This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Alex Abreham (አቡቹ) በነገራችን ላይ...
መርታት፤ መረታት፤ መገገም
(በእውቀቱ ስዩም)
@AlexAberham
-------//------
የሆነ ጊዜ ላይ ረከቦት ጎዳና፤ ባንዱ ካፌ ውስጥ፤ ቡን ስጠጣ፤አንድ ጎረምሳ ወደ ተቀመጥኩበት መጣ፤ልጁ ግድንግድ ነው፤ጎልያድ
ዳዊትን አዝሎ ያክላል፤ እኔ ደሞ እንደምታውቁኝ ነኝ፤ከፊቴ ሲቀመጥ የሚጥሚጣ ብልቃጥ አከልኩ፤ ግብዳው ብዙ ሳይቆይ የምነት ክርክር
ጀመረ፤በተቻለኝ መጠን ወደ ክርክሩ ላለመግባት ተግደረደርኩ፤ ሰውየው ግን አልከራከርም ብለው ንቀኸኝ ነው ብሎ ሊደበድበኝ
ይችላል፤ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ የነደደ ክርክር ውስጥ ራሴን አገኘሁት፤ሰውየው አረፋ እየደፈቀ ተተጋተገኝ፤
ጎረርህ በሉኝ ብትፈልጉ ! አስር ቀቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ልጁን መፈናፈኛ አሳጣሁት፤ መግብዳው ክርክክራችንን ያሳረገው እንዲግ
በሚል ቃል ነው፤
"‘ ልታሳምነኝ አትድከም ! እገግምብሃለሁ”
አሁን ሳስበው፤ አስተምረዋለሁ ያልሁት ያ ግብዳ ሰውየ ትልቅ ቁምነገር አስተምሮኛል ፤ ባፍለኝነቴ ፤የሰው ልጆች ለሀቅ እና ለምክንያታዊነት
የሚኖሩና የሚሞቱ ይመስለኝ ነበር፤ሰዎች በውይይት የሚያምኑ ይመስለኝ ነበር፤ አዋቂ ባላዋቂ ላይ የሚበረታ፤፤ እውነት የያዘ ሰው
ሀሰተኛውን የሚረታ ይመስለኝ ነበር፤ እየኖርኩ ስሄድ ይሄ እምነቴ ጥሎኝ ሲመንን ታዘብኩት፤ አብዛኛው ሰው ለውነት ደንታ የለውም፤
አብዛኛው ሰው፤ ስለ እውቀት ስለተጨባጭ መረጃ ግድ አይሰጠውም፤ በተፈጥሮ ይሁን በልማድ እንጃ፤ አብዛኛው ሰው ችኮ መንቻኮ ነው፤
ልብ አድርቅ ነው፤ የውይይት አላማ ከላይ ከላይ የእውቀት ልውውጥ ቢመስልም ውስጥ ውስጡን መሸናነፍ ነው ፤ሽንፈት መራራ ፍሬ
በሚያስለቅምበት አገር ውስጥ ደሞ፤ ማንም መሸነፍ አይፈቅድም፤ ብታሸንፈው ተሸነፍኩ አይልህም፤ ተዘርሮም ይፎክርብሃል!
ይገግምብሃል!
ቀኛማች በላይነህ የተባሉ ባላባት በዳግማይ ምኒልክ ጊዜ ነበሩ፤በዘመናቸው፤ ከስራቸው ጋራ የማይመጣጠን አንጀባ ስለሚያበዙ " ቁንን
በላይነህ" የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቱዋቸው ነበር፤የሆነ ጊዜ ላይ ከሸገር ወደ ጎንደር ይሄዱና ባንድ ደብር ውስጥ ይስተናገዳሉ፤ቁንን
በላይነህ ፊደል ያልቆጠሩ ጨዋ ቢሆኑም በሊቃውንቱ ፊት የተማሩ ለምምሰል ተጋጋጡ፤ ዳዊት እየደገምኩ ነው ለማለት ዳዊት ገለጡ፤
ግን የማያውቁትን ዳዊት ገልብጠውት ነበር የያዙት፤
ይህንን የሾፈ አንድ ደብተራ ሳቁን በጋቢው ለመጨቆን እየሞከረ፤
“ጌቶች ዳዊቱን ዘቅዝቀው ነው የያዙት” ቢላቸው፤
))“ጠላቴን እንዲዘቀዝቅልኝ ብየ ነው! ጠፍቶኝ እንዳይመስልህ ” አሉት ይባላል፤
ቁንን በላይነህ አላዋቂ ናቸው፤ግን አላዋቂነታቸውን አምነው ማረም አይፈልጉም፤ ማንን ደሰ ይበለው ብለው!?ተሸንፈው፤አሸናፊ መስለው
ቆመዋል! ገግመዋል!
ታዋቂው የታሪክ ፀሀፊ ተክለፃድቅ መኩርያ በግለታሪካቸው ላይ አንዲት ገጠመኝ ጠቅሰዋል፤ ገጠመኚቱን በኔ አማርኛ ሸክሽኬ ሳቀርባት
ይቺን ትመስላለች፤ የሃይለስላሴ ባለስልጣኖች በደርግ ወጣት መኮንኖች እየተለቀሙ በሚታጎሩበት ቀውጢ ወቅት ፤ ሁለት ወጣት
ታጣቂዎች ተክለፃድቅ ቤት ድረስ ይመጡና በቁጥጥር ስር ያውሉዋቸዋል፤ በገዛ መኪናቸው፤ይዘዋቸው በሚሄዱበት ጊዜ አንዱ ታጣቂ
ለጉዋደኛው_-_
“ከተማ ይፍሩ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት አስር ሚሊዮን ብር በኪሱ ተገኘ” ይላል፤(ከተማ ይፍሩ የዘመኑ ባለስልጣን ነው)
“ይሄን የሚያክል ገንዘብ በኪስ ሊያዝ አይችልም” አሉ ተማራኪው ተክለፃድቅ፤
“ባይኔ በብረቱ ያየሁትን” አለ ወታደሩ፤
“ይህን ጊዜ” ይላሉ ተክለፃድቅ መኩርያ “ ይህን ጊዜ ዝም አልኩ፤”
ዝም ባይሉ ኖሮስ?
ታጣቂው ይገግማል!
ጠመንጃውም ያስገመግማል፤
አስከሬን ይለቀማል
እና ይሄ ማን ይጠቀማል?
አንዳንዴ በፌስቡክ ማለቂያ አልባ ክርክር ውስጥ ዘልየ ለመግባት ሲቃጣኝ እኒህን ነገሮች አስታውሳለሁ፤አንዳንዴ ዝም አልክ ማለት
እውነቱን ከመናገር ተቆጠብክ ማለት አይደለም፤ሃይልህን ቆጠብክ፤ሰላምህን ቆጠብክ፤ ህይወትህን ቆጠብክ ማለት ነው፤

Forwarded from የኢትዮጵያ ዪንቨርስቲ ተማሪዎች(Ethio campus students)
😘አንድ ግዜ ካምፓስ ውስጥ ረብሻ ተፈጥሮ ፌደራሎች ተማሪውን አፍሰው አንድ ቦታ አስቀምጠዋቸው ሳለ....ለይዋቸው ተባለ።
ፌደራሉ፦ እናንተ ምንድናቹ?
ተማሪዎቹ፦ Mechanical department
ፌደራሉ፦ በሉ Mechanical በዚ Department በዚ ሁኑ😂😛😜
@ethio_campuss_infoz
@ethio_campuss_infoz
@ethio_campuss_infoz
@ethio_campuss_infoz
ፌደራሉ፦ እናንተ ምንድናቹ?
ተማሪዎቹ፦ Mechanical department
ፌደራሉ፦ በሉ Mechanical በዚ Department በዚ ሁኑ😂😛😜
@ethio_campuss_infoz
@ethio_campuss_infoz
@ethio_campuss_infoz
@ethio_campuss_infoz
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌀 @ethio_campuss_infoz 🌀
ተፈጥሮ ለሰው ልጅ በጣም አዳልታለች ብዬ አስባለው። የትኛው ነፍስ ያለው ፍጡር ነው፤ እራሱን መቀየር የሚችለው? ሰው ብቻ!!!
