Ethio Scholars Info
3.98K subscribers
282 photos
4 videos
17 files
108 links
Scholarships, call for papers, grants, projects, job vacancies, etc

For any comment @ethiolbot
Download Telegram
"ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም" ያለው የሜድስን ተማሪ ከሞት ተርፏል

እምሩ ሙስጠፋ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሜዲስን ተማሪ ሲሆን በማህበራዊ ትስስር ገፁ "ቤተሰቦቼን አደራ፣ እኔ ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም፣ እኔ መኖር እፈልጋለው መኖር ግን አልተፈቀደልኝም፣ ባልፈጠር ይሻለኝ ነበር ባልፈጠር እኔንም ቤተሰቤንም አላስቸግርም" በማለት ራሱን እንደሚያጠፋ ከገለፀ በኋላ በጓደኞቹ፣ በፖሊስ እና በዩኒቨርሲቲው ጥረት ራሱ ላይ ጉዳት ሳያደርስ ተይዟል። ቤተሰብ እስኪመጣ በነቀምት ከተማ ፖሊስ እንደሚቆይ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሃሰን ዩሱፍ (PHD) የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ገጠመኝ፦
ሰሞኑን ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ወሎ ደሴ ጎራ ብዬ ነበር፤ድሮ አስረኛ ክፍል የወደቀው ጓደኛዬን አገኘሁትና አንድ ሁለት እንበል ብሎ Golden Gate የሚባል ቅንጡ ሆቴል ውስጥ ይዞኝ ገባ፤ኑሮ እንደት ነው ስለው እኔ ጋር እጅግ በጣም አሪፍ ነው አለኝ አንተስ ጋር ሲለኝ ምንም አይልም ሶስተኛ ድግሪዬን (ፒኤችዲዬን) እየተማርኩ ነው ስለው ቤት ሰራህ? መኪና ገዛህ ወይ ሲለኝ ኸረ ቤትም አልሰራሁም፣መኪናም አልገዛሁም፣የሚከፈለኝ ወርሃዊ ደመወዝ እራሱ ወር እስከ ወር አድርሶኝ አያውቅም ስለው እጅግ በጣም አዝኖ እናንተ (ሌክቸረሮች ማለቱ ነው) አንደኛ ድግሪ፣ሁለተኛ ድግሪና ሶስተኛ ድግሪ እያላችሁ ትቆጥራላችሁ እኛ (ነጋዴዎች) ደግሞ አንድ ቤት፣ሁለት ቤት፣ሶስት ቤት፣አንድ ቦታ፣ሁለት ቦታ፣አንድ መኪና፣ሁለት መኪና፣ሶስት መኪና ወዘተ እያልን እንቆጥራለን አለኝ፤ለማንኛውም እኔ ሶስት መኪናና ሶስት መኖሪያ ቤት አለኝ ሲል አጫወተኝ፤የበላነውንና የጠጣነውን ወጭ ከፍሎ አይዞህ ነገ ሌላ ቀን ብሎ አፅናንቶኝ Golden Bus ትኬት በ 1030 ብር ቆርጦ፤ከደሴ ወደ አዲስ አበባ አሳፈረኝ።ድሮ የተማረ (መንግሥት ሰራተኛ) ከሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ አጠራቅሞ ቦታ ገዝቶ ቤት ሰርቶ ጥሩ ኑሮ ይኖር ነበር፤የአሁኑ መንግሥት ሰራተኛ ግን አይደለም ከደመወዙ አጠራቅሞ ቦታ ገዝቶ ቤት ሊሰራ ይቅርና የሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ ወር እስከ ወር በአግባቡ አያደርሰውም።ይሄን እያየ መጪው ትውልድ ለትምህርት ዋጋ ይሰጣል ማለት የማይታሰብ ነው።
ሙሳ ሙሃባ
ኢትዮጲያ ውስጥ ላለው ዋጋ ንረት የ200ብር ኖት በአንድ ወረቀት መታተሙ አባባሽ ምክንያት ሆኗል:-ኢኮኖሚስቶች

በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ የምትካለለዋ ማላዊ የ20ሚሊየን ህዝብ መኖሪያ ስትሆን ጠቅላላ ኢኮኖሚዋ 13ቢሊየን ዶላር ሲሆን ወደብ አልባ ድሃ ሀገር ነች፡፡ የማላዊ ኢኮኖሚ በ1993 የ50 እና የ100ብር የገንዘብ ኖት ካተመች በኋላ ከሁለት ዓመት በኋላ ማለትም በ1995 የ200ብር፤ ከስድስት ዓመት በኋላ ማለትም በ2001 የ500 ብር፤ በ2014 የ1,000ብር፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ማለትም በ2016 የ2,000ብር በመጨረሻ አሳድገው በ2022 የ5,000ብር ኖት (የማላዊ ገንዘብ ክዋቻ ይባላል) ገንዘብ አትማለች፡፡

