. . . #ፍቅር_ያሸንፋል . . .
በአንድ ወቅት ሁለት በጣም ሚዋደዱ ባለትዳሮች በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ የእነዚህ ጥንዶች ፍቅር ሙሉ መንደሩን ያስቀና ነበር፡፡ ከግዜ ወደግዜ ከመንደሩ አልፎ የግዛቱ አስተዳዳሪ ጋር ይህ የጥንዶቹ ጉዳይ ደረሰ፡፡ አስተዳዳሪውም በሰሙት ነገር ተገርመው እውነት ስለመሆኑ ማረጋገጥ ፈለጉ፡፡ በዚህም አንድ ነገር አስበው ባልና ሚስቱን አስጠሯቸው፡፡ ሁለቱንም ብቻ ለብቻ ማናገር ጀመሩ . . .
" ባለትዳር መሆናቹን ሰምቻለው፡፡ ነገር ግን የኔ ልጅ ባልሽን ስላፈቀረቸው ላጋባቸው ወስኛለው፡፡ "አሉ ወደ ሚስትየው እየተመለከቱ፡፡"ይሄንን በመፍቀዴ ለኔ ምን አገኛለው ?" አለች ሚስት ጥያቄውን በጥያቄ እየመለሰች፡፡ "ይሄንን ከፈቀድሽ እና ባልሽን ካሳመንሽ ላንቺ እድሜ ልክሽን ሚያኖርሽ ገንዘብ ለልጅ ልጅ ሚተላለፍ የእርሻ መሬት እና በርካታ ከብቶች ሰጥሻለው፡፡ እንዲሁም ከምትፈልጊው ሰው ጋር አጋባሻለው፡፡ "አሉዋት፡፡ "አሁን እርሶ በሚሰጡኝ ገንዘብ እና መሬት እንዲሁም በሚሰጡኝ ከብቶች ጠቅላላ ባሌን ይመልሱልኛል?ከፈለግሽው ሰው ጋር አጋባሻለው ብለውኛል አይደል፡፡ ስለዚ አሁንም መልሼ ማግባት ምፈልገው ባሌን ነው፡፡ ከባሌ ጋር መልሰው ያጋብኝ እና በክብር ወደቤት ይላኩን፡፡ "አለች አስተዳዳሪው ፊት እጅ እየነሳች፡፡ አስተዳዳሪው እጅጉን ተገረሙ፡፡ ለመሆኑ የፍቅራቹ ሚስጥር ምንድነው? ሲሉ ባልየውን ለብቻው አስጠርተው ጠየቁት፡፡ "እኔ ምወደው እሷን ነው፡፡ እሷ ምትወደው እኔን ነው፡፡ እኛ ምንፈላለገው እርስ በእርሳችን ነው፡፡ ከኛ ውጪ የለበስነው ልብስ እንኳ ለኛ ትርፍ ነው" ሲል መለሰ፡፡
የሁለቱ መልስ አስተዳዳሪውን አልፎ በመላው ግዛት ተሰማ፡፡ ሁለቱ ጥንዶች ለሌሎች ባለትዳሮች ተምሳሌት ሆኑ፡፡ በነሱ ቃል የመጣ የብዙዎች አመለካከት ተቀየረ፡፡ የተጣሉ ታረቁ ፣ ብዙዎች የነበረባቸውን ጉድለት አስተካክለው በትዳራቸው ደስተኛ መሆን ጀመሩ፡፡ ሰዎች አመኑ ለሰው ከሰው ውጪ ያለው ነገር ትርፍ ነው፡፡ ደስታችን በልባችን ነው ብለው ተቀበሉ፡፡ የፍቅር ሀያልነት በጉልህ ታየ፡፡
የዛኔ የተፈጠረው ነገር ዘመን ተሻግሮ ዛሬ እኛንም ለማስተማር በቃ፡፡ ፍቅር ይሻለናል፡፡ በፍቅር እንኑር፡፡

#ጠቃሚ_መልእክት
አንድ ንጉስ አስር ተናካሽ የሆኑ ውሾች ነበሩት ፤ እነዚህን ውሾችም አገላጋዮቹን ‹አሽከሮቹን› ሲያጠፉ ለማሰቃዬትና ለማስበላት ይጠቀምባቸዋል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን አንደኛው አሽከሩ ትክክል ያልሆነ ሃሳብ ንጉሱን ተናገረው ፤ በዚህም ምክንያት ንጉሱ እጅግ ተቆጣበት ፤ ወዲውኑም ወደ ውሾቹ እንዲወረወር ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ አሽከሩም በሀዘን "አስር አመታት አገለገልኩህ ፤ ተገዛውልህ ያልከኝን ሁሉ አደረኩልህ ፤ አሁን ግን ይህንን አደረክብኝ ፤ እባክህ ወደ ውሾች ውስጥ ከመወርወሬ በፊት አስር ቀን ስጠኝ" ብሎ ተማጸነው፡፡ ንጉስም ተስማማ ‹ፈቀደለት› ፡፡ ይወረወር ዘንድ የተፈረደበት አሽከር ውሾቹን ወደሚንከባከበው ሌላኛው አሽከር ሔደና ‹እባክህ እነኝህን ውሾች ለአስር ቀን ልንከባከባቸው › ብሎ ጠየቀው፡፡ የውሾቹ ጠባቂም ግራ በመጋባት ሁኔታ ፈቀደለት ፡፡
የተፈቀደለት አሽከርም ውሾቹን መንከባከብ ጀመረ ፤ ቆሻሻቸውን ማጸዳዳት ፤ ምግባቸውን በሰአቱ ማቅረብ ፤ ማጠብና አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ አደረገላቸው ፤ አስር ቀኑም አለቀ፡፡ ከዚያም በኋላ ከንጉስ ጋር በተነጋገሩት መሰረት …አሽከሩ ተጠርቶ ወደ ተናካሽ ውሾቹ ዘንድ ይወረወር ዘንድ አዘዘ ፤ ወረወሩትም ፡፡ ወርዋሪዎቹም ይህ አሽከር እንዴት በውሾቹ ሊበላ እንደሚችል እየዘገነናቸው መመልከት እንደጀመሩ ያላሰቡትን ሁኔታ በአይናቸው አዬ ፤ ንጉሱም በሚመለከተው ሁኔታ ግራ ተጋባና "በእነዚህ ተናካሽ ውሾቼ ላይ ምን ደረሰ ? ምንስ ገጠማቸው? ማለት እንደጀመረ… የተወረወረው አገልጋይ በውሾቹ መሃል እየተሻሼ በኩራት እየተራመደ እንዲህ አለ "እነዚህን ውሾች ለአስር ቀናቶች ብቻ መገብኳቸው ተንከባከብኳቸው እነርሱም ያደረኩላቸውን በፍጹም አልዘነጉም ፤ አንተን ግን አስር አመት ሙሉ ተገዛሁልህ አገለገልኩህ ነገር ግን በአንዲት ጥፋት ምክንያት ሁሉንም ረሳህና ለሞት አሳልፈህ ሰጠኸኝ" አለው ፡፡ ንጉሱም ሁኔታውን ሁሉ በማስተዋልና ፤ ከውሾች እንዳነሰም በመገንዘብ አገልጋዬ ነጻ እንዲሆን አዘዘ ፤ ነጻም ሆነ፡፡
#ይህ_መልእክት ሰው በጣም ብዙ ውለታ ውሎላቸው ነገር ግን በአንድ ጥፋት ምክንያት የተደረገላቸውን ሁሉ እየረሱ በክፋት ለሚነሳሱ ሁሉ ይሁን፡፡ በመልካም ነገር የተሞላ ታሪክን ፤ በአንድ ስህተት ምክንያት ከንቱ አናድርግ፡፡

