ጋዜጠኛ ገነት አስማማው በመጪው ግንቦት ወር የመከላከያ ምስክሮቿን እንድታሰማ ተቀጠረች!
በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሳ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘው ጋዜጠኛ ገነት አስማማው፣ በመጪው ግንቦት ወር 2018 ዓ.ም የመከላከያ ምስክሮቿን እንድትሰጥ የፌደራል ፍርድ ቤት ቀጠሮ መያዙ ተገለጠ።
ፍርድ ቤቱ ይህንን ቀጠሮ ያስቀመጠው፣ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው የምስክርነት እና የሰነድ ማስረጃ ክሱን ለማስቀጠል በቂ ነው የሚል ብይን ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ ላይ መስጠቱን ተከትሎ ነው። የመድሎት ሚዲያ ሪፖርተር የነበረችው ገነት አስማማው፣ መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሏ ይታወሳል።
በወቅቱ በቁጥጥር ስር ስትውል ፖሊሶች ድብደባና ማስፈራሪያ እንዳደረሱባት በድምፅ የተቀዳ መረጃ መውጣቱና ይህም በጠበቆቿ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረቡ የሚታወስ ነው። ጋዜጠኛዋ መጀመሪያ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ዓመፅን በማቀስቀስ እና መንግሥትን በኃይል ለመገልበጥ ወጣቶችን በማደራጀት ተጠርጥራ የነበረ ሲሆን፣ ሰኔ 2015 ዓ.ም ደግሞ በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመስርቶባታል።
ከገነት ጋር በዚሁ የክስ መዝገብ ላይ ጋዜጠኛ መስከረም አበራ፣ ዳዊት በጋሻው እና ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ 50 የሚሆኑ ሌሎች ተከሳሾች ይገኛሉ። ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው የክስ ሰነድ ላይ ጋዜጠኞቹ "የሽብርተኝነት መከላከልና መቆጣጠር አዋጅን" ተላልፈዋል ሲል ከሷቸዋል። ይህ አዋጅ በፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ ወይም በሌሎች ርዕዮተ ዓለማዊ ምክንያቶች ሕዝብን በማሸበር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ግለሰብ እስከ ሞት ቅጣት ሊፈረድበት እንደሚችል ይደነግጋል።
ዓቃቤ ሕግ በጋዜጠኛ ገነት ላይ ካቀረባቸው ክሶች መካከል "የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት" በሚባል ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ የፕሮፓጋንዳ ስልጠና መውሰድ፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከሥራቸው እንዲለቅቁ የሚቀሰቅስ ደብዳቤ ማሰራጨት እና በማኅበራዊ ሚዲያ የሽብር ተግባራትን ማራመድ የሚሉ ይገኙበታል። ጋዜጠኛዋ የቀረበባትን ክስ በሙሉ "ጥፋተኛ አይደለሁም" ስትል መቃወሟ ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ሲፒጄ (CPJ) በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና ከፍትሕ ሚኒስቴር ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረገው ጥረት ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች በሙሉ በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በመዘገባታቸው ምክንያት የታሰሩ መሆናቸውን ሲፒጄ ባወጣው የ2025 (እ.ኤ.አ) ሪፖርት አመልክቷል።
የጋዜጠኛ ገነት አስማማው እና የሌሎች ተከሳሾች ጉዳይ በመጪው ግንቦት ወር የሚሰማው የመከላከያ ምስክርነት ሂደት በትግሉ ደጋፊዎችና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተጠበቀ ይገኛል።
ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

❤30💔4
ዶክተሩ በአገዛዙ ሀይሎች ታፈኑ!
በጎጃም እንጅባራ ከተማ በሚገኘው ሆስፒታል ውስጥ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩት ዶ/ር አብርሃም አማረ፣ በፀጥታ ኃይሎች ከተወሰዱ ስምንት ቀናት ቢቆጠሩም እስካሁን ያሉበት ቦታና ሁኔታ አለመታወቁ ቤተሰቦቻቸው ገለፁ።
ዶ/ር አብርሃም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከስራ ገበታቸው ላይ ታፍነው ከተወሰዱበት ጊዜ አንስቶ፣ ቤተሰቦቻቸውና የቅርብ ባልደረቦቻቸው ስለ ደህንነታቸው ለማወቅ ጥረት ቢያደርጉም እስካሁን ምንም ዓይነት መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ታውቋል።
የህክምና ባለሙያው በምን ምክንያት እንደተወሰዱና በአሁኑ ወቅት የት እንደሚገኙ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት የተሰጠ ማብራሪያ የለም።
ይሁን እንጂ አንድ የጤና ባለሙያ በስራ ላይ እያለ ተይዞ የደረሰበት አለመታወቁ በሆስፒታሉ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል።
ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት
https://t.me/ethio251media

