iDesire Computer Ethiopia
9.99K subscribers
6.1K photos
111 videos
49 files
1.81K links
ምን አይነት ላፕቶፕ ለመግዛት አስበዋል?ለትምህርት, ለቪዲዮ ኤዲቲንግ, ለኦንላይን ስራ, ለሪሰርች መስሪያ, ለቢሮ ስራ, ጌሚንግ - እኛን ሳያማክሩ አይወስኑ

ይደውሉልን 0973424250
Download Telegram
ኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን ለመገበያያነት ለመጠቀም የሚያስችል መመሪያ ልታወጣ እንደምትችል የብሔራዊ ባንክ ገዢ ጥቆማ ሰጡ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “የክሪፕቶ አሴትን” እና የዲጂታል ገንዘብን በኢትዮጵያ መጠቀም የሚያስችል መመሪያ ወደፊት ሊያወጣ እንደሚችል የተቋሙ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ ገለጹ። ብሔራዊ ባንክ መመሪያውን የሚያወጣው በማዕከላዊ ባንኪንግ፣ በገንዘብ ፖሊሲ እና በገንዘብ አስተዳደር ያሉ ዓለም አቀፍ “ለውጦችን” እና “እድገቶችን” እያየ መሆኑን አቶ ማሞ ተናግረዋል።

አቶ ማሞ ይህን ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአዋጅ ማሻሻያ ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8፤ 2017 በተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀበት ወቅት ከፓርላማ አባል ለቀረበ ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ ነው። በዘጠኝ ክፍሎች እና በ57 አንቀጾች የተዘጋጀው ይህ አዋጅ፤ ከ16 ዓመት በፊት የወጣውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅን ያሻሻለ ነው።

የአሁኑ አዋጅ ካካተታቸው አዳዲስ ድንጋጌዎች መካከል ክሪፕቶ ከረንሲ እና የዲጂታል ገንዘብን መጠቀም የተመለከተው አንዱ ነው። አዋጁ “አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ብሔራዊ ባንክ ካልፈቀደ በስተቀር፤ ክሪፕቶ ከረንሲ ወይም ሌላ ማንኛውንም ዲጂታል ወይም የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ በመጠቀም ክፍያ መፈጸም አይችልም” ሲል ክልከላ ያስቀምጣል።

አዋጁን በመተላለፍ በእነዚህ መንገዶች ክፍያ የፈጸመ ማንኛውም ሰው፤ ከሶስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና ከአስር ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣም ተደንግጓል። ክሪፕቶ ከረንሲን በተመለከተ በአዋጁ የተቀመጠውን ድንጋጌ በዛሬው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የጠቀሱት ዶ/ር ፈትሂ ማህዲ የተባሉ የፓርላማ አባል፤ አፈጻጸሙን እና ቁጥጥርን የተመለከቱ ጥያቄዎች አቅርበዋል።

“የዲጂታል ከረንሲ [ግብይት] ቴክኖሎጂ ያመጣው ነው። ግዴታ መጠቀም አይቀርም። አለም በ21ኛው ክፍለ ዘመን እየሄደበት ያለ ነው። በቢት ኮይን፣ በዲጂታል ከረንሲ፣ በክሪፕቶ ከረንሲ እየተገበያየ ነው ያለው” ያሉት ዶ/ር ፈትሂ፤ የዲጂታል ገንዘቦችን የሚጠቀሙ ሰዎች “አድራሻቸው በግልጽ ሳይታወቅ፤ በኦንላይን፣ በምናባዊ የሚፈጽሙት ነገር መሆኑ” ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ጠቁመዋል።

የዲጂታል ገንዘብን የሚጠቀሙ ሰዎች “ሀገር ውስጥም ሆነው፣ ከሀገር ውጭም ሆነው፣ ትራንዛክሽኑ በማይታይ በምናባዊ መንገድ” ክፍያ እንደሚፈጽሙ የገለጹት የፓርላማ አባሉ፤ “ይህንን ብሔራዊ ባንክ እንዴት ነው የሚቆጣጠረው?” ሲሉ ጠይቀዋል። “[በአዋጁ] ‘ክፍያ መፈጸም አይቻልም” ተብሏል። ብሔራዊ ባንክ እንዴት ነው የሚፈቅደው? እንዴት ነው የሚቆጣጠራቸው? አሰራሩ፣ ስርዓቱ ምን ይመስላል? ለቁጥጥርስ ይመች ይሆናል? ቴክኖሎጂውስ አለን ወይ? መቆጣጠርስ በትክክል እንችላለን ወይ? መንግስት በትክክል ማግኘት የሚገባውን ግብር ማስከፈል እንችላለን ወይ?” ሲሉም ተጨማሪ ጥያቄ ሰንዝረዋል።

ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የብሔራዊ ባንክ ገዢ “ክሪፕቶ አሴት” ወይም “ቢትኮይን” የሚባለውን “በሁለት መንገድ” መመልከት እንደሚገባ ተናግረዋል። “ክሪፕቶ ማይኒንግ” የሚባለው የዳታ ማዕከል ኢንቨስትመንት “ምንም ችግር የሌለበት” እና በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ “በስፋት” “በስራ ላይ ያለ” መሆኑን አቶ ማሞ አስረድተዋል። ይህ ኢንቨስትመንት፤ በኢትዮጵያ “የኃይል አቅርቦት” እና “ግሪን ኢነርጂ” መስፋፋት ጋር የተገናኘ መሆኑንም ገልጸዋል።

“አሁን ኢትዮጵያ በስፋት የክሪፕቶ ማይኒንግ ኢንቨስትመንት መዳረሻ እየሆነች ነው ያለችው። ይሄ ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ ነው” ሲሉም የብሔራዊ ባንክ ገዢው ለፓርላማ አባላቱ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የክሪፕቶ ማይኒንግ በዚህ ደረጃ ላይ ቢገኝም፤ “የክሪፕቶ አሴትን” እንደ ገንዘብ መጠቀም በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ የተፈቀደ አለመሆኑን አቶ ማሞ አስገንዘበዋል።

“በአጠቃላይ የዓለም የገንዘብ ፖሊሲ ዳይናሚክ ምን እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል። ለምሳሌ አሁን የምንጠቀመው ገንዘብ (currency) ብር ነው። አሁን ብዙ ማዕከላዊ ባንኮች እየጀመሩ ያሉት የማዕከላዊ ባንክ ዲጄታል ገንዘብ አለ። አሁን ሰው የሚጠቀመው ካሽ እየቀረ፤ ወደ ዲጂታል ገንዘብ ሺፍት እየተደረገ ነው ያለው” ያሉት አቶ ማሞ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይህን የዓለም አቀፍ ሁኔታ ከግምት በማስገባት “በተለየ መልኩ” መመሪያ እንደሚያወጣ ጥቆማ ሰጥተዋል።

“ይሄ የክሪፕቶ አሴትን፣ ቢት ኮይንን፣ የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ከረንሲን በተመለከተ የዓለም የማዕከላዊ ባንኪንግ፣ የገንዘብ ፖሊሲ እና የገንዘብ አስተዳደር በሂደት እየተቀየረ ስለሚሄድ ዳይናሚክ የሆኑ ለውጦችን እና ዴቨሎፕመንቶችን እያየ ብሔራዊ ባንክ እንደሌሎቹ ማዕከላዊ ባንኮች፣ እንዳስፈላጊነቱ መመሪያ ሊያወጣ ይችላል” ብለዋል የብሔራዊ ባንክ ገዢው።

በአዲሱ አዋጅ “ክሪፕቶ አሴትን መጠቀም አይቻልም” ያሉት አቶ ማሞ፤ በአዋጁ የተቀመጠውን ድንጋጌ አፈጻጸም በተመለከተ ብሔራዊ ባንክ “ቁጥጥር እንደሚያደርግ” አስታውቀዋል። የክሪፕቶ ገንዘብ መጠቀም አሁን ቢከለከልም፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ ሌሎች ሀገራት መሰል ባንኮች “በሂደት ሁኔታዎችን እያየ” እና “ነገሮችን እያገናዘበ” መመሪያ እንዲያወጣ በአዲሱ አዋጁ ኃላፊነት እንደተሰጠውም ለፓርላማ አባላት አስረድተዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Source: Ethiopia_Insider
👍9
☄️ @ 7th Generation ☄️