“ከብቶች ሁሉ አንድ
አይነት ሳር እየበሉ ……..”
“ከብቶች ሁሉ አንድ አይነት ሳር እየበሉ ፋንድያቸው ለምን ተለያያ?” ፣ ይህ አባባል ለከብቶች መንጋ ብቻም ሳይሆን ለሰዎች መንጋም የሚሰራ መሰለኝ።
አንድ አይነት ትምህርት ቤት ገብተን፤ በአንድ አይነት መምህር ተምረን፤ በአንድ ክፍል ውስጥ ተቀምጠን፤ በስተመጨረሻ አንዳችን ከፍ ብለን ስንቆም ሌሎቻችን ግን ከጀመርንበት ፈቀቅ አንልም። ይህን ጥያቄ
ስንጠይቅ የሰውን ልጅ የህይወት መስመሮች ሊቀይሩ የሚችሉ ነገሮች እንዳሉ በማሰብ ጭምር ነው።
ሌሎቻችን የማናውቃቸው በእያንዳንዳችን ጎዳና ላይ የሚጋረጡ ውጣ ውረዶችን በመዘንጋት አይደለም።
ነገር ግን ብዙ ጊዜ እኩል እድል ተሰጥቶን፤ በተመሳሳይ ሰዓት ፊሽካ ተነፍቶልን እያለ፤
ለምንድነው ውጤታችን የሚለያየው? እርግጥ ነው በውድድሩ አለም ሁሉም ሰው አሸናፊ ሊሆን አይችልም። ህይወት ግን እርስ በእርስ የሚፎካከሩባት የሩጫ ሜዳ ሳትሆን ሁሉም በገዛ ሜዳው እሮጦ ሁሉም በራሱ ሜዳ
አሸናፊ ሊሆን የሚችልባት ቦታ ናት።
ከብቶች ሁሉ አንድ አይነት ሳር እየበሉ ፋንዳያቸው ለምን እንደሚለያይ ከአባባልነቱ በዘለለ እኔ በግሌ የማውቀውም ሆነ ያነበብኩት የለም። እንደው አባባሉ
ከሰው ልጆች ህይወት ጋር ተመሳስሎብኝ ብዕሬን አስነሳኝ እንጂ። እኔ እንኳን በአጭሩ እድሜዬ አንድ አይነት ትምህርት ቤት ተምረን እኩል ሀ ሁ ያልን
ልጆች አሁን በተለያየ የህይወት እርከን ላይ ሆነን ሳይ፤ ልዩነቱ ምን ላይ እንደሆነ ለማወቅ ጓጓሁኝ። የኑሮ እርከን ብዬ ስናገር፤ ስኬት በግል መመዘኛ የሚመዘን
መሆኑን በመዘንጋት አይደለም። ሆኖም ተመሳሳይ እድል ተሰጥቶን፤ በእኩል ሰዓት ፊሽካ ተነፍቶልን፤ አንዳንዶቻችን ለምን ከመንገድ እንቀራለን? ተመሳሳይ
እድል ገጥሞን ውጤታችን ለምን ይለያያል? አንድ አይነት የኑሮ ሳር ግጠን ለምን ከእኛ የሚወጣው ነገር የተለያየ ሆነ? ከታች የዘረዘርኳቸው ነጥቦች ጥቂቶችን ከብዙሃኑ ከሚለዩዋቸው ባህሪዎች ውስጥ ወሳኞቹ ናቸው።
አሸናፊዎችን ከብዙሃኖቻችን ነጥረው እንዲወጡ የሚያደርጓቸው የተለያዩ ነገሮች ቢኖሩም የሚከተሉት ግን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
1) አሸናፊዎች የሚፈልጉትን ያውቃሉ
የምንፈልገውን እንደአለማወቅ በዚህ ምድር ላይ እንድሜያችንን የሚበላ ምንም ነገር የለም። ብዙዎቻችን እራስን ፍለጋ በሚለው ፈሊጥ አቅጣጫው እንደጠፋበት መርከብ በባህር ላይ እንቀዋለላለን። የምንፈልገውን
ባለማወቃችን የማንፈልገውን ኑሮ ለመኖር እንገደዳለን። እዚህ ላይ ግን ልብ ልንለው የሚገባና
ብዙዎቻችን የተሳሳተ መስመር ውስጥ የሚከት አስተሳሰብ አለ። ይህም እራስን ፍለጋ በሚል ፈሊጥ የብዙ ሰዎች እድሜ ይባክናል። ብዙዎችን የሚያስማማው የእራስን የማግኘት ትርጉም ፤ የሚያስደስተንን ነገር ማድረግ ነው። አለን ዋትስ የተባለ ሊቅ በአንድ ወቅት ለወጣቶች እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር “ብዙ ወጣቶች እራሳቸውን እንዴት ማግኘት
እንዳለባቸው እንዳስረዳቸው ይጠይቁኛል። በተለይ ከከፍተኛ ደረጃ ት/ቤት ወጥተው አዲስ የኑሮ ምዕራፍ ለመጀመር የተዘጋጁ ወጣቶች በህይወታቸው ምን መምረጥ እንዳለባቸው ስለማያውቁ እርዳታ ይጠይቁኛል። የኔ መልስ እንዲህ ነው ገንዘብ ቅድሚያ ባይሰጠው ምን ማድረግ እንደሚያስደስታቸው እጠይቃቸዋለው? ገንዘብ ቦታ ባይኖረው ጊዜያቸውን ምን በማደረግ ማሳለፍ እንደሚሹ ሲነግሩኝ ፤ እራሳቸውን በዛ ውስጥ እንደሚያገኙት መክሬ እሰዳቸዋለው።” ብሏል።
እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን አንድ ነገር አለ። በተለይ በእኛ አገር ገንዘብን የሚያስገኝን ነገር ትተን
ተሰጥዎን በነጻ ልኑር ማለት ዘበት ነው። ስለዚህ አንዴ የምንፈልገውን ነገር ካወቅን በኋላ ያንን ተሰጥዎ ወደ ገንዘብ የምንለውጥበትን መንገድ መመርመር አለብን። ባጠቃላይ የምንፈልገውን ማወቅ፤ በነፍሳችን ውስጥ የተለየ ጉልበት እንዲኖረን ያደርገናል።
2) አሸናፊዎች ልዩ መሆንን አይፈሩም
እውነት እንነጋገርና ልጆች ሆነን እንደው ልዩ በመሆናቸው ብቻ የምናሾፍባቸው እኩዮቻችን እንደነበሩ እናስታውሳለን።
ከብዙሃኑ ጋር አብረው ባለመጓዛቸው የተወቀሱ፤
የተሾፈባቸው ልጆች ናቸው በስተመጨረሻ የሩጫው አሸናፊ ሆነው የምናያቸው። ሮል ሞይ የተባለ ጸሃፊ ሰዎች በህይወታቸው ስኬታማ እንዳይሆኑ ከሚያደርጓቸው ነገሮች ውስጥ ዋነኛው ልዩነትን መፍራትና ብዙዎች በሄዱበት መንገድ ለመሄድ መሞከር ወይም ብዙሃኑን መምሰል እንደሆነ ይናገራል።
3) አሸናፊዎች የራሳቸው አነቃቂዎች ናቸው
ብዙዎቻችን የሚያነቃቃን ነገር እንፈልጋለን። ለምሳሌ ልጅ ሆነን እንኳን አንዳንድ ተማሪዎች የቤት ስራቸውን የሚሰሩት ወይ የአስተማሪውን ቁጣ ፈርተው አልያም የቤተሰብን ግርፊያ ፍራቻ ነው። ጥቂት ተማሪዎች ግን
መምህሩ ኖረም አልኖረም፤ ቤተሰብ ተቆጣጠራቸውም አልተቆጣጠራቸውም የቤት
ስራቸውን መስራታቸው አይቀርም። እንደዚህ አይነቶቹ
ተማሪዎች ናቸው በኋላ በህይወታቸውም ለኑሮዋቸው
ሃላፊነትን መውሰድ የሚችሉት። እንደዚህ አይነት ሰዎች የሌላው ማነቃቂያ ሳይሆን የራሳቸው ፍላጎት ነው የኑሮዋቸው መቅዘፊያ።የመጀመሪያ ነጥብ
ማለትም ፍላጎትን ማወቅ ከዚህ ጋር ጥብቅ ግንኙነት አለው። የምንፈልገውን ነገር ስናደርግ ከራሳችን ፍላጎት ውጪ ማነቃቂያ አያስፈልገንም።
4) አሸናፊዎች ምክንያት ደርዳሪዎች አይደሉም የብዙዎቻችን ውድቀት ምክንያት ይህ ነው፤ የምንፈልገውን ላለመሆናችን ምክንያት መደርደር እንፈልጋለን። ለውድቀታችን እራሳችንን እንደመመልከት የስህተታችንን ሚስጥር ሌሎች ላይ ለመፈለግ እንጥራለን። ሃላፊነት መውሰድ ስለሚሳነን፤ ልክ እንደጦጣዋ ተረት “የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ” ማለት እናበዛለን። ስኬት ማለት ባህሪ ነው። ስኬታማ ሰዎች በየእለቱ በሚያከናውኗቸው ነገሮች ላይ ሙሉ ልባቸውን እና ትኩረታቸውን ሰጥተው ነው።
ባይሳካላቸው ስህተቱን ሌላው ላይ በመፈለግ ጊዜያቸውን አያባክኑም።
5) አሸናፊዎች ተስፋ አይቆርጡም ተስፋ የህይወት ሁሉ እስትንፋስ ነው። ምንም እንኳን እኩል እድል ተሰጥቶን፤ በተመሳሳይ ሰዓት ፊሽካ ተነፍቶልን ጉዞ ብንጀምርም ብዙዎቻችን ተስፋ በመቁረጥ ከመንገድ ቀርተናል። ምንም እንኳን እሩጫው ቢከብድም ተስፋ በውስጣቸው የሰነቁ ሰዎች በቀላሉ ከመንገዳቸው አይገቱም።
ከላይ የተዘረዘሩት አምስት ነጥቦች ከብዙዎቹ የአሸናፊ
ሰው ባህሪዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ከብቶች አንድ አይነት ሳር ግጠው ፈንዳያቸው እንደሚለያይ ሁሉ፤ የሰው ልጆችም ተመሳሳይ እድል ተሰጥቷቸው የተለያየ ቦታ ይወድቃሉ። ምንም እንኳን ምክንያቶቹ ተዘርዝረው ባያልቁም፤ ከላይ የሰፈሩት አምስጥ ነጥቦች ግን አንኳሮቹ ናቸው፤ በእርግጠኝነት እራሳችንን እንድንፈትሽ ያደርጉናል።
(Mistre)