❤29😢10👍1
📢የዝግጅት ጥቆማ!
"የአፋብን ዲፕሎማሲያዊ ግንባርና ዓለም አቀፍ ትኩረት"
የአፋብን የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ብሩክ ስለሺ ከመምሪያው ምስረታ ዓላማ ጀምሮ፣ በአማራ ሕዝብ እየደረሱ ስላሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተደራሽ ስለማድረግ፣ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች (UN, AU) ጋር ስላለው ግንኙነት እና የዳያስፖራውን አቅም ወደ አንድ ስለማምጣት ሰፊ ማብራሪያ የሰጡበት ልዩ ቆይታ አድርገናል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ቀውስ እንድትወጣ የአፋብን የውጭ ጉዳይ መምሪያ እንደ መፍትሄ የሚያስቀምጠውን ዲፕሎማሲያዊ መንገድና ቅድመ ሁኔታዎችን በዝርዝር ዳሰናል።
በኢትዮ 251 ሚዲያ ተዘጋጅቶ በ Amhara News Agency ዩቲዩብ ቻናል ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ ወደ እናንተ ይደርሳል።
የትግሉን የዲፕሎማሲ ምዕራፍ የሚቃኝበትን ይህን ዝግጅት እንዲከታተሉ ቻናሉን ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ ጠብቁን።
የሊንክ መግቢያ፦
👇👇
https://youtube.com/@amharanewsagency?si=q6nJlsX_gj2DvGCk

❤26👍12👏4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሰለጠነ ሰራዊት ማዘጋጄት እራሳቸውን አባገነን አድርገው ለሚጨቁኑ አምባ ገነን መንግስታት መድሃኒት ነው!!
እራሳቸውን አምባ ገነን አድርገው ሌለውን መጨቆን ለሚፈልጉ አካላት እራስህን ነፃ የምታወጠው ከእነሱ የበለጠ ጠንከራ የሰለጠነ ሰራዊት ገንብተህ እራስን መከላከል ስትችል ነው።
የአማራ ህዝብ ከተጋረጠበት የህልውና አዳጋ ለመመከት ይሁን ለመከላከል የሚታገልለትን ዓላማ ያወቀ የሰለጠነ ወታደራዊ ሰራዊት ማፍራት ትግሉን በአጭር እንዲቋጭ በመሉም ቦታዎች ስልጠናዎች መቀጠል አለባቸው።
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የበላይ ትንፋሹ አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር ልዩ ኮማንዶ