የገንዘብ ኖት መጠን እያደገ የሚመጣው በተለያየ ምክንያት ቢሆንም ዋናው ግን የዋጋ ንረት ማደጉን ተከትሎ የገንዘብ የመግዛት አቅም ስለሚዳከም ለመከላከል ከማሰብ ይመነጫል! ነገር ግን የማላዊ የዋጋ ንረት ባለ 5,000ብር ኖት ከታተመ በኋላ ማለትም በ2021 ዋጋ ንረቱ 21ከመቶ የነበረው በ2023 ዋጋ ንረቱ ወደ 28.8ከመቶ አድጓል (የ5,000 ብር ኖት ከታተም ከ2 ዓመት በኋል)፡፡

በዓለም ላይ የገንዘብ ኖቶች መጠን እና የዋጋ ንረት ቀጥተኛ ግንኙኘት አላቸው የሚሉ ጥናቶች አሉ ከላይ በጠቀስናት ማላዊ በ2020 በተደረገ አንድ ጥናት ትልልቅ የገንዘብ ኖት እና የዋጋ ንረት (Higher Banknotes and Inflation in Malawi) በሚል ርዕስ በተሰራ ጥናት የተገኘው ውጤት "…. indicated strong evidence of a bi-directional relationship between inflation and higher banknotes as some of the denominations had a positive and significant impact on inflation":: ማለትም በማላዊ ትልልቅ የገንዘብ ኖት መኖራቸው ዋጋ ንረትን ጨምረውታል! የገንዘብ ለውጥ እና ዋጋ ንረት ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው የሚል ነው፡፡

ለምሳሌ፡- 2013 በኢትዮጲያ 200ብር ከመተዋወቁ በፊት ማለትም በ2012 የዋጋ ንረቱ 15.81ከመቶ የነበረ ሲሆን 200ብር በተዋወቀበት 2013 ዋጋ ንረቱ 20.36ከመቶ ደረሰ፤ በ2014 ዋጋ ንረቱ 26.84ከመቶ፤ በ2015 ዋጋ ንረቱ 33.9ከመቶ፤ በ2016 ዋጋ ንረቱ 28.7ከመቶ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ጥያቄው የዋጋ ንረቱ ላለፉት አራት ዓመታት እየጨመረ ለመጣው የዋጋ ንረት 200ብር መታተሙ አዎንታዊ ወይስ አሉታዊ ተጽኖ ነበረው የሚለው ነው? በርግጥ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ጥናት ይፈልጋል! (ጥሩ የጥናት ርዕስ በመሆኑ ተማሪዎች አስቡበት!)

የኢትዮጰያ ኢኮኖሚ ከ10ዓመታት በላይ ተከታታይ የዋጋ ንረት ጭማሪ ባህሪ ያለው ነው፡፡ ከፍተኛ የብር ኖት ባላቸው ሀገራት (በሺ ብሮችን በአንድ ኖት ያሳተሙ ማለት ነው!) የዋጋ ንረት ዝቅተኛ የሆነበትን ያህል ትልልቅ ያልሆነ የብር ኖት በአንድ ወረቀት ያሳተሙ እንዲሁም አብዛኛው ክፍያቸው ከወረቀት ገንዘብ ውጪ (ዲጂታል) ባደረጉ ሀገራት ከፍተኛ የዋጋ ንረት ሊኖር ይችላል፡፡

ትልቅ የብር ኖት በጥሬ ብር ለሚኖር ግብይት ቀላል መሆኑ ሰዎች እንደዝቅተኛ የቁሳቁስም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ ተመን አድርገው ለመውሰድ እንዲያስቡ ሊያደርግ ይችላል (ለምሳሌ፡- ሻጮች ወይም አገልግሎት አቅራቢዎች 180ብር ያለን ክፍያ በሳይኮሎጂካል ዋጋ ተመን ወደ ድፍን 200ብር የማጠጋጋት ባህሪ እንደመፍጠር ማለት ነው!)፡፡

ጠቅላላ ኢኮኖሚው ከታሰበ ትልቅ የብር ኖት ከመኖሩ በላይ የአቅርቦት ማነስ፤ የገንዘብ አቅርቦት ሚዛን ማደግ፤ ግጭት፤ የፍላጎት መጨመር፤ ከዓለም አቀፍ የገበያ ዋጋ ጫና፤ የገንዘብ የመግዛት አቅም ሁኔታ፤ የህዝብ ቁጥር በፍጥነት ማደግ፤ ወዘተ ከሚፈጥሩት ጋር ሲነጻጻር ጠንካራ ምክንያት አለው ለማለት ያስቸግራል፡፡
The Ethiopian Economist view
#Salary @ EBC
(Ethiopian Broadcasting Corporation with #Fake Degree)
ኢትዮጵያ በመኖሪያ ቤት ውድነት ከአፍሪካ ሁለተኛ ከዓለም ሶስተኛ ናት ተባለ

በዓለም ዙሪያ የኑሮ ደረጃዎችን የሚከታተለው ነምቤኦ የተባለ ድርጅት፤ በ2024 በአፍሪካ ሀገራት ያለውን የመኖሪያ ቤቶች ዋጋ ዝርዝር ይፋ አደርጓል።

ነምቤኦ ያወጣው ሪፖርት በየጊዜው ተለዋለዋጭ ሲሆን፤ሪፖርቱ የሀገራቱን ዜጎች ገቢ እና የመኖሪያ ቤቶችን ዋጋ ጥምርታን በማነጻጸር የተሰራ እንደሆነም አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ከአፍሪካ የመኖሪያ ቤት ዋጋ በጣም ውድ በመባል ካሜሮን 1ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፤ከዓለም 2ኛ ደረጃን ይዛለች፤የሀገሪቱ ዜጎች ለመኖሪያ ቤት የሚያወጡት ዋጋ ከሚያገኙት ገቢ 43.9 በመቶውን እንደሚሸፍንም ተመላክቷል።

በሪፖርቱ ኢትዮጵያ በመኖሪያ ቤት ዋጋ ውድነት ከአፍሪካ 2ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን የሀገሪቱ ዜጎች ለመኖሪያ ቤት የሚያወጡት ዋጋ ከሚያገኙት ገቢ 43.1 በመቶውን እንደሚሸፍንም ተመላክቷል።
የስራ ባህላችን ሲፈተሽ

አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር እንደነገረኝ ከሆነ ከ7 አመት በፊት ተጨማሪ ተጓዳኝ ስራ ልጀምር ብዬ ዲሽ መግጠም ጀመርኩ አለ።

ታዲያ በሰዓቱ የገጠመኝ ነገር ይገርማል አለኝ። ምን መሰለህ የስራ ባህላችን እጅግ መቀየር አለበት! የስራ ባልደረቦቼ ሳይቀሩ አንተ እኮ ይህን ስራ መስራት የለብህም ምን ሆነህ ነው ይሉኝ ነበር። ለአንተ ይሄ አይመጥንህም ተው አታሰድበን እስከ ማለት ደርሰውም ነበር።

አንድ ቀን ደግሞ እንዲሁ ተደውሎልኝ ስሄድ የተማሪዎቼ ቤት ኖሯል ከዚያማ ከላይ ወጥቼ እየሰራሁ ቲቹ ነው እኮ እየሰራ ያለው ደሞዙ አንሶት ነው አሁን ይህን የሚሰራ ሲሉ ሰማዋቸው።

ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰፈር የሚያውቀኝ ሰው አንተ መምህርም አይደለህ ለምንድን ነው ከአቧራ ጋር የምትታገለው አሁን የመምህር ደሞዝ አልበቃህ ብሎህ ነው ሲል የዲሽ ጥገናውን እንዳቆም አሳስቦኝ ነበር።

ብቻ ምን መሰለህ ትንሽ ስራ ስትጀምር የሚተችህ መብዛቱ አለኝ!

እና አሁን የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ከፍቼ ጥሩ የሚባል ስራ እየሰራሁ እገኛለሁ በመምህርነቱም እየሰራሁ ነው ። 

ያው እንደምታውቀው ቅርብ ጊዜ ኑሮው እጅግ በመናሩ ብዙ መምህራን ጓደኞቼ ሲቸገሩ አያለሁ እኔ ግን ብዙ ጫና ቻል አድርጌ በመስራቴ ኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም ችያለሁ ።

ሳጠቃልልህ የስራ ባህላችን በጣም መስተካከል አለበት። የሚሰራን ሰው ለማደናቀፍ  የሚደረጉ ብዙ ጥረቶች አሉ። ቢቻል ብናበረታታው ካልተቻለ ደግሞ ዝም ብን ሲል GA ሃሳቡን አጠቃሏል ።

እናንተስ ምን ትላላችሁ?