🌀ዛሬ የቆምንበትን ቦታ ካልወደድነው፤ ዛሬ የተጎናጸፍነውን ማንነት ካልተደሰትንበት፤ ሀ ብለን መጀመር ሰው በመሆናችን ብቻ የተሰጠን ትልቅ ፀጋ ነው። ማህበረሰብ ወይም ቤተሰብ ፅፎ የሰጠንን ታሪክ ካልወደድነው፤ ገፁን ገንጥለን የገዛ ታሪካችንን ማስፈር እኮ……ሰው በመሆናችን ብቻ የታደልነው በረከት ነው። በስህተቶቻችን ውስጥ ፤ ባለማወቀችን ውስጥ የምንመኘውን ማንነት ፈልገን ማግኘት አንችልም።
🌀ይልቁንም በንፁህ አይምሮ……ማንነታችን ማነፅ፤ መፍጠር እንችላለን። በረከታችንን እንጠቀምበት!!!
ብዙ የሚወዱን ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሃሳባችን በቅጡ የማይገባቸው፤ የልባችን ትርታ በስርዓቱ የማይሰማቸው ከሆነ ፍቅራቸው እኛን ደግፎ የማቆም አቅም አይኖረውም…..
📘ፍቅር ከመረዳዳት ጋር ሲጣመር ምን ያህል ደስ ይላል
🌀🌀🌀🌀🌀🌀🌀🌀🌀🌀
ሼር እና ላይክ እንዳይረሳ
ይቀላቀሉን 👇👇👇

በመላው ሀገራችን የምትገኙ የ2011 ዓ.ም ተመራቂዎች በሙሉ እንኳን ለዚህች የምረቃ ቀን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን!!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Alex Abreham (አቡቹ) በነገራችን ላይ...
‹‹ኢትዮጲያ የቃል ኪዳን አገር ናት አትፈርስም ?››
(አሌክስ አብረሃም)
@AlexAberham
--------//---------
በእግዚአብሔር መኖር አምናለሁ! በሂደትም ይሁን በተዓምር የወደደውን እንደሚያደርግ አምናለሁ ! የህዝቡን ፆለት እንደሚሰማም
አምናለሁ! ሁሉንም የሚያደርገው ግን በሰዎች ፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ እንጅ በሃይልና በማስገደድ እንዳልሆነ ቃሉ ራሱ ይናገራል !
ለምሳሌ አታመንዝር ይልሃል አይ እኔ አመነዝራለሁ እንዳላመነዝር ከፈለክ በተዓምር ከልክለኝ ማለት የጅል ሃሳብ ነው ! እግዚአብሔር
አእምህን ተጠቅመህ ድጋፉንም ለምነህ ሃፂያት እንዳትሰራ ይመክራል የገስፃል እንጅ አንተ በሄድክበት እየተከተለ የሱሪህ ዚፕ እንዳይሰራ
አድርጎ አንተን ሲያስቆም አይኖርም !
አትግደል ይልሃል አንተ ልትገድል መሳሪያ ደግነህ እንዳልገድል ከፈለክ ቃታውን ስስብ ጥይቱን አክሽፈው አይነት ቁማር ውስጥ ከገባህ ጅል
ሃሳብ ነው! ‹‹ኢትዮጲያ የቃል ኪዳን አገር ናት አትፈርስም ›› በሚል ብሂል እንደፈለኩ እሆናለሁ ማለት ራስህን ማጥፋት ነው! የቃል ኪዳን
አገር ኢትዮጲያ ሚሊየኖችን በእርሃብ ተነጥቃለች …ለተረፈው እንጅ ለሞተው ቃልኪዳኑ አልሰራም ማለት ነው ? ወይስ የሞቱት ከተረፉት
በላይ ሃፂያተኞች ነበሩ ? የቃል ኪዳን አገር ኢትዮጲያ ብዙ መቶ ሽሆችን በአንባገነኖች ጥይት ፣በእርስ በርስ ጦርነት ተነጥቃለች … ለምን
ቃልኪዳኑ ከዛ ጥፋት አልጠበቀንም ?