👍41❤11👏5
#ሰበር_የአውደ_ውጊያ_ዜና‼️
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዘ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ጀግናው የአፄ ዳዊት ክፍለጦር አሃዶች ከ25 በላይ የብልፅግናውን 101ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር አባላት በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ።
መጋቢት 29/2018ዓ.ም
ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2018ዓ.ም ከንጋቱ 11:00 ጀምሮ በተካሔደው የተቀናጀ ተጋድሎ ሰራዊታችን ታላቅ ድል እየተጎናፀፈ ይገኛል ሲል የአፄ ዳዊት ክፍለጦር አስታወቀ።
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በሚዳና ሬማ ወረዳ ከአገዛዙ 101ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ጋር እየተደረገ ባለው ውጊያ ጀግናው የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ከአፄ ዳዊት ክፍለጦር ሻለቆች እና በቀጠናው የሚገኙት የአርበኞች ጦር ሰራዊት በተወጣጡ የወገን ሀይል ከአራት አቅጣጫ የመጣውን የስርዓቱ ወንበር አስጠባቂ ወራሪ ሀይል ላይ ከፍተኛ ድል መቀዳጀታቸውን ክፍለጦሩ በግንባር መረጃው አስታወቀ።
በጀግናው ሰራዊታችን ተደጋጋሚ ሽንፈት እያስተናገደ ያለው የብልፅግናው ዘራፊ ሰራዊት የፋኖን ሀይል ለማጥቃት አቅዶ መነሻውን ከሬማ ከተማ፣ በሚዳ መራኛ ከተማ፤ ከወሎ ቤተ አማራ ጃማ ደጎሎ ከተማ እንዲሁም ከአለም ከተማ በማድረግ የተንቀሳቀሰ ሲሆን በይጎቪያ ቀበሌ በተደረገበት የመልሶ ማጥቃት ከ25 በላይ የአየር ወለድ የሰራዊቱ አባላት የተደመሰሱ ሲሆን ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ የጥምር ጦር አባላቱ ሙትና ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ማስተናገዱን ክፍለጦሩ ገልጿል።
ይሕ ዜና እስከተጠናቀረበት ከቀኑ 9:30 ድረስ በርካታ የጠላት ሀይል በወገን ሀይል ከበባ ውስጥ ገብቶ ከፍተኛ ምት እያስተናገደ ሲሆን ውጊያው ተጠናክሮ መቀጠሉን ክፍለጦሩ በግንባር መረጃው አስታውቋል።
መረጃው የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ነው።
👉በሬማ ከተማና አዋሳኝ ቦታዎች ላይ እየተካሔደ ያለው ውጊያ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በጀግናው ሰራዊታችን በመልሶ ማጥቃት ከበባ ውስጥ የገባውን የአገዛዙ ሰራዊት ለማስወጣት ተጨማሪ የጠላት ሀይል ከአለም ከተማ በማምጣት በከተማዋ ዙሪያ ባሉ በድሬና መጅት ቀበሌዎች አድማሱን ያሰፋው ውጊያ በመቀጠሉ ዝርዝር የአውደ ውጊያ መረጃዎችን በቀጣይ ይዘን የምንመለስ መሆኑን ከወዲሁ መግለፅ እንወዳለን።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
መጋቢት 29 / 2018ዓ.ም

❤48👍10🤡6🔥5🌚3💊3🥰2🤪2
ተለቀቀ! 🚨 ልዩ የዲፕሎማሲ ግንባር ዳሰሳ!
"የአማራ ሕዝብ ትግል በዓለም አቀፍ መድረክ፤ የት ደረስን?"
የአፋብን የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ብሩክ ስለሺ በዲፕሎማሲው መስክ እየተከናወኑ ያሉ አዳዲስ እንቅስቃሴዎችንና ስልታዊ አቅጣጫዎችን በተመለከተ የሰጡት ሙሉ ቃለ-መጠይቅ አሁን በዩቲዩብ ቻናላችን ተለቋል።
በዚህ ዝግጅት የተዳሰሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
• 📍 የአፋብን ዲፕሎማሲያዊ ግቦችና ሂደቶች፤
• 📍 የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለዓለም አቀፍ ተቋማት (UN, AU) የማድረስ ሂደት፤
• 📍 የዳያስፖራውን አቅም ወደ አንድ የማምጣት ስራና ተግዳሮቶች፤
• 📍 ኢትዮጵያን ካለችበት ቀውስ ለማውጣት የተቀመጡ የዲፕሎማሲ ቅድመ ሁኔታዎች።
የትግሉን የዲፕሎማሲ ምዕራፍና ቀጣይ አቅጣጫዎች በዝርዝር ለመረዳት አሁኑኑ ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ።
ሙሉ ዝግጅቱን ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ፦
👇👇
https://youtu.be/U2hZv4-7oKE?si=OZ3lRcpaWN-LT2Qm

YouTube
ANA ልዩ መረጃ | "በወታደራዊ የተገኘውን ድል በዲፕሎማሲው እየደገምን ነው" | "በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለማድረግ ዝግጁ ነን"
#የAmhara News Agency_ANA - የዩቱዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 https://www.youtube.com/channel/UCRE9vr7W3dsTxhUe-xAOtbA

❤41🤔4
የኤቢሲ ቴቪ ወዳጆችና ቤተሰቦች፤
በተለመደው የሳይበር አፈና ምክንያት ከ80ሺህ በላይ ቤተሰብ የነበረው የኤቢሲ ቴቪ youtube ገፅ ተነስቷል።
በመሆኑም ተከታዩን አዲስ ገፃችንን በመቀላቀልና ለሌሎች በማጋራት ተደራሽነታችንን እንድናሰፋ ይሔንን #challenge ይቀላቀሉ።
Subscribe and SHARE ABC TV 👇
https://www.youtube.com/@abcmovement2026