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የጅማ ዩኒቨርስቲ መምህሩ የ 2 ሚሊዮን ብር እድለኛ ሆኑ

የጅማ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አብዮት ታከለ በቆረጡት 20ኛው ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ2ኛው ዕጣ የ2,000,000 ብር ዕድለኛ መሆናቸዉን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

መምህር አብዮት የረዥም ጊዜ የሎተሪ ደንበኛ ሲሆኑ ደግመው ደጋግመው በላኩት ቴክስት በ2ኛው እጣ የ2 ሚሊዮን ብር እድለኛ አድርጓቸዋል፡፡

መምህሩ በደረሳቸውም ገንዘብ የቢዝነስ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ እንደሚሰማሩ ገልጸዋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
" ከቀን ወደ ቀን እየተበባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ለጤና ባለሙያዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል " - የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ፕሬዚዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ያነሰ ትኩረት ምክንያት ብዙዎች የሚወዱትን የሙያ ዘርፍ በመልቀቅ፣ በመቀየር እንዲሁም አገር ጥለው በመውጣት ላይ ይገኛሉ " ብለዋል።

እንዲህ የሆኑት ምን ያህል የጤና ባለሙያዎች ናቸው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ዮናታን፣ " በቁጥር ይህ ነው ብዬ ባልገልጽም በonline apply እያደረጉ ብዙ ጤና ባለሙያዎች፦
- ነርሶች፣
- ሀኪሞች፣
- ሚድዋይፎች፣
- ጤና መኮነኖች በተለያዩ መንገዶች አገር ጥለው እየወጡ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ወደ ፊላንድ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳ በህጋዊም በህገ ወጥም መንገድ ብዙ ጤና ባለሙያዎች ከአገር እየለቀቁ ነው። ብዙ የጤና ባለሙያዎች የህክምና ሙያቸውን ጥለው ወደ ንግድ እንዲሁም ወደ ተለያዩ ዘርፎች እየቀየሩ እንደሆነ ብዙ ተጨባጭ መረጃዎች አሉን። በየቀኑ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ቅሬታዎችን የምንቀበልበት አካሄድ አለን " ሲሉ አክለዋል።

“ ጤና ባለሙያዎች ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ወደ ዩንቨርስቲ የሚቀላቀሉ ቢሆኑም በተቃራኒው ግን በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች ሆነው ይገኛሉ " ነው ያሉት አቶ ዮናታን።
 
በሥራ ላይ ያሉትም፣ " ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ የመብት ጥያቄዎችን ለመንግሥት ቢያቀርቡም እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ አለመሰጠቱ በባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል " ያሉት የማኀበሩ ፕሬዚዳንት፣ ቅሬታዎቹን እንዲጠቅሱ ሲጠየቁም፣ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ የጤና ባለሙያዎች ለመንግሥት ያቀረቧቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች፦
* የደሞዝ ማሸሻያ፣ 
* የነፃ ህክምና፣
* የHouse allowance፣
* የRisk /ተጋለሠጭነት /
* የቤት፣
* የትርፍ ስሃት ክፍያ ጥያቄዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ " በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ የመብት ጥያቄዎችን ማቅረብ እንደ ነውር ሊታይ አይገባም። የሰላማዊ ድምፆች ሊደመጡ ይገባል " ብለዋል።

" ከቀን ወደ ቀን እየተበባሰ የሚገኘዉ የኑሮ ውድነት  ለጤና ባለሙያዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል" ብለው፣" መንግሥት በጤና ስርዓቱ ላይ የሚከተለውን ፓሊስ ቆም ብሎ ሊመረምረው ይገባል። የቱንም ያክል የዘመነ እና የረቀቀ የጤና ፓሊሲ ቢኖር ጤና ባለሙያዎችን መሠረት ያላደረገ ፓሊሲ ምንም ያክል እርቀት አይሄድም፣ የታቀደውንም ውጤት አያመጣም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

“ መሠረታዊ ፍላጎቱን ማሟላት የማይችል ጤና ባለሙያ ለታካሚዎች ተገቢዉን ህክምና ይሰጣል ብሎ ማሰብ በፍፁም አይቻልም። መንግስት በጤና ባለሙያዎች ላይ እየደረሱ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እና የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችን ችላ ከማለት ወጥቶ በአገር ላይ የከፋ ችግር ከማስከተላቸው በፊት መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ ጥሪን አቀርባለሁ ” በማለት አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ፤ " የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ችግሮች አሉ። የእኛም ማኀበር ይህን በተመለከተ በመግለጫ ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ ጠይቋል። ችግሩ ግን መፍትሄ አላገኘም አሁንም ብዙ ቅሬታዎች አሉ " ብለዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው።

tikvah
የሚዘርፉን ሰዎች እንደ አራዳ መቁጠርና ማድነቅ እየተለመደ ነው

ንግድ ባንክ በሌቦች ተጭበርብሮ፥ ወይም የኦንላይን ቅጽሩ ተሰብሮ ከሆነ ብዙ አይገርምም፤ እጅግ ታላላቅ የሚባሉ የአለም ተቋማት ሳይቀር እንዲህ አይነት አደጋ አጋጥሟቸው ያውቃል፤ እዚህ ሰፈር፥ ንቁ ዘበኛ ቢኖሮ እዚያ ማዶ ደግሞ የበለጠ ንቁ ሌባ ይኖራል፤ እያንዳንዱ ጽኑ በር ፥ ብርቱ መስበርያ አለው፤” ብርቅ አይደለም፤ ወደፊት በሌሎች ባንኮች ላይ ተመሳሳይ ነገር መፈጸሙ አይቀርም፤