. . . #የመጨረሻ_ሰዓት . . .
በአንድ ወቅት አንድወጣት በአንድ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ሲሆን ከማንም እና ከምንም በላይ የሚወዳት ፍቅረኛ አለችው፡፡ ይህ ወጣት ከእለታት በአንዱ ቀን እጅግ ከፍተኛ ችግር ስላጋጠመው ለሁት ወር ፍቃድ እንዲሰጠው ከመስራ ቤት ጠይቆ ፍቃድ ወሰደ፡፡
ፍቃድ ካገኘበት እለት አንስቶ ልጁ እጅጉን ከሚያፈቀራት ልጅ ጋር ቀኑን ማሳለፍ ጀመረ፡፡ ይጫወታሉ ፣በየመዝናኛ ቦታ ይወስዳታል ፣በየመንገዱ ያዝላታል፡፡ ጎህ ሲቀድ የተገናኙ ጀምበር ስትጠልቅ ለመኝታ ብቻ ነው ሚለያዩት፡፡ የዚህንም ሰአት ቤቱዋ በር ድረስ አዝሎአት ነው የሚያደርሳት፡፡
እንዲህ እንዲህ እያሉ ሶስት ሳምንታትን በዚሁ የፍቅር መንፈስ አሳለፉ፡፡ በየቀኑ ድርጊታቸው ሁለቱም እጅጉን ደስተኛ ነበሩ፡፡ ሁለቱም ከማንኛውም ነገር እርቀው በራሳቸው የፍቅር ሀይቅ ውስጥ መዋኘት ጀምረዋል፡፡ ይህንን የተመለከቱት የልጁ ቤተሰቦች በድርጊቱ ኮነኑት፡፡ምንም ያህል ቢወዳት እንዲህ ሙሉ ግዜውን ሊሰጣት እንደማይገባ አጥብቀው ነገሩት፡፡ የስራ ባልደረቦቹም ሆኑ ጉዋደኞቹ በድርጊቱ ተቃውሞአቸውን አሰሙ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሁሉን ነገር በልኩ እንዲያደርግ ነገሩት፡፡ አዝሎ መዞር ፣ አጎንብሶ ጫማ ማሰር ስምህን እና ክብርህን ያጎድፍብሀል አሉት፡፡ እሱ ሊሰማ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡
ነገሩ በዚህ ቀጥሎ ወሬው የአለቃው ጆሮ ደረሰ፡፡ አለቃው እጅጉን ከመቆጣቱ የተነሳ ያለበት ድረስ ሄዶ ብቻውን አስቀምጦ ይቆጣው ጀመር፡፡ "በጣም ችግር አጋጥሞኝ ነው ብለህ ፍቃድ የጠየከኝ እንደዚ ለመንዘላዘል ነው!" ሲል አምባረቀበት፡፡ በዚህ ሰአት ልጁ በተረጋጋ አንደበት እንባ ያዘሉ አይኖቹን ወደ አለቃው ቀና አድርጎ እየተመለከተ እንዲህ አለው፡፡
" ሁላቹም ምታዩትን ትናገራላቹ፡፡ ስለምትናገሩት ነገር እርግጠኛ ናቹ፡፡ እርግጠኝነታቸ እውነት ስለመሆኑ ግን ራሳቹን አልጠየቃቹም፡፡ እናንተ እንደምታወሩት እየተንዘላዘልኩ አይደለም፡፡ እቺ ምታወሩባት ልጅ የልጅነት ፍቅረኛዬ ነች፡፡በፈጣሪ ፍቃድ ብዙ ነገሮችን አልፈን እዚህ ደርሰናል፡፡ እንደኛ ፍላጎት ቢሆንም ተጋብተን ወልደን አብረን እናረጃለን ብለን ነበር ሁሌም ምንፀልየው፡፡ አሁን ግን ያሰብነው ሀሳብ እዚህ ሊያበቃ ነው መሰለኝ፡፡ ፍቅረኛዬ የካንሰር ተጠቂ ሆናለች፡፡ ለመኖር ሁለት ወር ብቻ እንደሚቀራት ነው ሀኪም የነገራት፡፡ እነዚህን ሁለት ወራት ከእኔጋ ብቻ ነው ማሳለፍ ምትፈልገው፡፡ ለዛ ነው ሁለት ወር ፍቃድ ወስጄ ከእሷ ጋር ብቻ ሙሉ ግዜዬን ማሳልፈው፡፡ይሄ የፍቅሬ የመጨረሻዎቹ ቀናት ናቸው፡፡ ከሳምንታት ብሁላ መልሳ ላትመጣ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ትለየኛለች፡፡ እስከዛ ግን አይን አይኗን እያየው ከጎኑዋ መሆን አለብኝ፡፡ በዚ ሰአት ለሱዋ ያለዋት እኔ ነኝ፡፡ለኔ ያለችኝ እሷ ናት፡፡" ሲል በዛለ አንደበት ስለሁሉም ነገር አስረዳው፡፡
በመጨረሻም አንድ ጥያቄ አቀረበለት "አንተ በኔ ቦታ ብትሆን ምን ታደርግ ነበር?" አለቃው መልስ አጣ በይቅርታ ስሜት አንገቱን አቀረቀረ፡፡
በሰዎች ላይ ለመፍረድ እንቸኩላለን፡፡ እኔስ ብሆን ምን አደርግ ነበር? ብለን ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ እኔ ብሆን ምን አደርግ ነበር?
✍

ይህችን ታሪክ ተጋበዙልኝ።
የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ባንክ ገብተው “አንድም ሰው እንዳይንቀሳቀስ! ገንዘቡ የመንግሥት ነው፤ ህይወታችሁ ግን የእናንተ ነው” ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፡፡
ሁሉም ሰው ወለሉ ላይ በደረቱ ተኛ፡፡ ይኼ “Mind Changing Concept” ይባላል፤ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ የሰዎችን አስተሳሰብ መቀየር ነውና፡፡ ጠረጴዛ ላይ ተደፍታ የነበረች አንዲት ሴት የማጉረምረም ድምጽ ስታሰማ፣ ከዘራፊዎች አንዱ ቆጣ ብሎ፣ “እመቤት እንደሰለጠነ ሰው አስቢ እንጂ፡፡ ይህ እኮ ዘረፋ እንጂ አስገድዶ መድፈር አይደለም ” አላት፡፡ ፀጥ አለች፡፡ ይኼ “Being Professional” ነው፤ በሰለጠንክበት ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት ታደርጋለህና፡፡
ዘራፊዎቹ ያለምንም ችግር ቤታቸው ገቡ፡፡ ከዘራፊዎቹ መካከል ልጅ እግሩ እና የMaster of Business Administration ተመራቂው የተዘረፈው ገንዘቡ እንዲቆጠር ሃሳብ አቀረበ፡፡ ነገር ግን በዕድሜ ታላቅ የሆነውና እስከስድስተኛ ክፍል ብቻ የተማረው ዘራፊ፣ በቁጣ “አንተ የማትረባ ደደብ! ይህን ሁሉ ገንዘብ ማን ይቆጥራል? ዛሬ ማታ በቴሌቪዥን ዜና ላይ ስንት እንደዘረፍን ይነግሩናል፡፡” ይኼ “Experience” ይባላል፡፡ ዛሬ ዛሬ በትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት ይልቅ ‘ልምድ’ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡
ዘረፋው ከተፈፀመ በኋላ፣ የባንኩ ማናጀር የባንኩን ሱፐርቫይዘር ጠርቶ በአስቸኳይ ፖሊስ እንዲጠራ ነገረው፡፡ ሱፐርቫይዘሩ ግን፣ “ቆይ ተረጋጋ! እየውልህ፣ መጀመሪያ ከካዘና 10 ሚሊየን አንስተን ለራሳችን እንውሰድ፡፡ ከዚያም ባለፉት ወራት የወሰድነውን 70 ሚሊየን እንጨምርበት፡፡ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ያለብን ይህን ገንዘብ ዛሬ ከተዘረፈው ጋር ደምረን ነው” አለው፡፡ ይኼ “Swim with the tide” ይባላል፡፡ የተፈጠረን አስቸጋሪ ሁኔታ ለራስ ጥቅም ማዋል እንደማለት፡፡ ሱፐርቫይዘሩም አለ፣ “በየወሩ ዘረፋ ቢካሄድብን እንዴት መልካም ነበር!”
በሚቀጥለው ቀን፡፡ ከባንኩ የተዘረፈው ገንዘብ 100 ሚሊየን እንደሆነ በቴሌቪዥን ዜና ተነገረ፡፡ ዘራፊዎች ደነገጡ፤ የዘረፉትንም መቁጠር ጀመሩ፤ ማመን አቃታቸው፤ ደግመው ቆጠሩ፤ ያው ነው፡፡ ትንሽ ቆይተው እንደገና መቁጠር ጀመሩ፤ ተመሳሳይ መጠን – 20 ሚሊየን ብቻ! በጣም ተናደዱ፣ “እኛ ህይወታችንን ለአደጋ አጋልጠን 20 ሚሊየን ብቻ ስናገኝ፣ የባንክ ማናጀሩ ቁጭ ብሎ 80 ሚሊየን እንዴት ያገኛል?” ከንፈራቸውን ነከሱ፣ ጠረጴዛውን በቡጢ ነረቱ፡፡ ሌባ ከመሆን መማር ይሻላል ማለት ይህ አይደል?i (Africa’s elites are lords of poverty! ያለው ማን ነበር?)
የማናጀሩ ፊት በፈገግታ እንደ ማለዳ ፀሐይ አብረቅርቋል፤ የደስታ ግምጃ አድምቆታል፡፡ በሽርክና ገበያው የተፈጠረበት ጉድለት ተሞልቶለታልና፡፡ ይኼንን “Seizing the opportunity” ይሉታል፡፡ ዋነኞቹ ዘራፊዎች እነማን ናቸው? የሚል ጥያቄ ማስቀመጥ ፈልጌ የነበረ ቢሆንም ከወቅቱ ጋር ላይሄድ ይችላል ብዬ በማሰብ ትቼዋለሁ፡፡
#ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

