ኢትኤል
2.28K subscribers
97 photos
11 files
8 links
ስለ ጥንታዊው የኢትኤል ስልጣኔ እናወራለን! እንዘምራለን!
Download Telegram
መልካም ዜና ፥ ለሁሉም የሚድያ አካላት

💚💛❤️

📌ጉዳዮ:- የእንቦጭ አረም ማጥፊያ መድኃኒት በምናስተዋውቅበት ፕሮግራም የሚድያ ሽፋን እንድትሰጡን መጠየቅን ይመለከታል።


ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደ ሞከርነው የእንቦጭ አረም በሀገራችን ትልቁን የጣና ሐይቅ ጨምሮ በርካታ ሀይቆቻችንን በመውረር በሀይቁ ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ይታወቃል።የእንቦጭ አረም በተለያዮ ሀይቆች ላይ እየተንሰራፋ በመሆኑ ከተሰማ ጀምሮ አረሙን ለማጥፋት የተለያዮ ሙከራዎች ቢደረጉም ውጤታማነታቸው በሚፈለገው ልክ መሆን አልቻለም ።


አረሙ ኢትዮጵያ ያሏትን የውሃ ሀብቶች እያጠፋ መሆኑ ያሳሰበው የኢትዮጵያ ሊቃውንትና ምሁራን ማህበር አረሙን ለማጥፋት የሚያስችል ሀገራዊ ፕሮጀክት ቀርፆ ታዋቂ ባለሙያዎችን በማሳተፍ የምርምር ስራዎችን ሲያካሂድ ቆይቶ አረሙን ለማጥፋት የሚያስችል መድኃኒት ለማግኝት በቅቷል ።


የማህበሩ መስራችና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት እና የባህል መድኃኒቶች ላይ በመመራመር ስኬታማ ግኝቶችን በማበርከት የሚታወቁት መርጌታ በላይ አዳሙ ማህበሩ በቀረፀው የእንቦጭ አረም ግኝት ፕሮጀክት ሙያዊ አቅማቸውን አሟጠው አረሙን ለማጥፋት የሚያስችል መድኃኒት አግኝተዋል።


መርጌታ በላይ አዳሙ ያገኙት መድኃኒት በባሕር ዳር ዮኒቨርስቲ ፣ በአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት እውቅና የተሰጠው ሲሆን ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት የባለቤትነት የምስክር ወረቀት ተሰጧቸዋል።የኢትዮጵያ ሊቃውንትና ምሁራን ማህበርም መርጌታ በላይ አዳሙ ያገኙትን የእንቦጭ አረም ማጥፊያ መድኃኒት ለህዝብ በይፋ ለማሳወቅ ለማክሰኞ መስከረም 12/1/2013 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል ።


በመሆኑም ጋዜጣዊ መግለጫው በሚሰጥበት ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ከጥኋቱ 2:30 ባለሙያ መድበው የሚድያ ሽፋን እንዲሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን።

🕹አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ


《..#ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》
♡┈••✦ ሼር✦••┈♡

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
« ቻይና ልትጸድቅበት አይደለም! »

በማዕበል ፈጠነ

💚💛❤️

✦ከዐራት ዓመት በኋላ የቻይና ደራሲያን በአማርኛ ቋንቋ ረጅም ልበ ወልድ: ወግና የጉዞ ማስታዎሻ ምናምን ጽፈው ቋንቋውን ይራቀቁበታል። ከዚህ ቀጥሎ ጀርመኖች በግእዝ ቋንቋ መወድስ ይዘርፋሉ። የግእዝ ክሕሎታቸው እየዳበረ ሲሄድ በብራናው የተከተቡ ምሥጢራትን መመርመር ይጀምራሉ። ከዚያስ? በእኔ ግምት "ኁልቆ አእጋሪሃ ለፀሐይ እስራ ወክልኤቱ ምእት" ከሚለው ውስብስብ የፀሐይ አውታር ውስጥ ዘው ብለው ጥልቅ ይላሉ።