HP EliteBook 
Core i5 @ 7th Gen , up to 3 GHz with Turbo
Ram : 8GB ✔️
Storage: 500 + 256GB SDD✔️
Screen Size: 14.1 ’, Full HD
Color: Silver
Weight: 1.48 kg ( Very-slim )
Battery : 6 + hrs
Keyboard Backlight:  Available
SSD Support: Yes
Fingerprint Reader: Yes
SIM Support: Yes

💵Price: 30,500 birr

ይደውሉልን @ 0973424250

iDesire Computer Ethiopia
Elevating Your Tech Experience

With One Year Full Warranty

ያላችሁበት ከተማ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ በታማኝነት እንልካለን  ::

አጭር መልዕእክት ለመላክ 👇 @iDesireComputerBole

የTelegram ቻናላችን 👇
https://t.me/ethicomputer

#hp #elitebook
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥2
Forwarded from Birhan Nega (Birhan Nega)
HP 230 Watt Blue Pin Charger

8,000 birr

0973424250
1
🔼🔼Best Budget Gaming Laptop 🔼🔼

Asus Vivobook
Core i5 @ 11th Generation - 11400H Processor
6 Cores, 12 Logical Processors, 12M Cache, up to 4.5 GHz
Ram : 16GB DDR4
Storage : 512GB SSD
Display : 15.6", FULL HD
‼️Dedicated Graphics Card : 3050RTX 4GB ‼️
Battery : 6+hrs

💵Price : 89,999 birr

iDesire Computer Ethiopia
Fueling Your Digital Triumph 🚀

📞 0973424250

📍 https://g.co/kgs/hjqW4bB

With One Year Full Warranty

ያላችሁበት ከተማ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ በታማኝነት እንልካለን ::

Telegram 👇
https://t.me/ethicomputer

ለአጭር መልዕእክት 👇
@iDesireComputerBole

#Asus #gaming
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍1🔥1
#Telegram_Update

telegram ሰሞኑን በለቀቀው update ላይ አዳዲስ features አምጥቷል። ከነዚህም መካከል:-

Collages in Stories
በአንድ story ላይ እስከ 6 የሚደርሱ ፎቶ እና ቪድዮዎችን በአንድ ላይ post ማድረግ የምንችልበት feature ነው። አጠቃቀሙም story ወደምናረግበት tab ከገባን ቡኋላ ከላይ በኩል ያለውን የcollege ምልክት መንካት እና video ከሆነ video የሚጀምርበትን ጊዜ፣ የድምፅ መጠን በማስተካከል post ማድረግ እንችላለን።

Captions Above Media
እስከ አሁን ድረስ ማንኛውም telegram ላይ ያለ media caption መፃፍ የምንችለው ከmedia በታች ብቻ ነበር። ይሁንእንጂ ይህ update ከላይ caption ከታች media ማድረግ የሚያስችለንን feature አካቷል።

AI-Powered Sticker Search
sticker search ስናደርግ በAI የተደገፈ ፍለጋዎችን የምናገኝበት feature ነው። ይህም በቀላሉ የፈለግናቸውን stickers እንድናገኝ ያስችለናል።

©bighabesha_soft
👍6
OpenAI ChatGPTን በWhatsApp💬 መጠቀም እንደሚቻል አስታወቀ።

ChatGPT በWhatsApp ለመጠቀም
✔️በዚህ ቁጥር (1-800-242-8478)  text ማድረግ ወይም
✔️ከላይ attach ያደረግ ነውን QR code scan ማድረግ

WhsatsApp ላይ ለጊዜው መጠቀም የሚቻለው በtext ብቻ ሲሆን በድምፅ፣ በፎቶና በፋይል access ማድረግ አይቻልም።
1
⚡️⚡️Brand New Laptop☄️☄️