❤41🔥5👍1🤔1
ሰበር ዜና!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የሰዴ ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ሰዴ ከተማን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ስር የሚገኘው የቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ እና 206ኛ ኮሮች በጋራ ባደረጉት የተቀናጀ ወታደራዊ ኦፕሬሽን፣ የሰዴ ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ሰዴ ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን የዕዙ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታወቋል።
በጀነራል መንበሩ ጌትዬ ስም የተሰየመውን ይህንን ዘመቻ ያከናወኑት የፋኖ አባላት፣ በከተማዋ የነበረውን የአገዛዙን ጦር አይቀሬ ሽንፈት እንዳቀመሱት ተገልጿል።
በውጊያው ወቅት ከፍተኛ ድምሰሳ የደረሰበት የአብይ አህመድ የግል ጠባቂ ኃይል ተበታትኖ የቀረው ጦር ወደ ቀራኒዮ ከተማ መፈርጠጡ ታውቋል።
በዚህ መጠነ ሰፊ ውጊያ በርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች፣ የተለያዩ ተተኳሾች፣ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እና ምርኮኞች በፋኖ እጅ መውደቃቸው ተረጋግጧል።
የአገዛዙ ጦር ሽንፈቱን ለመከላከል ድሮን በመጠቀም ከተማዋን ሲደበድብ ቢውልም፣ የፋኖን ግስጋሴና የከተማዋን መያዝ ሊያስቆም እንዳልቻለ በወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በቀጣይ ዝርዝር የምርኮ መረጃዎችን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

❤44👍12👏7
ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች፦
ትብብራችሁ ያስፈልገናል!
ቻናሎቻችን በተደጋጋሚ ቢዘጉብንም እኛም ለመክፈት አልቦዘንም።
እናንተም Subscribe በማድረግ ተባበሩን!
👇👇👇
https://youtube.com/@asharareporter?si=uTMEgGxOnufZHd2Z
አሻራ ሚዲያ!

👍19❤15
የአፋብን ምክትል ወታደራዊ አዛዥ ልጅ ተማረከ የሚለው ወሬ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑ ተገለጸ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምክትል ወታደራዊ አዛዥ የዋርካው ምሬ ወዳጆ ልጅ በአገዛዙ ጦር እጅ ወድቋል ተብሎ በብልጽግና የሶሻል ሚዲያ አውታሮች የሚናፈሰው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ዋርካው ምሬ ወዳጆ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገለጸ።
በአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ክንፎች አማካኝነት "የምሬ ወዳጆ ልጅ ተማረከ" በሚል ሲሰራጭ የሰነበተው ወሬ የፋኖን የትግል ሞራል ለመንካት የታለመ የሥነ-ልቦና ጥቃት መሆኑን የገለጹት አዛዡ፣ መረጃው ፍጹም ከእውነት የራቀና መሬት ላይ የሌለ ድራማ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ዋርካው ምሬ ወዳጆ አክለውም፣ አገዛዙ በመሬት ላይ ባለው ውጊያ እየተሸነፈ በመምጣቱ መሰል የሀሰት ወሬዎችን በማምረት ሕዝብን ለማደናገር እየሞከረ መሆኑን ጠቁመው፣ ደጋፊዎችና መላው የአማራ ሕዝብ ከእንዲህ ያሉ የሴራ ፕሮፓጋንዳዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

