TIKVAH-ETHIO
709 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
የዩኒቨርሲቲ ምደባ !

በመቐለ ፣ አክሱም ፣ ዓዲግራት ፤ ራያ እንዲሁም ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ሲማሩ የነበሩና በፀጥታ ችግር ትምህርታቸውን መቀጠል ላልቻሉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ጊዜያዊ ምደባ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

ምደባውን በዚህ http://Placement.ethernet.edu.et መመልከት ይቻላል።

• ምደባዉ እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. የነበረዉን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን ጨርሰው የወጡት ተማሪዎችን ብቻ ይመለከታል፡፡

• ምደባዉ የተካሄደዉ መረጃዎችን በትክክል ላሰገቡ ተማሪዎች ሲሆን፣ በተጠየቀዉ መሰረት መረጃዎችን በትክክል ያላስገቡ ተማሪዎችና የኦን ላይን ፎርሙን በተለያየ ምክንያት በወቅቱ መሙላት ያልቻሉ ተማሪዎች ስማቸውን ኦንላይን ምደባ በሚረጋገጥበት ሶፍትዌር ላያገኙ ስለሚችሉ፣ በነበሩበት የትምህርት ክፍልና ዩኒቨርሲቲን መነሻ በማድረግ በዲፓርትመንት ስለተመደቡ፤ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።

• ተመዝግበው ሳይመደቡ የቀሩ ተማሪዎች በቂና ግልፅ መረጃ ያላቀረቡ መሆኑን በመገንዘብ ትምህርት ክፍላቸው የተመደበበትን ዩነቨርስቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።

• ያልተመዘገቡ እንዲሁም ቅሬታ ወይም አቤቱታ ያላቸው ተማሪዎች በቴሌግራም ቦት (@moeplacementbot) አቤቱታቸውን ማቅረብ ይችላሉ። ትምህርት ሚኒስቴር አቤቱታዎችን በአካል እንደማያስተናግድ በጥብቅ አሳስቧል።

• በዩኒቨርስቲዎች ተፈቅዶላቸው እረፍት (Withdrawal) ላይ የነበሩ ተማሪዎች የትምህርት ክፍላቸው ለተመደበበት ዩኒቨርስቲ ማስረጃቸውን አቅርበው የሚታይላቸዉ ይሆናል ተብሏል።

NB : ተማሪዎች የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ጥሪ ሲያደርግ ብቻ ነው በአካል ቀርበው ሪፖርት የሚያደርጉት።

#MoE

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA