Ethio 251 Media
44.6K subscribers
1.08K photos
708 videos
7 files
1.83K links
ETHIO 251 is an independent media offering you News, Political Analysis and Information feeds. መረጃ ለማድረስ :- @Ethio251MediaInfo
Download Telegram
ሰበር የድል ዜና!

በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በነጎድጓድ ክፍለ ጦር በአንበሳው ብርጌድ በነብሮ ሻለቃ በተደረገ የደፈጣ ውጎያ በጎሸባዶ ከተማ የስርዓቱ አስጠባቂ ሰራዊት  ላይ እርምጃ ተወሰደ።

   የስርዓቱ አስጠባቂ ቀይ ቦኔት ለባሽ ኮማንዶ በባለ አንድ ጋቢና ቶዮታ መኪና ከደብረ ብርሃን ጎሸባዶ ከተማ ድረስ  እየተመላለሰ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ አሰሳ እና ቅኝት ሲያደርግ  የነበረን ተሽከርካሪ የነብሮ ሻለቃ ደፈጣ በማድረግ ጎሸባዶ ከተማ ጫፍ ላይ ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ እርምጃ በመውሰድ 4 ባለ ቀይ ቦኔት ኮማንዶ የስርዓት አስጠባቂውን ሃይል እስከወዲያኛው ሲሸኙ 6ቱ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል። ሲጠቀሙባት የነበረችው ተሽከርካሪም ተመታ ከጥቅም ዉጪ ሆናለች።

  በተያዘ ዜና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር  አንበሳው ብርጌድ በፊት አውራሪ ገበየሁ ሻለቃ በተደረገ ልዩ ኦፕሬሽን በደብረብረሃን የስርዓቱ አስጠባቂ ሰራዊት ካምፕ ላይ እርምጃ ተወሰደ።

በ፶/አለቃ ይለፍ የምትመራዋ ፊት አውራሪ ገበየሁ ሻለቃ በደብረብረሃን ከተማ በጋራ ድንቁ የስርዓቱ አስጠባቂ ሰራዊት ካምፕ  ላይ በለሊት እርምጃ በመውሰድ በርካታ ሰራዊቱን ሙት እና ቁስለኛ አድርገው ልዩ የኦፕሬሽን ስራ ሰርተው  ፋኖዎች ከከተማው  ቢወጡም በካምፑ የገቡት የስርዓቱ ጠባቂ የመከላከያ ሃይሎች  በተቀያሪ አዲስ የገቡ በመሆናቸው ተደናግጠው እርስ በእርሳቸውም እንደተመታቱ በቦታው የነበረ መረጃ አድራሻችን አሳውቆናል።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ
ሚያዚያ 3 ቀን 2016 ዓ·ም
https://t.me/ethio251media
በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የፋኖ ኦፕሬሽን የመራው ጀግና ፋኖ ሻለቃ ናሁሰናይ አንዳርጌ❗️

በሻለቃ ናሁሰናይ አንዳርጌ መሪነት በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት እና ሚሊኒዮም አዳራሽ አካባቢ በአገዛዙ ላይ የመጀመሪያው ጥይት ተኩሷል፤ ለፋኖ ቀዳሚ የሆነውን ኦፕሬሽ በአዲስ አበባ ከተማ በመምራት የትግሉን ምዕራፍ ከፍ አድርጎታል።

ፋኖ ሻለቃ ናሁሰናይ እና በስሩ የነበሩ ጓዶቹ በዚህ ኦፕሬሽን በበርካታ የአገዛዙ ሠራዊት ላይ እርምጃ ወስደዋል፤  ጀግናው ሻለቃ ናሁሰናይ ጥይት በመጨረሱ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ሰውቷል።

የኦፕሬሽኑ ዋና ዓላማ አዲስ አበባ ላይ በአገዛዙ ሠራዊት ላይ እርምጃ ወስዶ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የትግል ፊሽካ መንፋት ነበር። ዓላማው ተሳክቷል!!

ከኦፕሬሽኑ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ አማራን ታርጌት በማድረግ የጅምላ እስር ዘመቻ ተጀምሯል ይህን የጅምላ አፈሳ እየመራ ያለው  ምክትል ኮሚሽነር ሐሰን ነጋሽ የተባለ የኦህዴድ ሰው ነው (ፎቶው ኮመንት ባር ላይ ይገኛል)

ፋኖ ናሁሰናይ አንዳርጌ በሰሜኑ ጦርነት የቤት መኪናውን ሽጦ ስናይፐር በመግዛት የአማራን ሕዝብ ከጥቃት የተከላከለ፣ በጦርነቱም በርካታ ጀብዱዎቹን የሰራ ወጣት ጀግና ታጋይ ነው።

ሻለቃ ናሁሰናይ አንደኛ ዓመቱን ሊያስቆጥር ጥቂት ወራት በቀሩት የአማራ ሕልውና ጦርነት የአማራ ፋኖ በጎንደር የአጼዎቹ ክፍለጦር አመራር በመሆን በጎንደር ቀጠና በርካታ ጀብዱዎቹን ፈጽሟል።

በዚህ ልዩ  ኦፕሬሽን አዲስ አበባ ላይ ቀጣዩ ትግል ምን መልክ ሊኖረው ይገባል የሚለውን ወሳኝ ጥያቄ ምላሽ ሰጥቶበታል።

አዲስ አበባ ውስጥ በየቤቱ የተቀመጠ  መሳሪያ ፋኖ በሚያቅደው ሰርጅካል ኦፕሬሽን መሠረት ጥቅም ላይ የሚውልበት ጊዜው ደርሷል!!

ሻለቃ ናሁሰናይ በአባቶቹ በነ አፄ ዳዊት ከተማ በክብር በጀግንነት ተሰውቷል‼️

አዲስ አበባ ላይ በዓይነቱ ልዩ የሆነው የትግሉ ፊሽካ ተነፍቷል‼️

ሁሉም በያለበት በተጠንቀቅ ይጠብቅ‼️
ለኢትዮ 251 ሚዲያ በደረሰው የውስጥ መረጃ መሰረት፦

ሚያዚያ 4/2016 ጀግናው ፋኖ ሻለቃ ናሁሰናይ አንዳርጌ በአዲስ አበባ ከመራው ኦፕሬሽን በኋላ (ምሳ ሰዓት ላይ) የፀጥታ እና ግብረ ኃይል ቡድን የሚባለው የዐቢይ አሕመድ የአፋና ስብስብ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።

በስብሰባው የተነሱ የግምገማ ነጥቦች፦

=> የአዲስ አበባ ሕዝብ የፋኖ ደጋፊ ሆኗል
=> ከተማው ከእጃችን እየወጣ ነው
=> ፋኖ በውስን የሰው ኃይል ከተማውን መረበሽ
ከቻለ ነገ የማንቋቋመው ሁኔታ ሊያጋጥመን
ይችላል ፣
=> የውስጥ አርበኞች የስርዓቱ ፈተና ሆነዋል፣
=> ፋኖ ውስጣችን ውስጥ ገብቷል …ወዘተ የሚሉ የግምገማ ነጥቦች ተነስተዋል።

በዚህ አስቸኳይ ውይይቱ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፦

1) በአምስቱም የአዲስ አበባ መግቢያ እና
መውጫ በሮች የፍተሻ ኬላዎች (check
points) እንዲጠናከሩ፣

2) የሪፐብሊካን ጋርድ የመረጃ ክንፍ የከተማዋን መረጃ በሙሉ በመሰብሰብ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ምሽት ላይ ሪፖርት እንዲያደርግ፣

3) በተመረጡ አካባቢዎች የቤት ለቤት ፍተሻዎች እንዲጠናከሩ፣

4) በአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የሚንቀሳቀሱ መኪኖች እንዲፈተሹ (ከምሽት 12:00 ጀምሮ)፣

5) ከዚህ ቀደም ታርጌት የተደረጉ ሰዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ፣

6) በአዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶች በሁኔታው እንዳይደናገጡ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ብሪፍ እንዲያደርግ፣

