Armageddon
6 subscribers
185 photos
21 videos
54 files
132 links
የ ፈራ ይመለስ
Download Telegram
ንስር የሚጋፋው አንድ ብቸኛ ተግዳሮት ነፋስ ነው፡፡ የሚያስገርመው ነገር ግን ንስር ወደ ከፍታው እንዲወጣ የሚደግፈውም ያው የሚጋፋው ነፋስ የተሰኘው ነገር ነው፡፡ የንስር አቋም “የሚጋፋኝን ይህንን ነፋስ ተጠቅሜ ወደ ከፍታዬ እበራለሁ፤ የነፋሱ ግፊያ ወደ ከፍታዬ ያወጣኛል፡፡” ንስር ከሚጋፋው ብቸኛ ጠላቱ ከነፋስ ተግዳሮት ውጪ ለመኖር ቢወሰንና ያንን ጥያቄውን ተግባራዊ የሚያደርግለት ኃይል ተገኝቶ ነፋስ ከፍጥረት ክስተት ውስጥ ቢወጣለት የሚጋፋው ብቸኛ ነገር ስለተወገደለት “እፎይ” ይላል፡፡ ታሪኩ ግን እዚያ ላይ ብቻ አያበቃም፡፡ የከፍታ ህይወቱንም እዚያው ያስረክባል፡፡ ከሚጋፋው ከብቸኛ ጠላቱ ከነፋስ ውጪ ንስር ከዶሮ ተለይቶ አይታይም፡፡”

ተግዳሮት በሌለበት ስኬት አይኖርም ነው አዝማሚያው፡፡ ስኬታማ ሰዎች ከፈተና ርቀው የኖሩ ሳይሆኑ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተው፤ በፈተና ተፈትነው ነጥረው የወጡ ወርቆች ናቸው፡፡ ወርቅ እነሱ ዘንድ የሚገኘውና ብርቅና ድንቅ የሚሆኑብንም ለዚህ ነው፡፡

ስኬታማ ሰዎች ችግሮችን እንደ ዕድሎች እንጂ እንደ ችግሮች አያዩዋቸውም፡፡ የተከፈተ በር የተከፈተ ስለሆነ ሌላ እምቅ ዕድል በውስጡ አላዘለ ይሆናል፡፡ የተዘጋ በር ግን የመከፈት ዕድልን የያዘ በረከት ነው፡ በተከፈተው በር መግባት ስኬት ሊሆን አይችልም፡፡ የተዘጋውን በር በብልሀት ከፍቶ መግባት ግን ስኬት ነው፡፡ ስለዚህ ስኬት ያለው ተግዳሮት ባለበት ነው፡፡ የንስሩ ከፍታ በሚፈታተነው ነፋስ መኖር እንደተሳካ ስኬታማነት ከችግሮት ማህፀን ይወለዳል፡፡
አስተውላችሁ አንብቡት
ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ

• አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር

• ምርጥ የሰዉነት አቋም ይኑርህ ራስህን ጠብቅ!

• ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን!

• ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት!

• ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን አስወግድ

• በአለህ ፀዳ በል

• ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን

• አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ

• በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን

• ሴቶችን በአስተሳሰባቸዉ መዝናቸዉ

• የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናር

• ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ

• ሃላፊነት መዉሰድን አትፍራ

• ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ

• የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ

• ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክል ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ ያሳምናቸዋል!

ሰላማችሁ ይብዛልኝ!!

ከDesu Werku
🌹🌹መልካም ለሊት ይሁንላችሁ🌹🌹
#አጠር_ያለ_አስተማሪ_ታሪክ👈

👤አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ በመዓበል ተመታና መርከብ ተሰባብሮ በባህሩውሰጥ ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል ... ምግብን ዓሳ እያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ።

አንድ ቀን 🐠ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ እየሄደ በመሀል እዛች ባህር ላይ ጭስ ይሸተዋል ዞር ብሎ ሲመለከት ያቺ 🌋ጎጆው እየነደደች ነው ... እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዎን ሊያድናት አልቻለም ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል አለቀሰ😪 ፈጣሪወን ወቀሰ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ለብቻዬ ጥለከኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለክኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራዋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለክ ብሎ አለቀሰ አማረረ ...

ከደቂቃዎች በዋላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ 🛳መርከብ አየ ተደሰተ ... የመርከብ ሰዎችም መጥተው ጭነው ወሰዱት
ከዚያም ለመርከብ ሰዎች ጠየቃቸው !
እንዴት አገኛችሁኝ እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት መጣችሁ 🤔 አላቸው ...

መርከበኞቹም እኛም በዛኛው በኩል ዞረን እየሄድን ነበር ከዚያ በኩል ጭሰ አየንና እዚህ ሰው ይኖራል ብለን መጣን አንተ አገኘን አሉት።

🙏አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃይ ልታወጣኝ ፈልገህ ነው ትንሻ ጎጆዬን ያፈርሰከው ወደ ትልቁ ቤቴ ልትወሰደኝ ነው አለ።

አንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣ ሲበላሽብን ፈጣሪንም ሰውንም ስናማርር እንኖራለን ግን ካጣነው ነገር ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን በችግራችን ጊዜ መጠጋት ያለብንን አንድዬን እንረሳለን ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን ።

ያጣነውን የሰጠን አንድዬ ! አህምሮችን ከሚያስበው በላይ ሊሰጠን እንደሚችል ማመን አለብን !
አንድ ምሽት ላይ ልክ ባለሱቁ ሱቁን ከመዝጋቱ በፊት አንድ ውሻ ወደ ሱቁ ይገባል። ውሻው በአፉ ዘምቢል ይዟል። ዘምቢሉ ውስጥ የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር እና ገንዘብ ተቀምጧል። ባለሱቁ ገንዘቡን ወስዶ እቃዎቹን በዘምቢሉ ውስጥ ያኖረዋል። ወዲያውኑ ውሻው ዘምቢሉን ይዞ ይሄዳል። ባለሱቁ ስለገረመው የውሻው ባለቤት ማን እንደሆነ ለማወቅ ውሻውን ይከተለዋል።ውሻው ከአውቶብስ ፌርሜታ ቆሞ ይጠብቃል። ከትንሽ ጊዜ በኋላ አንድ አውቶብስ ሲመጣ ውሻው አውቶብሱ ውስጥ ይገባል። ትኬት ቆራጩ እነደመጣ ወደፊት ጠጋ አለ የአንገት ቀበቶው ላይ ያለውን ገንዘብና አድራሻ ለማሳየት። ትኬት ቆራጩም ገንዘቡን ወስዶ ትኬቱን በአንገት ቀበቶው ውስጥ ያኖርለታል። የሚወርድበት ቦታ ሲደርስ ወደፊት ቀረብ ብሎ ጭራውን ያወዛውዛል መውረድ እንደሚፈልግ ለማመልከት። አውቶብሱ እንደቆመለትም ይወርዳል። ባለሱቁ አስከአሁን እየተከተለው ነበር። ውሻው ከአንድ ቤት ደርሶ በሩን በእግሮቹ ያንኳኳል። ባለቤቱ ከውስጥ ወጥቶ ውሻውን በዱላ ይመታዋል። በዚህ ግዜ ባለሱቁ ተናዶ " ውሻውን ለምንድነው የምትመታው?" ብሎ ይጠይቀዋል። ባለቤቱም እንዲህ ብሎ ይመልስለታል። "ከእንልፌ ቀስቅሶኛል። ቁልፉን ይዞ መሄድ ነበረበት።"
ይህ የህይወት እውነት ነው። ሰዎች ለአንተ የሚሰጡት ግምት ማብቂያ የለውም። ከዚህ በፊት የሰራሃቸው ጥሩ ነገሮች ሁሉ ይረሳሉ። ትንሿ ስህተትህ ጎልታ ትወጣለች። ይህ የዚህ ቁሳዊ ዓለም ተፈጥሯዊ ገጽታ ነው።
#የቶማስ_ኤዲሰን_እናት!


