘገቡበት የ2017 የ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና መቸ ይሰጣል ?

መስከረም ላይ የአ/አ ከተማ ባወጣው አመታዊ schedule መሠረት ከሰኔ 18-27 እንደሚሰጥ ገልፆአል ። በመሆኑም የእናንተ ፈተና የሚሆነው ከሪሜዲያል እና መውጫ ፈተና ቀጥሎ በመሆኑ ከሰኔ 15 በኋላ ነው ብሎ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል
ዝግጁታችሁን በዚህ ቀን መሠረት እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን። እናም በዚህ ሰአት የመደናገጥን ስሜት በማስወገድ ውጤታማ ንባብ አንብቡ።

@ethioaplus
የአቅማችንንን በመለገስ የወንድማችንንን ህይወት እንታደግ:ለህክምና የተጠየቀዉ ወጪ ከሱም ሆነ ከቤተሰቡ በላይ በመሆኑ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ስራ  በማቆማቸዉ  ንቅለ ተከላ ለማድረግ ደግሞ ብዙ ገንዘብ ስለተጠየቁ በምትችሉት ሁሉ ደጋግ እጆቻችሁን ዘርግታችሁ ቸርነትን ታደጉት።
👹ጥንቃቄ

ቀጥታ አካወንታችሁን ነው የሚጠልፉት ይህን ሊንክ ተጭናቹ እንዳትገቡ  ከምታምኑት  ሰውም ጭምር ቢላክላችሁ እንዳትነኩት የነዛም ሰዎች አካወንት ተጠልፎባቸው ነው።

ጥንቃቄ ጥንቃቄ ለሁሉም ሼር አድርጉት ይህ የነካችሁ ካላችሁ በቀጥታ አካወንታቹ ሀክ ተደርጓል ማለት ነው scam ነው

ይህን ሁለተኛ ፎቶ ላይ ያለውን setting በማስተካከል የተጠለፈባችሁን አካወንት አስመልሱ።

Settings -> devices -> በቀይ የተፃፈውን Terminat All Other session  የሚለውን ተጭናቹ  ok በማለት 24  ሰአት ሳይቆይ አስወግዱት 24  ሰአት ከቆይ እናንተን ሙሉ ለሙሉ የማስወገድ ሀይል አለው

ለሁሉም ሼር አድርጉት

@ethioaplus
አንድ ለዶክትሬት ዲግሪ ፍልስፍና የሚያጠና ወጣት ነበር። የእሱ አባት ደግሞ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ በእኛ አገር አጠራር መሀይም የሚባሉ ነበሩ። 

ወጣቱ ከረዥም የትምህርት ቆይታ በኋላ በፍልስፍና ዶክትሬቱን አግኝቶ ወደቤቱ ተመለሰ። አባትየውም አንድ የተጠበሰ ዶሮ ገዛና ለሚስቱ ለልጃቸው ምርቃት የደስደስ በማሰብ እራት እንድታዘጋጅላቸው አዘዛት። ሁሉም ሰው ጠረጴዛው ላይ ተቀምጦ ሳለ አባትየው ከመመገባቸው በፊት ልጁን፦“የኔ ዶክተር በቀኝ ትከሻዬ ስር ህመም ይሰማኛል። እራት ከበላን በኋላ ትመረምረኝና መድሃኒት ታዝልኛለህ” አለው።

ልጁም እየሳቀ፦“አባቴ እኔ የፍልስፍና ዶክተር እንጂ የህክምና ዶክተር አይደለሁም” አለው።

አባትየው በመገረምና ተስፋ በመቁረጥ ጭንቅላቱን እየወዘወዘ፦“የኔ ልጅ ይህ ፍልስፍና ምን እንደሆነ ልትነግረኝ ትችላለህ?” ሲል ጠየቀው።

ልጁም ፈገግ አለና “እዚህ ጠረቤዛ ላይ ያለውን ዶሮ አየኸው?” አለው።

አባትየውም፦ “አዎ” ሲል መለሰ።

ልጁም፦“አንድ ሳይሆን ሁለት ዶሮዎች መሆናቸውን ላሳምንህ እችላለሁ”

ይህንን የሰማው አባት ፈገግ በማለት፦“አንተ አሁን ነው የገባኝ” አለውና ጠረቤዛው ላይ ያለውን ዶሮ ወደራሱ እየሳበ፦“ይሄን እኔና ሚስቴ እንበላለን፤ ችግር የለውም አንተ ሁለተኛውን ዶሮ ብቻህን መብላት ትችላለህ”
🤝🏼

@ethioaplus
FOR MORE FULLY FUNDED SCHOLARSHIPS JOIN US👇

📌Telegram:- https://t.me/ethioaplus

🎓 If this isn’t for you, 📣 share it with others! 🌟
      አንድ ቀን እንዴት ነገሮችን ታግሰህ ፣ ተቋቁመህና አሸንፈህ እንደወጣህ አስደማሚ ታሪክህን ታጋራለህ እሱም ለብዙዎች አበርቺ ይሆናል.... ታገስ!ጽና!!
🤞 መልካም ቀን!!👋

@ethioaplus
ለእስልምና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች

🌙 እንኳን ለ1 ሺህ 446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!

