Ethio 251 Media
48.5K subscribers
2.16K photos
1.12K videos
8 files
2.53K links
ETHIO 251 is an independent media offering you News, Political Analysis and Information feeds. መረጃ ለማድረስ :- @Ethio251MediaInfo
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰበር መግለጫ ከአማራ ፋኖ በጎጃም‼️

            ቀን :- ግንቦት 20/2016 ዓ/ም

ወቅታዊ የአገዛዙን እንደራደር ጥያቄ አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ መግለጫ❗️

የአማራ ፋኖ በጎጃም ዋና ሰብሳቢ አርበኛ #ዘመነ_ካሴ

https://t.me/ethio251media
Ethio 251 Media
Photo
ኢትዮጵያ ‹‹መከላከያ›› የሌላት ሀገር…

10ሩ መራራ ሀቆች…

🔽🔽🔽
ቀደም ሲል ‹‹የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት›› ይባል የነበረው ተቋም ዛሬ ከፍ ሲል የኦሕዴድ-ብልጽግና ወታደራዊ ክንፍ፤ ዝቅ ሲል የዐቢይ አሕመድ የግል ዙፋን ጠባቂ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያ ዛሬ ከውጭ ወረራ የሚከላከልላት  ‹‹መከላከያ›› የሌላት አገር ሆናለች፡፡  

ዐቢይ አሕመድና የእርሱ ዙፋን ጠባቂ የሆኑ ጀኔራሎቹ በየሚዲያው እየወጡ የሚቀጥፉት ቅጥፈት ኢትዮጵያ መከላከያ የሌላት ሃገር የመሆኗን ሃቅ አይቀይረውም።

1)  ሰራዊቱ ከጦርነት ወደሌላ ጦርነት በመሸጋገሩ ከፍተኛ መሰላቸት አሳይቷል፤

2)  በሰራዊቱ አመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ የዝርፊያ እና ማኀበራዊ ብልግና ፉክክር እንጅ የወታደራዊ ሳይንስ ጥበብ ፉክክር የላቸውም፡፡ ፉክክሩ በዘረፋና በወሲብ ቅሌት ላይ ሆኖ ይታያል፤

3)  የሥልጣን ተረኝነት ስሜቱ በሠራዊቱ ዘንድ የፈጠረው ቅሬታ የውስጥ አርበኞችን ቁጥር ጨምሮታል፤

4)  አገዛዙ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳው ‹‹እየተገነባ ነው›› ቢሉትም ሰራዊቱ አንድነቱን አጥቶ እየተናደ ነው፤

5)  ከሰራዊቱ እየከዳ የሚኮበልለው ቁጥሩ እጅግ ጨምሯል፤

6)  ሰራዊቱ የሚዋጋለት ዓላማ የለውም፤ በከፍተኛ ሁኔታ ተሰላችቷል፤

7)  ሰራዊቱ በሕዝብ ዘንድ ገዳይና ዘራፊ ተደርጎ ይቆጠራል፤ ከሕዝብ ተነጥሏል፤

8)  መሬት የታደለው ኮለኔልና መስመራዊ መኮንን መኮብለሉንና ፋኖን መቀላቀሉን ቀጥሏል፤

9)  ኮማንዶ፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ የባሕር ኃይል ... ወደ ውጊያ ያልተጣደ ኃይል የለም ነገር ግን ጠብ ያለ ውጤት የለም፤

10) በሠራዊቱ ተስፋ የቆረጠው አገዛዙ ከኦሮሞ ክልል  አዲስ ተዋጊ በገፍ ጭኖ ወደአማራ ጠቅላይ ግዛቶች እያዘመተ ነው፤ ይህ የአንድ ፓርቲና ግለሰብ ወንበር ጠባቂ የሆነ ወራሪ ሰራዊት ዕጣ ፈንታው ምርኮ፣ መቁሰልና አፈር መግባት ከመሆን አይዘልም!!! 