👍40❤19👏3
ሰበር ዜና!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ከአንድ ሻለቃ በላይ የጠላት ኃይልን በመደምሰስ የሰዴ ወረዳን በቁጥጥር ስር አዋለ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰዴ ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ሰዴ ከተማንና መላውን ወረዳ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ንቅናቄው መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ 201ኛ እና 206ኛ ኮሮችን በማቀናጀት በጀነራል መንበሩ ጌትዬ ስም በተሰየመው በዚህ ኦፕሬሽን የጠላትን ካምፕ ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ከአገዛዙ ጭቆና ነፃ ማውጣት ተችሏል።
በቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ አመራሮችና በሁለቱ ኮሮች ጥብቅ ቅንጅት የተመራው ይህ ውጊያ በአገዛዙ ጦር ላይ ከፍተኛ የሞራልና የስነ-ልቦና ስብራት ያደረሰ ሲሆን፣ የአብይ አህመድ ጦር ከተማዋን ላለመልቀቅ ድሮንና መድፍን በመጠቀም ተደጋጋሚ ጥቃት ቢሰነዝርም የፋኖን ቆራጥነት መቋቋም ባለመቻሉ አካባቢውን ለቆ ለመውጣት ተገዷል።
በዚህ ስልታዊ አውደ ውጊያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደራዊ ትጥቅና ሎጅስቲክስ በፋኖ እጅ የገባ ሲሆን፣ ምርኮውም 5 ብሬን፣ 100 ክላሽንኮቭ፣ 17 ስናይፐር፣ 1 የመገናኛ ሬዲዮ፣ 140 ካዝናዎች፣ 50 የእጅ ቦንቦች እንዲሁም 35,000 የሚጠጉ የብሬንና የክላሽ ተተኳሾችን ያካተተ ነው። ከተሽከርካሪ አንጻርም 3 የአመራር መኪናዎች፣ 4 ዳብል ጋቢና ፓትሮሎች፣ 1 አምቡላንስ፣ 1 ኤፍ.ኤስ.አር እና 15 ሞተር ብስክሌቶች ተማርከዋል።
በተጨማሪም ለሠራዊቱ ቀለብ ተዘጋጅቶ የነበረ 60 ኩንታል ጤፍ፣ 10 ኩንታል ስኳር እና አንድ ኮንቴይነር ዘይት በንቅናቄው ቁጥጥር ስር ውሏል።
እንደ አፋብን ቴዎድሮስ ሕዝብ ግንኙነት መረጃ ከሆነ፣ በአውደ ውጊያው በአጠቃላይ 167 የአገዛዙ ታጣቂዎች የተደመሰሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል 90 የመከላከያ፣ 22 የሪፐብሊካን ጋርድ (ኮማንዶ) እና 55 ሚሊሻዎች ይገኙበታል።
ከተደመሰሱት መካከል በርካታ መኮንኖችና አዋጊዎች የሚገኙበት ሲሆን፣ አንድ የመቶ አለቃ ማዕረግ ያለው አዋጊ ለማምለጥ ሲሞክር መገደሉ ተረጋግጧል።
በሌላ በኩል ደግሞ አንድ የመቶ አለቃን ጨምሮ 29 የጠላት ኃይል አባላት በነፍስ የተማረኩ ሲሆን፣ ንቅናቄው ለምርኮኞቹ ተገቢውን ሰብዓዊ እንክብካቤ እያደረገላቸው መሆኑን ገልጿል።
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብን ከህልውና አደጋ ለመታደግ የሚደረገው የጠላትን ኃይል የማጽዳት ዘመቻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።

❤49👏7👍1🤔1
ሰበር ዜና!
በዳውንት ወረዳ የአፋብን ዕዞች በጥምረት ባደረጉት ውጊያ በአገዛዙ ጦር ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አደረሱ!
(መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም)
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ስር የሚገኙት የወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ እና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ፣ በዳውንት ወረዳ በገፍ ገብቶ በነበረው የአገዛዙ ጦር ላይ ታላቅ ድል ማስመዝገባቸውን አስታወቀዋል።
ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ለስምንት ሰዓታት በዘለቀው በዚሁ መጠነ ሰፊ ውጊያ፣ የምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር እና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት 206ኛ ኮር አሃዶች የተቀናጀ ኦፕሬሽን አከናውነዋል። በዚህም በአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ሰራዊት ላይ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ ማድረሳቸው ተገልጿል።
መረጃውን ይፋ እንዳደረገው የምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት ከሆነ፣ በጥምረት በተሰነዘረው ጥቃት ከ20 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ሲደመሰሱ፣ ከ32 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል። የአገዛዙ ጦር ቁስለኞቹን ወደ ዳውንት ጤና ጣቢያ በከፍተኛ ሁኔታ እያመላለሰ መዋሉንም ለኢትዮ 251 ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