አሁንም ቢሆን አገራችን በአለም ላይ በአሰቃቂ ድህነት ርሃብና ስደት ስማቸው ከሚጠሩ አገራት ተርታ ናት …በቃል ኪዳን አገር ነብስ
የማያውቁ ህፃናት በታይፎይድና በምግብ እጥረት አሁንም ይረግፋሉ !የት ሄደ ቃል ኪዳኑ? እንኳን እግዚአብሔር አንድ ሃብታም ቃል
የገባለት ህዝብ እንኳን የሚበላውና የሚለብሰው አያጣም ! ምናልባት (((የገዛ ሃፂያታችን ነው መዓት ያመጣብን)))) እንዳይባል
‹‹እግዚአብሔር የለም›› ከማለት ጀምሮ ለጆሮ የሚቀፍ ስንት ጉድ ሃጢያት እንደአገር የሚፈፀምባቸው አገራት በጥጋብና በተድላ በሰላምና
በብልፅግና ሲኖሩ ታያለህ …እንደውም ‹‹ለአማኙ ርሃብተኛ ›› ምግብ ሲረዱ ሁሉ ታያለህ !
እንግዲህ ጉዳዩ ከቃል ኪዳኑ ሳይሆን ቃል ከተገባለት ህዝብ መሆኑን እንረዳለን ….ህዝቡ በቃልም በድርጊትም አገሩን እያፈረሰ ‹‹የቃል
ኪዳን አገር ናት አትፈርስም›› በሚል ብሂል ላላግጥ ካለ …ቃል ኪዳን በቃል ሰጩ ሳይሆን በቃል ተቀባዩ ፈቃድ መፍረሱ ሳይታለም የተፈታ
ነው … መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ያለ ምሳሌ … ኢስራኤል ከግብፅ ባርነት እንዲወጣና ወደተስፋዋ ምድር እንደሚገባ ቃል ተገባለት… ቃሉን
አምኖ ወጣ ግን እግዚአብሔር ቃሉን ቢጠብቅም ህዝቡ በመንገዱ ቃልኪዳኑን ሲያፈርስና ሲያመቻምች ከግብፅ ከወጣው ትውልድ
ትገባለህ የተባለበት ምድር የገባው ሰው በጣት የሚቆጠር ብቻ ነበር !! ‹‹ቃል ኪዳን የተገባልኝ ህዝብ›› እያለ ያሻውን ሲሰራ የነበረው
ትውልድ በበርሃ ተንጠባጥቦ አለቀ !
አሁንም አገራችን ‹‹የቃል ኪዳን አገር ›› ተብላለች ለምንል ለኛ እግዚአብሔር ከድንጋይና ከዛፍ ከአፈርና ተራራ ጋር አይደለም ቃል ኪዳን
የሚገባው ….ከሰው ጋር ነው ! ከአንተ ጋር ከአንች ጋር ….ህዝብ አገሩን በአፉም በድርጊቱም እያፈረሰ ‹‹ቃልኪዳን አለን አንፈርስም›› እያለ
ቢኮፈስ ራሱን ፍርስራሽ ላይ ከማግኘት አይተርፍም !! ቃልኪዳን ካለህ ቃልኪዳንህ እጅህ ላይ እንዳለ ብርጭቆ ነው ….ይፈፀም ዘንድ
ተጠንቅቀህ ተራመድ !! ብርጭቆህን ቁልቁል እየወረወርክ ‹‹ቃል አለኝ አይሰበርም ›› ካልክ … ጅል ነህ!! ክፉነት ብቻ ሳይሆን ጅልነትም
ከክፋት እኩል ዋጋ ያስከፍላል !!

ሰላም የቻናላችን አባላት ወቅቱ የእረፍት በመሆኑ የተለያዩ ልቦለዶችን እንዲሁም ትረካ ወደናንተ ለማድረስ ዝግጅታችንን አጠናቀናል::
https://t.me/joinchat/AAAAAFCmPK7Bw5MIv32LFw

አብራቹን ስለሆናቹ እናመሰግናለን::