በድሮ ጊዜ ንጉሡ ጠቢቡን ሰው ጠርተው ጥያቄ ይጠይቃሉ "የዚህ ዓለም ደስታ ምንድነው?"
ጠቢቡም ፦ "መብላት ፣መጠጣት መፍሳት" ብለው መለሱ ። በዚህ ንግግራቸው የተበሳጩት ንጉሥ ከቤተ መንግሥታቸው አስገፍትሩው እንዲያስወጡ አሸከሮቻቸውን አዘዙ በዚህ ጊዜ ጠቢቡ አንድ ነገር ብቻ እንዲናገሩ በመለመን ፍቃድ አገኙና ይህን አሉ "የተከበርከው ሱልጣን! የተናገርኩት እውነት መሆኑን ታውቅ ዘንድ ትበላለህ ፣ትጠጣለህ ግን አትፈሳም/አትፀዳዳም/" በማለት ረገሟቸው ።
አንድ ሳምንት አለፈ ። ንጉሡ ይበላሉ ይጠጣሉ የሚወጣ ነገር ግን የለም። ሆዳቸው ተነፋ ፣ ቁርጠት አላስተኛ ፣አላስቀምጥ አላቸውና ስቃያቸው ሲበረታ ሊቁን አስጠርተው" አጥፍቻለሁ ይቅርታ አድርጉልኝ "በማለት ሲጠየቁ "ይቅርታ የማደርግልህ መንግስትህን ስትሰጠኝ ብቻ ነው " አሉ ። ንጉሡም ከስቃያቸው አንፃር ምርጫ ስላጡ በቃላቸው አረጋገጡላቸው ። ጠቢቡም ሰው የንጉሡ ሆድ በእጃቸው ጠሰቁት ። ሡልጣኑም አንድ ጊዜ ፈስተው "እፎይ !"አሉ።
ያኔ " አላመንከኝም እንጂ አስቀድሜ ነግሬሃለው ። አሁን ግን መንግስትህን በፈስህ ለወጥክ" በማለት የመጀመሪያውን የጠቢብ ንግሥናን በዚያን ዕለት አገኙ ።
***
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንባብ ለህይወት

🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏
“ዉድድርህ ከሰዎች ጋር አይደለም! ዉድድርህ:-
✓ ከገደልከዉ ሰአት
✓ ከፈጠርከዉ በሽታ
✓ መማር እያለብህ ችላ ካልከዉ እዉቀት
✓ መስዋእት ካረከዉ ጤናህ
✓ አዲስ ሃሳብን አልቀበልም ካልከዉ ማንነት
✓ ያንተን መጣር ከማይወዱ ሰዎች
✓ እድለ ቢስ እንደሆንክ ከሚነግርህ ሰይጣን ጋር ነዉ”
-ጀምስ አልሸር
🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌
“ዉድድርህ ከሰዎች ጋር አይደለም! ዉድድርህ:-
✓ ከገደልከዉ ሰአት
✓ ከፈጠርከዉ በሽታ
✓ መማር እያለብህ ችላ ካልከዉ እዉቀት
✓ መስዋእት ካረከዉ ጤናህ
✓ አዲስ ሃሳብን አልቀበልም ካልከዉ ማንነት
✓ ያንተን መጣር ከማይወዱ ሰዎች
✓ እድለ ቢስ እንደሆንክ ከሚነግርህ ሰይጣን ጋር ነዉ”
-ጀምስ አልሸር
🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌
አንድ ቀን አንድ ሽማግሌ ከልጁ ጋር በጫካ ውስጥ እየተንሸራሸሩ ሳሉ በድንገት አንድ ትንሽ ድመት በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ያያሉ። ድመቱ ከጉድጓዱ ለመውጣት እየተፍጨረጭረ ነበር። እና ሽማግሌው ድመቱ ከጉድጓዱ እንዲወጣ እጁን ሰጠው። ድመቱ ግን በፍርሃት እጁን ቧጨረ።
ሰውየውም በቡጭሪያው ህመም እየጮኸ እጁን ሰበሰበ ግን አላቆመም። ለድመቱ በድጋሚ እጁን ደጋግሞ ለመስጠት ሞከረ። አብሮት የነበረው ልጅ ትዕይንቱን እየተመለከተ በመገረም ጮኸ "በፈጣሪ ይሁንብህ አባዬ ይህንን ድመት መርዳት አቁም፤ ድመቱ እራሱን በራሱ ጊዜ ከዚያ ያወጣል" አለ። ልጅየው ስለድመቱ ደንታ አልነበረውም።
ሽማግሌው ግን ድመቱን ማዳን ቀጠለ፤ "ልጄ፤ እሱ እንዲቧጨር እና እንዲጎዳኝ የሚያደርገው የድመት ባሕርዩ ነው፤ እኔ ደግሞ መውደድ እና መንከባከብ ሰብአዊ ግዴታዬ ነው"
ብሎ በድጋሚ እጁን ለእርዳታ ዘረጋለት ድመቱ ባጨረው። እንዲህ እያሉ ከአድካሚ ሙከራዎች በኋላ በመጨረሻ ከጉድጓዱ አወጣው። እና ድመቱን ወደቤቱ ወስዶ የራሱ አደረገው።
*
ሞራል- በዙሪያዎ ያሉትን ሁሉ በራሳችሁ መልካም አመል አስተናግዱ እንጂ የሰዉን መጥፎ ባህርይ አትከተሉ። ያኔ ልታዩት የምትፈልጉት መልካምነት ሁሉ በዙሪያችሁ ይሆናል።
*
ለዚህ ታሪክ ተስማሚ ምሳሌያዊ ንግግር በኮሜንት ሳጥን ተዉልን
እናንብብ፣ እንወያይ ፣ነጻ እንውጣ

መህምሩ ለተማሪዎች ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ነገር በሙሉ ጽፋችሁ በነገው ዕለት እንድትመጡ ብሎ አዘዘ..
“በዚያ ምሽት ተማሪው ሕልሙን እና ማሳካት የሚፈልገውን ሁሉ ጻፈ እናም እንዲህ ይል ነበር በመጪው 10 ዓመታት የፈረስ እርሻ ባለቤት እንደሚሆን፣ አራት ሕንጻዎች እንደሚኖሩት፣ 200 ሄክታር የእርሻ መሬት እና 4,000 ካሬ ቤት እንደሚኖረው ጻፈ ለዚህም ዝርዝር የወለል ፕላን አዘጋጀ። እና በሚቀጥለው ቀን ለአስተማሪው አስረከበው። ከሁለት ቀናት በኋላ ወረቀቱን መልሶ ተቀበለ።
አስተማሪው ወረቀቱ ላይ ጉልህ "ኤፍ"አድርጎበታል። ልጁም ተበሳጭና መምህሩን ሄዶ አናገረ።
አስተማሪውም ይህ እንደ አንተ ላለው ወጣት ልጅ ከእውነታው የራቀ ሕልም ነው። ገንዘብ የለህም፣ የድሃ ቤተሰብ ልጅ ነህ፣ ምንም ሀብት የለህም። የፈረስ እርሻ ባለቤት መሆን ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል። 4ሺህ ካሬ እና ትልቅ እርሻ ላንተ "ላም አለኝ በሰማይ ነው" ብሎ ተዛባበተበት። እናም እንዲህ አለ "ማታ እንዳዲስ ሊሳካ የሚችል እቅድ ጻፍና ውጤትህን አስተካክልልሃለው"
"ልጁ ወደ ቤቱ ሄዶ ብዙ አሰበበት። አባቱንም ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀ። አባቱም "ተመልከት ፣ ልጄ፤ እዚህ ጋር የራስህን ሐሳብ መወሰን አለብህ። እኔ ግን በጣም አምንብሃለውና ልብህን ስማ" አለው።
በነገታው እቅዱን ምንም ሳይቀይር መልሶ ለአስተማሪቅ ሰጠ አስተማሪውም በ"ኤፍ ግሬዱ" ጸና።
ከዓመታት በኋላ ያ መምህር አርጅቶም እያስተማረ ሳለ አንድ ቀን ማለዳ ላይ በቴሌቭዥን የአንድ ወጣት ቃለመጠይቅ ይቀርብ ነበር... ወጣቱ ልጅ እያለ አሳካዋለሄ ካለው አንድም ያልቀረው የናጠጠ ሀብታም ሆኖ ነበር። እንዲህ አለ "ሕልሜን አስተማሪዬ ሊሰርቀኝ ሲታገል እንደምንም ነበር የተረፍሁት... እኔም ህልሜን እሱም ኤፉን ወሰደ"
የዛኑ ቀን መምህሩ ለተማሪዎቹ ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ጻፉልኝ ብሎ አዘዘ በነገታው መለሱለት ለሁሉም የሰጠው ውጤት "ኤ"ነበር።
*
ሞራል፡ መምህራን የጠቀሙ መስሏቸው የስንቱን ሕልም ሰረቁ። በሕልማችሁ አትደራደሩ ለማሳካት የምታስቡት ሁሉ የሚደረስበት እና የተደረሰበት ነው።
*
ይህ ጽሑፍ ላይ ያላችሁን ሐሳብ በኮሜንት አጋሩን
ከተስማማችሁም ሼር አድርጉት

ሌሊት ነበር፤ አንድ ሰው በመንገድ ላይ እየነዳ መኪናው በገዳሙ አቅራቢያ ይበላሽታል። እናም ወደ ገዳም ሄዶ በሩን አንኳኳ። መነኩሴው ወደ ውጭ ወጥቶ በሩን ሲከፍት “መኪናዬ ተበላሸ። እዚህ ለአንድ ሌሊት መቆየት እችላለሁን?” አለ። መነኩሴውም ጥያቄውን ተቀበለ። መነኮሳቱንም ማቆየት ብቻ ሳይሆን መገቡት አልፎ ተርፎም መኪናውን አስተካከሉለት።
ሰውየው ለመተኛት ሲሞክር እንግዳ የሆነ ድምጽ ሰማ። በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ስለዚያ ድምጽ መነኩሴውን ጠየቀ ነገር ግን መነኩሴው “መነኩሴ ስላልሆንክ ልንነግርህ አንችልም” አለው። ሰውየው ቅር ቢሰኝም አመስግኖት መንገዱን ቀጠለ።
ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ፣ ያው መኪና በተመሳሳይ ገዳም ፊት ለፊት ይበላሻል። አሁንም እንደበፊቱ ሁሉ መነኮሳት ተቀብለው መግበውት መኪናውን አስተካከሉለት። እናም ለመተኛት ሲሄድ ያኛው ሰውዬ ከዚህ ቀደም የሰማውን ተመሳሳይ እንግዳ ድምጽ ይሰማል።
በማግስቱ ጠዋት ስለዚያ ጫጫታ መነኩሴን ይጠይቃል፤ ግን መነኩሴም ተመሳሳይ መልስ ሰጡት “መነኩሴ ስላልሆንክ ልንነግርህ አልችልም" ሰውዬውም "ስለዚያ ድምጽ ለማወቅ መነኩሴ መሆን ግድ ከሆነ፤ እንዴት መነኩሴ መሆን እችላለሁ?” መነኩሴም መለሰ ፣ “መነኩሴ ለመሆን ከፈለክ የምድርን አሸዋ መቁጠር እና ቁጥሩን ለኔ መንገር አለብህ ይህን ስታገኝ መነኩሴ ትሆናለህ ”አለው።
ሰውየው ለዚህ ተግባር ተነስቶ ከአርባ ዓመታት በኋላ ተመልሶ የገዳሙን በር አንኳኩቶ “መላውን ምድር ተዘዋውሬ 222,345,323,954,110,958,203 የአሸዋ ጠጠር በምድር ላይ እንዳለ አገኘሁ” አለ።
መነኩሴ ሰውየውን በማመስገን “አሁን ወደ ድምጹ የሚወስደውን መንገድ እናሳይሃለን” አለው። መነኩሴ ወደ አንድ የእንጨት በር እየመራው “ሰውየው የሚፈልገው ድምፅ ከዚያ በር በስተጀርባ ነው” ሲል ሰው ተደሰተ። በሩን ለመክፈት ሲሞክር ግን ያ በር እንደተዘጋ ተረዳ። ስለዚህ በሩን ለመክፈት ቁልፉን እንዲሰጠው መነኩሴውን ጠየቀ። መነኩሴ ቁልፉን ሰጠው። ሰው በሩን ከፍቶ ከዚያ በር ጀርባ ከድንጋይ የተሠራ ሌላ በር አየ። ዳግመኛ ሰው በሩ እንደተቆለፈ ስላየ የዚያ በር ቁልፍ ጠየቀ። ሰው የድንጋይ በር ሲከፍት ከወርቅ የተሠራ ሌላ በር አገኘ ግን ተቆልፏል።
መነኩሴ የዚያን በር ቁልፍም ሰጠው። እንደገና ከሩቢ የተሠራ ሌላ በር ነበር። በሌላ ተከታታይ በር እስኪያልፍ ድረስ ይህ ይቀጥላል። በመጨረሻ መነኩሴ “ይህ የመጨረሻው በር እና እዚህ የዚህ በር ቁልፍ ነው” አለ። ሰውየው በመጨረሻ እፎይታ አግኝቶ በሩን ከፍቶ ገባ እና ከዚያ በር በስተጀርባ የድምፅ ምንጭ በማግኘቱ ተገረመ ግን ምን እንደ ሆነ ልነግራችሁ አልችልም .. ምክንያቱም እናንተ መነኩሴዎች አይደላችሁም።
*
ኃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን። ሌሎች ታሪኮችን እና የመጻሕፍት ጥቆማዎች ለማግኘት ገጻችንን ላይክ፤ ለሌሎች እንዲደርስ ደግሞ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን!
*
ሁሉንም ነገር ማወቅ አለብን ብላችሁ ታስባላችሁ?
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ

አባት እና ትንሽ ልጁ በጫካውና ኮረብታዎች ውስጥ ይጓዙ ነበር ፡፡ በድንገት ልጁ በመንገዱ ላይ ወድቆ “አአ!” እያለ በህመም ጮኸ ፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከተራራው ላይ ተመሳሳይ ድምፅ ሰማው "አአህ!" ልጁ በጉጉት “ይህ ማን ነው?” ሲል ጮኸ ፡፡ ድምፁ ግን ተመሳሳይ መልስ ሰጠ ፣ “ይህ ማን ነው?” ተቆጥቶ እንደገና “አንተ ደደብ ነህ!” ብሎ ጮኸ ፡፡ እናም እንደገና ድምፁ ተመሳሳይ መልስ ሰጠ ፣ "አንተ ደደብ ነህ!"
በዚህ ተበሳጭቶ ልጁ አባቱን “አባት ሆይ ፣ ምን እየተከናወነ ነው? ማን ነው ይሄ? ”
አባትም መለሰ ፣“ ልጄ ፣ በጥሞና እድምጥ እሰኪ ”አለውና ፡፡ አባትየው በተራ ጮኸ "አንተ በጣም ጥሩ ነህ" እናም ድምፁ ተመሳሳይ ምላሽ ሰጠ ፣ “አንቺ በጣም ጥሩ ነሽ!” አለ አባትየው እንደገና ፡፡ ድምፁም ብድጋሚ አስተጋባ ፡፡ “አመሰግናለሁ” ብለው ጮኹ አባትየው ፡፡ እናም ድምፁ እንደገና ተመሳሳይ ምላሽ ሰጠ ፣ "አመሰግናለሁ!" ልጁ በጣም ተገረመ ነገር ግን ምን እየሆነ እንዳለ አልገባውም ነበር ፡፡
አባትየው በእርጋት ያስረዳው ጀመር ፣ “ልጄ ፣ ሰዎች ይሆን ሂደት ማስተጋባት ብለው ይጠሩታል ፣ ግን ይህ የሕይወት እውነታ ነው። ህይወት የድርጊቶች ነፀብራቅ ነው ፡፡ ለሌሎች የምንሰጠውን ነገር እራሳችን በምላሹ በተመሳሳይ ሁኔታ እንቀበላለን ፡፡ ”
***
ንባብ ለህይወት
🤝 @Tesh5050

#ሰውየው አንድ ትልቅ በሬ አርዶ የብረት ምድጃዉን ለኩሶ ለልጁ እንዲህ አለው "የምንወዳቸውን እና የምናከብራቸዉን ጎረቤቶቻችን #አብረውን እንዲበሉ ሄደህ ጥራቸዉ።”
#ልጁ ወደ ጎዳና ወጥቶ እንዲህ ሲል መጮህ ጀመረ “እባካችሁ የአባቴ ቤት በእሳት ስለተያያዘ ለማጥፋት እርዱን ድረሱልን!" ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጥቂት ሰዎች መጡ ሌሎቹ የእርዳታ ጩኸቱን እንዳልሰሙ ሆነዉ ቀሩ። የመጡ ሁሉ ግን በሉ ጠጡ።
#ባየዉ ነገር የተደናገጠው አባት ወደ ልጁ ዞሮ እንዲህ አለ "የመጡትን ሰዎች እኔ አላውቃቸውም ከዚህ በፊትም አይቼአቸዉ አላውቅም ስለሆነም ወዳጆቻችን ቤተሰቦቻችን እና የሥራ ባልደረቦቻችን የት አሉ?"
#ልጁም "ከቤታቸው ወጥተዉ የመጡት ሰዎች ቤታችን ላይ የተነሳዉን እሳት ለማጥፋት ጩኸት ሰምተዉ ሊረዱን እንጂ በቤታችን የተዘጋጀዉን ፓርቲ ሊካፈሉ አይደለም። ግብዣችን እና እንግዳ ተቀባይነታችን የሚገባዉ ለእነዚህ ዓይነቶቹ ነዉ" አለ።
#ሁሉም የምትወዱአቸዉ እና የምታከብሩአቸዉ ሰዎች እዉነተኛ ወዳጆቻችሁ ላይሆኑ ይችላሉ። እዉነተኛ ወዳጅ ማለት በተቸገራችሁ እና የነርሱ ድጋፍ በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ ፈጥነዉ ከጎንዎ የሚገኙ ናቸዉ። ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ስለእርስዎ የሚጨነቁትን እውነተኛ ሰዎች ለማወቅ ጥረት ያድርጉ።
ሼር ሼር ሼር ሼር
https://t.me/joinchat/QHpaFsslt6WZOQEy

አንድ ሀብታም ሰው በመስኮቱን ተመለከተና አንድ ድሃ ሰው አንድ ነገር ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ሲመርጥ አየ ...እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ ድሀ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ድሃው ሰው ዘወር ብሎ ተመለከተና ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰው አየ ... እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ እንኳን እንደዚህ ሰዉዬ አልሆንኩ አለ"።
:
ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰውየ ወደ ፊት ተመለከተ እና አንድ አምቡላንስ አየ አምቡላሱን ላይ በሕመም ምክንያት የሚሰቃይና የሚያለቅስ በሽተኛ አየ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ በሽተኛ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ከዚያም የታመመው ሰውየ ሆስፒታል ሲደርስ የሞተን ሰው ተመለከተ ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ ምክንያቱም የሞተ ሰው ፈጣሪን አያመሰግንምና አለ"።
:
ዛሬ ስለ ሁሉም የፈጣሪን በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም? ከሌለን ነገር እኮ ያለን በእጅጉ ይበልጣል ፡፡
:
* # ሕይወት * # ምንድን_ነው ?
ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:
* 1. መቃበር *
* 2. ሆስፒታል *
* 3. እስር ቤት *
:
በመቃብር ቦታ ሕይወት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ትገነዘባለህ።
:
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ።
:
በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ።
:
የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው።
ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ እንሁን። ስንት ቤተሰቦቻችን ፣ ጓደኞቻችን ዛሬ በሕይወት የሉም እኛ ግን በፈጣሪ ፈቃድ ጊዜያችንን እየጠበቅን በሕይወት መቆየት ችለናል ፡፡ ከሞትን በኀላ ደግሞ በዚህች አለም በሰወች ዘንድ የሚቀርልን ትዉስታ ስራችን ከተጨመረ ደግሞ ፎቶአችን ነዉ ፡፡ ስለዚህ ለሰዋች ደግሞ ሁል ጊዜ መልካም ነገር ሰሪ እንሁን ፡፡ በተጨማሪ ሁሌ አመስጋኝ እንሁን ሌላዉ ቢቀር ይህን ፅሁፍ በማንበባችን አምላክን እናመስግን ምክንያቱም ብዙ ሰዋች
1.ማንበብ ስለማይችሉ አያነቡትም
2.ይህን መልዕክት ስላልጀረሳቸዉ አያነቡትም
3. 4. 5. ...
ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪያችን የተመሰገነ ይሁን።
መልካም ቀን
|
#Share if you really like it