⭐️ታዳጊው ቶማስ ኤዲሰን ከዕለታት አንድ ቀን ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲሄድ አንድ ወረቀት ለእናቱ ሰጣት።
''እማዬ መምህራችን ይህን ወረቀት ሰጠኝና ለእናትህ ብቻ ስጣት አለኝ'' አላት።
እናቱም ደብዳቤውን አንብባ በፍርሃት ተሸብባ፤ ዕንባ 😢😢በዓይኖችዋ ዙሪያ ግጥም አለ።
ነገርግን ድምጽዋን ከፍ አድርጋ ለልጅዋ ደብዳቤውን አነበችለት።

📌''ልጅሽ የሚገርም ክህሎት ያለው ብልህ ልጅ ነው። አሁን የሚማርበት ትምህርት ቤት ለእሱ በጭራሽ አይመጥነውም ያንሰዋል። የተሻሉ ጎበዝ መምህራን ያሉበት ትምህርት ቤት ቢገባ ይሻለዋል። ምክንያቱም እሱን የሚመጥነው ትምህርት ማግኝት ስለማይችል እባክሽ እራስሽ ልጅሽን ቤት ውስጥ አስተምሪው...!'' ይላል አለችው።

#እናቱ ከሞተች ከብዙ ዓመታት በኋላ ቶማስ ኤዲሰን በአሜሪካ ታላቁ የክፈለ ዘመኑ የፈጠራ ሰው ሆነ። ከእለታት አንድ ቀን የድሮ የቤተሰቡን ቁምሳጥን ሲከፍተው አንድ ተጣጥፎ የተቀመጠ ደብዳቤ አገኘ። ከፍቶ ሲያየው መምህሩ ልጅ እያለ ለእናቱ ብቻ እንዲሰጥ ያዘዘው ደብዳቤ ነበር።
ወዲያውኑ ደብዳቤውን ከፍቶ ማንበብ ጀመረ '' #ልጅሽ_የዓእምሮ_በሽተኛ_ነው። ለማንኛውም እዚህ ትምህርት ቤት እንዲማር አንፈቅድለትም። ስለዚህ ካሁን በኋላ ከትምህርት ቤቱ ተሰናብቷል።'' ይላል መልእክቱ።

✔️ቶማስ ኤዲሰን በስሜት ተመስጦ ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ በኋላ የግል ማስታወሻ ደብተሩ ላይ እንዲህ ብሎ አሰፈረ።
''ቶማስ አልቫ ኤዲሰን የዓእምሮ ህመምተኛ ታዳጊ ሕጻን ነበር። እናቱ ግን የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ሊቅ እንዲሆን አስቻለችው።''

📌ግብረገብ - የእናቶች ፍቅርና ማበረታታት ለልጆች መጻኢ ስኬታማ ሕይወት መሰረት ነው። በተፈጥሮዋቸው በተለይ እናቶች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸው ቅርበታቸው ከፍተኛ ነውና ሕጻናትን በሞራል በመደገፍ ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለአገራቸው እና ለዓለም የሚበጅ ስራዎችን ትተው የሚያልፍ ፍሬዎች እንዲሆኑ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው።

አትችልም፣ አትሞክሪ፣ የኔ ልጅ እኮ አይሆንለትም ወዘተ... መሰል ሞራል ገዳይ አሉታዊ ስሜት ንግግሮች ከማድረግ ይታቀቡ። በአንፃሩ ልጆችን ስሜታቸውን መረዳት፣ በእንክብካቤ መያዝ፣ ሳይታክቱ ምላሽ መስጠት፣ ትኩረት ሰጥቶ ማዳመጥ ይገባል።
ስወዳችሁ በብዛት!😍

😘😘 #ክብር ለእናቶች ሁሉ ይሁን!
#አንድ_አባት_እንዲህ_አሉ
ልጄ ሆይ፥
“..... ባጭሩ......

#ችኮላ ☞የትዕግስት ጠላት የጠብ አባት ነው።

#ምኞት ☞የቁም ህልም ነው።

#ማስተዋል ☞የራቀን ለማቅረብ የቀረበን ለማራቅ የሚያገለግል የልብ መነፅር
ነው።
#ህልም ☞ በሀሳብ ተቀርፆ በቅዠት የሚወለድ ነው።

#መከራ ☞ የፀባይ ማረምያ የስራ ማነቃቂያ የጥበብ ማቋቋሚያ ነው።

#ትግስት ☞ተደብቆ ቆይቶ ድል ማድረጊያ መሳርያ ነው።

#ፍቅር ☞ መያዣ የሌለውን የሰውን ልብ አስሮ ለመያዝ የሚያገለግል የሰላም
ገመድ ነው።” @hayu_addi
ልጄ ሆይ 👩‍👩‍👦‍👦፥በንዴትህ ወቅት እንደ ሞተ ሁን- ሞት የእንቅልፍ ታላቅ ወንድም ነው ይሉታል።

ከጸጥታ ሁሉ በላይ የከበደ ጸጥታ ሞት ነው። 🙀

በንዴት ውስጥ እንደሞተ ሰው ጸጥ ማለት፤ ከጥበቦች ሁሉ በላይ የገዘፈ ጥበብ ነው ።👏👏👏👏👏👏

እንደሞት ሁሉን የሚያሳልፍ ትዕግስት ይኑራችሁ ።
👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍
”ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ነገር አትስሩ” ።
😳😳😳😳😳😳😳
ንዴታችንን ለቅጸበት በጸጥታ ብናሳልፈው፤ ምን ያህል ከጸጸት እራሳችንን እናድን ነበር።

💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️

@ZePsychologist
አስቸጋሪ ሰዎችን ለመቋቋም የሚያግዙ ሶስት ኣጫጭር ምክሮች።

የእለት ተዕለት ኑሯችንን ስናከናውን ይብዛም ይነስም ባህሪያቸው አስቸጋሪ ከሆኑ ሰዎች ጋር መገናኘታችን አይቀሬ ነው። አንዳንዶቻችን እነዚህን ሰዎች በብልሃት እና በስልት ማለፍ እና ከእነሱ የምንፈልገውን ማግኘት
ስንችል፣ አንዳንዶቻችን ደግሞ በድርጊታቸው ተበሳጭተን ለጭቅጭቅ እና ለንትርክ እንዳረጋለን።
የሚከተሉት ሶስት አጫጭር ምክሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ከሆኑ ሰዎች ጋር የሚኖረንን አጋጣሚ ቀለል እንደሚያደርጉ በስነ ልቦና ባለሙያዎች ይነገራሉ።

1. ጊዜ ሰጥተው ያዳምጧቸው።
በሚናገሩበት ጊዜ ሙሉ ቀልብዎን ሰጥተው ምን ለማለት አየሞከሩ እንደሆነ እና የመጡበት አቅጣጫ
ምን እንደሆነ ያዳሙጧቸው፣ ተናግረው ሲጨርሱም
“ከንግግርዎ የተረዳሁት ይህንን ነው” ብለው መስማትዎን ያረጋግጡላቸው። ያሉትን ማዳመጥዎን ካረጋገጡ በኋላ አቋማቸውን መለወጥ ይቻል እንደሆነ በዚያው ይመርምሩ።

2. ያልተለመዱ አካሄዶችን ይጠቀሙ።
ስላበሳጫቸው ነገር ወይም ስለነሱ ጉዳይ እንደሚጨነቁና እንደሚያስቡ ይግለፁላቸው። እርስዎን በእነርሱ ጫማ ውስጥ አስቀምጠው አመለካከታቸውን ለመረዳት ይሞክሩ። "ጉዳዩን እረዳለሁ" ብለው ይንገሯቸው። ይህ ማለት የግድ እነርሱ በፈልጉት አቅጣጫ ለመሄድ መስማማት ማለት አይደለም። ነገር ግን እነሱን ለመረዳት መሞክርዎ ብዙ ሰዎች የማያደርጉትን ያልተለመደ መልካም ሙከራ ሞክረዋልና ይህን ማድረግዎ አብዛሃኛውን ጊዜ እነዚህን ሰዎች የማለዘብ ኃይል ይኖረዋል።