©️ ethioaplus
....ጥቁሮችን አብዝቶ የሚጠላ አንድ ነጭ አሜሪካዊ ወጣት፣ ለመዝናናት ኒዉዬርክ ዉስጥ ካሉ ሆቴሎች መሃል ወደ አንዱ ይገባል።

በሆቴሉ ዉስጥ ጥግ ይዞ ከተቀመጠዉ አንድ ጥቁር ሰዉ በስተቀር በሆቴሉ ውስጥ ይዝናኑ የነበሩት በሙሉ ነጮች ነበሩ።

ይህ ወጣት ብቻዉን የተቀመጠዉን ጥቁር ሰዉ በጥላቻ እየተመለከተ አስተናጋጇን በመጥራት ድምፁን ከፍ አድርጎ...

"ከዚያ ጥቁር ሰዉ በስተቀር!!እዚህ ሆቴል ዉስጥ ላሉት ሰዎች የሚፈልጉትን ምግብ ይመገቡ ሂሳቡን እኔ ነኝ የምከፈለዉ!!" በማለት ከኪሱ ብዙ ዶላሮችን አዉጥቶ ለአስተናጋጇ ይሰጣል።

አስተናጋጇም በሰጣት ብር፣ ከጥቁሩ ሰዉዬ ዉጭ፣ ሆቴሉ ዉስጥ ላሉት በሙሉ የሚፈልጉትን አይነት ምግብ አቀረበችላቸዉ።

ጥቁሩም ሰዉ ከመናደድ ይልቅ አሜሪካዊውን ወጣት አየተመለከተ "አመሰግናለሁ!!" ይላል።

ወጣቱ እንደጠበቀዉ ጥቁሩ ሰዉ ምንም እንዳልተበሳጨ ሲመለከት ፣ ድጋሜ አስተናጋጇን ይጠራና ድምፁን ከፍ አድርጎ.. "አሁንም ከዚያ ጥቁር ሰዉዬ ዉጭ ሆቴሉ ዉስጥ ላሉት በሙሉ ወይንና ሌላ የሚፈልጉት ነገር ይጠቀሙ እኔ ነኝ የምከፍለዉ!!"በማለት  ጥቁሩን ሰዉ በጥላቻና ቁጣ አየተመለከተ ብዙ ዶላሮችን ከኪሱ አዉጥቶ ለአስተናጋጇ ይሰጣል።

አስተናጋጇም እንደታዘዘችዉ ለሁሉም እንደየፍላጎቱ አቀረበችላቸዉ።

ጥቁሩ ሰዉዬም እንደቀድሞዉ ሁሉ ፈገግ በማለት ወጣቱን "አመሰግናለሁ" ይለዋል።

የጥቁሩ ሰዉ ፈገግታ አሜሪካዊዉን በጣም ያናድደዉና አስተናጋጇን ጠርቶ..."ይኼ ጥቁር ሰዉ ግን ያመዋል እንዴ? ከእሱ ዉጭ ሌላዉን ሰዉ ሁሉ ስጋብዝ መናደድ ሲገባዉ እየሳቀ አመሰግናለሁ ይለኛል። ጤነኛማ አይመስለኝም!!"ሲል አስተናጋጇን ይጠይቃታል።

አስተናጋጇም ፈገግ በማለት "ኧረ ጤነኛ ነዉ!! የሆቴሉ ባለቤት ስለሆነ ነዉ!!" በማለት ነበር የመለሰችለት።

ጥላቻ የነበረንን፣ ያለንን፣ ሊኖረን የሚችሉ ነገሮችን በሙሉ ሊያጠፋ የሚችልና የሰይጣንን ምግባር በሚገብሩ ጥቂት አወቅን ባይ አላዋቂዎች የሚፈበረክ፣ አሰተሳሰብን ለማዛባት በሚስኪኑ ህዝብ ላይ የሚለቀቅ የጭንቅላት ቫይረስ ነዉ።

ለዚህ አደገኛ ቫይረስ ሁነኛ '𝓪𝓷𝓽𝓲 𝓿𝓲𝓻𝓾𝓼'ፍቅርና መዋደድ ብቻ ነዉ!!