ወዘተ የሚሉ ውሳኔዎች ተላልፈዋል።

በዚህ ውሳኔ መሠረት፦

ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀረበት (በኢትዮጵያ ሠዓት 9:30) ድረስ 86 ንጹሃን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

እጅግ የሚያሳዝነው ነገር ቤተክርስቲያን ውስጥ በማስቀደስ ላይ ያሉ ምዕመናን ሳይቀር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የአማራ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ፣ እና ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የፌዴራልና የከተማው ፖሊሶች ላይ ክትትል እንዲጠናከር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከስምሪት ውጭ የማድረግ አቅጣጫ ተቀምጧል።

አገዛዙ አዲስ አበባ ላይ የተነፋው የትግል ፊሽካ አስደንግጦታል፤ ቢሆንም የተነቃነቀ ጥርሱ መነቀሉ አይቀሬ ነው!!

ፋኖ ሻለቃ ናሁሰናይ አንዳርጌ የአማራ ህልውና ትግልን ወደአዲስ ምዕራፍ አሳድጎታል። የዛሬው ኦፕሬሽን ትግሉ ከአማራ ክልል ለመውጣቱ አስረጅ ማሳያ ነው።

ዘመቻ ናሁሰናይ በአዲስ አበባ በቅርብ ቀን በረቀቀ መንገድ ይከሰታል … 💪
ተጨማሪ ሰበር መረጃ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ደርሷል።

ከጀግናው ፋኖ ሻለቃ ናሁሰናይ አንዳርጌ ኦፕሬሽን በኋላ የፀጥታ እና ግብረ ኃይል ቡድን የሚባለው የዐቢይ አሕመድ የአፋና ስብስብ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጦ እንደነበርና በስብሰባው ያነሳቸውን የግምገማ ነጥቦችና የውሳኔ ሀሳቦች ከሰዓታት በፊት ማሳወቃችን ይታወሳል።

አሁን ማምሻውን በደረሰን ተጨማሪ መረጃ በዐቢይ አሕመድ ትዕዛዝ የብልጽግና ፓርቲ ከመካከለኛ አመራሩ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ አመራሩ ድረስ ወደውጭ አገር መውጣት ታግዷል።

ትዕዛዙ ለኢሜግሬሽን የተላለፈ ሲሆን፤ ያለ ዐቢይ አሕመድ ፍቃድ የትኛውም ባለሥልጣን ከአገር እንዳይወጣ እገዳው ከዛሬ ሚያዚያ 04/2016 ምሽት ጀምሮ ተፈፃሚ እንደሚሆን የውስጥ መረጃ ምንጮቻችን አድርሰውናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ ምሽት አዲስ አበባ ውጥረት ነግሷል። የአገዛዙ ባለሥልጣናት "የደህንነት ሰጋት አለብን" በሚል ለደህንነት መስሪያ ቤቱ የሚደውለው በዝቷል።

የአካል ጠባቂዎቻቸውን እና የመኖሪያ ቤት የዙሪያ ጥበቃወቻቸውን ሰልክ እንዲፈቸሹላቸውና እንዲቀየሩላቸው የጠየቁ ከፍተኛ አመራሮች አሉ።

በፌዴራል ፖሊስ የተመደቡላቸውን ጠባቂዎቻቸውን ማመን ያልቻሉ የብልጽግና ባለስልጣናት በሪፐብሊካን ጋርድ ብቻ እንጠበቅ የሚል ጥያቄ በማቅረብ ላይ ናቸው።

በአምስቱም የአዲስ አበባ በሮች መኪኖች ቁመዋን ልዩ የፍተሻ ኦፕሬሽን ተጀምሯል።

(ተጨማሪ መረጃዎችን እየተከታተል እናቀርባለን)


https://t.me/ethio251media
የፍፃሜው መጀመሪያ ዓይን ገላጩ ኦፕሬሽን
***

የአማራ ፋኖ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት እና የአማራ ፋኖ በጎንደር የአጼዎቹ ክፍለ ጦር በጋራ ቅንጅት የሰሩት የዛሬው የአዲስ አበባ ኦፕሬሽን ትግሉ አማራ ተብሎ ከተከለለው አጥር በመውጣት ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት አድማሳዊ ትግል ለመጀመሩ ማሳያ ነው።