በአማራ ክልል አይቀሬ ሽንፈት እንደሚጠብቀው እየደረሰበት ካለው ከባድ ኪሳራ የተረዳው አገዛዙ፣ በእነ ሺመልስ አብዲሳ በኩል በኦሮሞ ክልል ምስኪን አርሶአደር እየሰበሰቡ በማሰልጠን "ሥልጣን ጠብቁ" በሚል ለለየለት የዘር ማጥፋት እያዘጋጀ ይገኛል፡፡

ነገር ግን የአማራ ሕዝብ የገባበት የህልውና ጦርነት ተገዶ ስለመሆኑ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰወረ አይደለም፡፡ ይህ ጦርነት ለአማራ ሕዝብ የህልውና ጦርነት ነው፤ ጠላቶቹ ሊያጠፉት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ እርሱም እንደሕዝብ ተነስቶ ጠላቶቹን በመመከት ላይ ነው…!

አማራ ጠሎቹ፦ የዓድዋ ድል ቁስለኞች፤ የፋሽስት ዓላማ ወራሾች፤ ኢትዮጵያን ‹‹መከላከያ›› የሌላት ሀገር ቢያደርጓትም፤ በአይቀሬው የአማራ ሕዝብ ድል ማግሰት ኢትዮጵያ የዓድዋ ድል ታሪክ ወራሽ፤መላ ልጆቿን የሚመስል ብሔራዊ ጦር ትገነባለች!!

ኢትዮ 251 ሚዲያ
https://t.me/ethio251media
በሕዳሴ ግድብ ስም ፋሽስቱ አብይ አህመድ ለድሮን መግዥያ ከዳያስፖራው ዶላር ለመሰብሰብ ለነገ የበይነመረብ ጥሪ አድርጓል።

ሆድ አደር ዳያስፖራውን በመከታተል እናጋልጥ።

https://t.me/ethio251media
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙት የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ምግብ እንዳያገኙ መከልከላቸው ተሰማ!

የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ምግብ መከልከሉን አምኖ "ይህንን ያደረኩት  ፋኖ በኦፕረሽን እስረኞቹን  አስፈታለሁ ማለቱን ስለደረስኩበት ነው" ብሏል።

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙት በእነ ዶክተር ወንደሠን አሰፋ መዝገብ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እና በጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ክስ መዝገብ የሚገኙት ጠቅላላ 11የህሊና እስረኞች እና በእነ ዮኋንስ ቧያሌው መዝገብ የሚገኙት ዮኋንስ ቧያሌውን ጨምሮ: ክርስቲያን ታደለ: ዶክተር ካሳ ተሻገር እና ዶክተር ጫኔ ከበደን ጨምሮ 4 የህሊና እስረኞች በእነ መላክ ምሳሌ መዝገብ ኤርሚያስ መኩሪያ  እና ኮማንደር ጌታዋይ ታደሰ ሆነው 4 እስረኞች  በድምሩ 19 የፖለቲካ እስረኞች ምግብ እንዳይገባላቸው መታገዱን ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምፅ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት  አስተዳደር ዳይሬክተር ኮማንደር  አስቻለው መኮነን ቱሉ ሲጠየቅ ከላይ ታዝዤ ነው ማለቱን የታሳሪ ቤተሰቦች ለጣቢያችን ጨምረው ገልፀዋል።

ይህንን አስመልክቶ ጉዳያቸውን እየተመለከተ የሚገኘው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የህገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል: 3ኛ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው እንደማንኛውም ታራሚ ቤተሠቦቻቸው እንዲጠይቋቸው እና ምግብም እንዲገባላቸው  ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም የማረሚያ ቤት አስተዳደር ዳይሬክተር ኮማንደር አስቻለው መኮነን ቱሉ "እኔ ስራዬን የምሰራው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይሆን ከላይ በሚሰጠኝ ትዕዛዝ በመሆኑ ምግብ እንዳይገባ የተባለውም ከላይ ስለሆነ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ቢልክልኝም የምፈፅመው ግን ይህንን ማረሚያ ቤት  እንዳስተዳድር የላከኝን መመሪያ ነው" ማለቱን የታሳሪ ቤተሰቦች ለአማራ ድምፅ ዜና አገልግሎት ገልፀዋል።