በግሌ ያስገረመኝ ሌላ ነገር ነው፤
ስለዝርፍያው የተሰጠው ማህበራዊ ምላሽ እጅን ባፍ ብቻ ሳይሆን በጆሮም ያስጭናል፤ አብዛኛው ማህበራዊ ሚድያ ላይ ያለው መንፈስ ፥በቀልድም ቢሆን ሌቦችን የሚደግፍ ነው፤ ጨዋታ ቢሆንም የጨዋታው አቅጣጫ ያሳስባል፤ የሆነ ማህበራዊ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፤

የበሽታው መነሾ ምን ይሆን? የኔ ግምቶች እኒህ ናቸው፤
ሀ) “ ሰርቶ መብላት” የሚባለው ነገር ለብዙ ሰው ፥ለብዙ ሰው የትም የማያደርስ የዳገት መንገድ ሆኖበታል፤ ድሮ ‘ ያልሰራ አይብላ” የሚባል መፈክር ነበር፤ አሁን የሰራም የማይበላበት የኢኮኖሚ ጣቢያ ላይ ደርሰናል ፤ ለመኖር መስረቅ፥ ማጭበርበር ፥ መቆመር ወይም የሎተሪ እድለኛ መሆን ብቻ ነው የሚያዋጣው ‘ የሚል መንፈስ ነግሷል፤ ስለዚህ ውስጥ ውስጡን ፥ የሚዘርፉ ሰዎች እንደ አራዳ መቁጠር፥ ማድነቅ እየተለመደ ነው፤

ለ) ገዥዎችን እና ሀገረ መንግስትቱን ለያይቶ ማየት አለመቻል ሌላው ችግር ይመስለኛል ፤ ዋና ዋና የሀገር ተቋማትን እንደ ራስ መቁጠር እየቀረ ነው፤ ብዙዎቻችን፥ እኒህ ትልልቅ ተቋማት ቢወድሙ ወይም ቢዳከሙ ፥ የማታ የማታ፥ ጦሱ ለሁላችንም እንደሚተርፍ አናውቅም፤ ወይም ለማወቅ አንፈልግም፤

ሐ) የሕግ ተቋማት እና የጸጥታ ተቋማት ፥ የመንግስትን መዋቅር ተጠግተው የሚዘርፉ ሰዎችን ለመቅጣት ያላቸው ቸልተኝነት ወይም አቅመቢስነት ያሳስባል፤ መንግስት የሚደራጀው በዋናነት የዜጎችን ሕይወት እና በላባቸው ያፈሩትን ንብረት ለመጠበቅ ነው፤ አሁን አሁን፥ ኢትዮጵያ ፥ ትልልቅ ቀማኞች፥ እንኳን ቅጣት ግልምጫ ሳያገኛቸው፥ እንደ ልብ እየፋነኑ እሚኖሩባት አገር ሆናለች፤ ሕገ-ወጥነት አትራፊ ከሆነ ሁሉም የሕገ-ወጥነት ተቋዳሽ ለመሆን መጣሩ አይቀርም::
በእውቀቱ ስዩም

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
Do you enjoy reading this channel?

Perhaps you have thought about placing ads on it?

To do this, follow three simple steps:

1) Sign up: https://telega.io/c/ethio_lecturers
2) Top up the balance in a convenient way
3) Create an advertising post

If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለዘጠኝ ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ምሁራኑ በየመስኳቸው የነበራቸውን ልዩ አበርክቶ በመገምገም የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷቸዋል።

የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ምሁራን፦

1. ሙሉጌታ አድማሱ ደለለ (Bio Systems Engineering)
2. ታምራት ተስፋዬ ይመር (Biorefinery Engineering)
3. አስማማው ጣሰው ወልዴ (Animal Production)
4. መላኩ አለማየሁ ወርቄ (Horticulture)
5. የሻምበል መኩሪያው ቸከኮል (Animal Nutrition)
6. አቻምየለህ ጋሹ አዳም (Land Governance)
7. ምርኩዝ አበራ አድማሱ (Plant Pathology)
8. ታደሠ መለሠ መራዊ (Curriculum and Instruction)
9. አስራት ዳኘው ከልካይ (Curriculum and Instruction)

