በዚችም ቀን የክብር ባለቤት የሆነው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ የአለም ፈጣሪ የሁሉ ህዢ ሁሉ በእጁ የሆነ አምላክ በቀራንዮ አደባባይ በዕፀ መስቀል ላይ እጆቹ ተዘርግተው ችንካር ላይ ዋሉ መከራ እንግልት ግርፋት ደረሰበት ፈጣሪዋ እጆቹ ተዘርግቶ በአየችው ሰዓት ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ግዜ ሥጋ ከመለኮት ሳትለይ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር እርሱ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያለ ልዑለ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በጌትነቱ ዙፋን ተቀምጦ ያለ ለእርሱም ምስጋና የክብር ክብር ገንዘቡ የሆነ ራሱን ስውቶ ያዳነን የመንግሥቱን ደጆች በፈሳሽ ደሙ የከፈተልን ለእርሱ ስግደት አምልኮት ይገባዋል ለዘላለሙ የመስቀሉ በረከት በላያችን ላይ ይደር እያልኩ በዛሬው ዕለት ይኽን ታላቅ ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በመሐል ስድስት ኪሎ አንድነቱ እና ገዳማዊ ሕይወትን ጠብቆ ለዘመናት የቆየው ታላቁ ገዳማችን ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ስብከተ ወንጌል ክፍል ትምህርተ ወንጌል ለሁሉም ይድረስ ዘንድ በማሰብ ለሁለት ቀን የተዘጋጀውን ጉባዔ የመዝግያ መርሐ ግብር ተከናውኗል በጉባዔውም መምህራን ወንጌል ስለ ይቅርታ ስለሰላም ስለፍቅር በደንብ አበክረው አስተምረዋል ዘማሪዎችም ወቅቱን የዋጀ ሕማም መስቀሉን መከራውን እንግልት ስቃዩን የሚገልጹ መዝሙሮች ተዘምረው በገዳሙ አስተዳደር መጋቤ ኅሩያን አባ ኤልያስ በልሁ እና በገዳሙ አበው መነኮሳት በጸሎት እና በምስጋና የጉባኤው ፍጻሜ ነበር በተለየየ የሥራ መደራረብ እና በቦታው ተገኝታችሁ ጉባኤውን መታደም ላልቻላችሁ መንበር ሚዲያ በዩቱዩብ ቻናል በቅርብ ቀን ስለሚለቀቅ like share subscrib በማድረግ ዕለታዊ እና ወቅታዊ ትምህርተ ወንጌልን ከአውደ ምህረቱ ሳይሸራረፍ በቀጥታ ያገኛሉ መንበር ሚዲያን ስለሚከታተሉ ከልብ እናመሰግናለን