የሁለቱ ጠቅላይ ግዛት ፋኖዎች የጋራ ኦፕሬሽን የፋኖ ታክቲካል ጥምረት ወደስትራቴጂያዊ የማጥቃት ስልት እያደገ ለመሆኑ ተጨማሪ ማሳያ ነው። 

በአራቱም ግዛቶች ያሉ ሰባቱም የአማራ ፋኖ ዕዞች ወታደራዊ ውህደት በመፈፀም ወደአንድ የመጡ ቀን አራት ኪሎ በእጃቸው እንደሚገባ፣ ከአማራ አልፎ መላ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ከተረኛው አገዛዝ ቀንበር ነጻ እንደሚወጡ ርግጥ ነው። 

የሸዋ እና የጎንደር ፋኖዎች ዓይን ገላጭ የሆነ ኦፕሬሽን በማድረግ በውስን የሰውና የመረጃ ኃይል መሀል አዲስ አበባ አገዛዙን አሸንተውታል። ይህን ኦፕሬሽን በተመለከተም የአማራ ፋኖ በጎንደር አስተዳደር ኃላፊና የአጼዎቹ ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ሰለሞን አጣናውና የአማራ ፋኖ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ቃል አቀባይ ፋኖ አበበ ሙላቱ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጸዋል።

አስራ ሰባት ዓመት የትጥቅ ትግል ያደረገው፣ ከሽምቅ ውጊያ ተነስቶ አገር ተቆጣጥሮ 27 ዓመት የገዛውና በየደረጃው የፖለቲካና ወታደራዊ ልሂቃንን ያፈራው ወያኔ በ2013-2014 ውጊያ  ደብረሲና ድረስ መጥቶ እንኳ አዲስ አበባ ላይ አንዲት ጥይት ለመተኮስ አልተቻለውም።

ብሶት የወለደው መገፋት ወደትግል ሜዳው ያወጣው የአማራ ፋኖ አንድ ዓመት ባልሞላ የትጥቅ ትግል ጉዞው፣ ያውም ጅምር እንጅ ወጥነት ያለው አደረጃጀት በሌለበት የትግል አውድ  ንስሮቹ የአማራ ፋኖዎች በአባታቸው አፄ ዳዊት ከተማ የፍፃሜው መጀመሪያ ዓይን ገላጩን የትግል ታሪክ ጽፈዋል።

አጠቃላይ የአማራ ፋኖ ብቻ ሳይሆን ሚሊዮኖች የአዲስ አበባ ወጣቶች የነፃነት ፈለጋቸውን ይከተላሉ የፋኖ ቅንጅታዊ ኦፕሬሽን ይቀጥላል…

https://t.me/ethio251media

(የአማራ ፋኖ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ቃል አቀባይ ስለ ኦፕሬሽኑ የሰጠው ማብራሪያ ከስር ተያይዟል)
የአማራ ፋኖ በጎንደር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር። ከ April 1:00 PM EAST ይጀምራል። ሁላችሁም ትሳተፉ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Forwarded from Ethio 251 Media
ከኢትዮ 251 ሚዲያ የቀረበ ጥሪ!

ኢትዮ 251 ሚዲያ ላለፉት አራት ዓመታት የዐቢይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋና ግፍ እየተከታተለ በመዘገብ የህዝብ ልሳን ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ሚዲያው በሚያቀርባቸው መረጃዎች አገዛዙን በማጋለጡ፤ አገዛዙ ሚዲያውን በመዝረፍ፣ ጋዜጠኞችን በማሳደድ እንዲሁም በተደጋጋሚ እና በተደራጀ መልኩ ቻናሎቹን እያዘጋበት ይገኛል፡፡

በዚህ የተነሳም የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የዘር ማጥፋት ጦርነት ሰሚ እንዳያገኝ የአገዛዙ ፍላጎትና እቅድ ቢሆንም፤ ኢትዮ 251 ሚዲያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም ለህዝብ ድምጽ በመሆን የአገዛዙን ገመና ያለማቋረጥ እያጋለጠ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን ጦርነት ለመመከትና ህልውናውን ለማስጠበቅ የሚዲያው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ኢትዮ 251 ሚዲያም ይህንን ኃላፊነቱን በመረዳት ባለሙያዎች በመጠናከርና በሁሉም ቀጠናዎች ዘጋቢዎችን በመመደብ እየሠራ ይገኛል፡፡ ይህ ጥረቱም የአገዛዙን ገመና ከማጋለጥም በተጨማሪ፤ የፋኖን እያንዳንዱን የትግል ውሎና ጀብዱ በመዘገብና ሰንዶ በመያዝ ላይ ነው፡፡

ይህን ጥረቱን በተጠናከረ መልኩ እንዲያከናውን የፋይናንስ ድጋፍ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡

ስለሆነም ኢትዮ 251 ሚዲያን በዚህ የጎፈንድሚ አካውንት በመደገፍ የአማራን ህዝብ ትግል ይደግፉ ስንል በአክብሮት ጥሪ እናቀርብለዎታለን፡፡

ኢትዮ 251 ሚዲያ!!

https://gofund.me/a2d99937
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ አበባ ላይ ምንም የሚፈጠር ነገር የለም ብለው ፕሮፓጋንዳ ነው ሲሉ ከርመው ጭናቸውን ተቆንጥጠው ደንግጠዋል። የአዲስ አበባው ፋኖ ኦፕሬሽን አገዛዙን ፈትኖታል። ትኩረታቸው ስልጣናቸው ላይ ብቻ ስለሆነ የደሕንነት ስጋት አለብን የሚሉ አቤቱታዎች በዝተዋል። አጃቢዎቻችን ይገምገሙልን ብለዋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
1) የፋኖ ናሁሰናይ አንዳርጌ እናት ወ/ሮ ሐረገወይን አዱኛ

2) የፋኖ አቢኔዘር ጋሻው እናት ወ/ሮ ኤልሳ ሰለሞን

ሁለቱም ከጎንደር መጥተው የተሰው ልጆቻቸውን አስክሬን አንሰጥም ተብለዋል።

አስክሬን ለመጠየቅ የሄዱ ቤተሰቦች ታስረዋል!
***

አንድ ሰው በየትኛውም የጦር ሜዳም ሆነ የግጭት ሁኔታ ሕይወቱ ካለፈ በኋላ አስከሬኑ ክብር አለው።
ዓለም ዓቀፍ የጦር ሕጎችም ይህንኑ ያሰገድዳሉ።

የዐቢይ አሕመዱ ፋሽስታዊ አገዛዝ ግን በአስከሬን ላይም የበቀል እርምጃ ይወስዳል።

አስከሬን ያገተው ነውረኛ ቡድን ቢያንስ ለእናቶች ሲል የጀግኖቻችን አካል ሊለቅ ይገባል!!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል የጀግኖቹ አካል በክብር ሊያርፍ ይገባል!!

https://t.me/ethio251media
የአማራ ሕዝብ ደመኛ ጠላቶቹን አምርሮ በመታገል
ዘላቂ ነጻነቱን ሊያረጋግጥ ይገባል!

(ከምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ)

ባለፉት ሃምሳ ዓመታት አማራን የመስበር ፖለቲካ በሰፊው ተሰርቶበታል፡፡ በዚህም አማራን በሕዝብ ብዛት ቁመቱን መቀነስ፣ በግዛት ወሰን ግዛቱን መቀማት፣ በኢኮኖሚያዊ አቅም ጥሪቱን በውረስና በመዝረፍ፣ በአገር ግንባታ ተሳትፎ ሂደት ከማግለል አልፎ አጠቃላይ ሕዝባዊ አቅሙን በመምታት አማራ ለማጥፋት ከሁለት ትውልዶች በላይ ተሰርቶበታል፡፡

ይህን ለዘመናት የቀጠለ የጥፋት ፕሮጀክ ለሰላሳ ሦስት ዓመታት በውክልና ያስቀጠለው ብአዴን፣ አማራን ለመስበር በተደረጉ ጥረቶች ሁሉ ቀዳሚው ተዋናይ ሆኖ የሕዝባችን ደመኛ ጠላት መሆኑን ደጋግሞ አሳይቶናል፡፡

ትላንት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) አገልጋይ፤ ዛሬ ደግሞ የኦሕዴድ ብልጽግና አሽከር ሆኖ አማራን የመስበር የጥፋት ፕሮጀክት አስፈጻሚ ሆኖ የቀጠለው ብአዴን፣ የአማራ ሕዝብ በከፈለው መስዋዕትነት ያስመለሳቸው ግዛቶቹን ከጠላቶቹ ጋር በዓይን ጥቅሻ በመግባባት ለዳግም ባርነት አሳልፎ እየሰጠው ይገኛል፡፡

ለሰላሳ ዓመታት በትሕነግ ወረራ ስር የነበሩት ራያ፣ ኦፍላ ኮረም፣ ወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት ነጻ የወጡ ታሪካዊ የአማራ ርስቶች ቢሆኑም በኦሕዴድ ብልጽግና ፍላጎት፣ ለቅኝ ገዥው ትሕነግ ዳግም አሳልፎ እየሰጠ ያለው የአማራ ሕዝብ የምንግዜም ጠላት የሆነው ብአዴን-ብልጽግና ነው፡፡

ይህን ለማስፈጸም በሰሜኑ ጦርነት ባለውለታ የነበሩ አደረጃጀቶችና ተቋማትን የመበተንና የማፈራረስ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ መቼውንም ቢሆን ታሪክ የማይዘነጋው ጀብዱ የፈጸመውን የአማራ ልዩ ኃይል በከንቱ ያፈረሰው፣ የአማራ ሕዝብ መዳኛ መስመር የሆነው የአማራ ፋኖ ላይ የብልጽግና ጦር ያዘመተው፣ የአማራ ተቆርቋሪዎችን በአካል፣ በሥነ-ልቦናና በኢኮኖሚ የማድቀቅ ዘመቻ፣ ወዘተ የተከፈተው አማራን ለመስበር ጊዜው አሁን ነው በሚል እምነት ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ በመቀልበስ ህልውናውን ለማስከበር ቆራጥ ተጋድሎ ማድረጉን ተክትሎ፣ አገዛዙ ተፍረክርኮ ሊወድቅ ጫፍ ላይ ደርሷል፡፡ አማራ በተጋድሎው ሊሰብሩት ያሰቡትን እንደጎመን እየቀነጠሰ፣ እንደአረም እየነቀለ፣ እንደቆሻሻ ከመንገዱ እያጸዳ ወደማይቀረው የድሉ ጫፍ በሚገሰግስበት በዚህ የታሪክ መታጠፊያ ምዕራፍ ላይ ከኋላው ለማስወጋት ራያና አካባቢው በትሕነግ ወራሪ ዳግም እንዲወረር ተደርጓል፡፡

ባለፈው መጋቢት 19/2016 በአበርገሌ ፃታ፣ ኮረም እና በራያ አላማጣ ቀበሌዎች ጨጓራ ኮሲም፣ ማሮ፣ዓዲ እደጋ የሚገኘው ህዝባችን የዐቢይ አሕመድ ሠራዊት ድጋፍ ባለው መልኩ በትሕነግ ታጣቂዎች ዘረፋ፣ ግድያና ወረራ ሲፈጸም መንግሥት ተብየው ያደረገው አንዳች ነገር አልነበረም፡፡

በመቀጠል መጋቢት 20/2016 በአዲስ መልክ ራያ ባላ ወረዳ ቀበሌዎች ውስጥ ዶዶታ፣ ማሩ፣ ዳርአይታ፣ ባሶ፣ ጦርነት ሲከፍት በመተሳሳይ ሁኔታ የብልጽግና ሠራዊት የሽፋን ድጋፍ ሰጥቶታል፡፡ ይህ ቅንጅታቸው እያደገ መጥቶ ሚያዚያ 6 እና 7 የራያ አላማጣ አማራ ግዛት ላይ ዳግም ወረራ ፈጽሟል፡፡ ትሕነግ ይህን ወረራ የፈጸመው በዐቢይ አሕመድ ፍቃድ፣ በብአዴን ታዛዥነት እንደሆነ የምስራቅ አማራ ፋኖ ያምናል፡፡

የምስራቅ አማራ ፋኖ ከዚህ ቀደም ከትሕነግ ጋር በተደረገው ጦርነት ከፊት ተሰልፎ በከፈለው መስዋዕትነት ዕዙ በተሰማራበት ቀጠና ያለው ራያ እና ኮረም ቀጠና ነጻ እንዲወጡ የአንበሳውን ድርሻ ወስዷል፡፡ ዛሬም የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት ኦህዴድ ብልጽግና በከፈተው ጦርነት ከሌሎች ወንድም የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር በመናበብ የህልውና ትግሉን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጅ የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል የማይቀለበስ ደረጃ መድረሱን ተከትሎ ከጀርባችን እንድንወጋ ከታሪክ የማይማረውን ትሕነግ ለዳግም ወረራ ራያና አካባቢውን እንዲወር ተደርጓል፡፡
እንደምስራቅ አማራ ፋኖ በአማራ እና በትግራይ ሕዝብ መካከል ዳግም ወደግጭት ላለመግባት ከፍተኛ ጥንቃቄ ስናደርግ ቆይተናል፤ አሁንም ጥንቃቄ ማድረጋችንን እንቀጥላለን፡፡ ይሁን እንጅ በትሕነግ ተደጋጋሚ የስሌት ስህተት የራያ አማራ ሕዝባችን ለዳግም ባርነት ተላልፎ እንዲሰጥ አንፈቅድም፡፡

በመሆኑም፡-
የራያ አማራ ህዝብ የመጥፋት አደጋ ውስጥ መሆኑን እንድትረዱ እያሳሰብን ታሪካዊ የትግል ጥሪያችንን እንደሚከተለው እናስተላለፋለን፡-

1) የአማራ ሕዝብ በብአዴን መሪነት የሚመጣ ውርደት እንጅ ነጻነት የሌለ መሆኑን ካወቀ ውሎ አድሯል፡፡ ይሁን እንጅ በዋና ዋና ከተሞች የሚታየው መዘናጋት ዋጋ የሚያስከፍለን በመሆኑ ዘላቂ ነጻነቱን ለማረጋገጥ ፍጹም መራራ ትግል በማድረግ ትግሉን ማቀጣጠል አለበት፡፡ የአማራ ሕዝብ በመስዋዕትነቱ ወደእናት ግዛቶቹ የመለሳቸውን እነ ራያ ወልቃይትን አሳልፎ እየሰጠ ያለውን ብአዴን፣ ገጠር ከተማ ሳይል የፈራረሰ መዋቅሩን ጨርሶ ግብዓተ መሬት ለማስገባት ሁሉም በያለበት እንዲፈንን (ፋኖ እንዲሆን) የትግል ጥሪያችንን እናቀርባለን!

2) የትግራይ ሕዝብ ከአማራ ሕዝብ ጋር እስከመጨረሻው ድረስ ደም ከመቃባት ይልቅ ሁኔታዎችን ቆም ብሎ እንዲመለከት ጥሪያችንን እያቀረብን፣ ሁልግዜም ቢሆን መሬት ላይ ያሉ ሁኔታዎችን የመገምገም ችግር ያለበት፣ በዚህ የስሌት ስህተት የተከበረውን የትግራይን ሕዝብ ዋጋ እያስከፈለ ያለው ትሕነግ የጀመረው የወረራ እንቅስቃሴ በጊዜ ካልተገታ ውሎ አድሮ የትግራይን ሕዝብ የበዛ ዋጋ እንደሚያስከፍለው አውቆ ድርጅቱ ከዚህ ራስን የማጥፋት ተግባር እንዲታቀብ እያሳሰብን የተከበረው የትግራይ ሕዝብ ከፍትሐዊው የአማራ ሕዝብ ትግል ጎን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን! በዚህ አጋጣሚ በቀደመው ጦርነት የተፈጠረውን ሁለተናዊ ቀውስ መፍታት የሚያስችል፣ የሕዝብ ለሕዝብ መተማመኖችን የሚያሳድር ነገን አሻግሮ የሚመለከት የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የመፍትሄ ሀሳቦችን መጠቆም ከአማራ እና ከትግራይ ልሂቃን እንደሚጠበቅ ማሳሰብ እንወዳለን፤

3) የአማራ ሕዝብ የገባበት የህልውና ጦርነት ተገዶ ስለመሆኑ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰወረ አይደለም፡፡ የአማራ ሕዝብ የጅምላ ግድያና መፈናቀል የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥት ህልውናን አደጋ ውስጥ የሚከት ብሔራዊ የደህንነት አደጋ መሆኑን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተግባር እያየው ነው፡፡ ይህን ብሔራዊ አደጋ ለመቀልበስ የምናደርገውን ፍትሐዊ ትግል በመደገፍ መላው ኢትዮጵያዊያን ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን!

4) በአገዛዙ መዋቅር በተለይም በጸጥታና ደህንነት ውስጥ ያላችሁ የአማራ ተወላጆችና የአማራ ትግል አጋር የሆናችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ ከዚህ የደም ግብር ከለመደ፣ ጦርነትን የሥልጣኑ ማስቀጠያ ካደረገ አገዛዝ ነጻ ወጥታችሁ ሕዝባዊ ትግላችንን እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን! ከትላንት ምሽት ጀምሮ ዘጠኝ መቶ ሰባ የሚሆን የራያና አካባቢው ሚሊሻዎች የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝን የተቀላቀሉ ሲሆን፤ ይህን አርዓያ በመከተል በፌዴራል፣ በክልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ ያሉ የጸጥታና ደህንነት አካላት በሕዝብ ትግል እየተቀበረ ያለውን አገዛዝ ጥላችሁ ሕዝባዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን!!
5) በሁሉም ቀጠና የምትገኙ ወንድም የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች እና አባላት የጀመርነው የህልውና ተጋድሎ በአጭር ግዜ ፍሬማ ሆኗል፡፡ በዚህ ትርጉም በሚሰጥ መስዋዕትነታችን የአገዛዙን መዋቅር በመናድ ነጻ መሬት መፍጠር ተችሏል፤ ሆኖም ግን ትግሉ ከዚህ በመረረ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ በመሆኑም ከበባ ውስጥ የገባው የአማራ ሕዝብ ከበባውን በመስበር ዘላቂ ነጻነቱን ለማስከበር ከየአቅጣጫ የተከፈተውን አማራዊ ጥቃት በአንድነት ለመመከት ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት በመቆም ለበለጠ ግዳጅ ዝግጁ እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባልን!

6) ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የትህነግን ወረራ በማውገዝ አካባቢው ወደማያባራ ቀውስ እንዳይገባ አስፈላጊውን ክትትል እንዲታደርጉ ይህንንም የአማራ ዲያስፖራ እንደተለመደው የትግሉ አካል አድርጎ ሁኔታዎችን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እንዲያስረዳ የትግል ጥሪያችንን እናቀርባለን!!

ሕጋዊና ፍትሐዊ የማንነት ትግል የትም ቦታ ተሸንፎ አያውቅም!

የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ
ምስራቅ-አማራ
ሚያዚያ 08 ቀን 2016 ዓ.ም.