🔼HP NoteBook 250 G10 🔼

✔️  Core i7-1355U

✔️  13th Generation

✔️  512 GB SSD storage

✔️   16 GB RAM 

✔️  15.6inch screen

✔️   Have  keyboard Backlight and fingerprint reader

✔️    BEST BATTERY LIFE

✔️Intel(R) UHD Graphics

💵PRICE : 99,999 birr

iDesire Computer Ethiopia
Fueling Your Digital Triumph 🚀

📞 0973424250

📍 https://g.co/kgs/hjqW4bB

With One Year Full Warranty

ያላችሁበት ከተማ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ በታማኝነት እንልካለን ::

Telegram 👇
https://t.me/ethicomputer

ለአጭር መልዕእክት 👇
@iDesireComputerBole

#hp # notebook
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2
✔️12th Generation RTX 3050 Ti 4GB

✔️144Hz - Refresh Rate

✔️Status : Brand New

VICTUS by HP Gaming Laptop
Core i7 @ 12th Gen, 12 Cores, 16 Logical Processor
✔️Ram : 16GB DDR5
Storage: 1TB PCIe-NVMe M.2 SSD
Screen Size: 15.6-inch FULL HD , 1920 × 1080 , 144Hz Refresh Rate

✔️Graphics: NVIDIA RTX 3050Ti 4GB

Battery: 4+hrs

💵Price: 119,999 birr

📞 0973424250

📍https://g.co/kgs/hjqW4bB

iDesire Computer Ethiopia
Elevating Your Tech Experience

With One Year Full Warranty

ያላችሁበት ከተማ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ በታማኝነት እንልካለን  ::

Telegram 👇
https://t.me/ethicomputer

ለአጭር መልዕእክት 👇
@iDesireComputerBole

#hp #victus
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መለስ ብየ ሳስብ አብዘሃኛውን የስራ ህይወቴ ከአንድ ስራ በላይ(over employed: multiple Full Time and part-time Jobs at the same time ) እየሰራሁ እንደነበር አስተዋልኩ:: ኮቪድ በሰው ልጆች ህይዎት ላይ ካመጣቸው ለውጦች አንዱ አብዘኛው ሰራተኛ ስራን ከቤት የመስራት(remote-work) ልምድ እንዲያዳብር ማድረጉ ነው።

Remote Work ጋር ተያይዘው ከመጡ መልካም ጉዳዮች አንዱ ከአንድ ስራ በላይ በተመሳሳይ የስራ ሰዓት መስራት ሲሆን አብዘሀኛው በ IT ዘርፍ የተሰማሩ ሰራተኞች የዚህ መልካም እድል ተጠቃሚዎች ናቸው።ተመሳሳይ አይነት privilege በሚሰጥ ሌላ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩም ሰራተኞች የዚህ መልካም እድል ተጠቃሚዎች ናቸው።
Over Employment ሁለትና ከሁለት በላይ ስራን መስራት የራሱ የሆነ መልካም ጎኖች ቢኖሩትም የራሱ የሆነ መልካም ያልሆኑ ገጾችም አሉት።

ከመልካም ጎኖቹ ስንጀምር

ከአንድ በላይ ስራን በመስራት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ማግኘት የሚቻል ሲሆን ይህም የፋይናንስን ግቦችን ለማፋጠንና ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ ደህነንት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል።

በተለያየ ድርጂት መስራት በአጭር ግዜ የተለኣይዩ ክህሎቶችን እንድሳድግና ባለብዙ ክህሎቶች እንድሆን ያደርጋል።

ከአንድ በላይ ስራን በመስራት የስራ ደህንነትን ይፍጥራል በዚህ ባልተራጋጋ ኢኮኖሚ ሁለት ስራ ቀርቶ አብዘሀኛው ወጣት አንድም ስራ ባጣበት ዘመን ከአንድ በላይ ስራን መስራት የተረጋጋና ከስጋት ነጻ የሆነ ኑሮ ለመምራት ይጠቅማል።