ኮማንደር አስቻለው ጉዳዩን ፍ/ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ቢደርሰውም ስራ ስላለብኝ አልሄደም ማለቱን የታሳሪ ቤተሰቦች ገልፀውልናል።

ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እንዳይጠቀስ ያሳሰቡን አንድ  የታሳሪ ቤተሰብ እንዳሉት "እስረኞቹን ከቃሊቲ እስር ቤት ለማስፈታት ፋኖ ኦፕረሽን ለመስራት እቅድ እንዳለው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት  ስለደረሰበት እስረኞቹ ለጊዜው ከሌላው እስረኛ በተለዬ ከቤተሰቦቻቸው እንዳይገናኙ ተደርጓል" የሚል ምላሽ ሰተውናል ሲሉ ተናግረዋል። 


በዚህ ምክኒያት ሐሙስ ቅዳሜ እና እሁድ የቃሊቲ እስረኞች ቤተሰቦቻቸውን ጠይቀው ሲገቡ ከላይ በስም የተጠቀሡት የህሊና እስረኞች ተለይተው 6:00 እስከ 7:00 ድረስ ብቻ ቤተሰብ እንዲገናኙ ተገድበዋል።

ከዚህ ሰአት ውጪ ምግብ ማስገባት እንደማይቻልና ከዚያ በኋላም ሆነ ከዚያ በፊት ቤተሰብ ሆነ ምግብ እንዳይገባ መከልከሉን የአማራ ድምፅ ዜና አገልግሎት ቤተሰቦቻቸውን አናግሮ ለማወቅ ችሏል።

ሚያዚያ 26  ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሎች እስረኞች ተለይተው ሲጠበቁበት ከነበረው ዞን ወጥተው የህግ ታራሚዎች ጋር እንዲቀላቀሉ የተደረገበትን ምክንያት  ማረሚያ ቤቱ ለፍ/ቤት እንዲያስረዳ ቢጠየቅም የአስተዳደሩ ዳይሬክተር እስቻለው መኮነን ቱሉ  ፍርድ ቤት መቅረብ አልቻለም።

የሕሊና እስረኞቹ ከህግ ታራሚዎች ጋር መቀላቀላቸውን አስመልክቶ ፍ/ቤት እንደሚከሱ ሲናገሩ ኮማንደር አስቻለው "እኔ በህወሓት ጊዜ እዚህ ነበርኩ በብልፅግናም ይሄው አለሁ።  ፍ/ቤቱን አውቀዋለሁ ። የእናንተን ጉዳይ  ፍ/ቤቱ አይመለከተውም"  ማለቱን  የታሳሪ ቤተሰቦች ነግረውናል።

የህሊና እስረኞቹ በተደጋጋሚ ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑን እና ወደ ሌላ ዞን እንዲያዛውሯቸው ሲጠይቁም ኮማንደር አስቻለው "የማረሚያ ቤት ፖሊስ መሳሪያውን ሸጦ እየጠፋ ስለሆነ ጥበቃ የለኝም። አዲስ ምልምል አለልቱ የማረሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በቅርቡ ስለሚያስመርቅ  እነሱን እየጠበቅን ነው" ብሎ መልስ መስጠቱን ቤተሰቦች ነግረውናል።

ከእነ ትጥቁ የሚኮበልል የማረሚያ ቤት ፖሊስ ከጊዜ ወደ ጊዜ መበራከቱን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ውስጥ የሚሰሩ አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የአማራ ድምፅ ዜና አገልግሎት  ጠቋሚ ነግረውናል።

የማረሚያ ቤት ጥበቃ ፖሊሶች በተለይ ጀማሪዎች  ወርሀዊ ደመወዝ ተጣርቶ እጃቸው ላይ 2100 ብር ብቻ ይደርሳቸዋል። መንግስት እንደምክኒያት የሚያቀርበው በካምፕ ውስጥ ስለሚኖሩ እና ካምፑ ምግብ ስለሚያቀርብ ገንዘቡ በቂ ነው በሚል ነው።

የደመወዝ ጭማሬ እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም "ይሄው ደመወዝም ሊቆም እንደሚችል እና ፖሊስ አገልጋይ እንጂ በደመወዝ የሚሰራ አይደለም" የሚል መልስ እንደተሠጣቸው ነው የአስተዳደሩ ሰራተኞች ለአማራ ድምፅ የተናገሩት።