✦ ይህን በአኀዝ የተጠቀለለ ፍልስፍና ዐርባ ዓመትም ቢሆን ዘግተው ማፍታታት ይጀምራሉ። ሲደርሱበት ዛሬ በነዳጅ የሚሠሩ የዓለም ቁሳቁሶችን ከሀ እስከ ፈ በፀሐይ ብርሃን ብቻ እንዲሠሩ ያደርጓቸዋል። ያም ማለት በፀሐይ ብርሃን ብቻ የሚበር አይሮፕላን ያመርታሉ። እየቆዩ በአየር ያሉ ደቃይቅ ብርሃናትን ብቻ እየለኩ ከቀዝቃዛ አየር ጋር አስማምተው ፈጣን ፈጣን በሰማይ በራሪ መርከቦችን ያመርታሉ።



✦ ክንፋቸው ከነፋስ አውታር ፍጥነታቸው ከብርሃንና ከነፋስ ሲዳቀል መንኮራኩራቸው ነፋስ መሥመራቸው የፀሐይ አውታር ይሆናል። እኒህ የፀሐይ እግሮች(አውታር) ቀላል ቀላል ነገሮችን መሸከም የሚችሉ ሲሆኑ በአውታራቸው ልክ ቅለትና ክብደት ያለው ቁስ ይሸከማሉ። ያንንም እንደ ካስማ ወጥረው በአውታራቸው ይሸክሙታል።


✦ ካስማ ድንኳኖኝችን ወጥሮ እንዲሸከም አውታሩም በልኩ የተሠሩ ማናቸውንም ቁሳቁስ ይሸከማቸዋል። ይህ ሁሉ የሚመጣው ግን ቋንቋ ከማወቅ ነው። ቻይና አማርኛ ቋንቋን መማር ማስተማር መጀመሯ ልትጸድበት ሳይሆን በኢትዮጵያ ሊቃውንት የተከተቡ ስውራንን ወደ ሥጋዊ ዓለም ለመሳብ ነው። ግን ግእዝ ቋንቋ ማስተማር ብትጀምር ይበልጣት ነበር።
.

《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

♡┈••✦ #ሼር ✦••┈♡

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
« የምስራች!»

የግዕዝ ትንሳኤ

💚💛❤️

✦በትግራይ ክልል ከ2 ሽህ በላይ ለሚሆኑ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የግዕዝ ቋንቋን በመደበኛ ትምህርት መርሃ ግብር ከዘንድሮው አመት ጀምሮ ለመስጠት እንደ ተዘጋጀ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አብስሯል! ትግራይ አሐዱ ብሎ ስለ ጀመረው ከልብ እያመሰገነ ነገር ግን በመላው ኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ ሊካተት ይገባል።


ግዕዝ
■ሔኖክ ስነ ህዋ የተመራመረበት
■ተዋናይ በቅኔ ሰረገላ የመጠቀበት
■ሊቁ ክፍለ ዮሐንስ የተቀኝበት
■በምስጢር የተሞሉ የብራና መፃሕፍት የተከተቡበት.....
.

《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》
♡┈••✦ #ሼር ✦••┈♡

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍2
«ደብረድማህ(ዲማ ጊዮርጊስ)»

💚💛❤️

በዜማ ምሰሶ ÷ በትርጉም ተማግራ፤
ገድ አፋፍ ላይ ቁማ ÷ ቅኔ ምታበራ።
የሊቆች መጠጊያ ÷ እልፍኝ የነበረች፤
"አስኳላ" ገፍትሯት ÷ ጋጥ ሁና ከረመች።

በፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ
.