❤45👏9🙏5👍1🔥1
ሰበር ዜና!
የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር ተወርዋሪዎች በባሶና ወረዳ መብረቃዊ ጥቃት መፈጸማቸውን አስታወቁ!
(መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም)
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ስር የሚንቀሳቀሰው የመሐመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር፣ በባሶና ወረዳ እሮብ ገበያ ቀበሌ ላይ በወሰደው ድንገተኛ ጥቃት ድል መቀዳጀቱን ገለጸ።
ክፍለ ጦሩ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ የአገዛዙ የመከላከያና የአድማ ብተና ኃይሎችን ያቀፈው "ጥምር ጦር" ከደብረ ብርሃን እና ከውሻውሽኝ በመነሳት እሮብ ገበያ ላይ የተሰበሰበውን ሕዝብ ከቦ ለምርጫ ካርድ እንዲመዘገብ ሲያስገድድና ሲያገላታ እንደነበር ተጠቁሟል።
ከኅብረተሰቡ በደረሰው መረጃ መሠረት የክፍለ ጦሩ 4ኛ ሻለቃ በቦታው በመድረስ በፈጸመው መብረቃዊ ጥቃት፣ የአገዛዙ ጦር የምርጫ ካርዶቹን በመበተን እንዲሁም ሙትና ቁስለኞቹን በመያዝ ወደ መጣበት እንዲመለስ መደረጉን ክፍለጦሩ አስታውቋል።
የአሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ጀግኖች ለአብይ አህመድ አስተዳደር ስልጣን ጠባቂ ለሆነው ሠራዊት በየቀኑ እንቅልፍ በመንሳት የውርደት ሽንፈትን እያከናነቡት መሆኑን የገለጸው መግለጫው፣ ሕዝባዊ ትግሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።