ቦርዱ የምሁራኑን የማስተማር ሥራ፣ የምርምር ተሳትፎ፣ የማህበረሰብ አገልግሎት እና በተቋማዊ ጉዳይ ያላቸውን አስተዋፆ በመገምገም የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማፅደቁን ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያሳያል።
አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 18 መምህራኑ እንደጠፉበት አስታወቀ

ጠፉ የተባሉት መምህራን የሶስተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን በመማር ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል:: ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ላይ ለነበሩ መምህራን ያላግባብ ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር እንደከፈለ እና ተመላሽ እንዳላደረገ ተገልጿል::

አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 18 መምህራኑ ደብዛቸው እንደጠፉበት አስታወቀ፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኦዲት ግኝት ሪፖርት ላይ መክሯል፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር  እና የዩኒቨርሲቲው አመራር አባላት በጋራ ባደረጉት ውይይት ላይ እንደተገለጸው ለሶስተኛ ድግሪ በሚል ለትምህርት የተላኩ እና የጠፉ የዩንቨርሲቲው መምህራን ጉዳይ ዋነኛው ነው፡፡

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ እና የፌደራል ዋና ኦዲተር አመራሮች ዩኒቨርሲቲው ለሶስተኛ ድግሪ ትምህርት ብሎ ስፖንሰር ሆኖ የላካቸው መምህራን በወቅቱ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዳልተመለሱ፣ ዩንቨርሲቲውም ለነዚህ መምህራን የከፈለውን ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር ገንዘብ ለምን ተመላሽ አላደረክም? በሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ 18 መምህራን ትምህርታቸውን በተቀመጠላቸው ጊዜ አጠናቀው እንዳልተመለሱ፣ የመመለሻ ጊዜያቸውም እንዳለፈ መናገራቸውን በምክር ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ በተላለፈው ላይ የቀጥታ ስርጭት ላይ ሲናገሩ ተደምጧል፡፡

በዩንቨርሲቲው ህግ መሰረት አንድ የዶክትሬት ወይም የሶስተኛ ድግሪ ትምህርትን ለማጠናቀቅ አራት ዓመት በቂ ሲሆን በተለያዩ አስቸጋሪ ምክንያቶች ትምህርቱን ማጠናቀቅ ላልቻሉ ደግሞ ሁለት ዓመት እንዲጨመርላቸው ይፈቅዳል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል፡፡

ይሁንና እነዚህ የዶክትሬት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተላኩ መምህራን መካከል ትምህርታቸውን በስድስት ዓመታት ውስጥ አጠናቀው ባለመምጣታቸው ከስራ መባረራቸው ተገልጿል፡፡
እነዚህ የቀድሞ የዩንቨርሲቲው መምህራን ከስራ በመባረራቸው ምክንያት ለትምህርት ስፖንሰር፣ ደመወዝ እና ትራንስፖርት ወጪ የወሰዱትን ገንዘብ ማስመለስ አለመቻሉን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ከ18ቱ ውስጥ አምስቱ ከሀገር ውጪ መሆናቸውን በማረጋገጣችን ዋሶቻቸው ላይ ክስ መስርተን ውሳኔው ለእኛ ተወስኖልናል ማስመለስ እንጀምራለን ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለውም 15ቱ ቀሪ የቀድሞ መምህራን ግን በሀገር ውስጥ እንዳሉ እና የትኛውም ተቋም እንዳልተቀጠሩ አረጋግጠናል ነገር ግን ከደመወዛቸው እና ስራቸው ስላገድናቸው ገንዘቡን ተመላሽ ማድረግ አልቻልንም ሲሉ ለጥያቄው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ #አልአይን

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዚህችን ግለሰብ ጉዳይ "ወደ ወሎ ዩኒቨርስቲ ደውዬ እውነታውን አጣርቻለው" በማለት የሰራው ዘገባ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ነው

ይህች እህት "ወሎ ዩኒቨርስቲ 12 አመት ልምድ አለኝ" አለች እንጂ ዩኒቨርስቲው አባረረኝ ወይም ከስራ ገበታ አፈናቀለኝ አላለችም፣ በማንኛውም ሁኔታ በተቋሙ ላይ ክስና አሉባልታ አላነሳችም።

በመቀጠል ወደ ዩኒቨርስቲው አንድ ኋላፊ ተደውሎ የዚህችን ሴት ችግር ያስረዳበት ቋንቋና በሚስጥር ሊጠበቅላት የሚገባ የግል ጉዳይ "የዐዕምሮ ታማሚ ነች" በመቀጠልም "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" እያለ ከአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የማይጠበቅ ቋንቋዎችን እየተጠቀመ ተቋሙን ባልከሰሰችበት ሁኔታ የግለሰቧን ሚስጥሮች ሲያዝረከርክ ነበር።