3. ጭቅጭቁ ከመፈጠሩ በፊት ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ይምሯቸው። ብዙ ሰዎች ሌሎችን የሚያስተናግዱበት አካሄድ እንደተስተናጋጁ ሰው ሁኔታ ተለዋዋጭ ነው። ሰዎች ደከም ብለው ሲታዩ ብዙ ጊዜ አላግባብ የሆነ ነገር በሌሎች ይደረግባቸዋል። ስለሆነም ሰዎች ከእርስዎ ጋር ሲሰሩ እና ክንዋኔን ሲያደርጉ የማይፈልጉት ነገር እንዳይፈጠርና አግባብ በሌለው ሁኔታ እንዳያስተናግዱዎ አስቀድመው ማንነትዎን እና በግንኙነታችሁ ውስጥ ስለሚጠብቁት የንግግር አግባብ
ብስለት በተሞላበት ሁኔታ ማሳወቅ እና መምራት ያስፈልጋል። ይህን በማድረግ ያለዎትን አክብሮት እያረጋገጡ ነገርግን የሰዎች መጠቀሚያ ለመሆን የማይፈቅዱ እንደሆኑ ያሳያሉ፣ ብሎም ግንኙነታችሁ መከባበር በተሞላበት ሁኔታ እንዲከናወን ይረዳል።
በአንድ ወቅት አንድ ወጣት በጫካውስጥ በተነሳ እሳት እንስሳት ሁሉ ለማምለጥ ሲሯሯጡ አንድ የተጎዳ እና መሮጥ ያቃተው የነብር ግልገል ተመለከተ፡፡ የነብር ግልገሉንም አምጥቶ እንደ ቤት እንስሳ ቤቱ ውስጥ ያሳድገው ጀመር ፡፡ ይህ ነብር ሚመገበውም ሆነ ሚጠጣው በዚህ ወጣት ሲቀርብለት ብቻ ነው፡፡
ከአመታት ቡሀላ ነብሩም አደገ ወጣቱም ጎለመሰ፡፡ ነብሩ እና ይህ ሰው እጅጉን ተቀራረቡ፡፡
ከግዜያት ቡሀላ የዚህ ነብር ፀባይ መቀየር ጀመረ፡፡ መመገብ አቆመ ፤ከፍ ካለ ነገር ላይ መዝለልንም የእለት ተግባሩ አደረገው፡፡ በዚህ የነብሩ ፀባይ መቀየር ግራ የተጋባው አሳዳጊው ነብሩን ይዞ ወደ አንድ አዋቂጋ ሄደ ፡፡ ስለ ጉዳዩም አስረዳው፡፡
አዋቂው ሁሉን ነገር በጥሞና ካዳመጠ ቡሀላ ለአሳዳጊው እንዲህ አለው "ነብሩ መመገብ ያቆመው ሆዱን ባዶ ሊያደርግ ነው፡፡ ከከፍታ ቦታ እየወጣ ወደመሬት ሚዘለውም እንዴት አድርጎ አንድ ነገር ላይ ዘሎ መስፈር እንዳለበት እየተለማመደ ነው፡፡ ያም አንድ ነገር አንተ ነህ፡፡ አንተን ሊበላህ ነው ሆዱን ባዶ ሚያደርገው ዘሎ ሚወጣውም አንተ ላይ ነው፡፡ አንተ በወዳጅነት እያሰብከው እሱ ግን ወዳጅነትህን በዚህ መንገድ ሊመልስልህ እየተዘጋጀ ነውና በፍጥነት ወደ ጫካ መልሰው" ሲል ከነማስጠንቀቂያ ነገረው፡፡
አሳዳጊውም የተባለውን አደረገ፡፡ ነብሩን ወደ ጫካ ለቀቀው፡፡ ለወዳጅነቱ በከፈለው ክፍያ ምትክ በተሰጠው ምላሽ ግን አላዘነም፡፡ ምክንያቱም እሱ መልካምነት ባህሪው ነው፡፡ ነብሩም አድኖ መብላት ባህሪው ነው፡፡ ከሞት ያተረፈው ግልገል አድጎ ዛሬ ላይ እውነተኛ ነብር መሆኑን በማሳየቱ አሳዳጊው ተደሰተ፡፡
አሁን ላይ ነብሩ ነገሮችን በራሱ ማድረግ ደረጃን ደርሶአል ማለት ነው፡፡ አሳዳጊውም ይሄንን ግዜ ድረስ በማቆየቱ ሀላፊነቱን ተወጥቶአል፡፡ ወዳጅነታቸው ታሪክን ጥሎ አለፈ፡፡ አሳዳጊውም ወደቤቱ ነብሩም ወደ ጫካው፡፡


💗በህይወታችን የሚገጥሙንን ነገሮች በሙሉ ከመልካም ጎኑ እንመልከታቸው፡፡💗
እንደ ሰው አዕምሮ ሰነፍ የለም፡፡ ካስተኛቹት መንቃት ፤መነሳት ፤ መስራት ፤ መለወጥ የማይወድ ነገር ቢኖር የሰው ልጅ አዕምሮ ነው፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ፊልም ብትጋብዙት ፤ ካፌ 6 ሰዓት ብታስቀምጡት ፤ኢንተርኔት ላይ ቀኑን ሙሉ ብትጥዱት ፤ ምን አለፋቹ ተነስተህ ዙር ብትሉት የማይደክም ማሽን ነገር ነው፡፡ ግን እስቲ 1 መፅሐፍ እንብብ በሉት ፤ 10 ገጽ ሀሳብህን ጻፍ በሉት ፤ ጠዋት ስፖርት ስራ በሉት፤ ቁጭ ብለህ ስራህን አቅድ በሉት በጣም ሰነፍ ነው፡፡
አዕምሮአችን አረም ማብቀል ይቀለዋል፡፡ ነገር ግን በጥበብ የገፉት ሰዎች ያሸንፉታል…..ማሰብ ፤ መስራት ፤ ብርታትን ያስለምዱታል፡፡ ያን ጊዜ ግን መተኛት አይወድም ፤ አሮጌ ነገር አይፈልግም ፤የለውጥ ረሀብተኛ ይሆናል፤መስራት ሲጀምር፤ ሰርተን እስካልጨረስን ድረስ እኛኑ እረፍት ይነሳናል……..እስቲ እንግፋው፡፡
ุุุุุุุุุุุุุุุุุุุุุุุุุ่่่่่่ြŦุุุุุุุุ่่่่ℛŲ€ุุุุ
#የበቀል_ተዋረድ

የሥራ አለቃዬ ከቢሮ ስገባ
ፊቱን አጨግጎ በልቡ እያደባ
ነገር እየበላ ተንኮል እያሴረ
ባለቅነት ቃና ብዙ ተናገረ

እኔም በተራዬ ወደ ቤቴ ሄጄ
ካለቃዬ አይቼ ከሳቸው ለምጄ
የቤት ሰራተኛ ሞግዚት የልጆቼ
ከወለሉ ውሀ ስታፈሰ አይቼ
ላጠፋችው ጥፋት ለሰራችው ስራ
ማካካሻ እንዲሆን ለሷም እንዲገባት
ይቺ ደነዝ ብዬ ክብሯን አዋረድኩት

እሷም በተራዋ ራሷን አንግሳ
በቀል አርግዛ ጥላቻን ፀንሳ
ከቤቴ መውጣቴን መራቄን ጠብቃ
ስትገርፈው ትውላለች ህፃን ልጄን አንቃ

ከቤቴ ስመለስ እንባውን ባላይም
ልጄ ቋንቋ ችሎ ቅሉ ባይነግረኝም
ግፍ እንደደረሰበት መጠርጠሬ አልቀረም
ቋንቋ ለማይችለው ለህፃኑ ልጄ
አይኖቹን እያየሁ ደባብሼ በጄ
ባፌ ባልነግረውም በልቤ እዲህ አልኩት
ብድርክን ለመክፈል አንተም ከፍ እስክትል
በቀል እስኪገባክ እስክትማር ተንኮል
ላንት አቅም የሚሆን ሰው እንኳ ቢጠፋ
በል ድመቷን ደብድብ አይዞህ አትከፋ
.
.


..
.
.ምን ተማራቹ ከግጥሙ?
🌹ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን ቻናል የተወሰደ🌹
"ሰሚ ያጡ ድምፆች!"

ልክ የዛሬ አምስት ዓምት ነበር የተለቀቀው እንደው ላስታውሳቹ ፈለኩ
:::***::::****:::::****:::::***:::::****:::::<<ይህን መሳጭና ልብ የሚነካ ገጠመኝ ዘወትር ተደጋግሞ ቢነበብ ፍጹም

የማይሰለችና ለሁላችንም አስተማሪ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ዛሬም በድጋሚ ለጥፌዋለሁ እናንተም በትእግስት

አንብባችሁት እንደምትጨርሱትም ሙሉ እምነቴ ነው>>፡❀✔❀✔❀✔❀✔❀✔❀✔❀☞እኔና ጓደኛዬ ከስራ በኋላ ተገናኝተን መኪና ውስጥ ሻይ እየጠጣን እያወጋን ነበር፤ በድንገት የመኪናችን መስኮት በር ተንኳኳ..:

☞አንድ ጎስቆል ያሉ አዛውንት… "ልጆቼ አንድ ብር ስጡኝ?" ብለው የተማፅኖ ቃና በሌለው አኳኋን ጠየቁን፡፡፡

☞ስጡኝ’ የምትለው ቃል ትንሽ ደስ ባትልም ጓደኛዬ ከአፍታ ማቅማማት በኋላ ከኪሱ አንድ ብር አውጥቶ ሰጣቸውና…"ጠጡበት ደግሞ" አላቸው ።፡

☞ሽማግሌው የኔ ቢጤ ቀበል አርገውም "አይ! የለም… ቤት እሰራበታለሁ!" ብለው በማፌዝ ሁኔታእየተመለከቱን መለሱልን፡

☞ይሄኔ እኔም ሆንኩ ጓደኛዬ ፈፅሞ ያልጠበቅነው መልስ በመሆኑ በሳቅ ፈረስን… ሳቄን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ…"ፋዘር… ምንለማለት ፈልገው ነው?" ስል ጠየቅኳቸው፤፡