Telegram
ንባብ ለ ሕይወት
አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደ አንተ ይመጣሉ። ንባብ ህይወት ይሰጥካል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና ብቻ ነው።
ይቀላቀሉን
ለማንኛውም አስተያየት እና ማስታወቅያ ስራ ያዋሩኝ👉 @Tesh5050

ንጉሥ ሻርያር በፋርስ ላይ ይገዛ ነበር። የወንድሙ ሚስት በባሏ ላይ እየማገጠች እንደሆነ ሲረዳ ቁጣው ነደደ። ሁሌም ሴቶች አንድ ናቸውም ብሎ ደመደመ። የገዛ ሚስቱንም ሰይፎ ገደላት። ከዚህ በኋላ ደናግላን ሴቶችን እያገባ አንድ ሌሊት ብቻ አብሯቸው አድሮ ፣ ማግጠው ሳያዋርዱት በፊት ያስገድላቸዋል። ደናግላቱን እየፈለገ የሚያመጣለት ሚኒስትሩ ነበር። ሚኒስትሩ በመጨረሻ ለንጉሡ የሚያቀርብለት ደናግላን አጣ።
ሚኒስትሩ ሁለት ሴት ልጆችን ወልዷል። ትልቋ ሻህራዛድ ታናሿ ዲናርዛድ ትባላለች። ዲናዛርድ ውብ ስትሆን ሻህራዛድ ደግሞ ጥበበኛ ናት። በዚያ ላይ ስል እና ደፋር ናት። አንዴ ያነበበችውን በፍጹም አትረሳም። ጥሩ የማስታወስ ችሎታ አላት። ራሷን በራሷ ፊዚክስ፣ ፍልስፍና፣ ታሪክ ከማስተማሯም በላይ የበቃች ገጣሚ ነች።
ሚኒስትሩ በመጨረሻ ሻህራዛድን ለንጉሡ ዳረለት። አያችሁ ምርጫ አልነበረውም። ከአንድ ሌሊት በኋላ እንደምትገደል ያውቃል። ግን ከንጉሡ ትእዛዝ መውጣት አይችልም።
ሻህራዛድ እና ንጉሡ በሰርጋቸው እለት እንግዶቻቸውን ከሸኙ በኋላ ወደ መኝታ ቤታቸው አመሩ። በዚያም ሻህራዛድ እፁብ ድንቅ የሆነ ተረት ለንጉሡ መንገር ጀመረች። ንጉሡ አፉን ከፍቶ በአድናቆት ይሰማል። ይህ ተረት እንዲያው ተረት ብቻ አይደለም። ምትሃት ነው። እንደ ጥሩ ወይን ልብ የሚያስደስት፣ በምናብ የሚያንሳፍፍ፣ በሃሴት የሚሞላ ነው። ግን ግን ታሪኩን ሳትጨርስ መሸ፣ በጣም መሸ፤ ሌሊቱ ተጋመሰ። ሻህራዛድ ታሪኩን ሳትጨርስ ማቋረጥ ነበረባት። ንጉሡ ልቡ እንደተንጠለጠለ ለራሱ እንዲህ አለ
... ዛሬ ልገድላት አልችልም። ታሪኩን ነገ ከጨረሰችልኝ በኋላ ነገ እገድላታለሁ ....
ምስኪን ንጉሥ! ዛሬ መሽቶ ነገ ነጋ። ሻህራዛድ እንደተለመደው ትላንት የጀመረችለትን ተረት ጨርሳ ሌላ ጀመረች። ታሪኮቹ የዋዛ እንዳይመስላችሁ። ነፍስን ሰቅዘው የሚይዙ፣ በለዛ የተዋቡ፣ በቋንቋ የረቀቁ ናቸው።
አሊባባ እና አርባዎቹ ሌቦች፤
አላዲን እና ፋኖሱ፤ መርከበኛው ሲንባድ . . . ወዘተርፈ ነበሩ።
ቀናቱ እንደዚህ ነጎዱ። አንድ ቀን፣ ሁለት ቀን፣ ሳምንት፣ ወር፣ አመት ሆነ። ንጉሡ የሻህራዛድ ተረቶች ሱሰኛ ሆነ። ሻህራዛድ በጥበቧ በተረት ላይ ተረት እየጨመረች፣ መጨረሻው ላይ ሳትደርስ እያቋረጠች፣ እያሳደረች አንድ ሺህ አንድ ሌሊት ተቆጠሩ። ንጉሡ በመጨረሻ ከሻህራዛድ ድብን ያለ ፍቅር ያዘው። እንኳን ሊያስገድላት፣ ከሷ መለየት አቃተው። የፍቅሯ ምርኮኛ ሆነ።
ታዲያ ይሄንን ሁሉ ተአምር የሰሩት ታሪኮች ናቸው። ታሪኮች የጨከነ ልብ ያራራሉ፤ የደደረ ልብ ይገራሉ። ሻህራዛድ በጥበቧ የታሪኮችን ጉልበት፣ የልቧን ብልጠት፣ የአእምሮዋን እውቀት ተጠቅማ ኃያሉን ንጉሥ አንበረከከችው።
***
የማትረሱት የልጅነት ተረት ምንድን ነው?

#ዛሬ_ቀኑ_ደስ_ይላል
አንድ እድሜያቸው የጠና ማየት የማይችሉ ሽማግሌ ሁል ጊዜ መንገድ ዳር ተቀምጠው ይለምኑ ነበር ፡፡ ሁሌም በሚለምኑበት ወቅት አንድ የማይለያቸው ጽሑፍ የያዘ ካርቶን ነበር ፡፡ በካርቶኑ ላይ " ማየት አልችልም እርዱኝ " ይላል ። አላፊው አግዳሚም ሰው ጽሑፉን እያየ በአጠገባቸው ያልፋል ፡፡ አንዳንዱ ያለውን ጣል ጣል ያረጋል የቀረው ደሞ ትቶ ያልፋል ፡፡
ነገር ግን አንድ ቀን በጠዋት ይህ ተከሰተ ፡፡ ከዚህ በፊት የማያውቁት ሰው ወደ እሳቸው ቀረብ ብሎ ጽሑፍ የያዘውን ካርቶን አንስቶ ጫር ጫር አድርጎ መልሶ ካስቀመጠው በኀላ ምንም ሳይሰጣቸው ጥሎ ሄደ ፡፡ ሽማግሌው በሚሰሙት ግራ ተጋቡ ። ሰውየው አጠገባቸው መጥቶ ሲቆም ብዙ ብር ሊሰጣቸው አልያሞ ችግራቸውን ሊጠይቃቸው መስሎቸው ነበር ነገር ግን ምንም ሳይል ነበር ጥሎአቸው የሄደው ፡፡
ትንሽ ቆይቶ ግን የሳቸውን ሁኔታ የሚቀይር ነገር ተፈጠረ ፡፡ አላፊ አግዳሚው ሁሉ ያለውን እያወጣ ይሰጣቸው ጀመረ ፡፡ ከሳንቲም አልፎ ብዙ ሰዎች ብር በእጃቸው ይሰጡአቸው ጀመር ። ሽማግልው ግራ ተጋቡ ቆይ ያ ሰውዬ ምን አርጎ ነው የሄደው ብለው ራሳቸውን ሲጠይቁና ግራ ሲጋቡ ዋሉ ፡፡ በዛች ሰአት ብቻ ሰዎች የረዱአቸው ወር ሙሉ ለምነው ካገኙት ይበልጥ ነበር ፡፡
በዚህ ግርምት ቆይተው ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደሳቸው ቀረበ ፡፡ እሳቸውም በጥርጣሬ "ቅድም አንተ ነህ ጽሑፍ የጻፍከው ? ቆይ ምን ብለህ ነው የጻፍከው? " ልጄ አሉት ። ሰውየውም በደስታ " አባቴ እኔ ሳይኮሎጂስት ነኝ ፡፡ በእርግጥ በገንዘብ አልረዳሆትም ነገር ግን ጽሑፉን እንዳየሁ የተጻፈው ነገር ሰዎች እንዲረዱዎት ብዙ እንደማያስችል ስላወኩ የተጻፈውን ነው የለወጥኩት ፡፡ መጀመሪያ ' #ማየት_አልችልም_እርዱኝ ' ይል ነበር እኔ ደግሞ ከጀርባው ' #ዛሬ_ቀኑ_ደስ_ይላል_ግን_እኔ_አላየውም ' ብዬ አስተካከልኩት ፡፡ አዩ አባቴ ሰው ይህን ሲያነብ የእርሷን አለማየት ሳይሆን የራሱን ማየት ስለሚያስብ በደስታ ለእርሶ ያለውን ይለግሳል ። " አላቸው ፡፡ ሽማግሌው እጁን ከያዙ በኀላ እያመሰገኑት እጁን ይስሙ ጀመር ፡፡
(በናሁሰናይ ፀዳሉ) ተፃፈ
መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ !
እወዳችኀለሁ!
መልዕክቱ መልካም ከሆነ መልካምነትን ለሌሎች አካፍሉ #Share
https://t.me/joinchat/QHpaFsslt6WZOQEy
አንድ እድሜያቸው የጠና ማየት የማይችሉ ሽማግሌ ሁል ጊዜ መንገድ ዳር ተቀምጠው ይለምኑ ነበር ፡፡ ሁሌም በሚለምኑበት ወቅት አንድ የማይለያቸው ጽሑፍ የያዘ ካርቶን ነበር ፡፡ በካርቶኑ ላይ " ማየት አልችልም እርዱኝ " ይላል ። አላፊው አግዳሚም ሰው ጽሑፉን እያየ በአጠገባቸው ያልፋል ፡፡ አንዳንዱ ያለውን ጣል ጣል ያረጋል የቀረው ደሞ ትቶ ያልፋል ፡፡
ነገር ግን አንድ ቀን በጠዋት ይህ ተከሰተ ፡፡ ከዚህ በፊት የማያውቁት ሰው ወደ እሳቸው ቀረብ ብሎ ጽሑፍ የያዘውን ካርቶን አንስቶ ጫር ጫር አድርጎ መልሶ ካስቀመጠው በኀላ ምንም ሳይሰጣቸው ጥሎ ሄደ ፡፡ ሽማግሌው በሚሰሙት ግራ ተጋቡ ። ሰውየው አጠገባቸው መጥቶ ሲቆም ብዙ ብር ሊሰጣቸው አልያሞ ችግራቸውን ሊጠይቃቸው መስሎቸው ነበር ነገር ግን ምንም ሳይል ነበር ጥሎአቸው የሄደው ፡፡
ትንሽ ቆይቶ ግን የሳቸውን ሁኔታ የሚቀይር ነገር ተፈጠረ ፡፡ አላፊ አግዳሚው ሁሉ ያለውን እያወጣ ይሰጣቸው ጀመረ ፡፡ ከሳንቲም አልፎ ብዙ ሰዎች ብር በእጃቸው ይሰጡአቸው ጀመር ። ሽማግልው ግራ ተጋቡ ቆይ ያ ሰውዬ ምን አርጎ ነው የሄደው ብለው ራሳቸውን ሲጠይቁና ግራ ሲጋቡ ዋሉ ፡፡ በዛች ሰአት ብቻ ሰዎች የረዱአቸው ወር ሙሉ ለምነው ካገኙት ይበልጥ ነበር ፡፡
በዚህ ግርምት ቆይተው ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደሳቸው ቀረበ ፡፡ እሳቸውም በጥርጣሬ "ቅድም አንተ ነህ ጽሑፍ የጻፍከው ? ቆይ ምን ብለህ ነው የጻፍከው? " ልጄ አሉት ። ሰውየውም በደስታ " አባቴ እኔ ሳይኮሎጂስት ነኝ ፡፡ በእርግጥ በገንዘብ አልረዳሆትም ነገር ግን ጽሑፉን እንዳየሁ የተጻፈው ነገር ሰዎች እንዲረዱዎት ብዙ እንደማያስችል ስላወኩ የተጻፈውን ነው የለወጥኩት ፡፡ መጀመሪያ ' #ማየት_አልችልም_እርዱኝ ' ይል ነበር እኔ ደግሞ ከጀርባው ' #ዛሬ_ቀኑ_ደስ_ይላል_ግን_እኔ_አላየውም ' ብዬ አስተካከልኩት ፡፡ አዩ አባቴ ሰው ይህን ሲያነብ የእርሷን አለማየት ሳይሆን የራሱን ማየት ስለሚያስብ በደስታ ለእርሶ ያለውን ይለግሳል ። " አላቸው ፡፡ ሽማግሌው እጁን ከያዙ በኀላ እያመሰገኑት እጁን ይስሙ ጀመር ፡፡
(በናሁሰናይ ፀዳሉ) ተፃፈ
መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ !
እወዳችኀለሁ!
መልዕክቱ መልካም ከሆነ መልካምነትን ለሌሎች አካፍሉ #Share
https://t.me/joinchat/QHpaFsslt6WZOQEy
Telegram
ንባብ ለ ሕይወት
አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደ አንተ ይመጣሉ። ንባብ ህይወት ይሰጥካል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና ብቻ ነው።
ይቀላቀሉን
ለማንኛውም አስተያየት እና ማስታወቅያ ስራ ያዋሩኝ👉 @Tesh5050
ይቀላቀሉን
ለማንኛውም አስተያየት እና ማስታወቅያ ስራ ያዋሩኝ👉 @Tesh5050
"ገነት እና ሲኦል የሚባል ነገር አለ?"
ዝነኛው ጦረኛ ወደ አንድ መነኩሴ ጋ በመሄድ ጥያቄ አቀረበላቸው። "እውነት ግን ሲኦልና ገነት የሚባል ነገር አለ?" አላቸው።
"ማነህ አንተ?"
"እኔ ማለት በምድር ላይ ሁሉም የሚፈራኝ ጀግና ጦረኛ ነኝ"
"አሃ ጦረኛ ነህ!?" አሉ መነኩሴው በፌዝ ፈገግ ብለው። ከዚያም "ለመሆኑ ምን አይነት ያገር መሪ ነው እንዳንተ አይነቱን ሰው ጠባቂ አድርጎ የሚቀጥረው። ፊትህን ሳየው እኮ አስቂኝ ለማኝ ነው የምትመስለው"
ጦረኛው ተናደደ። ሰይፉን ከሰገባው ለመምዘዝ ተዘጋጀ። መነኩሴው ግን ንግግራቸውን ቀጠሉ። "አሃ ለካ ሰይፍም ይዘሀል፤ ለነገሩ ሰይፍህ የዶሎዶመና የዛገ በመሆኑ የኔን አንገት ለመቁረጥ አይችልም"
በዚህ ጊዜ ጦረኛው በቁጣ ሰይፉን መዞ ሊሰነዝር እጁን ከፍ አደረገ። ያኔ መነኩሴው በፍጥነት "የሲኦል በር ይሄ ነው" አሉት።
በዚህ ጊዜ የመነኩሴው ጥበብ የተገለጠለትና ሊያስተምሩት የፈለጉት ነገር የገባው ጦረኛ ሰይፉን በቀስታ ወደ ሰገባው መለሰው። "የገነት በር ደግሞ እሱ ነው" አሉ መነኩሴው ግርማ ባለው ድምጽ።
***
ገነትን ትመኛላችሁ ወይስ ሲኦል ያስፈራችኋል?

አንድ ጊዜ አንድ ሰው በአንድ ፎቅ ቤት ስር ተቀምጦ በተመስጦ ስልኩን እየነካካ ሳለ በድንገት ከላይ “የአንድ ብር ሳንቲም” ጭንቅላቱ ላይ ነጥራ አጠገቡ አረፈች፡፡ ይህ ሰው በጣም ስላመመው ጭንቅላቱን በማሻሸት ወደላይ በማየት የመታውን ሰው ለመሳደብ ሲቃጣው ጭንቅላቱን የመታችው የአንድ ብር ሳንቲም መሆኗን በማየቱ አንስቶ ኪሱ በመክተት ጸጥ አለ፡፡
እንደገና ተመሳሳይ ሁኔታ ሲከሰት አሁንም የለመዳት አንድ ብር በመሆኗ ቀና ብሎ ከመጮህ ይልቅ ህመሙን ታግሶ አንድ ብሯን በማንሳት ኪሱ ከተተ፡፡ ሁኔታው ለሶስተኛ ጊዜ ከተደገመ በኋላ በአራተኛው ጊዜ ጭንቅላቱ ላይ ያረፈው የለመደው የአንድ ብር ሳንቲም ሳይሆን ጠጠር ነበር፡፡
በዚያን ጊዜ ነበር፣ እጅግ በተቆጣ ድምጽ “ማን ነው የመታኝ? በማለት ወደላይ ቀና ያለው፡፡
በግል ሕይወታችንም ሆነ በማሕበራዊ ግንኑነታችን፣ “ጥቅም እስካገኘሁ ድረስ ምን ቸገረኝ” በማለት የምናልፋቸው ጎጂ ነገሮች አጉል ተጽእኖ መጠነ ሰፊ ነው፡፡
እኛ ጊዜያዊ ጥቅም ስላገኘን ብቻ የተውናቸው ጤና ቢስ ተግባሮች የእኛኑ አመለካከትና ባህሪይ እያበሰበሱ መሄዳቸው አይቀርም፡፡ በተጨማሪም፣ በእኛ ዝምታ ምክንያት ተግባሩን የሚፈጽሙት ሰዎች እርማት ስለማያገኙና፣የእነሱን አጉል ምሳሌነት በመከተል ያንኑ ተግባር ወደመፈጸም የሚሄዱ የሕብረተሰቡ ክፍሎች ስለሚበራከቱ የበሰበሰ ሕብረተሰብ መፍጠሩ አይቀርም፡፡
***
ምን አገባኝ ብለን የተውነው ስንት አለ?