❤75🔥8🤯3👍2👏1
ከአንድ ሻለቃ በላይ ጠላትን በመደምሰስ የሰዴ ወረዳ መቀመጫ ሰዴ ከተማን ተቆጣጥረናል።
መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮርንና 206ኛ ኮር ሁለቱን ግዙፍ ኮሮች በማቀናጀት በተደረገው የተጠና ውጊያ የምስራቅ ጎጃም ዞን ሰዴ ወረዳ መቀመጫ ሰዴ ከተማን እና ሙሉ ወረዳውን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።
በጀኔራል መንበሩ ጌትዬ የተሰየመው ይህ ዘመቻ የጠላትን ካንፕ ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ የሰዴ ከተማን ማህበረሰብ ከአገዛዙ ነፃ ማድረግ ተችሏል።
ውጊያውን በቴዎድርስ ዕዝ በ201ኛ ኮር እና በ206ኛ ኮር ወታደራዊ አመራሮች በተናበበ መልኩ በመምራት የጠላትን ቅስም መስበር ችለዋል።
ፋኖ ለአላማው ታማኝ፣ ቆራጥና ውጊያ አዋቂ በመሆኑ በጠላት በኩል ድሮን በመጠቀም ከተማዋን ላለመልቀቅ ቢሞክርም ሳይወድ በግዱ ሊለቅ ችሏል።
አፋብን ቴዎድርስ ዕዝ በጠላት ላይ የሞራል፣ የስነ ልቦና፣ የውጊያ ጥበብ፣ የፖለቲካ የበላይነቱን በማረጋገጥ ድሮንና መድፍ ሳይበግረው የሰዴን ወረዳ ሕዝብ ከ አገዛዙ ጭቆና ነፃ በማውጣት የሰላም አየር እንዲተነፍስ ማድረግ ችሏል።
በዚህ አውደ ውጊያም :-
1ኛ መሳሪያና ተተኳሽ በተመለከተ፦
ብሬን ~5
ክላሽ ~ 100
ቆመህ ጠብቀኝ ~ 17
የተበላሽ መሳሪያ ~ 7
የመገናኛ ሬድዮ ~ ዐ1
የወገብ ትጥቅ ~ 16
የክላሻ ካዝና ~140 ከስቶር
የእጅ ቦንብ ~ 50
የብሬን ተተዃሽ - 20000
የክለሽ ተተኳሽ ~ 15000 በድምሩ 35000 ተተኳሽ መማረክ ተችሏል።
2ኛ ተሽከርካሪ
Long bas የአመራር መኪና ~ 3
ፓትሮል ዳብል ጋቢና~ 4
አንቡላስ ~ 1
ሞተር ሳይክል - 15
ኤፍ ኤስ አር- ዐ1
በድምሩ = ለጠላት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 09 መኪና 15 ሞተር ሳይክል መማረክ ተችሏል።
3ኛ ሎጅስቲክ
ጠላት ለሰራዊቱ ምግብና ሊጠቀምበት የነበረ
60 ኩንታል ጤፍ
10 ኩንታል ስኳር
ዐ1 ኮንቲነር ዘይት መማረክ ተችሏል።
4ኛ በእጅ የተያዘ ምርኮኛ
መከላከያ ~ o7 ከመካከላቸው አንድ መቶ አለቃ ማዕረግ ያለው= 100 አለቃ አንተነህ ገመቹ የሚባል አዋጊ መኮንን ተማርኳል።
ፍራ ኮማንዶ - 3
ፖሊስ ~ 5
ሚሊሽ ~ 10
ካድሬ ~4
በድምሩ 29 የጠላት ሀይል በነፍስ የተማረኩ ሲሆን ተገቢውን እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይገኛል።
5ኛ የተደመሰሰ ጠላት
90 መከላከያ
22 ፍራ ኮማንዶ
55 ሚሊሻ
ድምር 167 የጠላት ሀይልን በመደምሰስ ታሪክ መስራት ተችሏል።
ከተደመሰሰው ጠላት መካከልም በርካታ አዎጊ መኮነኖች የተደመሠሱ ሲሆን አንድ ሌላ ተጨማሪ መቶ አለቃ ማዕረግ ያለው አዋጊ ለማምለጥ እሩጫ ላይ እያለ መደምሰሱን አረጋግጠናል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የዕለቱ የተጋድሎ ውሎ በጎንደር ቀጠናም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፤ በማዕከላዊ ጎንደር ጫንድባ ላይ የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ እዝ ሁለት ክፍለ ጦሮች በቅንጅት ድንቅ ተጋድሎ አድርገዋል።
የጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ እዝ 202ኛ ኮር በጌምድር እና ዞብል ጃኖ ክፍለ ጦሮች በጫንድባ ከተማ በቅንጅት ባካሄዱት ውጊያ፤ የብልጽግናውን ሰሜን ምዕራብ እዝ ሠራዊት ላይጨከባድ ኪሣራ አድርሰውበታል፡፡ ክንቢ እና ዋንኪ በተባሉ ቀበሌዎች የተደረገው ትንቅንቅ፤ ከ25 በላይ የብልጽግናውን ሠራዊት እርምጃ የተወሰደበት ሲሆን፤ በፋኖ በኩል ቀላል መስዋዕትነት ብቻ ደርሷል፡፡
የጀግና ፋኖዎችን የተቀናጀና የተጠናከረ ፈጣን ምት መቋቋም ያልቻለው የብልጽግናው ሰሜን ምእራብ እዝ ሠራዊት፤ ወደመጣበት ለመመለስ ተገዷል፡፡
በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በሁለት እዝ ተከፍለው ሲታገሉ የነበሩት የፋኖ አደረጃጀቶች፤ አንድነታቸውን መስርተውና አርበኛ ዮሀንስ ንጉሱን መሪ አድርገው ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ፤ የጋራ ተጋድሎ በማድረግ፤ ታላላቅ ድሎችን እየተቀዳጁ ይገኛሉ፡፡ በጋራ ዘመቻ፣ በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል፣ የትግል ዓላማ ጥራት እና ሌሎች በትግሉ ዙሪያ አስፈላጊ በሆኑ ርእሰ ጉዳዮች ሰፊ የማጥራት ሥራ ሲሰራ የቆየው በላይ እዝ፤ በቅርቡ፤ የተለያዩ የኮር አደረጃጀቶችን ሪፎርም መሥራቱ ይታወሳል፡፡
