Ethio 251 Media
48.5K subscribers
2.13K photos
1.12K videos
8 files
2.52K links
ETHIO 251 is an independent media offering you News, Political Analysis and Information feeds. መረጃ ለማድረስ :- @Ethio251MediaInfo
Download Telegram
የአማራው በቤቱ በቀየው መፈናቀል!

በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ ጃሂማላ ቀበሌ ብልፅግና መራሹ ጨፍጫፊ ሰራዊት የአካባቢውን ነዋሪዎች ከቤት ንብረት አፈናቅሎ የትንሳኤ በአልን ጨምሮ ውሎ አዳራቸው ዛፍ ስር እንዲሆን አድርጓል።

የአካባቢው ማህበረሰብ አሁንም ለረሃብ፣ ለስቃይና እንግልት እየተዳረገ ይገኛል በዚህ መፈናቀል ውስጥ አረጋዉያን፣ ነፍሰ ጡር እናቶችና ህፃናትም ይገኙበታል።

አማራ መዳኛው ክንዱ ነው፣ የአማራው ሰቆቃ የሚቆመው፣ ፍትህ የሚሰፍነው ይህን ጨፍጫፊ ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስከወዲያኛው ስናስወግደው ይሆናል አለቀ!!

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
ዘመቻ አንድነት ወሎ ቤተ- አማራ ግንባር

አማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክ/ጦር ትናንት ሚያዚያ 12/2017 ዓ.ም ምሽት ቦርቦር ከተባለ ቦታ ታፍኖ የነበረውን የአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ምሽግ ድረስ ከበባ በማስገባት አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ በርካታዉን በመደምሰስ ገሚሱን ቁስለኛ አድርጎ ታላቅ ድል ተጎናጽፏል::

መብረቆቹ ከላይ በያጌ እና ሸመኔ ከታች ጊንዶ ጐራንዳ በመቁረጥ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያደቁት ውለው ካደሩ በኋላ እግሬ አውጭኝ ብሎ በታፈነበት ቦታ የሞቱበትን በርካታ አስከሬን በወጉ ሳይቀበር ለአራዊት ጥሎ ቁስለኛውን ጭኖ እግሬ አውጭኝ ብሎ የወጣ ሲሆን ከትላንት ምሽት አስካሁን ባለው ኦፕሬሽንና ተጋድሎ በጠላት ላይ የደረሰ ጉዳት :-
ያጌ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ የቀበራቸው 6
ቦርቦር ተብሎ ከመሚጠራው ቦታ የቀበራቸው 9
ወግዲ ሆስፒታል ገብተው የሞቱ እና ለሚ በር ከሚባለው ቦታ የተቀበሩ 7
በድምሩ = 22 ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት የተደመሰሰ
እና 9 አንቡላንስ ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ጭኖ ወጥቷል:: በተጨማሪም ጠላት ከቱሉ አውሊያ ተጨማሪ ሃይል ይዞ ለመግባት እየሞከረ ይገኛል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ በዘመቻ አንድነት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ዘመቻ አንድነት!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ)
ሚያዚያ 13/2017 ዓ.ም
ፋሽስቱ አገዛዝ ቆቦ ከተማ አገልግሎት ፅ/ቤትን በእሳት ሙሉ ለሙሉ አውድሞታል::

በሰሜን ወሎ ዞን የቆቦ ከተማ አገልግሎት ፅ/ቤት ትናትና ሚያዚያ 13/2017 ዓ.ም ምሽት ሆን ተብሎ በእሳት ሙሉ ለሙሉ ወድሟል::

በክልሉ ከፍተኛ ብልፅግና መር የመሬት ወረራ ዘመቻ ቁንጮ ላይ የሚገኘው ቆቦ ከተማ በጥቂት የፋሽስቱ አገዛዝ ሹማምንቶች ህገወጥ ደላላዎችና ይሄ ጊዜ አያልፍምና አይነጋም በመሰላቸው ባለ ሃብቶች ቅንጅት የተዘረፈዉን የህዝብ ሃብት እንዳይታወቅ በሚል መረጃ ለማጥፋት ፅ/ቤቱን ሙሉ ለሙሉ አውድመዉታል::