የኢትዮጵያ 86ቱ ብሄር ብሄረሰቦች ስም ያውቃሉ ?
እነሱም
1. ኦሮሞ
2. አማራ
3. ሶማሌ
4. ትግራይ
5. አፋር
6. ሲዳማ
7. አገው
8. ዎላይታ
9. ከምባታ
10. ሀዲያ
11. ጋሞ
12. ጉራጌ
13. ኢሮብ
14. አርጎባ
15. ቱለማ
16. ስልጤ
17. ሺናሻ
18. አኝዋክ
19. ኑዌር
20. ሀመር
21. ኩናማ
22. ጉምዝ
23. በርታ
24. በና
25. አሪ
26. ሙርሲ
27. ቡሜ
28. ካሮ
29. ፀማይ
30. ኮንሶ
31. ዳሰነች
32. ቦረና
33. ገርባ
34. አላባ
35. አርቦሬ
36. ባጫ
37. ቤንች
38. ባስኬቶ
39. ቡርጂ
40. ጫራ
41. ጋዋዳ
42. ጌዲኦ
43. ጊዶሌ
44. ጎፋ
45. አደሬ
46. ከፊቾ
47. ኮንታ
48. ኒያንጋቶም
49. ናኦ
50. ቀቤና
51. ሱርማ
52. ጠንባሮ
53. የም
54. ወርጂ
55. ዲዚ
56. ዶንጋ
57. ዳውሮ
58. ዲሜ
59. ምዓን
60. ኮሞ
61. ማረቆ
62. ሞስዬ
63. ኦይዳ
64. ቦዲ
65. ፈዳሼ
66. ኮሬ
67. ማሌ
68. ማኦ
69. መሰንጎ
70. መዠንገር
71. ቀዋማ
72. ቀጨም
73. ሸኮ
75. ዘየሴ
76. ዘልማም
77. ሽታ
78. ቤተ እስራኤል
79. ማሾላ
80. ኮጉ
81. ድራሼ
82. ገባቶ
83. ጌዲቾ
84. ብራይሌ
85. ሙርሌ
86. ኮንቶማ .... ናቸው።
ምንጭ - የኢትዮጵያ ታሪክ
በኔ አስተሳሰብ ግን ይሄ ውላ አላስፈላጊ ነገር ነው ብሄር የሚባል ነገር ባይኖር መልካም ነበር......አንድ ሀገር ብቻ ነበር መሆን ያለባት።

አንዲት አሮጊት እናት ዘወትር በረባው ባልረባው የሚጨቃጨቁ እና የሚጣሉ ሁለት ወንድ ልጆች ነበራት፡፡ አለመግባባቶቻቸውን በምክር እና በተግሳፅ ለመፍታት ብዙ ሞከረች ግን ቀላል አልሆነላትም። እናም ስለ መበደል እና መጥፎ ተግባር እንዲሁም በቅራኔ መለያየት ስለሚያመጣው ነገር በተግባራዊ ምሳሌ ልጆቿን ለማስተማር ወሰነች፡፡
አንድ ቀን ልጆቹን አንድ ጥቅል ጭራሮ እንዲያመጡላት ጠየቀቻቸው፡፡ ይህን ካደረጉ በኋላ ጥቀል ጭራሮውን እንደታሰረ በእያንዳንዳቸው እጅ ላይ በማስቀመጥ የታሰረውን ጥቅል ጭራሮ እንዲሰብሩት አዘዘች፡፡ እነሱ በሙሉ ኃይላቸው ሞከሩ ነገር ግን መስበር አልቻሉም ፡፡
በመቀጠልም ጥቅሉን ፈታችና፤ ጭራሮውን በተናጠል በተናጠል ወስዳ እንደገና በልጆቹ እጅ ላይ አደረገች፡፡ ልጆቹም በቀላሉ ይሰብሯቸዋል ጀመር፡፡ ከዚያም እንዲህ አለች
“ልጆቼ ፣ አንድ አስተሳሰብ ካላችሁ እና እርስ በእርስ ለመተባበር ከተስማማችሁ፤ ጠላቶቻችሁ በቀላሉ የማያሸንፋቹና የማትበገሩ ጠንካራ ትሆናላችሁ። ግን በመካከላችሁ መለያየትና መከፋፈል ካለ በቀላሉ ልትሰበሩ ትችላላችሁ፡፡ ስለዚህም ህብረታቹን አጠንክሩና ጠላትን አስደንግጡት"
ልጆቹ ግን የሰሙ አይመስልም።
***
የዚህች አሮጊት እናት ስም ማን ነው?
እናንብብ እንወያይ ነጻ እውንጣ

ጊዜው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ነው። ወታደሩ ፍቃድ አግኝቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ድንገት ቤቱ አከባቢ ደርሶ ሬሳ የጫነ የወታደር መኪና ሲመለከት ጠላት ከተማዋን እንዳጋያት ተረዳ። መኪናው እጅግ የበዛ ሬሳዎችን ለመቅበር ወደ ተዘጋጀለት የጅምላ መቃብር ለማምራት እየተሰናዳ ነበር።
ከተቆለሉት ሬሳዎች ፊት ቆሞ ወታደሩ ለመጨረሻ ጊዜ ሲመለከት ቀድሞ ለባለቤቱ የገዛላት የመሰለ ጫማ አጤነ።
ለማጣራት በፍጥነት ወደ ቤቱ አመራ። ነገር ግን ሬሳውን ለመርመር ወዲያው ተመለሰና ሚስቱን አገኛት።
ወታደሩ ድንጋጤው መለስ ሲልለት ባለቤቱ በጅምላ እንድትቀበር ስላልፈለገ እናም በስርዓት ግብዓቷን ለመፈፀም ፍቃድ ጠየቀ።
ድንገት ግን ሚስትዬው እስትንፋሷ ሰልሎም ቢሆን ትተነፍስ ነበር። ሆስፒታል ወሰዳት። አስፈላጊው ሕክምና ተደረገላት። ዳግም ሕይወት ዘራች።
ከአደጋው ዓመታት በኋላ ልትቀበር የነበረችው ሴትዮ ፀንሳ "ቭላድሚር ፑቲን" የሚባል ልጅ በሠላም ተገላገለች።
ልጅዬው የወቅቱ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ነው!
https://t.me/joinchat/QHpaFsslt6WZOQEy
ከተቆለሉት ሬሳዎች ፊት ቆሞ ወታደሩ ለመጨረሻ ጊዜ ሲመለከት ቀድሞ ለባለቤቱ የገዛላት የመሰለ ጫማ አጤነ።
ለማጣራት በፍጥነት ወደ ቤቱ አመራ። ነገር ግን ሬሳውን ለመርመር ወዲያው ተመለሰና ሚስቱን አገኛት።
ወታደሩ ድንጋጤው መለስ ሲልለት ባለቤቱ በጅምላ እንድትቀበር ስላልፈለገ እናም በስርዓት ግብዓቷን ለመፈፀም ፍቃድ ጠየቀ።
ድንገት ግን ሚስትዬው እስትንፋሷ ሰልሎም ቢሆን ትተነፍስ ነበር። ሆስፒታል ወሰዳት። አስፈላጊው ሕክምና ተደረገላት። ዳግም ሕይወት ዘራች።
ከአደጋው ዓመታት በኋላ ልትቀበር የነበረችው ሴትዮ ፀንሳ "ቭላድሚር ፑቲን" የሚባል ልጅ በሠላም ተገላገለች።
ልጅዬው የወቅቱ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ነው!
https://t.me/joinchat/QHpaFsslt6WZOQEy
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏
"ሳይፀልዩ ማደር"
የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ፣
ሚዳቋ ፀለየች...
አውጣኝ አውጣኝ አለች ለፈጠራት ጌታ።
ነብሩም ተርቦ፣
ወደ አምላኩ ቀርቦ።
ሚዳቆዋን አይቶ-አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ፣
ፈቅዶ እንዲሰጠው አምላኩን ጠየቀ።
የሁለቱም አምላክ የሁላችን ሰሪ፣
ጸሎታቸውን ሰማቸው ፈጣሪ።
አምላክም በድምፁ ሚዳቆዋን አላት፣
እሩጠሽ አምልጪ ከበረታ ጠላት።
ነብሩንም አለው እሩጥ ተከተላት፤ ምግብ አርገ ብላት።
ሚዳቆዋም ስትሮጥ ከነብሩ ለማምለጥ፣
ነብሩም ሲከተላት ሆዱን ሊሞላባት።
ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ፣
ሆዱን ብትረግጠው የተኛ ከርከሮ።
ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር፣
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነበር።
አውጣኝ ያለው ወቶ አብላኝ ያለው በላ፣
ሳይፀልይ የተኛው ከርከሮ ተበላ።
✍️ገጣሚ #በረከት_በላይነህ
@galaxyplc
"ሳይፀልዩ ማደር"
የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ፣
ሚዳቋ ፀለየች...
አውጣኝ አውጣኝ አለች ለፈጠራት ጌታ።
ነብሩም ተርቦ፣
ወደ አምላኩ ቀርቦ።
ሚዳቆዋን አይቶ-አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ፣
ፈቅዶ እንዲሰጠው አምላኩን ጠየቀ።
የሁለቱም አምላክ የሁላችን ሰሪ፣
ጸሎታቸውን ሰማቸው ፈጣሪ።
አምላክም በድምፁ ሚዳቆዋን አላት፣
እሩጠሽ አምልጪ ከበረታ ጠላት።
ነብሩንም አለው እሩጥ ተከተላት፤ ምግብ አርገ ብላት።
ሚዳቆዋም ስትሮጥ ከነብሩ ለማምለጥ፣
ነብሩም ሲከተላት ሆዱን ሊሞላባት።
ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ፣
ሆዱን ብትረግጠው የተኛ ከርከሮ።
ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር፣
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነበር።
አውጣኝ ያለው ወቶ አብላኝ ያለው በላ፣
ሳይፀልይ የተኛው ከርከሮ ተበላ።
✍️ገጣሚ #በረከት_በላይነህ
@galaxyplc