《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》
♡┈••✦ #ሼር ✦••┈♡

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
" የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም 3፥7)


《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍1
«አሐሜኔስ ኢትዮጵያዊ»

💚💛❤️

♡┈••✦#share_ሼር_Shere ✦••┈♡


✦ በ1900 ከክርስቶስ ልደት በፊት አሐሜኔስ የተባለ ኢትዮጵያዊ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሰው ነው። ይህ አሐሜኔስ የተባለው ኢትዮጵያዊ 16 ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሲሆን፤ ፀሀይን ለመዞር ስንት ግዜ እንደሚፈጅባቸው፤ በስንት ምህዋር እንደሚዞሩና በውስጣቸው ያሉትን ፍጥረታትን ጽፍል።


#NASA እንኳን አስካሁን እርገጠኛ የሆነው ዘጠኝ ፕላኔቶች እንዳሉ ነው ነገር ግን ገና 7 ፕላኔቶች ይቀራሉ።


✦ አሐሜኔስ መዝገበ ሰማያትና አውደ ከዋክብት የተባለው መፀሀፈ በታወቀው ቦታ ዋልድባ እሚገኝ ሲሆን ይህው መፀሀፍ ደግሞ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካ ውስጥ በስርቆት ተወስዶ በሚስጥር ተቀመጦ ይገኛል።


✦ እነዚህም ባለ ሥስት ማዕዘን ድንጋይ ያለስሚንቶና ያለጭቃ ሰው ሊሸከመው በማይችል በትልልቅ ድንጋይ ተነባብሮና ተደራርቦ በሚያስደነቅ ሁኔታ ታንጿል።የጥንት ስሟም ምሥር የተባለችውም ግብጽ ኢትዮጵያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ምሥርን ስላበቀሉባት ምሥር እየተባለች ትጠራ ነበር።


✦ ኢትዮጽያ ውስጥም እንደ ምሥር/ግብጽ/ሀውልቶች/ ከብዙ ድንጋዮች ሳይሆን ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተሰሩ 700 ፒራሚዶች 600 የአክሱም አይነት ሀውልቶች ከነ ቤተመንግስታቸው እና በዙ የላሊበላ አይነት ሀውልቶች ይገኛሉ። ይህም አንድ ግዙፍ ከተማ ማለት ነው።


✦ ነገር ግን እነዚህን ሀውልቶች ኢትዮጵያኖች አስቀብረዋቸዋል። እነዚህም ከተማዎች የጥንቷን ኢትዮጵያ ጥበብ ሸክፈው ይዘዋል። እነዚህን ሀውልቶች የት እንደሚገኙና በስንት ሜተር እርቀት ቆፍሮ ማውጣት እንደማቻል ዋልድባ ባለው መዝገብ ላይ እሚገኝ ሲሆን፤ ገር ግን ጊዜው እስኪደርስ በሚስጥር ተይዟል።


✦ ለምሳሌ ያህል ደግሞ በቅርቡ በቁፍሮ የወጣውን የዳግማዊ ላልበላን ሀውልት ማየት ይቻላል። ዮሐንስ በራዕዩ ሲከፈት ያየው ቤተ-መቅደስ እነዚሁ የላልበላን ሀውልቶች እንደሆኑ አባ ተስፍ ስላሴ ሞገስ ያስረዳሉ።


✦ እንደ ምንጭነት የተጠቀሰውም የምሥጢሮች ሁሉ ቁልፍ የሆነው መፀሀፈ ምሥጢር ዘአዶናይ ራፍኤል ሲሆን ይህም መፀሀፈ እጅግ በጣም ብዙ ምሥጢሮችን የያዘ ሲሆን መፀሀፍ ሙሉ በሙሉ ቢተረጎም እጅግ በጣም የሚያሥፈራና አስደንጋጭ ታይቶና ተስምቶ የማይታወቅ ከሰው ልጆች በላይ የሆነ ምሥጢር አለው፤ ሁሉም ነገር እንደ ፈጣሪ ፋቃድ በጊዜው ይሆናል።የተለየ መንፈሳዊ አይን ያለው ሰው ግን አሁንም እነዚህን የፒራሚድ ከተሞች መመልከት ይቻላል።
[በድጋሜ የተለጠፈ]

📚 ምንጭ፦ የሊቁ አባ ተስፍ ስላሴ ሞገስ መፃሕፍት
.

《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍2
«የቃል ኪዳን ምድር»


💚💛❤️


✦ << እነርሱም፡ ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ፡ ከትምክሕታቸውም፡ ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል" (ኢሳ. ፳፥ ፭)s።


#ቶማስ ሙር እኮ ዮቶጵያ ያላት እንዲሁም ፕሌቶ አትላንቲስ ያላት የቃል-ኪዳን ምድር ኢትዮጵያ ናት። #ፍራርሲክ ቤከን እኮ "ዘ ኒው አትላንቲክ" ያላት በኋላም ፕሮክለስ የተባለ 415-482 ዓ.ም የነበረ እንዲሁም የፕሌቶን አስተሳስብ የቀረፀ ሰው እንዲህ ይለናል "ፕሌቶ አትላንቲስ ፍፁማዊ አገር የሰላም አገር የፍቅር አገር :የበረከት አገር ያላት ፊክሽናል አለም ሳትሆን #የኢትዩጵያ_ግዛት ነው" ብሎ ያኔ ፅፋታል።>>



✦ ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን ሀገር ስለሆነች፣ የሚገነቧት ይገነባሉ፣ ሊያፈርሷት የሚሞክሩ ደግሞ ይፈርሳሉ" ይለናን ቀሲስ ዶ/ር ዘበነ ለማ ሰሞኑን ሰይፉ ጋ ባደረገው ቆይታ እጅግ ደስ የሚል ቆይታ ቢሆንም አንዳንዶች ግን ኢትዮጵያ የቃልኪዳን ሀገር አይደለችም ይላሉ እውነት ግን አይደለችምን እስቲ ከዚህ በታች ያሉ የተለያዩ ማስረጃዎችን እንመልከት:-



✦ በጥንት ልደተ ክርስቶስ የፐርሻዎ ንግስት እኮ ኢትዩጵያን ለመውጋት ዘምታ ጦሯን አስጨርሳ ተመለሰች ይላል ።ታላቁ እስክንድር 127 ሀገራትን ሲገዛ ኢትዩጵያን አልገዛም።ንግስት ማክዳ እኮ ጠቢቡ ሰለሞንን የጠየቀች ጠቢብ ነች።



✦ ኢትዮጵያ በግብፅ 18 የነገስታትን አንግሳለች። ሜምኖን የተባለዉ ኢትዮጵያዊ የግብፅ ንጉስ ከ1320 አ.አ እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 አ.ም የቆመ ሀዉልት እንደነበረዉና ሀዉልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሀይ ሲያርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበር ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል።



✦ ከማንም አገር ያልተዳቀለ የራሳችን የሆነ ይህም ብቻ ሳይሆን ለዓለም ፊደላት መሰረት የሆነ ፊደል፣ አሀዝ፣ የቀን መቁጠርያ ለአለም የሠጠች።ከአለም መጀመሪያ እግዚያብሔርን ስታመልክ የኖረች እስከ አለም መጨረሻ የምትኖር እና የምታሳምን ኢትዮጵያ ናት ምክንያተም የቃል-ኪዳን ምድር ናት።



✦ ከአራራት ተራራ ግርጌ ከግዮን መፍለቂያ ጀምረው ሜዴትራንያንን ተሻግረው እስከ የመን ድረስ ሰፊ ግዛት የነበራቸው የዛሬዎቹን የአትላንቲክና የሕንድ ውቅያኖሶችን ጨምሮ መላው አፍሪቃን በስማቸው የሰየሙ።ውቅያኖስን አቋርጠው በዛሬዎቹ አማሪካና አውሮፓ : ኢስያን ቀድመው የሰፈሩ።