☞"እንዴ! ጓደኛህ እራሱ ምን ለማለት ፈልጎነው? በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ብር ነው የሰጠኝ። ታዲያ በዚህ አንድ ብር ምንእንዳረግበት አስቦ ነው? ሲቀጥል ብሩንከመስጠቱ በፊት ምን ልታደርግበት ነው ብሎ አልጠየቀኝም፤ ታዲያ ከሰጠኝ በኋላ ምንስ ባደርግበት ብሩም፣ ነፃ ፈቃዱም የኔአይደል እንዴ? ምን ገዶት ያዘኛል በገዛ ብሬ?…"

፡☞የሽማግሌው መልስ በአንድ በኩል ትክክል ነው(ሎጂካል ነው) በሌላ በኩል ግን ድፍረታቸውና ግልፅነታቸው ገረመኝ።:

☞ጓደኛዬ ቀጠለ... "እሺ አሁን ልጠይቆት… ምን ሊያደርጉበት ነው?":

☞"ልጠጣበት!" አሉ ሽማግሌው…ቀለልአድርገው:☞አሁንም ሳቄ አመለጠኝ። "እውነቶትን ነው?" አልኳቸው፡፡:

☞"እውነቴን ነው እንጂ ልጄ… በዚህ እድሜዬ ለምን እዋሻለው…":☞አሁንም በምላሻቸው ተገርሜ… "ምግብበልተዋል?" ስል ጠየቅኳቸው:

☞"ቁርስ በልቻለው" አሉኝ:☞

"አሁን እኮ እራት ሰዓት ነው፤ አልራቦትም?" አልኳቸው፡

☞"መራቡንስ ርቦኛል…ግና የሌሊቱን ብርድከነረሃቤ ስለማልችለው ነው አረቄየን የምጠጣው…ውስጤን ለማሞቅ፤አየህ!… እናንተ ሁለቱንም ማድረግ ትችላላችሁ-እስኪበቃችሁ እራታችሁን መብላት እንዲሁምመጠጣት… እኔ ግን አንዱን መምረጥ አለብኝ፤ ስለዚህ የእንቅልፍ ኪኒኒዬን- አረቄዬን ጠጥቼ ለጥ እላለኋ…" አሉኝ፡

☞የሽማግሌው ንግግር እኔና ጓደኛዬ ሆድ ውስጥ እኩል ዘልቆ የገባ ይመስል ሁለታችንም እኩል ቀና ብለን ተያየን… በአይን ቋንቋ ብቻም ተግባባን… "ፋዘር መኪናው ውስጥ ይግቡ፤ እኛ እራትልንበላ ስለሆነ አብረን እንበላለን፤ በዛውም ጨዋታዎት ደስ ስላለን አንድ፣ ሁለት እያለን እናወጋለን…" አልኳቸው፡

☞ሽማግሌው ግን "የለም! መኪናችሁን አቆሽሽባችኋለው…"እያሉ መኪናው ውስጥ ላለመግባት አምባ ጓሮ ፈጥሩ።፡

☞በመከራ አሳመንናቸውና ከኋላ ገብተው ተሳቀው ተቀመጡ(ቁጢጥ አሉ ማለት ይቀላል)፡

☞በቅርብ ወደሚገኝ አንድ ሬስቶራን አመራን በዚህ መሀል ጨዋታ ተጀመረና ሽማግሌው የኔ ቢጤ ስማቸው ጋሽ በቀለ እንደሆነነገሩን፡

☞እኛ ግን ወዲያው ጋሽ በቄ ብለን ጠራናቸው።፡

☞መኪናችንን አንድ ምግብ ቤት ግቢ ውስጥ አቁመን ወደ ሬስቶራንቱ ልንገባ ስንል…የሬስቶራንቱ ጥበቃ "ወዴት ነው!" ብሎ ጋሽበቄ ላይ አፈጠጠባቸው።፡

☞ጓደኛዬ በንዴት ቦግ ብሎ "ከኛ ጋር ናቸው!" ብሎት ገፍትሮት ለመግባት ሞከረ።፡
☞ይህን ጊዜ… ሁኔታችንን ከውስጥ ሆኖ ይከታተል የነበረ የሬስቶራንቱ ማኔጀር ጥድፍ፣ጥድፍ እያለ ወደኛ መጣ… "ይቅርታ ችግር አለ?" ሲል ጠየቀ፡
☞ጥበቃው ቀልጠፍ ብሎ ለማኔጀሩ በጆሮው የሆነ ነገር ሹክ አለው።፡
☞ማኔጀሩም ትንሽ ካቅማማ በኋላ…"ይቅርታ ወንድሞቼ ሬስቶራንት ውስጥ ትልልቅ እንግዶች ስላሉ ውጪ ላይ መቀመጥትችላላችሁ?" ሲል በተማፅኖ እጅ ነሳ።፡
☞ይህን ጊዜ ጓደኛዬ ይብሱኑ ቱግ ብሎ… "እኛ ትንሽ ነን? ለምን! የቆሸሸ ልብስ ስለለበሱ ነው! ትልቅነት የሚለካው በአለባበስ ነው? በጣም ያሳዝናል…"
፡☞ጋሽ በቄ በፍፁም እርጋታና በብስለት ፈገግታ የጓደኛዬን ትከሻ መታ… መታ… እያደረጉ…"ተዋቸው ልጄ እነሱ እኮ የታዘዙትን የሚፈፅሙት፤ከህሊናቸው በላይ ደሞዛቸው ስለሚጠቅማቸው ነው። አትፍረድባቸው። አንተ እንዳልከው ትልቅነት በገንዘብና በቁስ የሚለካ አይደለም፤ የሰው ትልቅነቱ የሚለካው በአይምሮው ነው፤ በብስለቱ! ያ ብስለቱ ደግሞ ሁሉን ንቆና ስቆ እንዲያልፍ ሊያስችለው ይገባል…"
፡☞ጋሽ በቄ ከፊታችን እየተራመዱ…"ግድ የለም… ኑ! ለኛም የውጪው አየር ይሻለናል… እዚህ በነፃነት እንጫወታለን… አየሩም ግሩም ነው…" ብለው አንድ ጥግ ላይ ወዳለ ጠረጴዛ መሩን…፡☞የጋሽ በቄ እርጋታና አስተዋየነት ከእድሜያቸው የሚጠበቅ ቢሆነም የእርሳቸው ግን ለየት ያለ ነው.. ፍፁም ቅን፣ የዋህና ብሱል ናቸው…በነገሮች ቶሎ አይደነቁም፣ ቶሎም ቅር አይሰኙም።፡☞እራታችንን በአንድ ትሪ ተቋድሰን… ቢራችንን እየጠጣን ጋሽ በቄ ስለ ህይወታቸው አጫወቱን…
፡☞"…ልጆቼ! በአንድ ወቅት… እኔም እንደናንተው የራሴ ስራ የነበረኝ… ትንሽም ብትሆን ደሞዝ ተከፋይ ነበርኩ… ለብቻዬ ቤት ተከራይቼም እኖር ነበር… በአንድ ክፉ ቀን… ከሃላዬ የመጣ መኪና ድጦኝ እግሬ ተሰበረ… እናም ለረጅም ወራት ሆስፒታል ተኛሁ። ታዲያ በጥበቃነት የምሰራበት መስሪያ ቤት ለተወሰነ ጊዜ ደሞዜን እየከፈለ ቢያሳክመኝም… ቶሎ ባለማገገሜ የነሳ በኔ ቦታ ሰው ተክተው በየወሩ የሚሰጡኝንም ትንሽ ብር አቋረጡብኝ… አከራዮቼም በሌለሁበት ቤቴን አሰብረው… እቃዬን አውጥተው ክፍሌን አከራዩት… ታዲያ የቅርብ ዘመድም ሆነ ጓደኛ ስላልነበረኝ… በክራንች ድጋፍ መንቀሳቀስ ስጀምር ከሆስፒታል ወጥቼ ጎዳና ላይ መኖር ጀመርኩ… ይገርማል!… በአንዲት አጋጣሚ ህይወቴ እንዲህ ሆነ። ይኸው… እስከዛሬ እዚሁ ጎዳናአለሁ…"፡☞አንድ… ሁለት… ቢራ እያልን የጋሽ በቄን አፍ የሚያስከፍት ታሪክ ተመስጠን ስንሰማ ሳናስበው ሰዓቱ ስለሄደብን… ጋሽ በቄን ወደ ቦታቸው ሸኝተናቸው ለመለያየት ተስማማንና ወደ መኪናችን ተመለስን… መኪና ውስጥእንደገባን… ጓደኛዬ የተወሰነ ብር አውጥቶ…"ጋሽ በቄ… እቺን ይያዟት…" ሲላቸው...፡☞ጋሽ በቄ… ወደ ኋላቸው ሽምቅቅ ብለው…በግርምት ጓደኛዬን እየተመለከቱት… "ለምኔ ነው ብር የምትሰጠኝ? እስክጠግብ እራቴን በልቼ… የሚበቃኝን ያህል ጠጥቼ… ከዚህ በኋላ ብር ምን ሊያደርግልኝ ነው?"፡☞"አይ… ለነገ ይሆኖታል…" አልኩ ቀልጠፍብዬ…፡☞ይሄን ጊዜ… ጋሽ በቄ… ያን የብስል ፈገግታቸውን ብልጭ አድርገው… "ጎዳና ካስተማረኝ ነገሮች አንዱ ምን እንደሆነታውቃላችሁ ልጆቼ?" የኛን መልስ ሳይጠብቁ ንግግቸውን ቀጠሉ…"ጎዳና ካስተማረኝ ነገር አንዱ… ስለ ዛሬ ብቻ መኖርን ነው…የጎዳና ኑሮን በቅጡ ከተረዳሁበት ቀን ጀምሮ ገንዘብ ይዤ ተኝቼአላውቅም… እራቴን በልቼና አረቄዬን ጠጥቼ ብር ከተረፈኝ…የቀረኝን ገንዘብ ለሌላ የኔ ቢጤ ሰጥቼ እተኛለሁ እንጂ በኪሴ ገንዘብ ይዤ ተኝቼ አላውቅም። እኔ ገንዘብ በኬሴ ይዤ ተኝቼስለምን ሌላው ወንድሜ ፆሙን ያድራል?""…የቤት ኪራይ የለብኝ፣ ግብር አልከፍል፣ የመብራት፣ የውሃ አልል… ለምን ብዬስ ብር አጠራቅማለው? የዕለት ጉርሴንካገኘሁ… ተመስጌን ብዬ መተኛት ነው እንጂ":"…ልጆቼ እያንዳንዷ ቀን የራሷ
. . . #ፍቅር_ያሸንፋል . . .

በአንድ ወቅት ሁለት በጣም ሚዋደዱ ባለትዳሮች በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ የእነዚህ ጥንዶች ፍቅር ሙሉ መንደሩን ያስቀና ነበር፡፡ ከግዜ ወደግዜ ከመንደሩ አልፎ የግዛቱ አስተዳዳሪ ጋር ይህ የጥንዶቹ ጉዳይ ደረሰ፡፡ አስተዳዳሪውም በሰሙት ነገር ተገርመው እውነት ስለመሆኑ ማረጋገጥ ፈለጉ፡፡ በዚህም አንድ ነገር አስበው ባልና ሚስቱን አስጠሯቸው፡፡ ሁለቱንም ብቻ ለብቻ ማናገር ጀመሩ . . .
" ባለትዳር መሆናቹን ሰምቻለው፡፡ ነገር ግን የኔ ልጅ ባልሽን ስላፈቀረቸው ላጋባቸው ወስኛለው፡፡ "አሉ ወደ ሚስትየው እየተመለከቱ፡፡"ይሄንን በመፍቀዴ ለኔ ምን አገኛለው ?" አለች ሚስት ጥያቄውን በጥያቄ እየመለሰች፡፡ "ይሄንን ከፈቀድሽ እና ባልሽን ካሳመንሽ ላንቺ እድሜ ልክሽን ሚያኖርሽ ገንዘብ ለልጅ ልጅ ሚተላለፍ የእርሻ መሬት እና በርካታ ከብቶች ሰጥሻለው፡፡ እንዲሁም ከምትፈልጊው ሰው ጋር አጋባሻለው፡፡ "አሉዋት፡፡ "አሁን እርሶ በሚሰጡኝ ገንዘብ እና መሬት እንዲሁም በሚሰጡኝ ከብቶች ጠቅላላ ባሌን ይመልሱልኛል?ከፈለግሽው ሰው ጋር አጋባሻለው ብለውኛል አይደል፡፡ ስለዚ አሁንም መልሼ ማግባት ምፈልገው ባሌን ነው፡፡ ከባሌ ጋር መልሰው ያጋብኝ እና በክብር ወደቤት ይላኩን፡፡ "አለች አስተዳዳሪው ፊት እጅ እየነሳች፡፡ አስተዳዳሪው እጅጉን ተገረሙ፡፡ ለመሆኑ የፍቅራቹ ሚስጥር ምንድነው? ሲሉ ባልየውን ለብቻው አስጠርተው ጠየቁት፡፡ "እኔ ምወደው እሷን ነው፡፡ እሷ ምትወደው እኔን ነው፡፡ እኛ ምንፈላለገው እርስ በእርሳችን ነው፡፡ ከኛ ውጪ የለበስነው ልብስ እንኳ ለኛ ትርፍ ነው" ሲል መለሰ፡፡
የሁለቱ መልስ አስተዳዳሪውን አልፎ በመላው ግዛት ተሰማ፡፡ ሁለቱ ጥንዶች ለሌሎች ባለትዳሮች ተምሳሌት ሆኑ፡፡ በነሱ ቃል የመጣ የብዙዎች አመለካከት ተቀየረ፡፡ የተጣሉ ታረቁ ፣ ብዙዎች የነበረባቸውን ጉድለት አስተካክለው በትዳራቸው ደስተኛ መሆን ጀመሩ፡፡ ሰዎች አመኑ ለሰው ከሰው ውጪ ያለው ነገር ትርፍ ነው፡፡ ደስታችን በልባችን ነው ብለው ተቀበሉ፡፡ የፍቅር ሀያልነት በጉልህ ታየ፡፡
የዛኔ የተፈጠረው ነገር ዘመን ተሻግሮ ዛሬ እኛንም ለማስተማር በቃ፡፡ ፍቅር ይሻለናል፡፡ በፍቅር እንኑር፡፡
#ጠቃሚ_መልእክት

አንድ ንጉስ አስር ተናካሽ የሆኑ ውሾች ነበሩት ፤ እነዚህን ውሾችም አገላጋዮቹን ‹አሽከሮቹን› ሲያጠፉ ለማሰቃዬትና ለማስበላት ይጠቀምባቸዋል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን አንደኛው አሽከሩ ትክክል ያልሆነ ሃሳብ ንጉሱን ተናገረው ፤ በዚህም ምክንያት ንጉሱ እጅግ ተቆጣበት ፤ ወዲውኑም ወደ ውሾቹ እንዲወረወር ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ አሽከሩም በሀዘን "አስር አመታት አገለገልኩህ ፤ ተገዛውልህ ያልከኝን ሁሉ አደረኩልህ ፤ አሁን ግን ይህንን አደረክብኝ ፤ እባክህ ወደ ውሾች ውስጥ ከመወርወሬ በፊት አስር ቀን ስጠኝ" ብሎ ተማጸነው፡፡ ንጉስም ተስማማ ‹ፈቀደለት› ፡፡ ይወረወር ዘንድ የተፈረደበት አሽከር ውሾቹን ወደሚንከባከበው ሌላኛው አሽከር ሔደና ‹እባክህ እነኝህን ውሾች ለአስር ቀን ልንከባከባቸው › ብሎ ጠየቀው፡፡ የውሾቹ ጠባቂም ግራ በመጋባት ሁኔታ ፈቀደለት ፡፡

የተፈቀደለት አሽከርም ውሾቹን መንከባከብ ጀመረ ፤ ቆሻሻቸውን ማጸዳዳት ፤ ምግባቸውን በሰአቱ ማቅረብ ፤ ማጠብና አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ አደረገላቸው ፤ አስር ቀኑም አለቀ፡፡ ከዚያም በኋላ ከንጉስ ጋር በተነጋገሩት መሰረት …አሽከሩ ተጠርቶ ወደ ተናካሽ ውሾቹ ዘንድ ይወረወር ዘንድ አዘዘ ፤ ወረወሩትም ፡፡ ወርዋሪዎቹም ይህ አሽከር እንዴት በውሾቹ ሊበላ እንደሚችል እየዘገነናቸው መመልከት እንደጀመሩ ያላሰቡትን ሁኔታ በአይናቸው አዬ ፤ ንጉሱም በሚመለከተው ሁኔታ ግራ ተጋባና "በእነዚህ ተናካሽ ውሾቼ ላይ ምን ደረሰ ? ምንስ ገጠማቸው? ማለት እንደጀመረ… የተወረወረው አገልጋይ በውሾቹ መሃል እየተሻሼ በኩራት እየተራመደ እንዲህ አለ "እነዚህን ውሾች ለአስር ቀናቶች ብቻ መገብኳቸው ተንከባከብኳቸው እነርሱም ያደረኩላቸውን በፍጹም አልዘነጉም ፤ አንተን ግን አስር አመት ሙሉ ተገዛሁልህ አገለገልኩህ ነገር ግን በአንዲት ጥፋት ምክንያት ሁሉንም ረሳህና ለሞት አሳልፈህ ሰጠኸኝ" አለው ፡፡ ንጉሱም ሁኔታውን ሁሉ በማስተዋልና ፤ ከውሾች እንዳነሰም በመገንዘብ አገልጋዬ ነጻ እንዲሆን አዘዘ ፤ ነጻም ሆነ፡፡

#ይህ_መልእክት ሰው በጣም ብዙ ውለታ ውሎላቸው ነገር ግን በአንድ ጥፋት ምክንያት የተደረገላቸውን ሁሉ እየረሱ በክፋት ለሚነሳሱ ሁሉ ይሁን፡፡ በመልካም ነገር የተሞላ ታሪክን ፤ በአንድ ስህተት ምክንያት ከንቱ አናድርግ፡፡
“ከብቶች ሁሉ አንድ
አይነት ሳር እየበሉ ……..”

“ከብቶች ሁሉ አንድ አይነት ሳር እየበሉ ፋንድያቸው ለምን ተለያያ?” ፣ ይህ አባባል ለከብቶች መንጋ ብቻም ሳይሆን ለሰዎች መንጋም የሚሰራ መሰለኝ።
አንድ አይነት ትምህርት ቤት ገብተን፤ በአንድ አይነት መምህር ተምረን፤ በአንድ ክፍል ውስጥ ተቀምጠን፤ በስተመጨረሻ አንዳችን ከፍ ብለን ስንቆም ሌሎቻችን ግን ከጀመርንበት ፈቀቅ አንልም። ይህን ጥያቄ
ስንጠይቅ የሰውን ልጅ የህይወት መስመሮች ሊቀይሩ የሚችሉ ነገሮች እንዳሉ በማሰብ ጭምር ነው።
ሌሎቻችን የማናውቃቸው በእያንዳንዳችን ጎዳና ላይ የሚጋረጡ ውጣ ውረዶችን በመዘንጋት አይደለም።
ነገር ግን ብዙ ጊዜ እኩል እድል ተሰጥቶን፤ በተመሳሳይ ሰዓት ፊሽካ ተነፍቶልን እያለ፤
ለምንድነው ውጤታችን የሚለያየው? እርግጥ ነው በውድድሩ አለም ሁሉም ሰው አሸናፊ ሊሆን አይችልም። ህይወት ግን እርስ በእርስ የሚፎካከሩባት የሩጫ ሜዳ ሳትሆን ሁሉም በገዛ ሜዳው እሮጦ ሁሉም በራሱ ሜዳ
አሸናፊ ሊሆን የሚችልባት ቦታ ናት።
ከብቶች ሁሉ አንድ አይነት ሳር እየበሉ ፋንዳያቸው ለምን እንደሚለያይ ከአባባልነቱ በዘለለ እኔ በግሌ የማውቀውም ሆነ ያነበብኩት የለም። እንደው አባባሉ
ከሰው ልጆች ህይወት ጋር ተመሳስሎብኝ ብዕሬን አስነሳኝ እንጂ። እኔ እንኳን በአጭሩ እድሜዬ አንድ አይነት ትምህርት ቤት ተምረን እኩል ሀ ሁ ያልን
ልጆች አሁን በተለያየ የህይወት እርከን ላይ ሆነን ሳይ፤ ልዩነቱ ምን ላይ እንደሆነ ለማወቅ ጓጓሁኝ። የኑሮ እርከን ብዬ ስናገር፤ ስኬት በግል መመዘኛ የሚመዘን
መሆኑን በመዘንጋት አይደለም። ሆኖም ተመሳሳይ እድል ተሰጥቶን፤ በእኩል ሰዓት ፊሽካ ተነፍቶልን፤ አንዳንዶቻችን ለምን ከመንገድ እንቀራለን? ተመሳሳይ
እድል ገጥሞን ውጤታችን ለምን ይለያያል? አንድ አይነት የኑሮ ሳር ግጠን ለምን ከእኛ የሚወጣው ነገር የተለያየ ሆነ? ከታች የዘረዘርኳቸው ነጥቦች ጥቂቶችን ከብዙሃኑ ከሚለዩዋቸው ባህሪዎች ውስጥ ወሳኞቹ ናቸው።
አሸናፊዎችን ከብዙሃኖቻችን ነጥረው እንዲወጡ የሚያደርጓቸው የተለያዩ ነገሮች ቢኖሩም የሚከተሉት ግን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

1) አሸናፊዎች የሚፈልጉትን ያውቃሉ
የምንፈልገውን እንደአለማወቅ በዚህ ምድር ላይ እንድሜያችንን የሚበላ ምንም ነገር የለም። ብዙዎቻችን እራስን ፍለጋ በሚለው ፈሊጥ አቅጣጫው እንደጠፋበት መርከብ በባህር ላይ እንቀዋለላለን። የምንፈልገውን
ባለማወቃችን የማንፈልገውን ኑሮ ለመኖር እንገደዳለን። እዚህ ላይ ግን ልብ ልንለው የሚገባና
ብዙዎቻችን የተሳሳተ መስመር ውስጥ የሚከት አስተሳሰብ አለ። ይህም እራስን ፍለጋ በሚል ፈሊጥ የብዙ ሰዎች እድሜ ይባክናል። ብዙዎችን የሚያስማማው የእራስን የማግኘት ትርጉም ፤ የሚያስደስተንን ነገር ማድረግ ነው። አለን ዋትስ የተባለ ሊቅ በአንድ ወቅት ለወጣቶች እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር “ብዙ ወጣቶች እራሳቸውን እንዴት ማግኘት
እንዳለባቸው እንዳስረዳቸው ይጠይቁኛል። በተለይ ከከፍተኛ ደረጃ ት/ቤት ወጥተው አዲስ የኑሮ ምዕራፍ ለመጀመር የተዘጋጁ ወጣቶች በህይወታቸው ምን መምረጥ እንዳለባቸው ስለማያውቁ እርዳታ ይጠይቁኛል። የኔ መልስ እንዲህ ነው ገንዘብ ቅድሚያ ባይሰጠው ምን ማድረግ እንደሚያስደስታቸው እጠይቃቸዋለው? ገንዘብ ቦታ ባይኖረው ጊዜያቸውን ምን በማደረግ ማሳለፍ እንደሚሹ ሲነግሩኝ ፤ እራሳቸውን በዛ ውስጥ እንደሚያገኙት መክሬ እሰዳቸዋለው።” ብሏል።
እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን አንድ ነገር አለ። በተለይ በእኛ አገር ገንዘብን የሚያስገኝን ነገር ትተን
ተሰጥዎን በነጻ ልኑር ማለት ዘበት ነው። ስለዚህ አንዴ የምንፈልገውን ነገር ካወቅን በኋላ ያንን ተሰጥዎ ወደ ገንዘብ የምንለውጥበትን መንገድ መመርመር አለብን። ባጠቃላይ የምንፈልገውን ማወቅ፤ በነፍሳችን ውስጥ የተለየ ጉልበት እንዲኖረን ያደርገናል።

2) አሸናፊዎች ልዩ መሆንን አይፈሩም
እውነት እንነጋገርና ልጆች ሆነን እንደው ልዩ በመሆናቸው ብቻ የምናሾፍባቸው እኩዮቻችን እንደነበሩ እናስታውሳለን።
ከብዙሃኑ ጋር አብረው ባለመጓዛቸው የተወቀሱ፤
የተሾፈባቸው ልጆች ናቸው በስተመጨረሻ የሩጫው አሸናፊ ሆነው የምናያቸው። ሮል ሞይ የተባለ ጸሃፊ ሰዎች በህይወታቸው ስኬታማ እንዳይሆኑ ከሚያደርጓቸው ነገሮች ውስጥ ዋነኛው ልዩነትን መፍራትና ብዙዎች በሄዱበት መንገድ ለመሄድ መሞከር ወይም ብዙሃኑን መምሰል እንደሆነ ይናገራል።

3) አሸናፊዎች የራሳቸው አነቃቂዎች ናቸው
ብዙዎቻችን የሚያነቃቃን ነገር እንፈልጋለን። ለምሳሌ ልጅ ሆነን እንኳን አንዳንድ ተማሪዎች የቤት ስራቸውን የሚሰሩት ወይ የአስተማሪውን ቁጣ ፈርተው አልያም የቤተሰብን ግርፊያ ፍራቻ ነው። ጥቂት ተማሪዎች ግን
መምህሩ ኖረም አልኖረም፤ ቤተሰብ ተቆጣጠራቸውም አልተቆጣጠራቸውም የቤት
ስራቸውን መስራታቸው አይቀርም። እንደዚህ አይነቶቹ
ተማሪዎች ናቸው በኋላ በህይወታቸውም ለኑሮዋቸው
ሃላፊነትን መውሰድ የሚችሉት። እንደዚህ አይነት ሰዎች የሌላው ማነቃቂያ ሳይሆን የራሳቸው ፍላጎት ነው የኑሮዋቸው መቅዘፊያ።የመጀመሪያ ነጥብ
ማለትም ፍላጎትን ማወቅ ከዚህ ጋር ጥብቅ ግንኙነት አለው። የምንፈልገውን ነገር ስናደርግ ከራሳችን ፍላጎት ውጪ ማነቃቂያ አያስፈልገንም።