የንባብ አለም 📗🌍

𝓢𝓱𝓪𝓻𝓮 𝓪𝓷𝓭 𝓳𝓸𝓲𝓷
@ethioaplus
ሮበርት ሙጋቤ ይህን ብለው ነበር👇

"የአፍሪካ የትምህርት ስርአት አስገራሚ ውጤቶች አሉት።

አንደኛ ደረጃ የሚይዙ ቀለሜ ጎበዝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት አምጥተው ኢንጂነሪንግና ሜዲሰን እዲማሩ እድል ያገኛሉ።

ሁለተኛ ደረጃ የሚይዙት ደግሞ ህግና
ማኔጅመንት ተምረው አንደኛ ደረጃዎቹን
ያስተዳድሯቸዋል።

ዝቅ ብለው በ ሶስተኛ ደረጃ የሚገኙት
ተማሪዎች ደግሞ ፖለቲካ ውስጥ ይገቡና አንደኛም ሁለተኛም ደረጃ ላይ ያሉትን ከላይ ሆነው ይቆጣጠራሉ።

በትምህርት ወዳቂዎች ደግሞ ፖሊስና ወታደር ይሆናሉ እነዚህ ደግሞ ፖለቲከኞችን ይቆጣጠራሉ ደስ ያላላቸውን ፖለቲከኛ እስከ መግደል ድረስ ።

ከሁሉም ግን ምርጡ ጭራሽ ክላስም ሆነ ትምህርት ቤትም ገብቶ የማያውቀው ደግሞ ነብይና ጠንቋይ ይሆናል ይሄን ደግሞ ሁሉም ይከተሉታል፡፡

𝓣𝓱𝓮 𝓵𝓮𝓰𝓮𝓷𝓭 🫡

@ethioaplus
👍2👎2💯1
እስኪ react ማድረግ እጃቹ ይልመድ 🙁 እዚ ቤት ምንድን ነው ዝምታው 🫠 Subscribe, like, Share እያደረግን ቻናላችንን ተደራሽ እናድርጋት 👍🏽 ❤️

https://t.me/ethioaplus
4
ሮበርት ሙጋቢ

... ሮበርት ሙጋቤ እንዲህ ብለው ነበር...ለነጫጭ መኪኖች ጥቁር ጎማ መጠቀም እስካልቆመ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም

ከሌሎች ቀለማት በፊት ነጫጭ ልብሶችን አስቀድሞ ማጠብ እስካልቆመ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም

ጥቁር ቀለምን ለመጥፎ ገድ፣ ነጭን ደግሞ ለሠላም ምልክት መጠቀም እስካልቆመ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም

ጥቁር ቀለምን ለሐዘን፣ ነጭን ግን ለሠርግ መጠቀም እስካልቆመ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም

ዕዳቸውን ያልከፈሉ ሰዎችን ከነጭ መዝገብ ይልቅ ጥቁር መዝገብ ላይ መመዝገብ እስካልቆመ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም

በፑል ጨዋታ ላይ ጥቁሩ ድንጋይ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ነጩ ድንጋይ በሜዳው ውስጥ ብቻውን በድል መንከባለሉ እስካልቀረ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም

እኔ በበኩሌ ችግር የለብኝም፤ ሽንት ቤት ገብቸ የምጠርገው በነጭ ወረቀት ( ሶፍት) እስከሆነ ድረስ ብዙ ቅር አይለኝም 😍

ሮበርት ሙጋቤ

@ethioaplus
@ethioaplus
Ethio A+
Photo
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።

ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ በቀረበ ጥናት ላይ  ውይይት ሲደረግ፣ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።

ላለፉት ዓመታት(እሳቸው  በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ)፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ  እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።

ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

''የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ'' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ "በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል"ሲሉ ተናግረዋል። ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።

ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።

ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።

በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ "የመምህራን ባንክ" ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።

ባንኩ "በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን" ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

#Reporter

@ethioaplus
@ethioaplus
🔀Kind of paragraph 📒

🥇 Expository paragraph

The purposes of an expository paragraph are:

To instructor teach readers about something, and to change or add to the knowledge or attitude of the readers
To explain processes and give directions
To explain a new idea or a method of doing something

🥈 Narrative paragraph

The purpose of a narrative paragraph are:

Telling a story
A History text about historical events
A letter you write to your friend about your journey

🥉 Descriptive paragraph

The purpose of this Descriptive paragraph is:

To show the reader what someone or something looks like
To create pictures in the reader's mind

4️⃣ persuasive( argumentative) paragraph

The purpose of this study is:

For Advertisement
To convince or persuade


🆒 Likeℹ️ Share 🛂

𝚓𝚘𝚒𝚗 𝚞𝚜 
@ethioaplus
👍1