✦በጥንት ስሟም ምሥር የተባለች የምትጠራዋን ግብጽን ኢትዮጵያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ምሥርን ስላበቀሉባት ምሥር እየተባለች እንጥትጠራ ያደረጉ። #ኢትዮጵያ ከሌሎች የዓለም ሀገራት በተለየ የምስጢራት እና የጥበባት መገኛ ነች ፡፡ ለዚህም ዋንኛው መንስኤ በምድራዊ ሰማያትና በሰማያተ ሰማያት በሚገኙት መላእክት ቅዱሳን አባቶች ብሎም የአዳም ልጆች መካከል ግንኙነት ከሚፈጠርባቸው በምድር ላይ ከሚገኙት ሰባቱ የክብር ቦታዎች መካከል አራቱን ይዛ መገኘቷ ነው፡፡



✦ሀገራችን ኢትዩጵያ ብዙ የመከራ ጊዚያት እንደምታሳልፍና ንጋት እንደሚመጣ አስቀድመው በማየት ለብዙዎቻችን ተናግረዋል፣ ጽፈዋል፣ በየበረሀውም ጩኸዋል። ብዙ ቅዱሳንም ከፍ ከፍ ያሉት እንደሚወርዱ፣ ዝቅ ዝቅ ያሉትም ከፍ እንደሚሉ፣ የወጡት እንደሚገቡና የገቡትም እንደሚወጡ በምልክት አይተው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አምላክ አገራችንን አይጥላትም ።


✦ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃ የኖረችው ረጅም ወንዝ ስላለን ነው? ተራሮች ስላሉን ነው? አይደለም። በአፍሪካ ከሌሶቶ በላይ ተራራ ላይ የተመሰረተ አገር የለም፣ ከኪሊማንጃሮ የሚበልጥ ተራራም የለም፤ ነገርግን ከቅኝ ግዛት አላመለጡም።


✦ኢትዮጵያ ለማጥፋት የሳጥናኤል ልጆች ለ700 አመታት ስትፈተን የነበር እንዲሁም በአድዋ ጊዜ ከሰራዊቱ ጋር ሆኖ የተዋጋ የረዳት እኮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው።ለምን ካልኸኝ የቃል ኪዳን ምድር ስለሆነች እናቶቻችን “የኢትዮጵያ አምላክ” የሚሉት ጠንካራ አምላክ ስላለን እንጅ በኛ ሀይል አይደለም።


✦ኢትዮጵያ የዓለም መነሻ ነበረች፤አሁንም የዓለም መጨረሻና መደምደሚያ የቃል ኪዳን አገር መሆኗ ገሀድ እየሆነ ነው፡፡ይህንን እኛ ኢትዮጵያውያውያን አናምንም፤አንቀበልም፡፡ሌላው ዓለም ግን አምኗል ተቀብሏል፡፡ "ኢትዮጵያ የቃል ኪዳን ሀገር ስለሆነች፣ የሚገነቧት ይገነባሉ፣ ሊያፈርሷት የሚሞክሩ ደግሞ ይፈርሳሉ" ።


[በምክንያት በድጋሜ የተለጠፈ]

《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍21🥰1
💚💛❤️

« ስለ ኢትዮጵያ ሳስብ አልደነግጥም መቼም አልደነግጥም የቆምኩበትን የአባቶቼን መሠረት አውቀዋለሁ። ኢትዮጵያ ባንተ አልተጀመረችም ባንተም አትፈርስም!!! »


ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ ከ2 ዓመት በፊት የተናገሩት ዘመን ተሻጋሪ ንግግር!


《... #ኢትዮጵያ_በዳግም_ትንሳኤ_ትነሳለች !..》

💚 @ethale 💚
💛 @ethale 💛
❤️ @ethale ❤️

⤵️⤵️⤵️
👍2