ዩኒቨርስቲው አስተማሪዋን ከስራ ሳትለቅ ህክምናዋን እየተከታተለች ከተቋሙ ጋር እንድትቀጥል ቢለምንም "ህመሜን ለመከታተል አዲስ አበባ በቅርብ ህክምናዬን ለመከታተል ይመቸኛል በማለት በአቋማቸው በመፅናታቸው መልቀቂያ ሰጥቶ እንዳሰናበታቸውም ዩኒቨርስቲው ገለፀ" ብሏል።

አንድን ተቋም 12 አመት ያገለገለችንና ስራ ማጣቷን ብቻ ገልፃ ትብብር የጠየቀችን ሴት በብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ "የአዕምሮ ታማሚ ነች" እና "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" የሚሉ መልዕክቶችን በ Fact Check ስም በአደባባይ ማስተላለፍ የተፈለገው የትኛውን ሃገራዊ መልካችንን ለመከላከል ነው?

አንድን ስራ ማጣቱን ብቻ ገልፆ ትብብር የጠየቀን ሰው ስም በአዕምሮ ህመምተኝነት እየፈረጁ እዝነት በሌላቸው ቃላቶቾ ለአደባባይ ሃሜት ማስጣትስ የግለሰቧን የጤና ሁኔታ አያባብስም ወይ?

ይህ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የወረደ ዘገባ እና የወሎ ዩኒቨርስቲ ሃላፊዎች መረን የቃላት አጠቃቀምና ባልተከሰሱበት ጉዳይ ራስን የመከላከል ጥድፊያ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም።

ይህች እህታችን የስራ ቦታቸውን ለመልቀቅ ያስገደዳቸውና እንደተባለውም የዐዕምሮ ህመም ገጥሟቸው ከሆነ ለህመማቸው መነሻና መባባስ የሆኑ ምክንያቶች ከዩኒቨርስቲው የስራ ከባቢ የተወለደ ቢሆንስ? የሸሹት ለጤናቸው ቢሆንስ?

ሚድያው የግለሰቧን መልሶች ሰምቶ ሚዛናዊ ዘገባ ከመስራት ይልቅ አስከፊ ሀገራዊ ሁኔታችንን ለመሸፈን በሚመስል መልኩ ሌላ የዘቀጠ ዘገባ መስራቱ እንደ ኢቲቪ ያሉ ተቋማት ያሉበትን ደረጃ የሚያሳዩ ናቸው።

ምንጭ: ሙሉቃል ቃል

እኔም እላለሁ፣ Fact Check ማለት አንድን አካል ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ ግለሰቧን፣ የህክምና ማስረጃ ካላት እሱን፣ የትምህርት ማስረጃዎቿን፣ ዩኒቨርስቲውን... በማናገር መረጃዎችን አመሳክሮ የሚሰራ እንጂ ግለሰቦችን ለማጥቃት ወይም የተቋማትን ስም ለመገንባት የሚከናወን ስራ አይደለም።

*ግለሰቧ የምትገኝበትን ስልክ ወይም አድራሻ የሚያውቅ ካለ በኮመንት ወይም ቴሌግራም ላይ @ContactElias ላኩልኝ።

@EliasMeseret
የሀገር መፍረስ ማለትኮ ይሄው ነው !

አንድ ሰው በድግሪ ተመርቆ ማስትሬቱን ይዞ የዶክትሬት ድግሪውን እየተማረና 12 አመት በዩኒቨርስቲ ሌክቸርነት ያሳለፈ ምሁር የሚበላው ምግብ የሚጠለልበት ቤት አጥቶ ጎዳና ላይ ከወደቀ ለልመና ከተጋለጠ ሀገር በትክክልም ፈርሳለች !

የህዝብ አገልጋዮችና ምሁራን ከስራቸው እየተባረሩ ይከፈላቸው የነበረው ደመወዝ ወደ ህንፃና ፓርክ መገንቢያ ዞሯል ።
ሀብታም የነበረው ፤ ምሁር የነበረው ደህና ኑሮ የነበረው ሁሉ በአስደንጋጭ ቅፅበት ወደ ለማኝነት እየወረደ ያለበትን አሳዛኝ ክስተት ለማየት በቅተናል ።

ታድያ መማር ምን ይሰራል የሚል ትውልድ ላይፈጠር ነው እንዴ ?
ሀገሪቱ በመሀይማን እጅ ገብታ የተማሩት ልጆቿን ካሰደደች ካወደመች ያች ሀገር ያልፈረሰቺው ለሚዘውሯትና ለሚገዟት ብቻ ነው !