ስለሆነም የህዝብ ሃብት ተዘርፎ ተድበስብሶና ተዳፍኖ የሚቀርበት ሁኔታ እንደሌለና ጊዜዉን ጠብቆ የህዝብ ሃብት ለህዝብ መሆኑ እንደማይቀር እየገለፅን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) ይህንን ጉዳይ በጥልቀት በመመርመርና በማጣራት ፀረ-ህዝብ የሆኑ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ለህዝብ ማሳወቅና መግለፅ እንወዳለን::

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ)
ሚያዚያ 14/2017 ዓ.ም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአማራ ፋኖ በጎጃም የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ እሸቱ ጌትነት ይናገራል፣ ያድምጡት!

https://t.me/ethio251media
ሰበር ዜና
1: ሀዲስ አለማየሁ 7ኛ ክፍለጦር!

የአማራ ፋኖ በጎጃም የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክፍለ ጦር ድል ቀንቶታል። አዋበል መብረቁ ብርጌድ: አነደድ ተድላ ጓሉ ብርጌድ እና የቦቅላ አባይ ብርጌድ በጋራ በመሆን ሉማሜ ከተማ ገብተው ጠላትን መግቢያ መውጫ ሲያሳጡት አርፍደዋል። ማርያም ሰፈር፣ ሚካኤል ሰፈር እና ሉማሜ ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት ውጊያ የተደረገ ሲሆን 48 የጠላት በመደምሰስ፣ 23ቱን ከባድ ቁስለኛ በማድረግ፣ 8ቱን በመማረክ እና መሳሪያ በመማረክ ታሪክ ተሰርቷል። የሉማሜ ከተማ ምንሻ ፅ/ቤት እና ፓሊስ ጣቢያ የቦንብ ጥቃት አድርሰውበታል።

አገዛዙ ሲጠቀሙበት የነበረ በርካታ ላፕቶፕ መማረክ ተችሏል።

ከየትኖራ ወደ ሉማሜ ለድጋፍ የተንቀሳቀሰን 1 ካሶኒ ሙሉ የአብይ አሽከር ዘሪሁን13 በመጠቀም ማውደም ተችሏል። መቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን፣ በመቶ አለቃ ገረመው አጋዥ እና በክፍለጦሩ እንቁ መሪዎች የተመራው ይህ ዘመቻ በታሰበው ልክ ውጤታማ ነበር።

2 በላይ ዘለቀ 8ኛ ክፍለጦር ፣

የአብይ አህመድ ሰራዊት አስር መኪና ይዞ ወደ ኦናርጅ እናውጋ ወረዳ ገደብ ቀበሌ የገባ ቢሆንም መጋቢት14/2017ዓ.ም ከምሽቱ 1:30 የፋኖ ሀይሎችን አባሪሪያለሁ ብሎ ከገደብ ከተማ ተነስቶ ወደ ደብረ-ወርቅ ከተማ በመሄድ ላይ ያለው የአገዛዙን ሀይል ሶማ ብርጌድ ቡሽት ኮኛ ቀበሌ ላይ በደፍጣ አንድ ኦባማ የጫነ የጠላት ሀይ በቦንብ እና የጥይት በረዶ በማዝነብ ወንፊት አድረገውታል።

የጠላት ሀይል የድሻቃ ማት እየተኮሰ ጉዞውን አቋርጦ አድሯል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ

[የአማራ ፋኖ በጎጃም]
ሚያዚያ 15/2017 ዓ.ም
ዘመቻ አንድነት ወሎ ቤተ-አማራ ግንባር

ተጠናክሮ በቀጠለው ዘመቻ አንድነት በዛሬው ዕለት ማለትም ሚያዚያ 14 እና 15/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) ልጅ እያሱ ኮር የየጎፍ ክ/ጦር አንድ የተመረጠ ሻንበል ለደሴ ከተማ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አልብኮ_ጦሳ_ጀብል ሰርጎ በመግባት ደፈጣ በመያዝ በጨፍጫፊው ዙፋን አስጠባቂ ሚሊሻና አድማ ብተና ላይ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ አራት ሚሊሻ እስከ ወዲያኛው ሲሸኝ በርካታ ቁስለኛ በማድረግ ድል ተቀናጅተዋል። ለቀጠናውና አካባቢው ህዝባችን ምሽት እንቅስካሴ ባለማድረግ ቀጣይ ለምሰራው ልዩ ኦፕሬሽን ይተባበሩን ሲል የየጎፍ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ሱልጣን የሱፍ ገልጿል::

ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር ሁለተኛ ሻለቃ ቃኝ ጉባላፍቶ ወረዳ ዶሮ ግብር የመሸገ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ላይ ዛሬ ሚያዚያ 15/2017 ዓ.ም ጧት ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ከአስር በላይ በመደምሰስና በማቁሰል ታላቅ ድል ሰርተዋል:: አካባቢው ላይ ያለ የጠላት ሃይልም በእውር ድንብር ሞርተርና ዲሽቃ እየተኮሰ አርፍዷል:: ተጋድሎውም በደፈጣ እና በመደበኛ ዉጊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ በዘመቻ አንድነት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ዘመቻ አንድነት!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ)
ሚያዚያ 15/2017 ዓ.ም
ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 7ኛ ሐዲስ አለማየሁ ክፍለ ጦር በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ሉማሜ ከተማ በተደረገ ውጊያ በርካታ ድሎችን አስመዝግቧል።

በዚህ ውጊያ የአማራ ፋኖ በጎጃም 7ኛ ሐዲስ አለማየሁ ክፍለ ጦር ሶስት ብርጌዶችን በማቀናጀት ማለትም መብረቁ ብርጌድ፣ አባይ ብርጌድ እና ተድላጓሉ ብርጌድ በተደረገ ውጊያ ጠላት ከ46 በላይ የተደመሰሰ ሲሆን ከ20 በላይ ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።

በዚህ ውጊያ የተገኙ ድሎች:-

01 ሰው የወረዳው ምክር ቤት አባል ከአመራሮች ጋር በመሆን አድራጊ ፈጣሪ የነበረ፣ 01 ሰው የፍርድቤት ሰራተኛ፣ 01 ሰው የወረዳው የገቢዎች ሰራተኛ ሕዝብ በግድ ግብር ሲሰበስብ የነበረና በውጊያ ላይም የተገኘ፣ 08 ሚሊሻ ሲሆኑ በዚህ ውጊያም በተደረገ ኦፕሬሽን ከ20 በላይ የግፍ እስረኛ የነበሩ የተለቀቀ ሲሆን 05 ጠላት ሲጠቀምበት የነበረ ላፕቶፕ እና 06 ከፋኖ ቤተሰብ ተወሰደው የነበሩ የቀንድ ከብት ተይዘዋል።

ውጊያውን የአማራ ፋኖ በጎጃም የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ መቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን፣ የ7ተኛ ክፍለጦር ዋና አዛዥ መቶ አለቃ ገረመው እና የክፍለ ጦሩ ምክትል ጦር አዛዥ ዶክተር መቶ አለቃ ሐብታሙ በጋራ መርተውታል።
#የድል_ዜና‼️
    ==============
የአማራ ፋኖ በሸዋ የአፄ ይኩኑ አምላክ ክ/ጦር ብሩኬ ደምሴ ብርጌድ አልገዛም አለ ሻለቃ በወረኢሉ ግንባር ዛሬም ድል በድል ሆና ውላለች።

በዚህ አውደ ውጊያ ከወረኢሉ ተነስቶ ወደ ግሼ ራቤል ሬሽን አጅቦ ለመከላከያ አሻግራለሁ ብሎ የተንቀሳቀሰው ሆድ አደሩ ሚኒሻ ፖሊስና አድማ ብተና በወረኢሉ ወረዳ ልዩ ቦታው
#ሺኮኮ_በር በሚባለው ቦታ ላይ በጀብድ አይጠግቤው ዘመቻ መሪ እየተመራች ብሩኬ ደምሴ ብርጌድ አልገዛም አለ ሻለቃ ተጋድሎ ላይ ውላለች።

   በዚህ ውጊያ
1. 6 ሚኒሻ የቆሰለ
2. 5 የሞተ ሚኒሻ
3. 1 አድማበ በተኛ የሞተ

በንብረት ላይ ሁለቱም ሬሽን የጫኑ አይሱዚዎች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል ሲሉ ፋኖ መ/ር ከበደ ወርቁ የብሩኬ ደምሴ ፖለቲካ ዘረፍ ሃላፊ ገልፀዋል‼️
ዘመቻ አንድነት ወሎ ቤተ-አማራ ግንባር!