4) አሸናፊዎች ምክንያት ደርዳሪዎች አይደሉም የብዙዎቻችን ውድቀት ምክንያት ይህ ነው፤ የምንፈልገውን ላለመሆናችን ምክንያት መደርደር እንፈልጋለን። ለውድቀታችን እራሳችንን እንደመመልከት የስህተታችንን ሚስጥር ሌሎች ላይ ለመፈለግ እንጥራለን። ሃላፊነት መውሰድ ስለሚሳነን፤ ልክ እንደጦጣዋ ተረት “የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ” ማለት እናበዛለን። ስኬት ማለት ባህሪ ነው። ስኬታማ ሰዎች በየእለቱ በሚያከናውኗቸው ነገሮች ላይ ሙሉ ልባቸውን እና ትኩረታቸውን ሰጥተው ነው።
ባይሳካላቸው ስህተቱን ሌላው ላይ በመፈለግ ጊዜያቸውን አያባክኑም።

5) አሸናፊዎች ተስፋ አይቆርጡም ተስፋ የህይወት ሁሉ እስትንፋስ ነው። ምንም እንኳን እኩል እድል ተሰጥቶን፤ በተመሳሳይ ሰዓት ፊሽካ ተነፍቶልን ጉዞ ብንጀምርም ብዙዎቻችን ተስፋ በመቁረጥ ከመንገድ ቀርተናል። ምንም እንኳን እሩጫው ቢከብድም ተስፋ በውስጣቸው የሰነቁ ሰዎች በቀላሉ ከመንገዳቸው አይገቱም።
ከላይ የተዘረዘሩት አምስት ነጥቦች ከብዙዎቹ የአሸናፊ
ሰው ባህሪዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ከብቶች አንድ አይነት ሳር ግጠው ፈንዳያቸው እንደሚለያይ ሁሉ፤ የሰው ልጆችም ተመሳሳይ እድል ተሰጥቷቸው የተለያየ ቦታ ይወድቃሉ። ምንም እንኳን ምክንያቶቹ ተዘርዝረው ባያልቁም፤ ከላይ የሰፈሩት አምስጥ ነጥቦች ግን አንኳሮቹ ናቸው፤ በእርግጠኝነት እራሳችንን እንድንፈትሽ ያደርጉናል።

(Mistre)
. . . #የመጨረሻ_ሰዓት . . .

በአንድ ወቅት አንድወጣት በአንድ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ሲሆን ከማንም እና ከምንም በላይ የሚወዳት ፍቅረኛ አለችው፡፡ ይህ ወጣት ከእለታት በአንዱ ቀን እጅግ ከፍተኛ ችግር ስላጋጠመው ለሁት ወር ፍቃድ እንዲሰጠው ከመስራ ቤት ጠይቆ ፍቃድ ወሰደ፡፡
ፍቃድ ካገኘበት እለት አንስቶ ልጁ እጅጉን ከሚያፈቀራት ልጅ ጋር ቀኑን ማሳለፍ ጀመረ፡፡ ይጫወታሉ ፣በየመዝናኛ ቦታ ይወስዳታል ፣በየመንገዱ ያዝላታል፡፡ ጎህ ሲቀድ የተገናኙ ጀምበር ስትጠልቅ ለመኝታ ብቻ ነው ሚለያዩት፡፡ የዚህንም ሰአት ቤቱዋ በር ድረስ አዝሎአት ነው የሚያደርሳት፡፡
እንዲህ እንዲህ እያሉ ሶስት ሳምንታትን በዚሁ የፍቅር መንፈስ አሳለፉ፡፡ በየቀኑ ድርጊታቸው ሁለቱም እጅጉን ደስተኛ ነበሩ፡፡ ሁለቱም ከማንኛውም ነገር እርቀው በራሳቸው የፍቅር ሀይቅ ውስጥ መዋኘት ጀምረዋል፡፡ ይህንን የተመለከቱት የልጁ ቤተሰቦች በድርጊቱ ኮነኑት፡፡ምንም ያህል ቢወዳት እንዲህ ሙሉ ግዜውን ሊሰጣት እንደማይገባ አጥብቀው ነገሩት፡፡ የስራ ባልደረቦቹም ሆኑ ጉዋደኞቹ በድርጊቱ ተቃውሞአቸውን አሰሙ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሁሉን ነገር በልኩ እንዲያደርግ ነገሩት፡፡ አዝሎ መዞር ፣ አጎንብሶ ጫማ ማሰር ስምህን እና ክብርህን ያጎድፍብሀል አሉት፡፡ እሱ ሊሰማ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡
ነገሩ በዚህ ቀጥሎ ወሬው የአለቃው ጆሮ ደረሰ፡፡ አለቃው እጅጉን ከመቆጣቱ የተነሳ ያለበት ድረስ ሄዶ ብቻውን አስቀምጦ ይቆጣው ጀመር፡፡ "በጣም ችግር አጋጥሞኝ ነው ብለህ ፍቃድ የጠየከኝ እንደዚ ለመንዘላዘል ነው!" ሲል አምባረቀበት፡፡ በዚህ ሰአት ልጁ በተረጋጋ አንደበት እንባ ያዘሉ አይኖቹን ወደ አለቃው ቀና አድርጎ እየተመለከተ እንዲህ አለው፡፡
" ሁላቹም ምታዩትን ትናገራላቹ፡፡ ስለምትናገሩት ነገር እርግጠኛ ናቹ፡፡ እርግጠኝነታቸ እውነት ስለመሆኑ ግን ራሳቹን አልጠየቃቹም፡፡ እናንተ እንደምታወሩት እየተንዘላዘልኩ አይደለም፡፡ እቺ ምታወሩባት ልጅ የልጅነት ፍቅረኛዬ ነች፡፡በፈጣሪ ፍቃድ ብዙ ነገሮችን አልፈን እዚህ ደርሰናል፡፡ እንደኛ ፍላጎት ቢሆንም ተጋብተን ወልደን አብረን እናረጃለን ብለን ነበር ሁሌም ምንፀልየው፡፡ አሁን ግን ያሰብነው ሀሳብ እዚህ ሊያበቃ ነው መሰለኝ፡፡ ፍቅረኛዬ የካንሰር ተጠቂ ሆናለች፡፡ ለመኖር ሁለት ወር ብቻ እንደሚቀራት ነው ሀኪም የነገራት፡፡ እነዚህን ሁለት ወራት ከእኔጋ ብቻ ነው ማሳለፍ ምትፈልገው፡፡ ለዛ ነው ሁለት ወር ፍቃድ ወስጄ ከእሷ ጋር ብቻ ሙሉ ግዜዬን ማሳልፈው፡፡ይሄ የፍቅሬ የመጨረሻዎቹ ቀናት ናቸው፡፡ ከሳምንታት ብሁላ መልሳ ላትመጣ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ትለየኛለች፡፡ እስከዛ ግን አይን አይኗን እያየው ከጎኑዋ መሆን አለብኝ፡፡ በዚ ሰአት ለሱዋ ያለዋት እኔ ነኝ፡፡ለኔ ያለችኝ እሷ ናት፡፡" ሲል በዛለ አንደበት ስለሁሉም ነገር አስረዳው፡፡
በመጨረሻም አንድ ጥያቄ አቀረበለት "አንተ በኔ ቦታ ብትሆን ምን ታደርግ ነበር?" አለቃው መልስ አጣ በይቅርታ ስሜት አንገቱን አቀረቀረ፡፡

በሰዎች ላይ ለመፍረድ እንቸኩላለን፡፡ እኔስ ብሆን ምን አደርግ ነበር? ብለን ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ እኔ ብሆን ምን አደርግ ነበር?