የማጥራትና ማብቃት ሥራ ከመሥራትና የአደረጃጀት ሪፎርምን ከማስተካከልም ባለፈ፤ በመደበኛ ውጊያም፤ ከበለሳ እስከ ደንቢያ፣ ከጋይንት እስከ እስቴና እብናት፤ ከስማዳ እስከ ቋራና መተማ፤ ከአርማጭሆ እስከ ወገራ በተዘረጉ ሰፊ ቀጠናዎች፤ ተከታታይ ውጊያዎችን አካሂዷል፡፡ አፋብን በተከታታይ የሚያደርገውን በድል የታጀበ ፈጣን ማጥቃት ተከትሎም፤ የብልጽግናው ሰሜን ምዕራብ እዝ ሠራዊት አዛዡ ጄኔራል ብርሀኑ በቀለ በዳዳ፤ ‹‹ሀይል ይጨመርልን፤ የአየር ሀይል ድጋፍም ይደረግልን›› ብለው በጠየቁት መሠረት፤ የምሥራቅ እዝ ሠራዊት ከፍተኛ ቁጥር ይዞ ወደ ጎንደር መግባቱ ይታወቃል፡፡ የድሮን አሰሳ እና ቅኝትም በተከታታይ እየተካሄደ ሲሆን፤ ንጹሃንን ዒላማ ያደረጉ አራት የድሮን ጥቃቶች ተፈጽመዋል፡፡
በአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ እና ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ በኩል ደግሞ፦ በጋራ ውጊያዎች ተካሂደዋል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ የ106ኛ ኮር አሃዶች እና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ የ206ኛ ኮር አሃዶች በጥምረት በዳዉንት ወረዳ ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል።
የአፋብን ዕዞች የተቀናጀ ተጋድሎ በዳዉንት ወረዳ ዛሬ መጋቢት 30/2018 ዓ.ም ከጧቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ቀን 8:00 ድረስ በገፍ የገባዉን የአቢይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ ሲያደርጉት የዋሉ ሲሆን ጠላት ላይ በጋራ በመሆን ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ አድርሰውበታል::
በአውደ ውጊያውም ከ20 በላይ የጠላት ሃይል ሲደመሠሱ ከ32 በላይ ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ተደርጓል። ጠላት ከድምሰሳ የተረፈ ቁስለኛዉን ወደ ዳዉንት ጤና ጣቢያ ሲያመላልስ ውሏል።
በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ በኩል ደግሞ
መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ጀግኖቹ እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር 4ተኛ ሻለቃ በባሶና ወረዳ እሮብ ገበያ ቀበሌ ላይ መከላከያና አድማ ብተና ከደብረ ብርሃንና ከውሻውሽኝ በመምጣት ህዝብን ከቦ ለብልፅግና የውሸት ማጭበርበርያ ምርጫ ካርድ በግድ አውጡ እያለ ህዝባችንን ሲያገላታ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት የክፍለ ጦሩ 4ተኛ ሻለቃ በቦታው በመድረስ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም የምርጫ ካርዱን በትኖ ሙትና ቁስለኛውን እየሰበሰበ ወደ መጣበት ተመልሷል።
ቀጠናውን የሚያስተዳድሩት ጀግኖቹ ጣይቱ ክፍለ ጦር የአብይ አህመድን ጡት ቆራጭ ስልጣን ጠባቂ ሰራዊት በየቀኑ እንቅልፍ እየነሱት ይገኛሉ። በዚሁ ቀጠና በሌላ ግንባር፦
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘረያዕቆብ 1ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለጦር የአገዛዙን ዙፋን ጠባቂ መከላከያ እና አድማ ብተና እንዲሁም ሚሊሻ ከደብረብረሀን አሰባስቦ አምጥቶ ነጎድጓድ ክፍለጦር ላይ ከበባ ለመፈፀም የሞከረ ሲሆን ልዩ ቦታው ማጥቅሪያ እና ግፍት ላይ በመጣበት አግባብ በጀግኖቹ ተመክቶ ባለበት እንዲቆም ተደርጓል። ዝርዝሩን ከሌሎች የግንባር መረጃ ጋር የምንመለስበት ይሆናል።
ሕዝባችን ከደረሰበት የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የተጠኑ አውደውጊያዎችን በማድረግ ጠላትን የማፅዳት ዘመቻው ይቀጥላል።
"በአጠቃላይ በዛሬው ውሎ ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበት ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ ተደርጓል። የጀግናው ሠራዊታችን ግስጋሴም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

❤51👏4👍2
"ሠራዊታችን በማንኛውም ግንባር የሚሰነዘሩበትን ጥቃት ለመቀልበስ በተሟላ ዝግጁነት ላይ ይገኛል። ወቅታዊ መረጃዎችን ከግንባር ማቅረባችንን እንቀጥላለን።
ለህዝባቸው ክብር ሲሉ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖቻችን ዘላለማዊ ክብር ይሁን፤ ለቆሰሉትም ፈጣን ማገገምን እንመኛለን።"
ድል ለአፋብን!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ሰላም ለሀገራችን!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ወታደራዊ ቃል አቀባይ
መጋቢት 30/2018 ዓ.ም

❤49👍11🏆3👏1🤯1