ብቻ ህዝባችንን አላህ ይድረስለት 😢

Seid Social
መምህሯን ለማገዝ ለምትፈልጉ

ሙሉ ስሟ ፦ ትዝታ ገረመው ወልደ ሰማያት
ነዋሪነቷ ፦ አዲስ አበባ ገነት ጨፌ ሰፈር
የባንክ አካውንቷ ፦1000577632409 (ንግድ ባንክ)
ስልኳ፦ 0904819904

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
Ethiopia ranks 130th from 143 countries in World Happiness Report 2024

Ethiopia has been ranked 130th out of 143 countries in the World Happiness Report 2024. The report, which examines the happiness levels and well-being of nations across the globe, sheds light on the challenges faced by Ethiopia in fostering a happier society.

According to the report, Ethiopia’s ranking reflects the overall level of happiness and life satisfaction experienced by its citizens.

Factors contributing to Ethiopia’s ranking include social, economic, and political challenges that have affected the population’s happiness levels. Issues such as poverty, unemployment, limited access to quality healthcare and education, as well as political instability, have impacted the overall well-being of Ethiopians.

Source: Capital
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ጸደቀ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 3ኛ የሥራ ዘመን 19ኛ መደበኛ ስብሰባ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅን አጸደቀ።

በዛሬው ዕለት በሦስት ድምጽ ተአቅቦ ያለተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ የጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1320/2016 በምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ተስፋዬ በልጂጌ ማብራሪያ ሰጥተውበታል።
የመንግስት ዋና ተጠሪው በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እና ፍላጎት የተጣጣመ እንዳልሆነ ገልጸው በዚህ ሳቢያ ምክንያታዊ እና ፍትሃዊ ያልሆነ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪዎች በአገሪቱ ይስተዋላል ብለዋል።

ተስፋዬ በልጂጌ ለምክር ቤት አባላቱ እንዳስረዱት ነባራዊ ሁኔታው እና የዜጎች እሮሮ በመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ የመንግስት አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ አዋጅ ተዘጋጅቷል። የአዋጁ ዋና ዓላማ ግልጽና ተገማች የሆነ የመኖሪያ ቤት ኪራይ አስተዳደር መዘርጋት እንዲሁም የአከራይ እና ተከራይ መብትን ሚዛናዊ ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።

ስድስት ክፍሎችና 32 አንቀጾች አሉት። በውስጡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ፣ የአስፈጻሚ አካላት ስልጣን እና ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተካተቱበት ተገልጿል።

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ክፍል 2 አንቀጽ 8 ላይ የዋጋ ጭማሪን በተመለከተ ከዚህ በፊት አከራዮች በፍላጎታቸው የሚጨምሩትን ገንዘብ ተከራዮች በግዴታ መቀበል ቢኖርባቸውም፤ አሁን በመንግስት ተቆጣጣሪ አካል ጣልቃ ገብነት በዓመት አንድ ጊዜ የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታና የኢኮኖሚ ሁኔታ ታይቶ በመቶ በሚሰላ ጭማሪ ፈቃድ ብቻ የቤት ኪራይ እንደሚጨምር ተገልጿል።

በተጨማሪም የቤት አከራዮች ቅድመ ክፍያ መጠየቅ የሚችሉት የሁለት ወር ብቻ እንዲሆን የሚደነግግ ሲሆን ተከራዮችን ለማስለቀቅም የሁለት ወራት የዝግጅት ጊዜ እንዲሰጥ ያስገድዳል። ከዚህ ባለፈም መንግስት ማግኘት ያለበትን ግብር እንዲያገኝ እንደሚያስችል የምክር አባላት ተናግረዋል።

በአዋጁ ላያ አስተያየት የሰጡ የምክር ቤቱ አባላት አዋጁን ደግፈው ለብልሹ አሰራር ክፍት እንዳይሆን ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ አሳስበዋል። አዋጁ በተለምዶ ለአከራዮች ሰፊ እድልና መብት የሚሰጠውን ስርዓት ለማመጣጠን ያግዛልም ተብሏል።

ነምቤኦ (NUMBEO) የተባለ በሰርቢያ አገር መቀመጫውን ያደረገ የአገራትን የኑሮ ደረጃ የሚመዝኑ መረጃዎችን የሚያጋራ ድረ ገጽ የአገራቱን ዜጎች ገቢ እና የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጥምርታን በማነጻጸር ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያውያን ለመኖሪያ ቤት የሚያወጡት ዋጋ ከገቢያቸው ላይ 43 ነጥብ 1 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል። #አዲስ_ማለዳ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library