✍
ይህችን ታሪክ ተጋበዙልኝ።

የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ባንክ ገብተው “አንድም ሰው እንዳይንቀሳቀስ! ገንዘቡ የመንግሥት ነው፤ ህይወታችሁ ግን የእናንተ ነው” ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፡፡
ሁሉም ሰው ወለሉ ላይ በደረቱ ተኛ፡፡ ይኼ “Mind Changing Concept” ይባላል፤ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ የሰዎችን አስተሳሰብ መቀየር ነውና፡፡ ጠረጴዛ ላይ ተደፍታ የነበረች አንዲት ሴት የማጉረምረም ድምጽ ስታሰማ፣ ከዘራፊዎች አንዱ ቆጣ ብሎ፣ “እመቤት እንደሰለጠነ ሰው አስቢ እንጂ፡፡ ይህ እኮ ዘረፋ እንጂ አስገድዶ መድፈር አይደለም ” አላት፡፡ ፀጥ አለች፡፡ ይኼ “Being Professional” ነው፤ በሰለጠንክበት ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት ታደርጋለህና፡፡
ዘራፊዎቹ ያለምንም ችግር ቤታቸው ገቡ፡፡ ከዘራፊዎቹ መካከል ልጅ እግሩ እና የMaster of Business Administration ተመራቂው የተዘረፈው ገንዘቡ እንዲቆጠር ሃሳብ አቀረበ፡፡ ነገር ግን በዕድሜ ታላቅ የሆነውና እስከስድስተኛ ክፍል ብቻ የተማረው ዘራፊ፣ በቁጣ “አንተ የማትረባ ደደብ! ይህን ሁሉ ገንዘብ ማን ይቆጥራል? ዛሬ ማታ በቴሌቪዥን ዜና ላይ ስንት እንደዘረፍን ይነግሩናል፡፡” ይኼ “Experience” ይባላል፡፡ ዛሬ ዛሬ በትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት ይልቅ ‘ልምድ’ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡
ዘረፋው ከተፈፀመ በኋላ፣ የባንኩ ማናጀር የባንኩን ሱፐርቫይዘር ጠርቶ በአስቸኳይ ፖሊስ እንዲጠራ ነገረው፡፡ ሱፐርቫይዘሩ ግን፣ “ቆይ ተረጋጋ! እየውልህ፣ መጀመሪያ ከካዘና 10 ሚሊየን አንስተን ለራሳችን እንውሰድ፡፡ ከዚያም ባለፉት ወራት የወሰድነውን 70 ሚሊየን እንጨምርበት፡፡ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ያለብን ይህን ገንዘብ ዛሬ ከተዘረፈው ጋር ደምረን ነው” አለው፡፡ ይኼ “Swim with the tide” ይባላል፡፡ የተፈጠረን አስቸጋሪ ሁኔታ ለራስ ጥቅም ማዋል እንደማለት፡፡ ሱፐርቫይዘሩም አለ፣ “በየወሩ ዘረፋ ቢካሄድብን እንዴት መልካም ነበር!”
በሚቀጥለው ቀን፡፡ ከባንኩ የተዘረፈው ገንዘብ 100 ሚሊየን እንደሆነ በቴሌቪዥን ዜና ተነገረ፡፡ ዘራፊዎች ደነገጡ፤ የዘረፉትንም መቁጠር ጀመሩ፤ ማመን አቃታቸው፤ ደግመው ቆጠሩ፤ ያው ነው፡፡ ትንሽ ቆይተው እንደገና መቁጠር ጀመሩ፤ ተመሳሳይ መጠን – 20 ሚሊየን ብቻ! በጣም ተናደዱ፣ “እኛ ህይወታችንን ለአደጋ አጋልጠን 20 ሚሊየን ብቻ ስናገኝ፣ የባንክ ማናጀሩ ቁጭ ብሎ 80 ሚሊየን እንዴት ያገኛል?” ከንፈራቸውን ነከሱ፣ ጠረጴዛውን በቡጢ ነረቱ፡፡ ሌባ ከመሆን መማር ይሻላል ማለት ይህ አይደል?i (Africa’s elites are lords of poverty! ያለው ማን ነበር?)
የማናጀሩ ፊት በፈገግታ እንደ ማለዳ ፀሐይ አብረቅርቋል፤ የደስታ ግምጃ አድምቆታል፡፡ በሽርክና ገበያው የተፈጠረበት ጉድለት ተሞልቶለታልና፡፡ ይኼንን “Seizing the opportunity” ይሉታል፡፡ ዋነኞቹ ዘራፊዎች እነማን ናቸው? የሚል ጥያቄ ማስቀመጥ ፈልጌ የነበረ ቢሆንም ከወቅቱ ጋር ላይሄድ ይችላል ብዬ በማሰብ ትቼዋለሁ፡፡

#ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
በድሮ ጊዜ ንጉሡ ጠቢቡን ሰው ጠርተው ጥያቄ ይጠይቃሉ "የዚህ ዓለም ደስታ ምንድነው?"
ጠቢቡም ፦ "መብላት ፣መጠጣት መፍሳት" ብለው መለሱ ። በዚህ ንግግራቸው የተበሳጩት ንጉሥ ከቤተ መንግሥታቸው አስገፍትሩው እንዲያስወጡ አሸከሮቻቸውን አዘዙ በዚህ ጊዜ ጠቢቡ አንድ ነገር ብቻ እንዲናገሩ በመለመን ፍቃድ አገኙና ይህን አሉ "የተከበርከው ሱልጣን! የተናገርኩት እውነት መሆኑን ታውቅ ዘንድ ትበላለህ ፣ትጠጣለህ ግን አትፈሳም/አትፀዳዳም/" በማለት ረገሟቸው ።

አንድ ሳምንት አለፈ ። ንጉሡ ይበላሉ ይጠጣሉ የሚወጣ ነገር ግን የለም። ሆዳቸው ተነፋ ፣ ቁርጠት አላስተኛ ፣አላስቀምጥ አላቸውና ስቃያቸው ሲበረታ ሊቁን አስጠርተው" አጥፍቻለሁ ይቅርታ አድርጉልኝ "በማለት ሲጠየቁ "ይቅርታ የማደርግልህ መንግስትህን ስትሰጠኝ ብቻ ነው " አሉ ። ንጉሡም ከስቃያቸው አንፃር ምርጫ ስላጡ በቃላቸው አረጋገጡላቸው ። ጠቢቡም ሰው የንጉሡ ሆድ በእጃቸው ጠሰቁት ። ሡልጣኑም አንድ ጊዜ ፈስተው "እፎይ !"አሉ።
ያኔ " አላመንከኝም እንጂ አስቀድሜ ነግሬሃለው ። አሁን ግን መንግስትህን በፈስህ ለወጥክ" በማለት የመጀመሪያውን የጠቢብ ንግሥናን በዚያን ዕለት አገኙ ።
***
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንባብ ለህይወት
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏



“ዉድድርህ ከሰዎች ጋር አይደለም! ዉድድርህ:-

✓ ከገደልከዉ ሰአት

✓ ከፈጠርከዉ በሽታ

✓ መማር እያለብህ ችላ ካልከዉ እዉቀት

✓ መስዋእት ካረከዉ ጤናህ

✓ አዲስ ሃሳብን አልቀበልም ካልከዉ ማንነት

✓ ያንተን መጣር ከማይወዱ ሰዎች

✓ እድለ ቢስ እንደሆንክ ከሚነግርህ ሰይጣን ጋር ነዉ”


-ጀምስ አልሸር

🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌
አንድ ቀን አንድ ሽማግሌ ከልጁ ጋር በጫካ ውስጥ እየተንሸራሸሩ ሳሉ በድንገት አንድ ትንሽ ድመት በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ያያሉ። ድመቱ ከጉድጓዱ ለመውጣት እየተፍጨረጭረ ነበር። እና ሽማግሌው ድመቱ ከጉድጓዱ እንዲወጣ እጁን ሰጠው። ድመቱ ግን በፍርሃት እጁን ቧጨረ።

ሰውየውም በቡጭሪያው ህመም እየጮኸ እጁን ሰበሰበ ግን አላቆመም። ለድመቱ በድጋሚ እጁን ደጋግሞ ለመስጠት ሞከረ። አብሮት የነበረው ልጅ ትዕይንቱን እየተመለከተ በመገረም ጮኸ "በፈጣሪ ይሁንብህ አባዬ ይህንን ድመት መርዳት አቁም፤ ድመቱ እራሱን በራሱ ጊዜ ከዚያ ያወጣል" አለ። ልጅየው ስለድመቱ ደንታ አልነበረውም።

ሽማግሌው ግን ድመቱን ማዳን ቀጠለ፤ "ልጄ፤ እሱ እንዲቧጨር እና እንዲጎዳኝ የሚያደርገው የድመት ባሕርዩ ነው፤ እኔ ደግሞ መውደድ እና መንከባከብ ሰብአዊ ግዴታዬ ነው"
ብሎ በድጋሚ እጁን ለእርዳታ ዘረጋለት ድመቱ ባጨረው። እንዲህ እያሉ ከአድካሚ ሙከራዎች በኋላ በመጨረሻ ከጉድጓዱ አወጣው። እና ድመቱን ወደቤቱ ወስዶ የራሱ አደረገው።
*
ሞራል- በዙሪያዎ ያሉትን ሁሉ በራሳችሁ መልካም አመል አስተናግዱ እንጂ የሰዉን መጥፎ ባህርይ አትከተሉ። ያኔ ልታዩት የምትፈልጉት መልካምነት ሁሉ በዙሪያችሁ ይሆናል።
*
ለዚህ ታሪክ ተስማሚ ምሳሌያዊ ንግግር በኮሜንት ሳጥን ተዉልን
እናንብብ፣ እንወያይ ፣ነጻ እንውጣ