መብረቅ ክፍለጦር የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት የሻለቃ አመራርና አምሳ አለቃም ጭምር የተደመሰሱበት ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

ተጠናክሮ በቀጠለው ዘመቻ አንድነት አማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክ /ጦር አሳምነው ፅጌ ብርጌድ እና ነብሮ ብርጌድ ልዩ ኮማንዶወች በጋራ በመሆን እንደተለመደው ጠላትን ስቦ በማስገባት በወግዲ ወረዳ ሰኮሩ ቀጠና በተለምዶ አበራ ሸለቆ እና 023 ቀበሌ አዳታ ከተባለ ቦታ እንከን የለሽ ኦፕሬሽን በመስራት 1 (አንድ) መቶ አለቃ እስከወደኛው ሲሸኝ 1 (አንድ) 50 (ሃምሳ) አለቃ ከባድ ቁስለኛ እንድሁም 20 ( ሃያ) ወንበር ጠባቂ ሰራዊት እስከወደኛው አሸልበዋል ::

እንዲሁም ሁለት እንቡላንስ ከባድ ቁስልኛ ሪፈር ጭኖ ወግዲን ከተማ አልፎ እንደወጣ ከውስጥ መረዳችን ጭምር ማወቅ ችለናል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ወግዲ ሆስፒታል በቁስለኛ እንደተጥለቀለቀ የአይን እማኞች እንዳሉን ከ25 በላይ ቁስለኛ አገልጋ ይዘው እርዳታ እየተደረገላቸው ቢሆን በህይወት የመትረፍ እድላቸው ዝቅተኛ ነው። ይህ የባሰበት እና መላ ቅጡ የጠፋው ሲቪል ታካሚ እያስወጡ መከላከያ ብቻ ይታከም በማለት ታማሚም አስታማሚም በዱላ እንደደበደቡ ቦታ ላይ የነበረ የአይን እማኞች አስረ ተውናል::

በደረሰበት ሽንፈት እና ኪሳራ የተበሳጨው ግባተ መሬቱ የደረሰው የብልፅግና ወንበር ጠባቂ አራዊት ሰራዊት መቶ አለቃውን ለመቅበር የተኮሱት ከባድ መሳሪያ ማህበረሰቡን ሁከት ፈጥሯል።

እንዲሁም ከከተማዋ ዙሪያ ያሉ እደሚያቸው 12 - 15 የሆኑ ከየቤቱ የፋኖ ቤተሰብ በማለት 18 ህፃናት እና ከቤት መሸሽ የማይችሉ አዛውንቶችን ደብድቦ በረካታ ገበሬዎችን እና የህዝብ ተቋም አገልጋዮችን ባገኘው አጋጣሚ አፍኖ የት እንደደረሳቸው አይታወቅም ሲል የንጉስ ሚካኤል ኮር ቃል አቀባይ ፋኖ አምሳ አለቃ ሁሴን ኡመር ገልጿል::

ታፍነው የተወሰዱ ግለሰቦች ስም ባገኘነው መረጃ :-
1. ንጉሴ ሀብት ነው
2. ታለማ እሸቱ ከነ ልጁ
3. አባተ እርገጤ
4. ተመስገን አስሜ ... ህፃን የ 12 ዓመት ልጁ 023 ቀበሌ
5. የቆየ አድነው
6. ካሳ ሽመልስ
7. ዋላልኝ ያዘው 023 ቀበሌ ግብርና ባለሙያ
8 . ስንደው .. መምህር
9 .ሀይሉ ማማሩ ... ህፃን የ13 ዓመት ልጅ 023
10 . አሳመረ ጋተው ... ህፃን
11. አብየ ተሾመ
12 . ስንደው ዋሌ
13. ዳኜ አብነው
14 . ብርሃን አደም በስም ያልተገለፁ ሌሎች በርካቶች ታፍነው ተወስደዋል ::
ተስፋ የቆረጠው ጠላትም ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት በአመራሩ መሞት የተበተነውን አራዊት ለማውጣት በዕውር በድብሩ ዙ 23
ጠላትም መውጫ አጥቶ ከወግዲ ዙ 23 እና ሞርተር እየ እየተኮሰ የግለሰብ ቤት እና ንብረት እያወደመ ይገኛል።

ዘመቻ አንድነት!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) ንጉስ ሚካኤል ኮር
ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም
ሰበር የድል ዜና!!