ከአሉታዊ ገጾቹ መካከል አብዘሀኛው ሰው ቅንጦት አድርጎ የሚያስበው የስራና የግል ህይዎት(work-life balance) ሚዛን መሳትና በከፍተኛ የስራ ጫና የሚመጣ ድካም ዋናወቹ ናቸው።

አንድ ስራ ብቻ መስራትን ስራ መፍታት የሚመስላቸው የስራ ባልደረቦች አሉኝ እዚህ ደረጃ የሚደረሰው ጠንካራ የሆነ የ ሰዓት አጠቃቀምና የለት ተለት ስራን አቅዶ የመስራትን ክህሎት በማዳበር እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ጫና ዉስጥ ሁኖ ስራን ማከናዎን ልምድን በማዳበር ነው

@mohammedBurahaba
👏3👍2
🔖TradingView በፕላትፎርሙ ወደ2500 ቀናት ገደማ እንደተጠቀምኩ አስታወሰኝ። ጊዜ ይነጉዳል። በእነዚህ ጊዜያት በትሬዲጉ አለም በተለይ ደግሞ በክሪፕቶከረንሲው መስክ ማየት ያሉብኝን ሁሉ ሁነቶች ከታች እስከታች አይቻለው ብል ማጋነን አይሆንብኝም። በአፍጢሜ ተደፍቻለው፤ ጣሪያ እስክነካ ዘልያለው፤ በቃኝ ለማለት ከጫፍ እስክድረስ አማርሬያለው፤ አፌን በእጄ እስክይዝና ከማስበው በላይ እንዳልም የሚያረጉ ትርፋማ ግብይቶችን አይቻለው፤ ብቻ ምን አለፋችሁ እጅግ በጣም ለብዙ ሁነቶች እማኝ ሆኛለው።

📌ቅሉ ግን 2500 ቀናት ከቻርት ጋር መፋጠጡ ሳይሆን በእነዚህ የከፍታ እና ዝቅታ ቀናት መያዝ ያሉብንን ነገራቶች ይዘናል ወይ? የሚለው ቁምነገር ነው።

🗣️እናማ ምን ልልህ ነው ሶቅራጠስ እንዳለው "እኔ የማውቀው አለማወቄን ነው።"

🎯ትሬዲንግ እጅግ በጣም ሰፊ፤ የማያልቅ፤ በየእለቱ የሚጎለብት እና በዛ ውስጥም የሚለዋወጥ ግን ደግሞ ካወክበት አይደለም ያንተና የቤተሰብህን የማህበረሰብ እና የቀዬህንም ኪስ በፋይናንሱ ነፃ ማውጣት የሚያስችልህ መስክ ነው። ትእግስት፤ የማወቅ ፍላጎት እና ጉጉት በስተመጨረሻም ትጋት ካሉህ እመነኝ አይደለም 2500 ቀናት በ250 ቀናትም ሚስጥሩን አውቀኸው ቁልፉን በእጅ ማስገባት ይቻልሀል።

እማኝ ነኝና ወንድማዊ ምክሬን ታደምጠኝ ዘንድ ለመጠየቅ ወደድኩ - በትሬዲንጉ ዓለም ታገስ፤ ተማር ፤ ታትር!!! ያንን ካደረክ መልሱ እሩቅ አይሆንም።

💬በስተመጨረሻም: Alt Season የጀመረ ለመሠላችሁ ገና ምኑንም እንዳልጀመርነው ለማስታወስ እወዳለው። አለፍ ሲል ደግሞ ከሰሞኑ እንዳያችሁት አይነት ደም በደም የሆነ የገበያ ሁነት ከዚህ በፊትም የነበረና ያለ ሁነት ነው። የራሳችሁን ጥናት አድርጋችሁ የተለያዩ ጠንካራ የምትሏቸውን አልት ኮይኖች ምረጡ: ካፒታላችሁን ከፋፍላችሁ ግዙ: ሚያዚያና ግንቦት ላይ ተመለሳችሁ ተመልከቱት። It's simple as that.

-ET
👍4😁3