ተስፋ የቆረጡ የጥበቃ ፖሊሶች ትጥቅ ይዘን  አንራብም በሚል አብዛሀኛዎቹ  ትጥቃቸውን እየሸጡ መኮብለላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

አንድ ክላሽንኮቭ መሣሪያ አዲስ አበባ ውስጥ  እስከ 120 ሺህ ብር ሸጠው እንደሚሄዱ የተናገሩት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ሰራተኞች ከሚያዚያ ወር ወዲህ 53 ፖሊሶች መኮብለላቸውን ለአማራ ድምፅ ዜና አገልግሎት ገልፀዋል።

በቃሊቲ ከሚገኙት የአማራ የሕሊናና የፖለቲካ እስረኞች በተጨማሪም በቂሊንጦ፣በአዋሽ አርባ፣ በሰመራና በሌሎች ባልታወቁ ቦታዎች በርካታ ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ የሕግ ባለሙያዎች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ታስረው ይገኛሉ።

መረጃው የአማራ ድምፅ ሚዲያ ነው
https://t.me/realthevoiceofamhara
ከኢትዮ 251 ሚዲያ የቀረበ ጥሪ!

ኢትዮ 251 ሚዲያ ላለፉት አራት ዓመታት የዐቢይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋና ግፍ እየተከታተለ በመዘገብ የህዝብ ልሳን ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ሚዲያው በሚያቀርባቸው መረጃዎች አገዛዙን በማጋለጡ፤ አገዛዙ ሚዲያውን በመዝረፍ፣ ጋዜጠኞችን በማሳደድ እንዲሁም በተደጋጋሚ እና በተደራጀ መልኩ ቻናሎቹን እያዘጋበት ይገኛል፡፡

በዚህ የተነሳም የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የዘር ማጥፋት ጦርነት ሰሚ እንዳያገኝ የአገዛዙ ፍላጎትና እቅድ ቢሆንም፤ ኢትዮ 251 ሚዲያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም ለህዝብ ድምጽ በመሆን የአገዛዙን ገመና ያለማቋረጥ እያጋለጠ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን ጦርነት ለመመከትና ህልውናውን ለማስጠበቅ የሚዲያው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ኢትዮ 251 ሚዲያም ይህንን ኃላፊነቱን በመረዳት ባለሙያዎች በመጠናከርና በሁሉም ቀጠናዎች ዘጋቢዎችን በመመደብ እየሠራ ይገኛል፡፡ ይህ ጥረቱም የአገዛዙን ገመና ከማጋለጥም በተጨማሪ፤ የፋኖን እያንዳንዱን የትግል ውሎና ጀብዱ በመዘገብና ሰንዶ በመያዝ ላይ ነው፡፡

ይህን ጥረቱን በተጠናከረ መልኩ እንዲያከናውን የፋይናንስ ድጋፍ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡

ስለሆነም ኢትዮ 251 ሚዲያን በዚህ የጎፈንድሚ አካውንት በመደገፍ የአማራን ህዝብ ትግል ይደግፉ ስንል በአክብሮት ጥሪ እናቀርብለዎታለን፡፡

ኢትዮ 251 ሚዲያ!!

https://gofund.me/a2d99937
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"የሰበርነው ነፍጠኛ እንደ አዲስ ሊሰብረን ተነስቷል" ሲል ሽመልስ አብዲሳ በመደንፋት የኦሮሚያ ክልል በራሱ በጀት ወደ አማራ ክልል ጦር አሰልጥኖ ልኳል።

..... የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት ሁሉም ሰራዊት ተሰባስቦ ወደ አማራ ክልል እንዲዘምት ዝግጅቱ ተጠናቋል።

ዝርዝሩን እነሆ ያድምጡት ።

https://t.me/ethio251media
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ ከኮሎኔል አለሙ ሞላ ጋር የተደረገ ቆይታ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"አማራ የምትባለው እየመጣሁልህ ነው" የኦሮሞ ክልል ልዪ ኃይል ኮማንዶ

ይሄን የምትሰሙትን ንግግር የተናገሩት ከሰሞኑ በአሮሞ ብልጽግና ስብሰባ ላይ "የሰበርነው ነፍጠኛ ማለቴ አማራ እንደ አዲስ ተነስቷል፤ ስለሆነም በጊዜ ልንደመስሰው ይገባል።" በሚል ንግግር ያደረገው የሽመልስ አብዴሳ የኦሮሞ ክልል ልዪ ኃይል ኮማንዶ "አማራ የምትባለው እየመጣሁልህ ነው።" እያለ ይደመጣል።

ይሰማል⁉️

https://t.me/ethio251media
ከሰማይ መና እየወረደልን ነው📌

ምድር ጦር በታንከኛና በሜካናይዝድ፤ አየር ኃይል ከራሺያ ሰራሽ ሃሊኮኘተሮች እስከ ቱርክ ሰራሽ ድሮኖች

በኮማንዶ በኩል
አየር ወለድ ኮማንድ
ሪፐብሊካን ኮማንዶ
የባሕር ኃይ ኮማንዶ
ኤሊት ፎርስ
መደበኛ እግረኛ ሰራዊት
የፌዴራል ፖሊስ ኮማንዶ
አማራ አድማ ብተና
አማራ ፖሊስ
አማራ ሽምቅ ተዋጊ
አማራ ሚሊሺያ
ግዞተኛ ካድሬዎች

በአስራ አንድ ወራት አከርካሪውን መተነዋል። ይሄ ኃይል አማራ ክልል ገብቶ ቀርቷል። የአገሪቱ core የተባለው ኃይል ተበልቷል።

አሁን የኦሮሚያ ሚሊሺያ የመከላከያ መለዮ ለብሶ እየመጣ ነው። በሁለት ቀናት 119ሽ ኃይል ተጭኗል። ይህንን መልካም ዕድል በፍፁም አናሳልፈውም። ጦርነቱን ዐማራ ክልል ጨርሰን የተጓደለ መሣሪያ አሟልተን የነፃነት ቀናችን እናበስራለን።

የወለጋ፣የሻሸመኒ፣የአርሲ፣የአመያ አማራን ጨፍጫፊ የሞት ትኬት ቆርጦ ያውም ስንቅና መሣሪያ ይዞ ወደ ቤትህ ሲመጣ አለመደሰት ትችላለህ ወይ⁉️

አንድ የፋኖ መሪ የላከው መልዕክት!

https://t.me/ethio251media
📌ከነገ ጀምሮ በጎጃም መንገድ ተከፍቷል!

"የአርሶ አደሩ ግብዓት ተጓጉዞ እስኪጠናቀቅና ነባራዊ ሁኔታው ታይቶ ሌላ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስ የተዘጉ መንገዶች ከነገ ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ክፍት ይደረጋሉ።" የአማራ ፋኖ በጎጃም

https://t.me/ethio251media
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ!!

የመርሃቤቴ  አውራጃ አፄ ዳዊት ክፍለጦር በሚዳ ሬማ  ስለ አማራ ህዝብ ህልውና በመድረክ ዙሪያ ህዝባቸውን በዝህ መልኩ አወያይተዋል።

   ድል ለህዝባችን!!

https://t.me/ethio251media
mereja.docx
42.5 KB
ላልተወቁ ኃይሎች ይድረስ📌

የብልጽግና "የእግር መትከል ምዕራፍ ስራችን እና የቀዉስ ጊዜ እቅድ አፈፃፀም ያለበት ሁኔታ" በሚል ያወጣው ልዩ ሰነድ

https://t.me/ethio251media
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አዳዲስ ፋኖዎችን አሰልጥኖ አስመረቀ!

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዡ ሻለቃ ሀብቴ ወልዴና ሌሎችም የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ለስድስት ወር ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ፋኖዎች ተመርቀዋል።

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሀብቴ ወልዴ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ "የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ስልጠናውን በድል ተወጣችሁታል፤ እናንተ የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ቀልባሽና የአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁ በዚህ ልትኮሩ ይገባል።" ብሏል።


https://t.me/ethio251media