በሪፎርም ማግስት የተገኜ ጣፋጭ ድል በጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር የአማራ ፋኖ በጎጃም በጠላት ላይ ደማቅ ድልን ተቀዳጅቷል። የብልፅግናው ዘራፊ የጠላት ሃይል በቀን 10/08/2017 ዓ.ም በዕለተ ስቅለት ከጃዊ ከተማ ወደ ጃሂማላ ቀበሌ ሲንቀሳቀስ ከ20 በላይ የጠላት ሀይል መደምሰሱ የሚታወስ ነዉ።

ይሁንና የብልፅግናው ሰራዊት የጃሂማላን ማህበሰሰብ በማፈናቀል የትንሳኤ(ፉሲካ) በዓልን ሳያከብር ቀርቷል ይባስ ብሎ ንፁሃንንን ከቀያቸው በማፈናቀል በከተማዋ ውስጥ ያሉ ከነገዴ መካዝኖች እስከ ግለሰብ የቤት እቃና የቁም እንስሳትን ሲመዝረፍ ሰንብቷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በዛሬዉ እለት በ16/08/2017 ዓ.ም የበረሃው መብረቅ ነበልባሎቹ የአማራ ፋኖ በጎጃም ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ጥምር ጦር ታሪክ መስራት ችለዋል።

በውጊያው ተሳታፊ ብርጌዶች ነበልባሎቹ ኤፍሬም ብርጌድ እና የክ/ጦሩ ተወርዋሪ የምድር ድሮን ሻለቃ እንዲሁም ነጋሽ ብርጌድ፣ ደምስስ ብርጌድ፣ መተከል ጣና በለስ ብርጌድ፣ መብረቁ ብርጌድ ፣ አስር አለቃ አብየ ነጋሽ ብርጌድ በጥምረት የጠላትን አከርካሪ በመስበር በርካታ የጠላት ሀይል መደምሰስ ተችሏል በውጊያው ጠላት ከእግረኛ እስከ ብረት ለበስ ታንክና ድሮን ቢጠቀምም ራሱን መታደግ አልቻለም። ከ51 በላይ የጠላት ሀይል ሲደመሰስ ከ20 በላይ ከባድና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ሲቻል እጣ ፈንታው በኤክስከባተር በጅምላ መቀበር ሁኗል።

በዚህ የተበሳጨዉ የብልፅግና ጨፍጫፊ ሰራዊት የንፁሃን አርሶ አደሮችን ቤት በድሮን በመምታት 9 ንፁሃን ገድሏል 7 የሚደርሱ ንፁሃንን ደግሞ ከባድ ቁስለኛ አድርጓቸዋል።

በየጥሻው እግሬ አውጭኝ ያለውን የጠላት ሃይል ለማትረፍ ከጃዊ ከተማ በመነሳት 2 ብረት ለበስ ታንክ እና 1 ዙ 23 ይዞ  በመንቀሳቀስ አስከሬኑን ቀብሮ ተመልሷል።

ዘመቻ አንድነት ይቀጥላል...

አዲስ ትዉልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

[የአማራ ፋኖ በጎጃም]
ሚያዚያ 16/2017 ዓ.ም
የድል ዜና!

በአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜ/ጀ/ል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ስር የሚገኘው ጣና ገላዎዴዎስ ክ/ጦር ዛሬም እንደ ትናንቱ የጠላትን ኃይል የሐዘን ካባ አልብሶታል።

የዐቢይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት በቀን 13/08/2017 ዓ.ም ከባህርዳር ተነስቶ በሐሙሲት ወደ እስቴ መካነ ኢየሱስ ቀጠና እየተንቀሳቀሰ በነበረበት ሰዓት ዐርብ ገበያ ወልዴ ተራራ  ከተባለው አካባቢ ፈጣንና ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት ደርሶበታል።

ጥቃቱን ያደረሰበት ጠላትን  የአመራሮቹንና የሠራዊቱን ቁስለኛና አስከሬን ተሸክሞ ቀጠናውን ለቆ ለመንቀሳቀስ ተገዷል።

ድል ለተገፋው አማራ
በአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፣ ሜ/ጄ/ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር የጣና ገላዎዴዎስ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት